Search

布道

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 8-3] ክርስቲያን ማነው? ‹‹ሮሜ 8፡9-11›› 

‹‹ሮሜ 8፡9-11›› 
‹‹እናንተ ግን የእግዚአብሄር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም፡፡ የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም፡፡ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በሐጢአት ምክንያት የሞተ ነው፤ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው፡፡ ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል፡፡›. 
 
 
አንድ ሰው እውነተኛ ክርስቲያን እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ የሚለየው የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጡ የሚኖር በመሆኑ ወይም ባለመሆኑ ነው፡፡ አንድ ሰው በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ሳይኖረው በኢየሱስ ቢያምን ወይም ባያምን እንዴት ክርስቲያን ሊሆን ይችላል? ጳውሎስ እጅግ አስፈላጊው ጥያቄ በኢየሱስ ማመናችን ሳይሆን በእርሱ ያመንነው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ተረድተን ነው ወይስ ሳንረዳ የሚለውን እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ቅዱሳን የሚያስፈልጋቸው እውነተኛው እምነት መንፈስ በውስጣቸው ይኖር ዘንድ ዝግጁ የሆነ እምነት ነው፡፡ በእናንተ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ መኖሩ ክርስቲያን መሆናችሁን ወይም አለመሆናችሁን ይወስናል፡፡
 
ስለዚህ ጳውሎስ እንዲህ አለ፡- ‹‹የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም፡፡›› ጳውሎስ ‹‹ይኸው›› ብሎዋል፡፡ ግለሰቡ አገልጋይ፣ ወንጌላዊ ወይም የተሐድሶ መሪ መሆኑ ከቁም ነገር የሚገባ አይደለም፡፡ አንድ ሰው በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከሌለው ያ ሰው የእርሱ አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንድትቀበሉ በሚመራችሁ የእግዚአብሄር ጽድቅ የማታምኑ ከሆነ ለሲዖል የታጫችሁ ሐጢያተኞች መሆናችሁን ማሰብ አለባችሁ፡፡ ስለዚህ ሁላችንም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ስለያዘው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማሰብ አለብን፡፡
    
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ኖረ ማለት በክርስቶስ ጥምቀት ባለን እምነት ለሐጢያት ሞተናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በደረስንበት አዲስ ጽድቅ ምክንያት መንፈሳችን ሕያው ነው፡፡ ከዚህም በላይ ጌታችን ዳግመኛ በሚመጣበት ቀን የሚሞተው ሰውነታችን ሕይወትን ያገኛል፡፡ መንፈስ ቅዱስን ስለሰጠን አምላክ ማሰብ ያለብን ለዚህ ነው፡፡
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን እምነት ከሌላችሁ የክርስቶስ አይደላችሁም፡፡ በሌላ በኩል በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምን ይህ እምነት ካላችሁ የእግዚአብሄር መንፈስ በውስጣችሁ ይኖራል፡፡ ያለዚህ እምነት መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ አይነግስም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄርን ጽድቅ የያዘው የደህንነት ቃል ከሌላችሁ በየእሁድ አገልግሎት ለይምሰል የሐዋርያቶችን የእምነት መመሪያ ብትናዘዙና ብታነበንቡም የክርስቶስ አይደላችሁም፡፡ የክርስቶስ ካልሆናችሁ መንፈሳችሁ ይረገማል፡፡ ይህም ምንም ያህል አብዝታችሁ በጎ ነገር ለማድረግ የፈለጋችሁ ብትሆኑም ወደ ዘላለም ጠፋት ይነዳችኋል፡፡