Search

关于基督教信仰的常见问题解答

话题1:重生于水和圣灵

1-17. ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተው ለምንድነው? 

የኢየሱስ ሞት በጥምቀቱ አማካይነት ለተወሰዱ ሐጢያቶች በሙሉ የተከፈለ ክፍያ ነበር፡፡ ሰዎች ለሐጢያቶቻቸው ዘላለማዊ የሲዖል እሳት ተጋፍጦዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ስለወደደን ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ራሱ የተላለፉበትን ጥምቀት ተቀብሎ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ 
እርሱ እኛን ከሐጢያትና ከሲዖል እርግማን ለማዳን ራሱን መስዋዕት አደረገ፡፡ የእርሱ ሞት ለሰው ዘር ሐጢያቶች የተከፈለ ክፍያ ነበር፡፡ እርሱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ተጠመቀ፡፡ ሁላችንንም ከሐጢያት ከሞት ከፍርድና ከኩነኔ ለማዳንም በመስቀል ላይ ራሱን ለፍርድ ሰጠ፡፡    
ኢየሱስ የሞተው ለሰው ዘር ሐጢያቶች ፍርድን ይቀበል ዘንድ በዮርዳኖስ በራሱ ላይ ለወሰዳቸው የዓለም ሐጢያቶች ነበር፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ዳግመኛ ጻደቃን ሆነን እንድንኖር ሊፈቅድልን ከሙታን ተነሳ፡፡