Search

关于基督教信仰的常见问题解答

话题1:重生于水和圣灵

1-31. እግዚአብሄር ባለጠጋና ርህሩህ ስለሆነ በልባችን ውስጥ ሐጢያት ቢኖርብንም በኢየሱስ ብናምን ጻድቅ አድርጎ አይመለከተንምን? 

እግዚአብሄር ፍቅር ነው፤ ጻድቅም ደግሞ ነው፡፡ ስለዚህ ምንም ይሁን ሐጢያትን በቅንነት ይፈርዳል፡፡ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው፡፡›› (ሮሜ 6፡23) ይህ ማለት አንድ ሐጢያተኛ ከተፈረደበት በኋላ ለሲዖል የታጨ ነው ማለት ነው፡፡ እርሱ ብርሃንን ከጨለማ እንደለየ ጻድቃንን ከሐጢያተኞች ይለያል፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስ በጥምቀቱና በስቅለቱ አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ እንዳስወገደ በማመን ሐጢያት የሌለባቸውን ሰዎች ጻድቃን ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ 
ሆኖም በኢየሱስ ጥምቀት ባለማመን አሁንም ድረስ በውስጣቸው ሐጢያት ያለባቸው ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር በኖህ ዘመን የነበሩት ሰዎች እንዳደረጉት እነርሱም በውሃው ማለትም በኢየሱስ ጥምቀት የማያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር አሁንም ድረስ ሐጢያት ያለባቸውን ሐጢያተኞች ጻድቃንና ሐጢያት አልባ አድርጎ የሚያያቸው ከሆነ እየዋሸ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ፍጥረቶቹን ሁሉ ሊኮንን ወይም ሊገዛ አይችልም፡፡ 
እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ ሐጢአተኛውን አላጸድቅምና፡፡›› (ዘጸአት 23፡7) ሐጢያተኞች እግዚአብሄር እኛን እጅግ ቀናና ተገቢ በሆነ መንገድ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ያዳነበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ትተው የሰዎችን ትውፊቶች የሚከተሉና የሚደግፉ ሰዎች ናቸው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ስለ ሐጢአት በእኔ ስለማያምኑ ነው፡፡›› (ዮሐንስ 16፡9) አሁን በዚህ ምድር ላይ የቀረው ሐጢያት ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና አዳኛችን እንደሆነ እውነቱን አለማመን ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ ይቅር የማይባል መንፈስ ቅዱስን የመሳደብ ሐጢያት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደቡ ሰዎች የሚድኑበት ፈጽሞ ሌላ መንገድ የለም፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ እንዳስወገደላቸው አያምኑምና፡፡ 
ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሐጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመጽን ያደርጋል፡፡ ሐጢአትም ዓመጽ ነው፡፡ እርሱም ሐጢአትን ሊያስወግድ እንደተገለጠ ታውቃላችሁ፡፡ በእርሱም ሐጢአት የለም፡፡ በእርሱ የሚኖር ሁሉ ሐጢአትን አያደርግም፡፡ ሐጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 3፡4-6) ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የመውሰዱን እውነት አለማመን ዓመጸኝነት ነው፡፡ እርሱ እንዲህ ያለውን ዓመጽ የሚያደርጉ ሰዎችን በመጨረሻው ቀን አይቀበላቸውም፡፡ 
በእርሱ የሚኖሩ ሰዎች ሐጢያት የለባቸውም፡፡ በእርሱ ውስጥ በመጠመቅም ከኢየሱስ ጋር ተጣምረዋል፡፡ የሕይወት ዘመናቸውን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ ላይ ባላቸው እምነታቸው አማካይነት በእርሱ ላይ ያኖሩ ሰዎች አሁንም ድረስ ከሥጋቸው ድክመቶች የተነሳ ሐጢያት ቢሰሩም ሐጢያት የለባቸውም፡፡ 
እግዚአብሄር ሐጢያቶቻቸውን በኢየሱስ ላይ ያኖሩትንና በሕይወት መንፈስ ሕግ የተቀደሱትን ሰዎች ጻድቃን ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ይሰጣቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በልባቸው ውስጥ ሐጢያት ባለባቸው ሰዎች ላይ ፈጽሞ አይመጣም፡፡ ዳዊት በመዝሙረ ዳዊት ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም፡፡›› (መዝሙረ ዳዊት 5፡4) የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ በውስጣቸው ሐጢያት ባለባቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ፈጽሞ አይኖርም፡፡ በውስጡ መንፈስ ቅዱስ የሌለበት ሐጢያተኛ እንኳን በሐይማኖት ትምህርቶችና በራሱ አስተሳሰቦች ላይ ተመርኩዞ ከሐጢያት እንደዳነ ይናገር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰው ሕሊናው ስለሚወቅሰው በእምነት ሐጢያት የለብኝም፤ ጻድቅ ነኝ ማለት አይችልም፡፡ 
ስለዚህ ይህ ሰው በሌሎች ሰዎች ፊት ሐጢያተኛ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ደግሞ በእርግጥም ጻድቅ ሰው እንደሆነ ያስባል፡፡ እግዚአብሄር ግን ሐጢያተኛውን ፈጽሞ ጻድቅ ብሎ አይጠራውም፡፡ ሐጢያተኛ ለእግዚአብሄር ፍርድ የተመደበ ነው፡፡ ሐጢያተኛ ለመዳን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለበት፡፡