שאלות נפוצות על האמונה הנוצרית
נושא 1: לידה מחדש מהמים והרוח
1-7. ሮሜ 8፡30 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡›› ታዲያ ይህ ምንባብ በሒደት የሚሆን ቅድስናን ይደግፋልን?
ይህ ምንባብ በሒደት ስለሚሆን ቅድስና አያስተምርም፡፡ ብዙ የሥነ መለኮት ምሁራንና ሐሰተኛ ሰባኪዎች ‹‹በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ቀስ በቀስ ይለወጡና በሥጋና በመንፈስ ሙሉ በሙሉ ይቀደሳሉ›› ብለው አስተምረዋል፡፡ ብዙዎችም ይህንን አምነዋል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ገና ዳግም ያልተወለዱ ክርስቲያኖች ራሳቸውን ይበልጥ ግትር ሆነው ያገኙታል፡፡ በልባቸው ውስጥ ያለው ሐጢያት እያረጁ ሲሄዱ ያድጋል፡፡ ቅድስናችን እንዴት በጊዜ ላይ የሚመሰረት ሊሆን ይችላል? ‹‹በሒደት መቀደስ›› የሚሉት ቃሎች እግዚአብሄር አብዝቶ የሚጠላቸውና ዲያብሎስም ሊጠቀምባቸው የሚወዳቸው ቃሎች ናቸው፡፡
እኛ ጻድቃን መሆን የምንችለው በራሳችን መውጪያ መንገድ በማይኖረን ጊዜ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስላስወገደና ለእነርሱም ዋጋ ለመክፈል ራሱን መስዋዕት ስላደረገ ጽድቃችን የተመሰረተው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ላይ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰዱ እውነታ ላይ ባለን እምነት አማካይነት ጻድቃን ሆነናል፡፡
‹‹ቅድስና›› የሚለው ቃል ‹‹ቅዱስ መሆን›› ማለት ነው፡፡ በራስ ቅዱስ ለመሆን መሞከር በእውነት ማመን ሳይሆን በራስ ደካማ ሥጋ መታመን ነው፡፡
ቀስ በቀስ በሚሆን ቅድስና ላይ ተስፋ ማድረግ የሚመጣው ከራሳችን መንፈሳዊ ፍላጎቶች ነው፡፡ እያንዳንዱ ሐይማኖት የራሱ የሆነ የቅድስና ቃል አለው፡፡ ነገር ግን እኛ በኢየሱስ የምናምን ሰዎች በቃሉ ላይ ፈጽሞ ጠቀሜታን ማኖር አይገባንም፡፡
በኢየሱስ በማመን ቀስ በቀስ አንቀደስም፡፡ የመንፈሳዊ ግርዘት እውነት በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም በማመን ለአንዴና ለመጨረሻ ጻድቃን እንሆናለን፡፡ በእውነት ጻድቃን የሆኑ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ወንጌል እምነት ዳግም የተወለዱ ሰዎች ናቸው፡፡