Search

שאלות נפוצות על האמונה הנוצרית

נושא 2: רוח הקודש

2-8. የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት መቀበል ማለት ምን ማለት ነው? 

ኢየሱስ የተጠመቀበትን ምክንያት ማወቅ ይገባናል፡፡ ጳውሎስ የኢየሱስን ጥምቀት ለኤፌሶን ሰዎች የሰበከው እነርሱ የተጠመቁት ‹‹የዮሐንስን ጥምቀት›› ብቻ መሆኑን ከሰማ በኋላ ነው፡፡ እነርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጠመቁትና መንፈስ ቅዱስንም በልቦቻቸው ውስጥ የተቀበሉት ጳወሎስ ስለ ኢየሱስ ጥምቀት የተናገረውን በማመናቸው ነበር፡፡ ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት ባህርይና የዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት ባህርይ የተለያዩ ነበሩ፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላችን ጋር በቀጥታ ተዛማጅነት ያለውን ሐጢያቶቻችንን ለማንጻት ነበር፡፡ 
ታዲያ የዮሐንስ ጥምቀት ባህርይ ምን ነበር? እርሱ ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች ንስሐ ግቡ! ስታገለግሉዋቸው የነበሩትን እንግዳ አማልክቶች ተዉና ወደ እውነተኛው አምላክ ተመለሱ›› እያለ ጮኸ፡፡ የእርሱ ጥምቀት ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር እንዲመለሱ የሚያደርግ የንስሐ ጥምቀት ነበር፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ራሱ የወሰደበት ነበር፡፡ በዮሐንስ ጥምቀትና በዮሐንስ በኩል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀት መካከል ያለው ልዩነት ይህ ነው፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነበር፡፡ 
ታዲያ ጽድቅን ሁሉ የፈጸመው ጥምቀት ምንድነው? ይህ ኢየሱስ በአለም ላይ ከአዳም ጀምሮ እስከ መጨረሻው ሰው ድረስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደበት ጥምቀት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በዮሐንስ በኩል የሆነው የኢየሱስ ጥምቀት ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነበር፡፡ 
ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ማለት እግዚአብሄር ልጁ በመስቀል ላይ በመሰቀል ስለ እኛ ይፈረድበት ዘንድየዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ እንዲወስድ በዮሐንስ እንዲጠመቀ ፈቀደለት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን ከሞት አስነሳውና አማኞችን ሁሉ ቀደሰ፡፡ 
ይህ የተደረገው ለሰው ዘር ነበር፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙ የዘላለምን ደህንነት ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ይቅርታንና ከእግዚአብሄር ጋር በአንድ ላይ ለዘላለም የመኖርን ዕድል አመጣልን፡፡ ይህ ለሰው ዘር ሁሉ የእግዚአብሄር ጽድቅ፣ ፍቅርና ደህንነት ነው፡፡ እዚህ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ መፈጸሙን ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ 
እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመጠመቅ የዚህ ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን የሚያምን ምስክር እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን የሐጢያትን ስርየት የተቀበለ እያንዳንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቅ ይገባዋል፡፡  
ስለዚህ እኛም በኢየሱስ ላይ ጥምቀት ላይ ላለን እምነት ማረጋገጫ እንዲሆንና ‹‹እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው›› (ማቴዎስ 28፡19) ከሚለው ጋር በመስማማት ተጠምቀናል፡፡ ኢየሱስ በዮሐንስ የተጠመቀው የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ነበር፡፡ ይህ እውነት ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ስለሚመራቸው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተብሎ ተጠራ፡፡