Search

مسیحی ایمان اُتے عام سوالنامہ

مضمون 1: پانی تے رُوح نال نویں سریوں جمنا

1-6. የንስሐ ጸሎቶች ሐጢያቶቻችንን ማስወገድ ይችላሉን?  

ቤዛነት ፈጽሞ በሥራዎቻችን አማካይነት ስለማይመጣ የንስሐ ጸሎቶችም ሐጢያቶቻችንን በፍጹም ማንጻት አይችሉም፡ ሐጢያቶቻችን ፈጽሞ ለዘለቄታው ይነጹ ዘንድ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም እንደዚሁም ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ ማመን ይኖርብናል፡፡ እውነተኛ ቤዛነት የሚሰጠው ኢየሱስ አዲስ ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰሱ ሐጢያቶቻችንን እንዳነጻ ለሚያምኑ ሰዎች ነው፡፡   
የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ በየቀኑ የምንሰራቸውን ሐጢያቶች ማንጻት እንችላለን? አንችልም፡፡ በሕይወታችን የሰራናቸው ሐጢያቶች በሙሉ ኢየሱስ በጥምቀቱ በወሰዳቸው ጊዜ ቀድሞውኑም ከ2,000 ዓመታት በፊት ነጽተዋል፡፡ እኛም በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ለዘላለም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጽተናል፡፡ እርሱ ለእኛ ለምዕመናን የመስዋዕት በግ ሆነ፡፡ ሐጢያቶቻችንንም በሙሉ አስወገደ፡፡ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙም የሁሉንም ዋጋ ከፈለ፡፡   
በኢየሱስ ካመንን በኋላ የምንሰራቸው ሐጢያቶችም እንኳን የቤዛነት እውነት በሆነው የጥምቀቱ ደህንነት ምንጭ እምነት ተወግዶዋል፡፡ ኢየሱስ ቀድሞውኑም አዳኛችን ሆኖ እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ የምንሰራቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶዋል፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ‹‹እንዲህ›› (ማቴዎስ 3፡15) በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወስዶ ጽድቅን ሁሉ ፈጸመ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ በጥምቀቱ የሐጢያቶቻችንን ሐላፊነት ወሰደ፡፡   
የኢየሱስ ጥምቀት ‹‹መታጠብ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደ እርሱ ስለተላለፉ እኛ ፈጽሞ ከሐጢያቶቻችንን ሁሉ ነጻ አውጥቶናል፡፡  
ጥምቀት ማለት ‹‹መጥለም፣ መቀበር›› ማለትም ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ስለተላለፉ እርሱ ለእኛ ለሐጢያተኞች መሞት ነበረበት፡፡ ሐጢያቶች በሙሉ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ የሚያምኑ ሰዎች ለዘላለም ሐጢያት አልባ ሆነዋል፡፡  
እውነተኛ እምነት ሐጢያቶቻችን በሙሉ፤ አሁንና ወደፊት የምንሰራውም ሐጢያቶች እንኳን ኢየሱስ ጥምቀትን ከዮሐንስ በተቀበለና ‹‹እንዲህ›› የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሁሉ በፈጸመ ጊዜ ከ2,000 ዓመታት በፊት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ በሙሉ ልብ ማመን ነው፡፡ 
እርሱ ቀድሞውኑም በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን ከረጅም ጊዜ በፊት ባያስወግድ ኖሮ አሁን እኛ ከሐጢያቶቻችን የምንነጻበት መንገድ አይኖረንም ነበር፡፡ ኢየሱስ ከረጅም ጊዜ በፊት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንዳስወገደ አስታውሱ፡፡ 
ዛሬ እውነተኛ እምነትና መንፈሳዊ ደህንነት ማለት ‹‹እነዚህን ሐጢያቶችም ደግሞ አስወግደሃል አይደል?›› በማለት ቀድሞውኑም መንጻታቸውን ለማረጋገጥ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በኢየሱስ ፊት ማቅረብ ማለት ነው፡ ይህ ማለት እርሱን ማመንና ማመስገንም ማለት ነው፡፡ ወደ ምድር የመጣው፣ የተጠመቀው፣ በመስቀል ላይ የሞተው፣ ከዚያም በሦስተኛው ቀን የተነሳውና በዚህም አዳኛችን የሆነው ለዚህ ነው፡፡  
ሐጢያቶቻችንን ባነጻው የኢየሱስ ጥምቀት በማመን ሐጢያቶቻቸውን ያስወገዱ ሰዎች የተባረኩ ናቸው፡፡ ይህ በየቀኑ ከምንሰራቸው ሐጢያቶች የመንጻት እውነት ነው፡፡ እውነተኛ እምነት በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በወሰደው በኢየሱስ ማመን ነው፡፡