Search

مسیحی ایمان اُتے عام سوالنامہ

مضمون 3: مُکاشفہ

3-2. በምዕራፍ 11 ላይ የታዩት ሁለቱ ምስክሮች እነማን ናቸው? 

በምዕራፍ 11 ላይ የታዩት ሁለቱ ምስክሮች እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን የእስራኤልን ሕዝብ ለማዳን በተለየ መንገድ ያስነሳቸው ሁለት የእግዚአብሄር ባሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ለአብርሃም የገባውን ተስፋ ለመፈጸም እስራኤሎችን ከሐጢያት ለማዳን የተላኩት እነዚህ ሁለት ነቢያቶች ምልክቶችንና ተዓምራቶችን እንዲያደረጉ በእነርሱ የተመሩት እስራኤሎችም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሰው እርሱን አዳኛቸው አድርገው እንዲያምኑ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ምስክሮች ለ1,260 ቀናት ማለትም ከታላቁ የሰባት ዓመት የመከራ ዘመን ውስጥ ለመጀመሪያው ሦስት ዓመት ተኩል ክፍለ ጊዜ የእግዚአብሀርን ቃል ለእስራኤል ሕዝብ ይመግባሉ፡፡ እግዚአብሄር በሁለቱ ምስክሮች አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲያምኑ በማድረግ አሕዛቦች በእምነት አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንደዳኑ ለአሕዛቦች የሰጣቸውን ያንኑ ደህንነት ለእስራኤሎችም ይሰጣቸዋል፡፡ 
ዮሐንስ ራዕይ 11፡4 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እነዚህ በምድር ፊት የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፡፡›› በሁለቱ የወይራ ዛፎች ላይ የተሰጡ ብዙ የተለያዩ ትርጓሜዎች አሉ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች እነርሱ የወይራ ዛፎች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ሁለቱ የወይራ ዛፎች የሚያመለክቱት ቅቡዓንን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች ነቢያቶች፣ ነገሥታቶች ወይም ካህናቶች ሆነው ሲሾሙ ይቀቡ ነበር፡፡ በተቀቡ ጊዜም መንፈስ ቅዱስ ወርዶባቸዋል፡፡ ስለዚህ የወይራ ዛፍ ከመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰውን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያመለክታል፡፡ (ሮሜ 11፡17) 
ነገር ግን በዮሐንስ ራዕይ 11፡1 ላይ ‹‹በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባለልኝ፡- ተነስተህ የእግዚአብሄርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ ተባለልኝ›› የሚለውን ስንመለከት የምዕራፍ 11 ትኩረት በእስራኤል ሕዝብ ደህንነት ላይ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለእስራኤሎች የሚሰራጭበት በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠው የደህንነት ጸጋ አማካይነት ከሐጢያቶቻቸው የሚድኑበትና እውነተኛ የእግዚአብሄር ሕዝብ የሚሆኑበት ሥራ ይጀምራል፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ምስክሮች እግዚአብሄር በመጨረሻው ዘመን የእስራኤልን ሕዝብ ለማዳን የሚያስነሳቸው የአምላክ ነቢያቶች ናቸው፡፡ 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መቅረዝ የሚያመለክተው የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ መቅረዞች የሚያመለክቱት በአሕዛቦችና ለእስራኤሎች በተፈቀደ ቤተክርስቲያን መካከል የተመሰረተችውን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ነው፡፡ እግዚአብሄር የእስራኤሎች አምላክ ብቻ ሳይሆን የአሕዛቦችም አምላክ ነው፡፡ እርሱ የሁሉም ሰው አምላክ ነውና፡፡ ስለዚህ በእስራኤሎችና በአሕዛቦች መካከል እግዚአብሄር በሁለቱም ውስጥ የራሱን ቤተክርስቲያን መስርቷል፡፡ በእርሱ ቤተክርስቲያን አማካይነትም እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ነፍሳቶችን ከሐጢያት የማዳን ሥራ ይሰራል፡፡ 
ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምሮ እስራኤሎች በእግዚአብሄር ሕግ የተደነገገ ነቢያቶች ነበሩዋቸው፡፡ በእነርሱ በኩልም የእግዚአብሄርን ቃል ሰምተዋል፡፡ እነርሱ የሙሴ ሕግና ነቢያቶች ነበሩዋቸው፡፡ በመሆኑም ስለ መስዋዕት ስርዓትና ስለ ብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡ ከራሳቸው ሕዝብ የተሾሙትን የእግዚአብሄር ነቢያቶች የሚጠይቁትም ለዚህ ነው፡፡ 
እነርሱ የእግዚአብሄር ምርጥ ሕዝብ እንደሆኑም ያምናሉ፡፡ ስለዚህ አሕዛቦች የእግዚአብሄርን ቃል ሲነግሩዋቸው የምር አድርገው አይወስዱትም፤ አያዳምጡትምም፡፡ ከዚህ የተነሳ እነርሱ በመጨረሻ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚቀበሉትና የሚያምኑት እግዚአብሄር የሾማቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ነቢያቶች ሲነሱ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሄር ራሱ ከእስራኤል ሕዝብ ሁለት ነቢያቶችን አስነስቶ ወደ እስራኤሎች የሚልከው ለዚህ ነው፡፡ እነዚህ ነቢያቶች በተጨባጭ ከዚህ ቀደም በብሉይ ኪዳን ታዋቂ የሆኑ የእግዚአብሄር ባሮች ያደረጉዋቸውን ብዙ ድንቆች ያደርጋሉ፡፡ ዮሐንስ ራዕይ 11፡5-6 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ማንምም ሊጎዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል፤ ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጎዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል፡፡ እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፡፡ ውሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ፣ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሰፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው፡፡
ለእስራኤል ሕዝብ የተሾሙት እነዚህ የእግዚአብሄር ባሮች እንዲህ ያለ ሥልጣን እስከሌላቸው ድረስ እስራኤሎች ንስሐ አይገቡም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ለሁለቱ ምስክሮቹ ሐይሉን አለበሳቸው፡፡ የትንቢትን ቃል ሁሉ ለእስራኤሎች ሁሉ ይሰብኩ፣ ይመሰክሩና ኢየሱስ ክርስቶስ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቁት የነበረው መሲሃቸው መሆኑን እንዲያምኑ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሄር ለሁለቱ ምስክሮች ልዩ የሆነውን ሥልጣኑን ይሰጣቸዋል፡፡ እስራኤሎች በተጨባጭ የፈጸሙዋቸውን ድንቆች በማየት እነርሱን ይሰሙዋቸውና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሳሉ፡፡ 
ሁለቱ ምስክሮች ወንጌልን ለእሰራኤሎች ማሰራጨት ሥራቸውን ሲያጠናቅቁ ጸረ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ላይ ይገለጥና የእነርሱን የወንጌል ስብከት ይቃወማል፤ ይገድላቸውማል፡፡ ዮሐንስ ራዕይ 11፡8 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል፡፡ እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞም ጌታቸው የተሰቀለባት ናት፡፡›› 
ሁለቱ ምስክሮች ወንጌልን ለመላው እሰራኤሎች ከሰበኩና የተጠሩባቸውን ሥራዎቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ከዚህ ቀደም በተሰቀለበት ስፍራ ይገደላሉ፡፡ ይህ እውነታ እነዚህ ሁለት ምስክሮች የሚወጡት ከእስራኤሎች የመሆኑን ትርጓሜ ይደግፋል፡፡ እነርሱ ለእስራኤል ሕዝቦች የእግዚአብሄር ባሮች ናቸውና፡፡ 
በጥቅሉ እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን አሻፈረኝ ላሉትና እርሱን ለናቁት፤ በመንፈሳዊ ምሳሌም ሰዶምና ግብጽን ለመሰሉት እስራኤሎች ኢየሱስ በእርግጥም ለረጅም ጊዜ ሲጠብቁት የነበረው መሲሃቸው እንደሆነ የሚመሰክሩትን ሁለቱን ምስክሮቹን ያስነሳል፡፡ እግዚአብሄር ሐይሉን ባለበሳቸው በእነዚህ ሁለት ምስክሮች አማካይነት እስራኤሎች በኢየሱስ እንዲያምኑ ያደርጋል፡፡