مسیحی ایمان اُتے عام سوالنامہ
مضمون 4: ساڈیاں کتاباں دے پڑھن والیاں ولوں عام سوالنامہ
4-2. ‹‹በልባችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን ፈጽሞ ሐጢያት አልባ መሆን እንችላለን›› ብለህ ጻፍህ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፡- ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም፡፡ በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ ሐጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 1፡8-10) ይህንን ምንባብ እንዴት ትተረጉመዋለህ? ምንባቡ የሚለው እኛ እስከ ምንሞት ድረስ ሐጢያተኞች እንደሆንንና በየቀኑም የሐጢያቶቻችንን ይቅርታ ለማግኘት የንስሐ ጸሎቶችን ማቅረብ እንዳለብን አይደለምን?
1ኛ ዮሐንስ 1፡8-10 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም፡፡ በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ ሐጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡››
‹‹ሐጢአት የለብንም ብንል›› ማለት ‹‹ሐጢያተኛ ሆነን እንደተወለድን ካልተናዘዝንና በሕጉ ፊትም በሕይወት ዘመናችን በሙሉ ሐጢያት እየሰራን የምንቀጥል ከሆነ›› ማለት ነው፡፡ እንደምናውቀው ሁሉም ሰው ሐጢያቱን መናዘዝ አለበት፡፡ ሆኖም ይህ ማለት ለእነዚያ ሐጢያቶች በየቀኑ ይቅርታን ለማግኘት የዘወትር ሐጢያቶቻችንን መናዘዝ አለብን ማለት ሳይሆን በኢየሱስ ሳናምን በራሳችን ሐጢያት መስራትን ለመሸሽ በጣም ደካሞች መሆናችንን መናዘዝ ይገባናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በልቡ ውስጥ ሐጢያት ይዞ በጨለማ ውስጥ እየኖረ ሐጢያት እንደሌለበት የሚናገር ከሆነ በእርሱ ውስጥ እውነት የለም፡፡
‹‹ሐጢአታችንን ብንናዘዝ›› ማለት ‹‹ከውልደታችን ጊዜ ጀምሮ እስከምንሞትበት ቀን ድረሰ ሁሌም ሐጢያት እንደምንሰራና ሐጢያት መስራትን መሸሽ ብንፈልግም እንኳን ሐጢያት ሳንሰራ መኖር እንደማንችል መናዘዝ ነው፡፡›› ሐጢያት በምንሰራበት ጊዜ ሁሉ ንስሐ መግባትና የጌታን ይቅርታ መጠየቅ ማለት አይደለም፡፡ ጌታ ከ2,000 ዓመት በፊት በጥምቀቱና በመስቀሉ ቀድሞውኑም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ደምስሶዋል፡፡ አሁን እኛ ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር እኛ ያለ እርሱ ሐጢያተኞች እንደሆንንና የእርሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ እንደደመሰሰ መናዘዝ ነው፡፡
‹‹ሐጢአት አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም›› ማለት የሚከተለውን ነው፡፡ ሕጉ የሐጢያትን ዕውቀት ይሰጠንና በልቦቻችን ውስጥ የተደበቁትን ሐጢያቶች ይገልጣል፡፡ ስለዚህ በሕጉ ፊት ሐጢያት መስራታችንን መናዘዝ ይኖርብናል፡፡ ሆኖም ሕጉን የማይቀበሉ ሰዎች ሐጢያት እንደሰሩ አይናዘዙም፡፡ ሕጉ ሐጢያቶቻችንን እንድንናዘዝ ያደርገንና በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወዳነጻው ኢየሱስ ይመራናል፡፡