Search

免費印刷書籍、
電子書和有聲讀物

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (I)
  • ISBN9788928200207
  • 頁碼381

阿姆哈拉語 9

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (I)

Rev. Paul C. Jong

ማውጫ
 
መግቢያ 
1. በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠው የሐጢያተኞች ደህንነት (ዘጸዓት 27፡9-21) 
2. ስለ እኛ የተሰቃየው ጌታችን (ኢሳይያስ 52፡13-53፡9) 
3. ያህዌህ ሕያው አምላክ (ዘጸዓት 34፡1-8) 
4. እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ሲና ተራራ የጠራበት ምክንያት (ዘጸዓት 19፡1-6) 
5. እስራኤላውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዴት መስዋዕቶችን ያቀርቡ እንደነበር፡- ታሪካዊው ዳራ (ዘፍጥረት 15፡1-21) 
6. በግርዘቱ ኪዳን ውስጥ የጸናው የእግዚአብሄር ተስፋ አሁንም ለእኛ ይሰራል (ዘፍጥረት 17፡1-14) 
7. የእምነትን መሠረት የጣሉት የመገናኛው ድንኳን የግንባታ ቁሶች (ዘጸዓት 25:1-9) 
8. የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ቀለም (ዘጸዓት 27:9-19) 
9. በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ የተገለጠው እምነት (ዘጸዓት 27:1-8) 
10. በመታጠቢያው ሰን የተገለጠው እምነት (ዘጸዓት 30:17-21) 
11. የደህንነት ምስክርነቶች 
 
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተደበቀውን እውነት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ መረዳትና ማወቅ የምንችለው የመገናኛው ድንኳን እውነተኛ ጭብጥ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወቅ ብቻ ነው፡፡
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ የተገለጡት ሰማያዊው፤ ሐምራዊው፤ ቀዩና ጥሩው በፍታ በአዲስ ኪዳን ዘመን የሰውን ዘር ያዳኑትን የኢየሱስ ክርስቶስ ስራዎች ያሳዩናል፡፡ በዚህ መንገድ የብሉይ ኪዳኑ የመገናኛው ድንኳን ቃልና የአዲስ ኪዳን ቃል ልክ እንደ ጥሩው በፍታ እርስ በርሳቸው በጣም የተቆራኙና የተያያዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ እውነት በክርስትና ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ እውነት ፈላጊ ሰው ለረጅም ጊዜ መደበቁ ያሳዝናል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር በመምጣት በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ በመስቀል ላይም ደሙን አፈሰሰ፡፡ ማናችንም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳናስተውልና ሳናምን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠውን እውነት ማግኘት አንችልም፡፡ አሁን ይህንን የመገናኛውን ድንኳን እውነት መማርና በእርሱም ማመን አለብን፡፡ ሁላችንም በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ባለው በሰማያዊው፤ በሐምራዊው፤ በቀዩ ማግና በጥሩ በፍታ በር የገለጠውን እውነት መረዳትና ማመን ያስፈልገናል፡፡
電子書下載
PDF EPUB
有聲讀物
有聲讀物

與該標題相關的書籍