Rev. Paul C. Jong
ማውጫ
መቅድም
1. እኛ በሐጢያቶቻችን ምክንያት ወደ ጥፋት የምናፈገፍግ አይደለንም (ዮሐንስ 13፡1-11)
2. የቅደስቱ ስፍራ መጋረጃና ምሰሶዎች (ዘጸዓት 26፡31-37)
3. እነዚያ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችሉት (ዘጸዓት 26፡31-33)
4. የተቀደደው መጋረጃ (ማቴዎስ 27፡50-53)
5. ለእያንዳንዱ የመገናኛው ድንኳን ሳንቃ ሁለት የብር እግሮች ሁለት ማጋጠሚያዎች (ዘጸዓት 26፡15-37)
6. በምስክሩ ታቦት ውስጥ የተደበቁት መንፈሳዊ ምስጢሮች (ዘጸዓት 25፡10-22)
7. በስርየት መክደኛው ላይ የሚቀርብ የሐጢያት ስርየት ቁርባን (ዘጸዓት 25፡10-22)
8. የሕብስቱ ገበታ (ዘጸዓት 37፡10-16)
9. የወርቁ መቅረዝ (ዘጸዓት 25፡31-40)
10. የዕጣኑ መሰውያ (ዘጸዓት 30፡1-10)
11. ለስርየት ቀን የሚሆነውን መስዋዕት ያቀረበው ሊቀ ካህን (ዘሌዋውያን 16፡1-34)
12. በመገናኛው ድንኳን መደረቢያዎች ውስጥ የተደበቁት አራቱ ምስጢሮች (ዘጸዓት 26፡1-14)
13. የአንባቢያን ግምገማዎች
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የመገናኛውን ድንኳን እንዲሰራ ሙሴን እንዳዘዘው በአዲስ ኪዳንም በውስጣችን ያድር ዘንድ እግዚአብሄር በእያንዳንዳችን ልቦች ውስጥ መቅደስ እንድንሰራ ይፈልጋል፡፡ ይህንን መቅደስ በልቦቻችን ውስጥ የምንሰራበት የእምነት ቁስ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ቃል ነው፡፡ በዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ማጠብና ማንጻት አለብን፡፡ እግዚአብሄር መቅደስን እንድንሰራ ሲነግረን ልቦቻችንን ባዶ እንድናደርግና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንድናምን እየነገረን ነው፡፡ ሁላችንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ልቦቻችንን ማንጻት አለብን፡፡
በዚህ የወንጌል እውነት በማመን የልቦቻችንን ሐጢያቶች በሙሉ ስናነጻ ያን ጊዜ እግዚአብሄር በውስጣችን ይኖራል፡፡ በልቦቻችሁ ውስጥ ቅዱስ መቅደስ መስራት የምትችሉት በዚህ እውነተኛ ወንጌል በማመን ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ አንዳንዶቻችሁ ምናልባትም በራሳችሁ ጥረት መቅደሶችን ለመስራት በመሞከር ልቦቻችሁን ለማንጻት የንስሐ ጸሎቶቻችሁን ስታቀርቡ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ጊዜው ይህንን የሐሰት እምነት ትታችሁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን አእምሮዋችሁን የምታድሱበት ነው፡፡