Search

佈道

ርዕስ 8፡ መንፈስ ቅዱስ

[8-5] ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁን? ‹‹ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-10 ››

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁን?
‹‹ 1ኛ ዮሐንስ 1፡1-10 ››
‹‹ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን፣ በዓይኖቻችንም ያየነውን፣ የተመለከትነውንም፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፡፡ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፡፡ በአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፡፡ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን፡፡ ሕብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን፡፡ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራት መልዕክት፡- እግዚአብሄር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ፍጹም የለም የምትል ይህች ናት፡፡ ከእርሱ ጋር ሕብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፡፡ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ሕብረት አለን፡፡ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጢአት ሁሉ ያነጻናል፡፡ ሐጢያት የለብንም ብንል ራሳችንን እናሰታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም፡፡ በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡ ሐጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡›› 
 
 
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ ከሆነ በመጀመሪያ በጌታ ፊት ትንሽ ሐጢያት እንኳን እንዲህ ያለውን ሕብረት አዳጋች እንደምታደርገው ማወቅ አላባችሁ፡፡ ‹ሰው በጌታ ፊት እንዴት ቅንጣት ሐጢያት ላይኖርበት ይችላል?› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከጌታ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ከልባችሁ የምትመኙ ከሆነ በልባችሁ ውስጥ ጨለማ ሊኖር አይገባም፡፡ ስለዚህ ከጌታ ጋር ሕብረት ይኖራችሁ ዘንድ በቤዛነት ወንጌል ማመንና ራሳችሁን ለሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ማንጻት ያስፈልጋችኋል፡፡ 
በእውነት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ የምትመኙ ከሆነ እንግዲያውስ በመጀመሪያ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና ማመን በእምነት አማካይነትም ሐጢያቶቻችሁን ማንጻት ይኖርባችኋል፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማታውቁና በልባችሁ ውስጥም የማትቀበሉት ከሆነ ከጌታ ጋር ሕብረት የሚኖራችሁ ስለመሆኑ ማሰብ አይኖርባችሁም፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ማድረግ የሚቻለው ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ከልቦቻችሁ ውስጥ ሲነጹ ብቻ ነው፡፡
ሐጢያቶች በሙሉ ከማንኛውም ሰው አእምሮ ውስጥ መንጻት የሚችሉት በእርሱ የውሃና የመንፈስ እውነት ነው፡፡ በውቡ የውሃና የመንፈስ ወንጌል ስታምኑ ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ይባርካችኋል፡፡ በእርግጥ ከጌታና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ሐጢያቶቻችሁን ተገንዘቡና ራሳችሁን ከሐጢያት ለማንጻት በውቡ ወንጌል እመኑ፡፡ ከዚያ በኋላ በእርግጥ ከጌታ ጋር ሕብረት ሊኖራችሁ ይችላል፡፡   
ከጌታ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት ማመንና በመስቀል ላይ ደሙም ደግሞም ማመን አለባችሁ፡፡ ሰዎች በእርግጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራቸው የሚመኙ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ማን እንደሆነ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቅዱሱ ነው፡፡ ስለዚህ ሊኖር የሚችለው በውቡ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ውስጥ ብቻ ነው፡፡ 
እስቲ በዮሐንስ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በማመን ሐጢያቶቹ የነጹለትና አሁን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ያለው አንድ ሰው የሰጠውን ኑዛዜ እንመልከት፡፡
‹‹በዚህ ምድር ላይ ብዙ አይነት የተለያዩ ሰዎች አሉ፡፡ እያንዳንዳቸውም የሚኖሩት በራሳቸው አስተሳሰቦችና መንገዶች ነው፡፡ እኔም በአንድ ወቅት ልክ እንደ እነርሱ ነበርኩኝ፡፡ በጣም ተራ ሕይወት ነበረኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ እናቴን ተከትዬ ወደ ቤተክርስቲያን እሄድ ነበር፡፡ በተለምዶም በእግዚአብሄር ወደ ማመን መጣሁ፡፡ አባቴ በእግዚአብሄር የሚያምን ስላልነበረ አዘውትሮ አመኔታዎቼን ይነቅፍ ነበር፡፡ የቀረው ቤተሰብ በሙሉ ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳል፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ የሕይወቴ ትልቁ ክፍል ነበር፡፡   
ሆኖም በጉርምስና ዕድሜዬ ወቅት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን አባቴን ካየሁ በኋላ ስለ ሕይወትና ሞት፣ ስለ ሰማይና ሲዖል ያሉ እንዲህ ያሉ ነገሮችን በሚመለከት ብዙ አሳቦች መጡብኝ፡፡  ብዙ ሰዎች በእግዚአብሄር ካመንሁ ሰማይ መግባትና የእግዚአብሄር ልጅ መሆን እንደምችል ይናገራሉ፡፡ እኔ ግን በዚህ ነገር እርግጠኛ አልነበርሁም፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ ልሆን እችላለሁ ብዬ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አልሆንኩም ነበር፡፡ በምድር ላይ ጥሩ ነገር ካደረግሁ ሰማይ መግባት እንደምችል ተምሬ ነበር፡፡ ስለዚህ ለችግረኞች ጥሩ ለማድረግ ሞከርሁ፡፡
በአንዱ የልቤ ወገን ግን ሐጢያት እንደሰራሁ አወቅሁ፡፡ ለሌሎች ጥሩ ሰው ሆኜ ታይቼ ይሆናል፤ ነገር ግን ለሐጢያቶቼ የሚሰማኝ ጸጸት ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ‹‹እባክህ በእውነት ያንተ ልጅ እንድሆን ይፈቀድልኝ፡፡ እባክህ እውነቱን ልወቅ›› እያልሁ መጸለይን ልማድ አድርጌው ነበር፡፡ እየጸለይሁ ሳለሁ በልቤ ውስጥ አዲስ ጉትጎታን አዳበርሁ፡፡ የቃሎቹን ትምህርቶች ባደመጥሁ ጊዜ ሁሉ ቃሎቹን መረዳትም ሆነ ማየት አልቻልኩም፡፡ በሕይወቴ ባዶነት፣ በሐጢያቴ፣ በሞት ወ.ዘ.ተ ታከትሁ፡፡  
‹‹ዳግም መወለድ እፈልጋለሁ፡፡ ዳግም መወለድ የምችል ከሆነ እንዲህ አልኖርም›› የሚሉ አሳቦች ነበሩኝ፡፡ እነዚህ አሳቦች ቢኖሩኝም ወደ ቤተክርስቲያን መሄዴን ቀነስሁ፡፡ የጉርምስና አመታቶቼም ነጎዱ፡፡ አሁን ስራ ማግኘት አስፈለገኝ፤ ነገር ግን ካሰብኩት በላይ አዳጋች ነበር፡፡ ይበልጥ ታወክሁ፡፡ ምንም ያህል ጠንክሬ ብሞክርም ፈገግ ማለት አልቻልሁም፡፡ ባዶ ልብ ይዤ ራሴን ስመለከት ወደ ድባቴ ሁኔታ ውስጥ ወደቅሁ፡፡ በዚያን ጊዜ ወንጌልን ከታላቅ ወንድሜ ሰማሁ፡፡  
‹‹እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ ሐጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 3፡19) ይህ በትክክል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነበር፡፡ ቀደም ባሉት የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ የተማርሁት ነገር ቢኖር ኢየሱስ ለሐጢያቶቻችን በመስቀል ላይ እንደሞተ ነበር፡፡ ይህ ወንጌል ግን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ለመውሰድ በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀና በመስቀል ላይም ለሐጢያቶቻችን እንደተፈረደበት ነገረኝ፡፡  
በዘመኔ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድሁ፤ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆንሁ ባስመስልም አልተሳካልኝም፡፡ የቃሎቹን ትርጉም ለመረዳት ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡ ሆኖም ውቡን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ከሰማሁና በእርሱ ካመንሁ በኋላ በውስጤ ያለው ሐጢያትና ያሰቃዩኝ ነገሮች በሙሉ ከሰሙና ልቤ ሰላማዊ ሆነ፡፡ 
በእግዚአብሄር ብቻ በግለት አምኜና እንከን በሌለበት መገኘት ወደ ቤተክርስቲያን ሄጄ ቢሆን ኖሮ ሰማይ እገባ ነበር ብዬ አሰብሁ፡፡ እግዚአብሄር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ላከልኝና ሐጢያቶቼም ይቅር ተባሉ፡፡ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ሰጠኝ፡፡ የእርሱን ቤዛነት ከመቀበሌ በፊት ስለ መንፈስ ቅዱስም ሆነ በልሳን ስለመናገር የማውቀው አሳብ አልነበረኝም፡፡ ዝም ብዬ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድሁና እውነተኛ ሆኜ ከኖርሁና ቤተክርስቲያኔን ካገለገልሁ እግዚአብሄር ይባርከኛል ብዬ አመንሁ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መቀበል የምችለው ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያቶቼ ይቅር ሲባሉ ብቻ እንደሆነ ወደ መገንዘብ ደረስሁ፡፡     
በቀድሞው ሕይወቴ በእግዚአብሄር ያመንሁ ብሆንም ገናም በሐጢያት ውስጥ ነበርሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የመቀበልን ጠቀሜታ ሳላውቅ ለብ ያለ ሕይወትን ኖርሁ፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ውቡን ወንጌል በሰበከው የእርሱ ባርያ በኩል መንፈስ ቅዱስ በእኔም ውስጥ እንደሚኖር አመንሁ፤ አወቅሁም፡፡ 
ቤዛነትን ከተቀበልሁ በኋላ መጀመሪያ ላይ መንፈስ ቅዱስ በውስጤ እንደነበር ወይም እንዳልነበር ማመን አልቻልሁም፡፡ ነገር ግን ቃሎቹን በተደጋጋሚ አጠናሁና በልቤ ውስጥ አዲስ እምነት እያበበ እንደሆነና ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ እንደተቀበልሁም ወደ መገንዘቡ ደረስሁ፡፡ አሁን ይህ እውነት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጤ እንደሚኖርም አረጋግጫለሁ! እርሱ ሐጢያቶቼን ይቅር ባለ ጊዜ የእግዚአብሄር ልጆች መሆንና መንፈስ ቅዱስን መቀበል የሚችሉት ከሐጢያት ነጻ የወጡት ብቻ እንደሆኑ አወቅሁ፡፡  
በእርሱ አይኖች ፊት ፍጹም ለመምስል ወይም ያለ እንከን ለመኖር ያደረግሁዋቸው ጥረቶቼ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በጭራሽ እንዳልፈቀዱልኝም ደግሞ አወቅሁ፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያተኞች መሆናቸውን ወደሚያውቁት ነገር ግን ሐጢያተኞች ስለመሆናቸው ምን እንደሚያደርጉ ወደማያውቁ ሰዎች ይመጣል፡፡ እርሱን በጉጉት የሚሹትንና የሚፈልጉትን ይገናኛቸዋል፡፡  
መልካምን ማድረግና በግድየለሽነት በእግዚአብሄር ማመን ሰማይ እንደማያደርሰኝና ኢየሱስ ወደዚህ አለም የመጣው በውቡ የውሃና የመንፈስ ወንጌል አማካይነት ከሐጢያቶቼ ሊያድነኝ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ ለዘላለም በውስጤ እንዲኖርም መንፈስ ቅዱስን ሰጠኝ፡፡
ልጁ ስላደረገኝና በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ስለባረከኝ ጌታን አመሰግነዋለሁ፡፡ በጌታ ባይሆን ኖሮ አሁንም ድረስ በልቤ ውስጥ ሐጢያት በኖረብኝና በሲዖል ውስጥ ለዘላለም በሕይወት እስር ቤት ውስጥ በተኮነንሁ ነበር፡፡   
እንደዚሁም እኔ በአንድ ወቅት በመስቀል ላይ ደም ብቻ አምኜ ስለነበር ፈልጌም እንኳን መንፈስ ቅዱስን መቀበል አልቻልሁም፡፡ በዚያን ጊዜ በኢየሱስ አመንሁ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ከመቀበል የሚከለክለኝ ሐጢያት በልቤ ውስጥ ነበረብኝ፡፡ ሐጢያተኛ በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን መቀበል አይችልም፡፡ ነገር ግን አሁንም ብዙ ሐጢያተኞች ልቦቻቸው በሐጢያት ተሞልተው እንኳን መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይሞክራሉ፡፡
በእርግጥ መንፈስ ቅዱስን መቀበልና ከእርሱም ጋር ሕብረት ማድረግ የምትፈልጉ ከሆነ ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ማመንና ቤዛነትን ማግኘት ያስፈልጋችኋል፡፡ አሁንም ገና ሐጢያተኞች ናችሁን? እንግዲያውስ ቀደም ብለው መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉት ሰዎች እውነተኛውን ወንጌል መስማት ትችላላችሁ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ሰዎች የተጠማ ልብ ሊኖራቸውና ውብ በሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ሊታመኑ ይገባቸዋል፡፡
በቤተክርስቲያን በኩል የመንፈስ ቅዱስን ቃሎች መስማት የሚችሉት ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱ ውብ የሆነውን ወንጌል በመስማት የታመነ ሕይወታቸውን መኖር ይችላሉ፡፡ ሐጢያተኞች ግን መቼም ወንጌልን ሳይሰሙ ለሲዖል የተመደበውን የተረገመ ሕይወታቸውን ይኖራሉ፡፡
ስለዚህ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መማር አለባችሁ፡፡ በዚህ ወንጌል ማመን የሚያስፈልጋችሁ ለምንድነው? ከሐይማኖት ሕግ ማምለጥና በእግዚአብሄር ቃሎች ላይ በተመሰረተው ውብ የሆነ ወንጌል ላይ እምነታችሁን መገንባት ያስፈልጋችኋል፡፡ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ይህንን ውብ ወንጌል ተከተሉ፤ አሁን ይህ ወንጌል መንፈስ ቅዱስን ለተቀበሉ ሰዎች የተሰጠ ነው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ውብ ወንጌል ሐዋርያቶች በጥንቷ ቤተክርስቲያን መጀመሪያ ላይ ከተከተሉት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ክርስቲያኖች በሙሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል አለባችሁ፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የሚችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡   
እነዚያ እስከ አሁን ድረስ ውብ በሆነው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያቶች አሉባቸው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ከእርሱ ጋር ሕብረት ይኖራቸው ዘንድ መጀመሪያ እግዚአብሄር በሰጣቸው የውሃና የመንፈስ ወንጌል ማመንና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ያስፈልጋቸዋል፡፡ 
 
 

መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን ደጋግሞ ይጠቅሳል
 

ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የጀመረው ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ነው፡፡ የደህንነት ቀን አሁን ነው፡፡ የእርሱ ወሰን የለሽ ፍቅር ጊዜ አሁን ነው፡፡ ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማንቀበልና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሳይኖረን የምንኖር ከሆነ በእርግጥም አሳዛኝ ነው፡፡
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት አላችሁን? በሐጢያቶቻችሁ ምክንያት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዳይኖራችሁ ተከልክላችኋልን? እንግዲያውስ እግዚአብሄር ስለሰጣችሁ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ተማሩና በእርሱ እመኑ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምታምኑ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ በልባችሁ ውስጥ ያድርና አጋራችሁ ይሆናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ መኖር የሚችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ልቦች ውስጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ብዙውን ጊዜ በጻድቃን ልቦች ውስጥ ፈቃዱን ይገልጣል፡፡ ጳውሎስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረው አገልግሎት ውብ የሆነውን ወንጌል ማሰራጨት ነበር፡፡     
መንፈስ ቅዱስን የተቀበለን ሰው የምታውቁት እንዴት ነው? መለኪያው ምንድነው? መለኪያው ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሚያምን መሆኑ ወይም አለመሆኑ ነው፡፡ አንድ ሰው ውብ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚያውቅና የሚያምን ከሆነ ያ ሰው ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ አለው፡፡    
መንፈስ ቅዱስ በውቡ ወንጌል በማያምኑት ውስጥ አይኖርም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው ኢየሱስ ከመጥምቁ ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በተገኘው የሐጢያት ስርየት በሚያምኑት ሰዎች ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁን?
መንፈስ ቅዱስን ትቀበሉና ከእርሱ ጋር ሕብረት ይኖራችሁ ዘንድ መረዳት የሚያስፈልጋችሁ ወንጌል ምን አይነት እንደሆነ ታውቃላችሁን? ውብ የሆነው ወንጌል የሚገኘው በዮሐንስ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ ውስጥ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማታምኑ ከሆነ ሐጢያቶቻችሁ ይቅር ሊባሉ ስለማይችሉ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችሁ ሊኖር አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሰዎች እንዲቀበሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን እንደሚገባቸው ይጠይቃል፡፡  
መንፈስ ቅዱስ በሐጢያተኞች ልቦች ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የምትፈልጉ ከሆነ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ ለማንጻት በመጀመሪያ ውብ በሆነው ወንጌል ማመን አለባችሁ፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ውብ የሆነውን ወንጌል በመስበክ ታማኝ ልትሆኑ ይገባል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መመራት የምትፈልጉ ከሆነ ሁሌም ውብ የሆነውን ወንጌል መውደድና በምትሄዱበት ሁሉ ወንጌሉን ለማሰራጨት መሞከር አለባችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ከሚሰብኩ ሰዎች ጋር አብሮ ነው፡፡
ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ለጻድቃን ማለትም ውብ በሆነው ወንጌል ለሚያምኑ ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው የሚችለው ጻድቃን ማለትም ውብ በሆነው ወንጌል የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ያረጋገጠው ውብ የሆነው ወንጌል በዮሐንስ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የታጀበው ወንጌል ነው፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡3-7)   
ጴጥሮስም እንደዚሁ ውብ በሆነው ወንጌል አመነና እንዲህ አለ፡- ‹‹ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡ የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ አይደለም፤ ለእግዚአብሄር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፡፡ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ነው፡፡›› (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ውሃ›› ብዙውን ጊዜ የሚጠቁመው ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀት ነው፡፡ 
መንፈስ ቅዱስ መቀበል የሚችሉ ሰዎች ውብ በሆነው ወንጌል አማካይነት ቤዛነትን ተቀብለው ከሐጢያት ሁሉ ነጻ ናቸው፡፡ ውብ በሆነው ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ምሪት አብን በመንፈስና በእውነት ያመልካሉ፡፡ (ዮሐንስ 4፡23) መንፈስ ቅዱስ ጻድቃን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ሕይወታቸውን እንዲኖሩ ያግዛቸዋል፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ያላቸው ሰዎች ጌታን እያመሰገኑ ለዘላለም መኖር ይችላሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር ልጆች ለመሆናችን ዋስትና ይሰጣል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ለዘላለም እንኖራለን፡፡
 
 

መንፈስ ቅዱስ ራሳቸውን ከሚያስቱ ጋር ሕብረት የለውም
 

መንፈስ ቅዱስ በ1ኛ ዮሐንስ 1፡8 ሐጢያተኞችን ይናገራቸዋል፡፡ 
‹‹ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም፡፡›› መንፈስ ቅዱስ ራሳቸውን በሚያስቱ ሰዎች ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሐጢያተኞችን ‹‹በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በተከናወነው ውብ የሆነ ወንጌል ለምን አታምኑም?›› በማለት ይወቅሳቸዋል፡፡ 
ያለ ኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማስረጃ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበሉ መጀመሪያ ላይ ያመነ አንድ ዳግም የተወለደ ክርስቲያን የሰጠውን ምስክርነት እንመከታለን፡፡ ይህ ሰው አሁን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምኖ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎዋል፡፡ እዚህ ላይ መንፈስ ቅዱስ በማን ውስጥ እንደሚኖር በትክክል መጠቆም ይገባናል፡፡ 
‹‹እግዚአብሄር በውስጤ መኖር የጀመረው እኔ በዚህ ምድር የምኖርበትን ምክንያት በተረዳሁበት ወቅት ነው፡፡ ራሴን ስመለከት በዚህ አስቀያሚ አለም ላይ ለመኖር ያለኝ አለመነሳሳት እግዚአብሄርን እንድራብ እንዳደረገኝ አስባለሁ፡፡ እግዚአብሄርን ለማግኘት አላሰስኩም፡፡ ነገር ግን እርሱ ባይታይም እዚያው ስላለ የእርሱን ኑባሬነት ተቀበልሁ፡፡ በእርግጥ ‹እርሱ በእርግጥ አለ› ብዬ ራሴን ጠየቅሁ፡፡ ነገር ግን እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ለመሆኑ ጽኑ እምነት ስለነበረኝ ይህንን ማሰቡ እንኳን አስፈራኝ፡፡
እግዚአብሄርን የማይቀበሉ ሰዎች ሞኞች ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ መንገዶች ከእኔ ይልቅ ብርቱ ናቸው፡፡ እነርሱ በራሳቸው በማንኛውም ነገር ውስጥ ማለፍ የሚችሉ ይመስላሉ፡፡ በሌላ በኩል እኔ ልክ እንደ ደካማ ሞኝ ታየሁ፡፡ ነገር ግን ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ተስፋዎች ስለነበሩኝ እግዚአብሄርን ይበልጥ በላቀ ክብር ተመለከትሁ፡፡ ሰማይ ሁልጊዜም ጉድለት ለሚሰማው እንደ እኔ ላሉ ሰዎች የተዘጋጀ ስፍራ ስለመሆኑ ጥያቄ አለኝ፡፡ ያ ጥያቄ ሰማያዊውን ገነት ከልቤ እንድመኝ አደረገኝ፡፡
ቤተሰቦቼ ሐይማኖት ያላቸውን ሰዎች ይንቁ ነበር፤ የእኔ ወንድሞችም ቤተክርስቲያን ይሄዱ የነበሩት ቀናዒነት ሳይኖራቸው ነው፡፡ እኔ ለቤተክርስቲያን ያለኝ ቀናዒነትም ፈጥኖ እንደሚሞት ስላሰቡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከምገባ ድረስ ወደ ቤተክርስቲያን ከመሄድ አላቆሙኝም፡፡ ስለዚህ ከቤተክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን ሄድሁ፡፡ በመጨረሻም ኮሌጅ እስከምገባ ድረስ ቤቴ አጠገብ ወዳለች ትንሽዬ ቤተክርስቲያን መሄድ ጀመርሁ፡፡  
በዚህች ቤተክርስያን ላይ መገኘት የፈለግሁበት ምክንያት በወንጌል ላይ ጠንከር ያለ ትኩረት ስለምታደርግ ነበር፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃሎች የሚጥስ አንዳች ነገር ያላደረገ ወንጌላዊ አነቃቂ ነበር፡፡ በትምህርት ጥናቶቼ ውጥረት ውስጥ ብሆንና ብጨናነቅም እንኳን ሐይማኖታዊ ሕይወትን በታማኝነት ለመምራት ምክንያቶች ነበሩኝ፡፡ 
ለዚህ ምክንያቱ ሰዎች አብረውኝ ያሉትን የቤተክርስቲያን አባሎች አሕዛቦች ብለው በሚጠሩበት ጊዜ እኔ ቤተክርስቲያኔ ትክክል እንደነበረችና ሰማይ መግባቴም እንደዚሁ የተረጋገጠ መሆኑን ማመኔ ነው፡፡ ያ በእርግጥም የተመሰረተው በወንጌል ላይ ነበር፡፡ እነርሱ ሐጢያተኞች ወደ ሰማይ ደጆች መግባት አይችሉም ይላሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች ቤተክርስቲያናት ሰዎችም ልቦቻቸው በሐጢያት እንደተሞሉ ይናገራሉ፡፡ እኔም እንደዚሁ ቤተክርስቲያን ከማዘውተሬ በፊት የእኔም ቤተክርስቲያን ሰዎች ሐጢያተኞች እንደነበሩ አመንሁ፡፡ ከዚህ የተነሳ በዚህ ወቀሳ ላይ ብዙም አላሰብኩበትም፡፡         
ነገር ግን እነዚያ ወንጌላውያን አነቃቂዎች ተብዬዎች እኔ ከዚህ ቀደም ከተለማመድሁት የተለዩ ነበሩ፡፡ እነርሱ በትክክለኛው መንገድ በኢየሱስ አምነን ከሆነ ሐጢያት አልባ ነን፤ ሰማይ የሚገቡትም ሐጢያት አልባ የሆኑት ብቻ ናቸው ይላሉ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ፍትህን ስላመጣልን ጻድቅ ሰዎች እንጂ ሐጢያተኞች አይደለንም ይላሉ፡፡ እኔ መጀመሪያ ላይ ይህንን አላመንኩም፡፡ ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ ስሜት ሰጠኝ፡፡ ወጣት ስለነበርሁ ሰማይ መሄድ ፈልጌ ከሆነ እግዚአብሄር እንድገባ የሚፈቅድልኝ ሐጢያት አልባ ስሆን ብቻ እንደሆነ አሰብሁ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ሐጢያትን ይጸየፋልና፡፡      
ይህ ቤተክርስቲያን ከለመድሁት የተለዩ እምነቶች ነበሩት፡፡ የአምልኮ አገልግሎቶቹ ስርዓትም እንደዚሁ በጥቂቱ የተለየ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰማይ የተመረጡት ጥቂቶች ብቻ የሚገቡበት በመሆኑ በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ትክክለኛ እምነቶችን ይዘዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ በኢየሱስ ስጋና ደም ላይ ትኩረት ስለምታደርግ በየእሁዱ ሕብስት እንበላለን፤ ወይንም እንጠጣለን፡፡ ይህ ስርአት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ላይ የተመሰረተ ስለነበር ተቀበልሁት፡፡ በኋላ ግን ሰዎች በስርአቱ ውስጥ የተሳተፉት እውነተኛ ትርጉሙን ሳይረዱ እንደነበር ተረዳሁ፡፡   
መንፈስ ቅዱስ በምዕመናን ልቦችና በጻድቃን ልቦች ውስጥ እንዳደረ ጸሎቶቻቸውንም በሙሉ እንደሰማ አመንሁ፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ እንዳደረም አመንሁ፡፡ እግዚአብሄር አጋሬ እንደሆነ በጣም እርግጠኛ ነበርሁ፡፡ ያመንሁትንም በጭራሽ አልተጠራጠርሁም፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሳልፍ ልክ አጠገቤ እንዳለ አድርጌ ከእግዚአብሄር ጋር ተነጋገርሁ፡፡ ለሌላ ለማንም ሰው ልነግረው ያልቻልኩዋቸውን ነገሮች ስነግረው እንዳደመጠኝ አመንሁ፡፡ ከዚህ የተነሳ ታመንሁበት፤ በእርሱም ላይ ተደገፍሁ፡፡        
በልሳናት ለመናገር ወደ መነቃቃት ስብሰባዎች የሄዱ ሰዎች ሊገቡኝ አልቻሉም፡፡ የጾም ጸሎት አገልግሎቶች ላይ በሚገኙ ሰዎችም ሳቅሁ፡፡ እነዚህን ጥረቶች ተመለከትሁና ‹መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል እንዲህ ባለ ትርጉም የለሽ ጥረቶች ውስጥ የሚያልፉት ለምንድነው? መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ የሚመጣው ሐጢያት አልባ ሲሆኑና ሁሌም ከአንተ ጋር አብረው ሲሆኑ ነው፡፡ እነርሱ ሐጢያተኞች መሆን አለባቸው፡፡ ጥረቶች ሁሉ ቢያደርጉም መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አይወርድም› ብዬ አሰብሁ፡፡ ለእነርሱ አዘንሁላቸው፡፡ እነርሱ በጣም ሞኞች እንደነበሩ አሰብሁ፡፡ ያንን በአእምሮዬ ይዤ እኔ በወንጌል ማመኔ ምርጥ እንደነበርና የሌሎች እምነቶች በሙሉ ውሸት እንደሆነ አሰብሁ፡፡
ዕብሪተኛው ልቤ ጫፍ ላይ ደረሰ፡፡ ለ10 አመታት ያህል የራሴን ሐይማኖታዊ ሕይወት ኖርሁ፡፡ ነገር ግን ጊዜ ሲያልፍ በአእምሮዬና በልቤ ውስጥ ጥያቄዎች መነሳት ጀመሩ፡፡ ‹በመስቀሉ ደም ወንጌል ምክንያት ሐጢያት አልባ ነኝ፡፡ ነገር ግን ሌሎች ምዕመናኖችም ሁሉ እንደዚሁ ሐጢያት አልባ ናቸውን? እነርሱም ደግሞ በእርግጥ በዚህ ወንጌል ያምናሉን?› ብዬ አሰብሁ፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለምን መጠየቅ እንደጀመርሁ አላወቅሁም፡፡ ጥያቄዎቹ ዝም ብለው ወደ አእምሮዬ መጡ፡፡ ማንንም መጠየቅ አልቻልሁም፡፡ ይህ የግል እምነት ስለነበር መጣስ አይገባውም፡፡ ሌላውን ሰው መጠየቅ አስቸጋሪ ጥያቄ ይሆን ነበር፡፡      
ነገር ግን ራሴን እነዚህን ጥያቄዎች መጠየቅ ጀመርሁ፡፡ ኮሌጅ በነበርሁ ጊዜ በሐይማኖታዊ ስርዓቶች የተከለከሉ ነገሮችን ማድረግ ጀመርሁና ልቤ በጣም በመጨለሙ እምነቶቼ ማሽቆልቆል ጀመሩ፡፡ ዳግመኛ ስለ እምነቶቼ እርግጠኛ አልነበርሁም፡፡ ‹ራሴን ጻድቅ ሰው ብዬ መጥራት እችላለሁን? በእርግጥ ኢየሱስ ሐጢያቶቼን በሙሉ አንጽቶዋልን?› በዚህ ሁሉ ግራ መጋባት መካከል ራሴን ስለ መስቀሉ ወንጌል እንዲያስብ አስገደድሁትና ራሴንም በዚህ ወንጌል አሳመንሁት፡፡ ነገር ግን ራሴን ይበልጥ ባስጨነቅሁ ቁጥር ይበልጥ ጠፋሁ፡፡ ዳግመኛም በቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ላይ አልተገኘሁም፡፡ እንደ ማማኻኛም የክለብ ተግባራቶቼን አዘወተርሁ፡፡ 
በግራ መጋባትና ውዝግብ ሁሉ መካከል በመጨረሻ ከእውነቱ ጋር ተገናኘሁ፡፡ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ሰማሁ፡፡ ልክ እንደ መብረቅ በእኔ ላይ መጣ፡፡ ምቱ በጣም ታላቅ ስለነበር የማልቀስ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ነገር ግን ወንጌሉን ሳዳምጥ እሰከ አሁን ድረስ ያመንሁት በሙሉ ውሸት እንደነበር አምኜ መቀበል ነበረብኝ፡፡  
እኔ ሐጢያቶቼን በጭራሽ ወደ ኢየሱስ አላስተላለፍኩም፡፡ እርሱ ሐጢያቶቼን እንደወሰደና እኔም ሐጢያት አልባ ሰው እንደነበርሁ ያመንሁት በደብዛዛው ነበር፡፡ ጉዳዩ ግን ያ አልነበረም፡፡ ኢየሱስ ለመጠመቅ ወደዚህ አለም ለምን መጣ? ልክ እንደ ጠቦት የዋህ መሆኑን ሊያሳየን ስለፈለገ? ሰው ሆኖ መምጣቱን ለማረጋገጥ? ወይስ የማይቀረውን ሞቱን ለመተንበይ? የነበረኝ ደብዛዛ የጥምቀት እውቀት ምንም ይሁን እንዲህ ያለ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ በጭራሽ አልሜ አላውቅም፡፡ እውነቱ ኢየሱስ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በዮሐንስ መጠመቁና በዚያ ጥምቀትም ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ መተላለፉ ነው፡፡
‹ኦ! ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የተሸከመ የእግዚአብሄር በግ የሆነው ለዚያ ነው!› አሁንም እያንዳንዱ ነገር ስሜት ይሰጣል፡፡ ‹ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለሐጢያቶቼ ተፈረደበት፡፡ በልቤ ውስጥ ሐጢያት አልባ የሆንኩት ለዚያ ነው፡፡› የውሃውን (የኢየሱስ ጥምቀት)፣ የደሙን (መስቀሉ) እና የመንፈስ ቅዱስን (ኢየሱስ አምላክ መሆኑ) ወንጌል ባወቅሁበት ቅጽበት በልቤ ውስጥ የተሰሙኝ ሐጢያቶች በነኑ፡፡   
አሁን በእርግጥም ሐጢያት አልባና ጻድቅ ሰው ነኝ፡፡ በመጨረሻም መንፈስ ቅዱስ በውስጤ አደረ፡፡ በመስቀሉ ላይ የነበረኝ እምነት በልቤ ውስጥ የነበሩትን ሐጢያቶቼን ለማንጻት በቂ አልነበረም፡፡ ሐጢያቶቻችሁ እንዴት ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ በትክክል የማታውቁ ከሆነ ሐጢያቶቻችሁ ይቅር ሊባሉ አይችሉም፤ መንፈስ ቅዱስም በውስጣችሁ ሊኖር አይችልም፡፡ እኔ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የቻልኩት ውብ በሆነው ወንጌል አማካይነት ነው፡፡
እኔ ያለ ምንም ጥረት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ይቅርታን አገኘሁ፡ መንፈስ ቅዱስም አሁንና ለዘላለም በውስጤ ይኖራል፡፡ አሁን ራሴን በኩራት ሐጢያት አልባ ሰው ብዬ መጥራት እችላለሁ፡፡ መንግስተ ሰማይም የእኔ በመሆኑ መኩራት እችላለሁ፡፡ እንዲህ ያለውን በረከት ያለ ምንም ክፍያ ስለሰጠን ጌታን ለማመስገን ይህንን ዕድል እጠቀማለሁ፡፡ ሐሌሉያ!›› 
መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት አልባ መሆናቸውን መናገር ይችላሉ፡፡ ምንም ያህል ለረጅም ጊዜ በኢየሱስ ያመናችሁ ብትሆኑም እግዚአብሄር በሰጠን ውብ በሆነው ወንጌል የማታምኑ ከሆነ በእርግጠኝነት በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት አለ፡፡ እንደዚያ ያሉ ሰዎች ራሳቸውን እንደዚሁም እግዚአብሄርን እያታለሉ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ጌታን በፍጹም አልተገናኙትም፡፡ አንድ ሐጢያተኛ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖረው የሚፈልግ ከሆነ በመጀመሪያ ራሱን ማታለል ማቆምና ሐጢያት እንደሰራ መናዘዝ አለበት፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለማመን ብቁ የሚሆነው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ውብ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ብቁ ናቸው፡፡   
መንፈስ ቅዱስ ለሐጢያተኞች ምን ይላቸዋል? በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የታጀበውን ውብ የሆነ ወንጌል በማመን ለሐጢያቶቻቸው ይቅርታን እንዲቀበሉ ይመክራቸዋል፡፡ ሐጢያት ሰርታችሁ ሳለ ሐጢያተኛ እንዳልሆናችሁ የምትናገሩ ከሆነ በጭራሽ መንፈስ ቅዱስን አትቀበሉም፡፡ ውብ በሆነው ወንጌል የማያምኑና ሐጢያት እንዳልሰሩ የሚናገሩ ሰዎች ራሳቸውንና እግዚአብሄርን ያታልላሉ፡፡ ሐጢያተኞች ውብ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማወቅና መንፈስ  ቅዱስን መቀበል አለባቸው፡፡ ከእግዚአብሄር ከባድ ፍርድ መዳን የሚችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡    
 

 
ቅዱሳን ሐጢያቶቻቸውን በመናዘዝ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው ይችላል
 

በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምኑና በዚህም መንፈስ ቅዱስን ለተቀበሉት ሰዎች እናገራለሁ፡፡ እግዚአብሄር ለጻድቃን የተናገረውን እንመልከት 1ኛ ዮሐንስ 1፡9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡›› ይህ ጥቅስ ማለት ተጨባጭ ሐጢያቶቻችንን ከረከሱት ልቦቻችን ማንጻት የምንችለው ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና በመሰቀልም ለእነዚያ ሐጢያቶች ስርየት መስጠቱን ያወጀውን ውብ የሆነ ወንጌል ራሳችንን ማስታወስና ማመን ማለት ነው፡፡ ጻድቃን ተጨባጭ ሐጢያቶቻቸውን ለእግዚአብሄር መናዘዝ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው የሚችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ጻድቃን ተጨባጭ ሐጢያቶቻቸውን መናዘዝና ውብ በሆነው ወንጌል በማመን መቀጠል ይገባቸዋል፡፡  
ከረጅም ጊዜ በፊት የኢየሱስ ጥምቀትና የደሙ ውብ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አነጻ፡፡ ስለዚህ ጻድቃን በዚህ ወንጌል ማመንና ከሐጢያቶቻቸው በሙሉ ነጻ መውጣት ይገባቸዋል፡፡ ጌታ ቀድሞውኑም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ ይቅር ብሎዋል፡፡ ጻድቃን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ነጻ ለመውጣት ውብ በሆነው ወንጌል ማመን አለባቸው፡፡ ጻድቃን በተጨባጭ ሐጢያቶቻቸው በረከሱ ጊዜ ውብ በሆነው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ልቦቻቸውን ማንጻት ይችላሉ፡፡ 
ጌታችን በጥምቀቱና በደሙ ከረጅም ጊዜ በፊት የጻድቃንን ሐጢያቶች በሙሉ አነጻ፡፡ ስለዚህ የሚያምኑ ሰዎች በእርግጥም ከሐጢያቶቻቸው በሙሉ ነጻ ናቸው፡፡ ሆኖም ጻድቃን በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያቶቻቸውን መናዘዝና አምነው መቀበል ይገባቸዋል፡፡ ከዚያም ጻድቃን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ነጻ ለመውጣት ውብ የሆነውን ወንጌል ወዳዋቀረው የኢየሱስ ጥምቀትና የደሙ እምነት መመለስ አለባቸው፡፡ ስለዚህ እነርሱ ሁሌም በመንፈስ ቅዱስ የታጀበ ትኩስ አዲስ ሕይወት መምራት ይችላሉ፡፡ ለድካሞቻቸው ሳይጨነቁ ወደ ጌታ መመልከት የሚችሉ ሰዎች ውብ ለሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ምስጋና ይሁንና ከእግዚአብሄር ጋር እውነተኛ ሕብረት ሊኖራቸው ይችላል፡፡  
 
 
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እውነተኛ ሕብረት የማድረግ ስሜት ላይ እንዴት መድረስ እንችላለን?
 
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ ቢያምኑም ይህንን ፍላጎት እንዴት ተግባራዊ እንደሚያደርጉት አያውቁም፡፡ ሰዎች ሁሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን መንፈስ ቅዱስን መቀበልና ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው ይችላል፡፡   
ልክ እንደዚሁ ጻድቅ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖረው የሚችለው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት ሲያውቅና ሲያምን ነው፡፡ በጻድቃንና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ሕብረት ያለ እውነተኛው ወንጌል ሊደረስበት አይችልም፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ማድረግን በሚመለከትስ? ይህ መሆን የሚችለው ውብ በሆነው ወንጌል እውነት በማመን ነው፡፡
 
 
እግዚአብሄር ሰው በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሐጢያትን እንደሚያደርግ ይናገራል
 
1ኛ ዮሐንስ 1፡10 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ ቃሉም በውስጣችን የለም፡፡›› በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት ያላደረገ ማንም የለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንኳን እንዲህ ይላል፡- ‹‹በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ ሐጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ የለም፡፡›› (መክብብ 7፡20) ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያትን ይሰራሉ፡፡ ሐጢያት አልሰራሁም የሚል ሰው ካለ እርሱ ውሸታም ነው፡፡ ሰዎች እስከ ዕለተ ሞት ሰአታቸው ድረስ በሕይወታቸው ሁሉ ሐጢያትን ይሰራሉ፡፡ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ ለመሸከም ኢየሱስ በዮሐንስ የተጠመቀው ለዚህ ነው፡፡ ሐጢያት ካልሰራን እግዚአብሄርን አዳኛችን አድርገን ማመን አያስፈልገንም ነበር፡፡   
ጌታ ሐጢያት እንዳልሰሩ የሚያስቡትን ሰዎች ‹‹ቃሌ በውስጣችሁ የለም›› ይላቸዋል፡፡አንድ ሰው ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እምነት ከሌለው ጥፋት ይገባዋል፡፡ አንድ ጻድቅ ወይም ሐጢያተኛ ሰው በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት እንዳልሰራ የሚናገር ከሆነ ውብ በሆነው ወንጌል ማመን አይገባውም፡፡  
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ውብ የሆነው አስደናቂ የወንጌል ስጦታ ሰጠ፡፡ ውብ በሆነው ወንጌል የሐጢያቶችን ይቅርታ ለመቀበል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ተናዘዝንና ንስሐ ገባን፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ይኖረን ዘንድም እግዚአብሄር የሐጢያቶቻችን ይቅርታ አድርጎ ወደለገሰን ውብ ወንጌል መመለስ ቻልን፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚደረግ እውነተኛ የሕብረት ስሜት ያለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ሕብረት ሊኖራቸው የሚችለው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡  
የሰው ዘር ከአዳምና ከሔዋን በወረሰው ሐጢያቶች ምክንያት ከእግዚአብሄር ራቀ፡፡ አሁን ግን የሐጢያትን ዘር የወረስነው እኛ እንደገና ከእግዚአብሄር ጋር ሕብረት ለማድረግ አርቀን መመልከት እንችላለን፡፡ ያንን ለማድረግም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የውሃና የመንፈስ ወንጌል እምነት መመለስና ከእግዚአብሄር ላራቁን ሐጢያቶች ይቅርታን ማግኘት አለብን፡፡
ውብ በሆነው ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይድናሉ፤ እግዚአብሄርም በመንፈስ ቅዱስ ይሞላቸዋል፡፡ ጻድቃን መንፈስ ቅዱስን ስለተቀበሉ ከእግዚአብሄር ጋር ሕብረት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ከእግዚአብሄር የተቆረጡ ሰዎች ውብ ወደሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል መመለስና በእርሱ ማመን አለባቸው፡፡ 
ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው ውብ በሆነው ወንጌል በሚያምን እምነት ነው፡፡ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ የሚመጣው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ ውብ በሆነው ወንጌል ማመን ወደ እግዚአብሄር የሚወስድ አዲስ ጎዳና ፈጠረ፡፡ ጌታ በጥንተ አብሶና (የአዳም ሐጢያት) በተጨባጭ ሐጢያቶች ምክንያት ከእርሱ የለየንን በመካከል ያለውን ግድግዳ አፈረሰና ውብ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እምነታችን በኩል ከእግዚአብሄር ጋር ሕብረት እንዲኖረን ፈቀደልን፡፡
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዳግመኛ ሕብረትን መመስረት አለብን፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እውነተኛ ሕብረት የሚደረገው እምነትን ለመታዘዝ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመረዳት አማካይነት ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት የሚደረገው የሐጢያቶቻችን ይቅርታ የሚመጣው ውብ ከሆነው ወንጌል በመሆኑ እውነታ ነው፡፡ የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ ያልተቀበሉ ሰዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ በሌላ አነጋገር ማንም ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ሊኖረው አይችልም፡፡
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት ይኖራችሁ ዘንድ አዳጋች የሚሆንባችሁ ከሆነ በመጀመሪያ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንዳላመናችሁና ሐጢያቶቻችሁም ይቅር እንዳልተባሉ መቀበል ይገባችኋል፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረት እንዲኖራችሁ ትመኛላችሁን? እንግዲያውስ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በተከናወነው ወንጌል እመኑ፡፡ ለሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ይቅርታን የምታገኙትና ሽልማት ይሆናችሁ ዘንድም በልባችሁ ውስጥ መንፈስ ቅዱስን የምትቀበሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህ ውብ የሆነው ወንጌል በእርግጠኝነት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሕብረትን እንድታደርጉ ያስችላችኋል፡፡