Search

關於基督教信仰的常見問題解答

話題 3:启示錄

3-11. ኢየሱስ ቅዱሳኖችን ለመንጠቅ ይመጣል፤ እንደዚሁም የአርማጌዶንን ጦርነት ለመዋጋት ወደዚህ ምድር ይወርዳል ብለሃል፡፡ ጌታ በዚህ ምድር ላይ ሁለት ጊዜ ይወርዳል እያልህ ነውን? በእነዚህ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው? 

ኢየሱስ ቅዱሳንን ለመንጠቅ ከሰማይ ወደ አየር መውረዱና በአርማጌዶን ጦርነት አማካይነት በዲያብሎስ ላይ ለመፍረድ ወደዚህ ምድር መምጣቱ እርስ በርሳቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ 
የታላቁ መከራ የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት ተኩል ሲያበቁና በጸረ ክርስቶስ መገለጥ ከሚሆነው የቅዱሳን ሰማዕትነት በኋላ ወዲያውኑ ጌታ ከሰማይ ይወርዳል፡፡ በዚህ ጊዜ በመቃብሮቻቸው ውስጥ ያንቀላፉ ቅዱሳኖችና የአውሬውን ምልክት ሳይቀበሉ እምነታቸውን በመጠበቅ በመከራው ውስጥ አልፈው በሕይወት የተረፉ ሁሉም ትንሳኤን አግኝተው ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ፡፡ ጌታንም በአየር ላይ ይገናኙታል፡፡ ከዚህ ቅጽበት ጀምሮ ቅዱሳን ሁልጊዜም ከጌታ ጋር ይሆናሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታ ወደ ምድር አይወርድም፡፡ ለምን? ምክንያቱም በሰይጣንና በጸረ ክርስቶስ ላይ የሚፈርዱት የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች በዚህ ምድር ላይ መውረዳቸውን ይቀጥላሉና፡፡ 
ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ተሰሎንቄ 4፡17 ላይ እንዲህ ነግሮናል፡- ‹‹ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡›› ጸረ ክርስቶስን ተዋግተው እምነታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ሰማዕት የሆኑት ቅዱሳን የመጀመሪያውን ትንሳኤ ያገኛሉ፡፡ ጌታን በዚህ ምድር ላይ ሳይሆን በአየር ይገናኙታል፡፡ የእነርሱ ሙሽራ ከሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰማይ ወደሚሆነው የበጉ ሰርግ ይገባሉ፡፡ 
ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር ከፍጥረት ጀምሮ በትዕግስት የያዛቸውን በእግዚአብሄር ቁጣ የተሞሉ የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶች በዚህ ምድር ላይ በቀሩት በክርስቶስ ተቃዋሚ፣ በተከታዮቹና በሐጢያተኞች ሁሉ ላይ እንዲያፈስሱ መላእክቶቹን ያዛቸዋል፡፡ ስለዚህ ዓለም ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ ከፍተኛ መቅሰፍቶች ይገጥሙዋታል፡፡ ጌታን በአየር የተገናኙት ቅዱሳን አሁን በዚህ ምድር ላይ ስለወረዱት የሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶች ጌታን በአየር ላይ ሆነው ያመሰግኑታል፡፡ 
እነርሱም በጌታ አማካይነት የመጀመሪያ ትንሳኤያቸውንና ንጥቀታቸውን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሄር በዚህ ምድር ላይ ያመጣውን የጽድቅ ፍርድ ለማወደስ በእሳት በተቀላቀለወ የብርጭቆ ባህር ላይ ይቆማሉ፡፡ ስለዚህ ሰማዕት የሆኑትና በጌታ ሐይል ትንሳኤን አግኝተው የተነጠቁት ቅዱሳን እርሱ ለሰጣቸው ደህንነት ሁሉን በሚያውቀውና ሁሉን በሚገዛው ሐይሉ በጸረ ክርስቶስና በባርያዎቹ ላይ ለፈረደው ፍርድ ጌታን ያለ መቋረጥ ያመሰግኑታል፡፡ 
ሰባቱን ጽዋዎች የያዙት መላእክቶች እያንዳንዱን ጽዋ ሲያፈስሱ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር እያንዳንዱ ሰው የሚነዘንዝ ቁስል ባመጣው መቅሰፍት በአያሌው ይሰቃያል፡፡ በባህር ላይ የሚወርደው መቅሰፍትም ባህሩን ወደ ደም ይቀይረዋል፡፡ የጸሐይ ሙቀት የሚያቃጥልበት መቅሰፍትም አለ፡፡ ጨለማና ስቃይ የሚያመጣም መቅሰፍት ይወርዳል፡፡ ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ ሲያፈስስ ውሃው ይደርቃል፡፡ ከምስራቅ ለሚመጡ ነገሥታቶችም መንገድ ይዘጋጃል፡፡ በዚህ መቅሰፍትም በመላው ምድር ላይ ታላቅ ረሃብ ይከሰታል፡፡ በሰው ዘር ላይም እጅግ ታላቅ የሆነ መከራን ያመጣል፡፡ አጋንንቶችም በጸረ ክርስቶስና በሐሰተኛው ነቢይ አማካይነት የሰዎችን ልብ በማነሳሳት ይርመሰመሳል፡፡ 
ያን ጊዜ የአጋንንት መናፍስቶች የምድርን ነገሥታት ለጦርነት ያነሳሱዋቸዋል፡፡ ሁሉን ከሚገዛው አምላክ ጋር ይዋጉ ዘንድም አርማጌዶን ወደተባለ ስፍራ ያከማቹዋቸዋል፡፡ በሰይጣንና በእግዚአብሄር መካከል የሚደረገው የመጨረሻው ጦርነት የሚደረገው በዚህ ስፍራ ነው፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ሁሉን የሚገዛ አምላክ ስለሆነ ከጭፍሮቹ ጋር በፈረስ ላይ ተቀምጦ ከአየር በመውረድ ሰይጣንን ድል ያደርገዋል፡፡ አውሬውንም በዲን ወደሚቃጠል የእሳት ባህር ይጥለዋል፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 19፡11-12) አሁን ኢየሱስ የዳግመኛ ምጽዓት ጌታ ሆኖ ፍጹም የሆነ ሥልጣን ስላለው ዓለምን ለመፍረድና አውሬውን ለማጥፋት በዚህ ምድር ላይ ይገለጣል፡፡ 
ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን በሚነጠቁበት ጊዜ ከሰማይ ሲወርድ በአየር ላይ እንዲገናኙትና በሰማዩ የሰርግ እራት ላይ እንዲገኙ በመፍቀድ ቅዱሳኖችን እርሱ ወዳለበት ስፍራ ከፍ ለማድረግ አየር ላይ ይወርዳል እንጂ ወደዚህ ምድር አይወርድም፡፡ ጌታ ወደዚህ ምድር ሲመጣ የሚመጣው እግዚአብሄርን የሚቃወሙትን ሰይጣንንና ጭፍሮቹን በአርማጌዶን ጦርነት በሐይሉ ቃል አማካይነት ለማሸነፍ፣ ዲያብሎስንም በዲን ወደሚቃጠል እሳት ለመጣልና የእርሱን ቅሪተ ተከታዮች በሙሉ ለማጥፋት ነው፡፡ ይህ የጌታ ዳግመኛ ምጽዓት ነው፡፡ ጌታ በአየር ላይ በመውረዱና በምድር ላይ ዳግመኛ በመምጣቱ መካከል መለየት የሚችል ትክክለኛ እውቀትና እምነት ያስፈልገናል፡፡ 
ሆኖም ብዙ ሰዎች ጌታ ንጥቀት በሚሆንበት ጊዜ ፈጥኖ ወደ ምድር እንደሚወርድ ያስባሉ፡፡ ይህ ትክክል እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ንጥቀት በሚሆንበት ጊዜ ጌታ አየር ላይ ይሆናል እንጂ ወደ ምድር አይመጣም፡፡ በሌላ አነጋገር ቅዱሳኖችን በአየር ላይ ከፍ ያደርጋቸውና ይቀበላቸዋል፡፡ 
ስለዚህ ጌታ በንጥቀት ዘመን እንደገና ወደዚህ ምድር ይመጣል የሚለውን አስተሳሰብ ልታስወግዱ ይገባችኋል፡፡ በምትኩ በተጻፈው ቃል ላይ በመመስረት የቅዱሳን ንጥቀት የሚመጣው ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ሲነፋ እንደሆነ መረዳት ይገባችኋል፡፡