Search

關於基督教信仰的常見問題解答

話題 4:讀者的經常提問及解答

4-1. በመጽሐፍህ ውስጥ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ለአንዴና ለመጨረሻ የሐጢያት ስርየትን መቀበል እንደምንችል ጽፈሃል፡፡ ታዲያ በጌታ ጸሎት ውስጥ ‹‹እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን›› የሚለውን ምንባብ እንዴት ትተረጉመዋለህ?

የጠቀስከው ሐረግ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ጋር የሚቃረን ይመስላል፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እንደሆነና በውስጡም ተቃርኖ እንደሌለው ታምን ይሆናል፡፡
ታዲያ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስህተት ነውን? አይደለም ፈጽሞ አይደለም! 
እግዚአብሄር በመላው ቃል አማካይነት ይህ ወንጌል ብቸኛው እውነተኛና ፍጹም ወንጌል እንደሆነ ያሳየናል፡፡ 
በብሉይና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተዛምዶዎች አሉ፡፡ የብሉይ ኪዳን የመስዋዕት ስርዓት ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መስዋዕት ጋር ፈጽሞ ይዛመዳል፡፡ በመስዋዕቱ ስርዓት ውስጥ አንድ ሕጋዊ መስዋዕት ሦስት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጉታል፡- 1) ነውር የሌለበት የመስዋዕት እንስሳ 2) እጆችን መጫን 3) ደም (ምትካዊ ሞት)፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለመን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ ወደዚህ ምድር መጥቶ ሐጢያት የሌለበት በመሆን ከድንግል ማርያም በመወለድ የሰው ዘር ሁሉ ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ከዚያም የእኛን ሐጢያቶች በሙሉ ይዞ ተሰቅሎ ሞተ፡፡ ነገር ግን በሦስት ቀናት ውስጥ ከሙታን ተነሳ፡፡ እኛም ጌታ ያጠናቀቀውን ይህንን እውነት በማመን አሁን ከሐጢያቶቻችን (ያለፉ፣ አሁን ያሉና የወደፊት) ሁሉ ይቅርታን አግኝተናል፡፡
ታዲያ ‹‹እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይውር በለን›› የሚለውን ምንባብ በሚመለከትስ?
ይህ ማለት እግዚአብሄር የእርስ በርሳችንን አለመብቃቶች ይቅር ማለት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለድን ብንሆንም እንኳን አሁንም ያለነው በደካማው ስጋችን ውስጥ ነው፡፡ ብዙ ስህተቶችንም እንሠራለን፡፡ እርስ በርሳችን መተላለፎቻችንን የምንኮንና የምንገስጽ ከሆነ የእውነተኛው ወንጌል ሐይልም ሳይቀር ይደበዝዛል፤ ዳግም የተወለዱ ሰዎችም ሕብረት ይፈርሳል፡፡     .
‹በደል› የሚለው ቃል ‹ዕዳዎች› ተብሎ ሊታረም እንደሚገባ መረዳት አለብህ፡፡ እንዲያም በኒው ኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ባለ ዕዳዎቻችንን ይቅር እንደምንላቸው ዕዳዎቻችንን ይቅር በለን፡፡›› (ማቴዎስ 6፡12)
በማቴዎስ ውስጥ የጌታ ጸሎት በቀጥታ ‹‹ለሰዎች ሐጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤ ለሰዎች ግን ሐጢአታቸውን ይቅር ባትሉ አባታችሁም ሐጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም›› የሚሉ ትምህርቶችን አስከትሎዋል፡፡ 
ጌታ ኢየሱስ የጌታን ጸሎት የሰጠን እንደተጻፈው እንድናነበንበው አይደለም፡፡ ይህ ጸሎት በየቀን የእምነት ሕይወታችን ልናስታውሳቸው የሚገቡን አስፈላጊ የጸሎት ርዕሶች ስብስብ ነው፡፡
እባክህ ማቴዎስ 18፡21-35ን ተመልከት፤ ያን ጊዜ ይቅርታን ላላደረገው ባርያ የእግዚአብሄር ፈቃድ ምን እንደሆነ ወደ መረዳት ትደርሳለህ፡፡    
‹‹በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፡- እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም፡፡ ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች፡፡ መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ የሚከፍለው ቢያጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ፡፡ ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና፡- ጌታ ሆይ ታገሠኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፤ ዕዳውንም ተወለት፡፡ ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና፡- ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ፡- ታገሠኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱም አልወደደም፤ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወህኒ አኖረው፡፤ ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፤ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ፡፡ ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፡- አንተ ክፉ ባሪያ ስለለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው፡፤ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡ ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል፡፡››       
ይህ ማለት ወንድሞቻችን በሚበድሉን ጊዜ ሁሉ ሁልጊዜም ወንድሞቻችንን ይቅር ማለት አለብን ማለት ነው፤ ምክንያቱም ጌታችን በጥምቀቱና በመስቀሉ አማካይነት ያለፉትን፣ አሁን ያሉትንና የወደፊት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ቀድሞውኑም ይቅር ብሎዋል፡፡ ስለዚህ እርሱ በበኩል የእነርሱን ሐጢያቶች በሙሉ ቀድሞውኑም ይቅር ቢልም ወንድሞቻችንን ይቅር የማንላቸው ከሆነ ይቅር በማይለው ልባችን ይቆጣና በወንድሞቻችን ላይ የሰራናቸውን ሐጢያቶች ይቅር አይለንም፡፡ እርሱ በእኛ የሚደሰተው እግዚአብሄር በኢየሱስ ጥምቀተና በመስቀሉ አማካይነት ቀድሞውኑም ሁላችንንም ይቅር እንዳለን በማመን ወንድሞቻችንን ይቅር ስንል ብቻ ነው፡፡ 
ስለዚህ ምንባቡ በዚህ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ አንተ አሰቀድመህ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ይቅር ስላልህ እኛም ወንድሞቻችንን ይቅር እንላለን፡፡ ስለዚህ እባክህ በሐጢያቶቻችን አትቆጣ፡፡›› ኢየሱስ እንደዚያ የተናገረው እርሱ ቀድሞውኑም የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ያነጻ በመሆኑ መሠረት ላይ ቆሞ ነው፡፡ እንደዚያ የሚያምን ሰው ወንድሞቹ ሲበድሉት ይቅር ይላቸዋል፡፡