Search

關於基督教信仰的常見問題解答

話題 4:讀者的經常提問及解答

4-4. ኢየሱስ በዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በተጨባጭ ወሰደ ብለሃል፡፡ ታዲያ ይህ ማለት በአገልግሎት ሕይወቱ ወቅት ሐጢያተኛ ሆንዋል ማለት አይደለምን?

የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፡፡ ይህ ግን እርሱ ሐጢያተኛ ሆኖዋል ማለት አይደለም፡፡ ሐጢያቶች ወደ መንፈሱ አልተላለፉም፡፡ የተላለፉት ወደ ስጋው ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር የተላከው በሰው ስጋ ነበር፡፡ ይህ ማለት እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ የሰው ስጋ ለበሰ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አምለክ ሆኖ የዓለምን ሐጢያቶች ብቻ ተሸከመ፡፡
ኢሳይያስ 53፡6ን ተመልከት፡- ‹‹እግዚአብሄርም የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡›› ስለዚህ ሐጢያቶች ሁሉ በጥምቀቱ አማካይነት በተጨባጭ በእርሱ ላይ ተጭነው ነበረ፡፡ ሮሜ 8፡3ም እንደዚሁ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከሥጋ የተነሣ ስለደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሄር የገዛ ልጁን በሐጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በሐጢያትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፡፡ ሐጢያትን በስጋ ኮነነ፡፡››
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ ተሸከመና ወደ መስቀል ወሰዳቸው፡፡ እርሱ በአደባባይ አገልግሎቱ ወቅት በመስቀል ላይ ከመሰቀሉ በፊት ሐጢያቶችን ተሸክሞ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹በዚያን ጊዜ  ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደምትባል ስፍራ መጣ፤ ደቀ መዛሙርቱንም፡- ወዲያ ሄጄ ስጸልይ ሳለ በዚህ ተቀመጡ አላቸው፡፡ ጴጥሮስንም ሁለቱንም የዘብዴዎስን ልጆች ወስዶ ሊያዝን ሊተክዝም ጀመረ፡፡ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው፡፡ ጥቂትም ወደፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ፡- አባቴ ቢቻልህ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን አንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ፡፡›› (ማቴዎስ 26፡36-39)    
ፊልጵስዩስ 2፡6-8 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሄር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም፡፡ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፡፡ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፤ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ፡፡›› 
ምንም እንኳን ስቃይ የተሞላበት ቢሆንም ኢየሱስ የአብን ፈቃድ ለመፈጸም መሰቀል ነበረበት፡፡ ኢየሱስ የተሰቀለበት ምክንያት በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በመሸከሙ ነበር፡፡ ስለዚህ እርሱ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፡፡ (ዮሐንስ 19፡30) የኢየሱስ ጥምቀትና መስቀሉ እርስ በርሳቸው በሚገባ የተዛመዱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱ የተሟላ ደህንነት ያበጃሉ፡፡ 
   
ስለዚህ ብዙ ሰዎች እንደሚሉት የኢየሱስ ጥምቀት ምልክት ብቻ አይደለም፡፡ የደህንነት ምሳሌ ነው፡፡