• 所有新生命宣教會 The New Life Mission 網站上的電子書和有聲書均可免費下載
  • 探索以多種語言提供的全球性講道
  • 查看我們已翻譯成27種語言的網站
  • 第1、2卷新修訂版已全新推出
Search

關於基督教信仰的常見問題解答

話題 4:讀者的經常提問及解答

4-12. የዘመኑን የክርስቲያን ተዓምራቶች የምታስባቸው እንዴት ነው? የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አይደሉምን? መንፈስ ቅዱስ አሁንም በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚሠራ አስባለሁ፡፡

በዛሬዎቹ የክርስቲያን ተዓምራቶች ጉዳይ ላይ በጠየከው ጥያቄ በከፊል ትክል ነህ፡፡ 
ነገር ግን መለኮታዊ ተዓምራቶች በሙሉ ለሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ የማመን እምነት ሊሰጡዋቸው እንደሚገባ ማስታወስ ይኖርብሃል፡፡ (ዮሐንስ 2፡11) በሌላ አነጋገር ጌታ ተዓምራቶችን የሚፈቅደው ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ለመፍቀድ ነው፡፡
በሐዋርያትና በደቀ መዛሙርት በተለይም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የተፈጸሙ ብዙ ተዓምራቶችን ማግኘት እንችላለን፡፡ እነርሱ በተዓምራቶቹ አማካይነት ኢየሱስ አምላክ ለመሆኑ፣ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ ለመውሰዱና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስም ለሐጢያቶቻችን በሙሉ ካሳ ለመክፈል ለመሞቱ እውነት ያላቸውን እምነት መሰከሩ፡፡  
ነገር ግን የተጻፈው የእግዚአብሄር ቃል ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚአብሄር አብ ተዓምራዊ ማስረጃዎችን ከመሻት ይልቅ የእርሱን ቃል እንድንታዘዝ ይፈልግብናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚለው ለዚህ ነው፡- ‹‹ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል፡፡ ከእወቀት ከፍለን እናውቃለንና፤ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል፡፡›› (1ኛ ቆሮንቶስ 13፡8-10) 
  
እውነተኛ እምነት ቀድሞውኑም ከጌታ በተቀበልከው የእግዚአብሄር ቃል ላይ እንጂ በተለማመድካቸው ተዓምራቶች ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡
ወደ ዝርዝሩ ተመለስ
The New Life Mission

參加我們的調查

您是如何得知我們的?