Search

Проповіді

ርዕስ 3፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል

[3-5] እውነተኛው ዳግም የመወለድ ወንጌል ትርጉም፡፡ ‹‹ ዮሐንስ 3፡1-6 ››

እውነተኛው ዳግም የመወለድ ወንጌል ትርጉም፡፡
‹‹ ዮሐንስ 3፡1-6 ››
‹‹ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፡- መምህር ሆይ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡ መምህር ሆነህ ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሄርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው፡፡ ኒቆዲሞስም፡- ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማህጸን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው፡፡ ኢየሱስም መለሰ እንዲህ ሲል፡- እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው፡፡››      
 
 

በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ዳግም የመወለድ ትርጉም ምንድነው? 

 
ዳግም መወለድ ከሥጋዊ ስሜትና ለውጥ ጋር የተዛመደ ነውን? 
አይደለም፤ ዳግም መወለድ ተዛምዶው ከመንፈሳዊ ለውጥ ጋር ነው፡፡ ይህም ሐጢያተኛ ሐጢያት አልባ ሆኖ ሲወለድ ነው፡፡   

በዚህ ምድር ላይ በኢየሱስ በማመን ዳግም ለመወለድ የሚፈልጉ ብዙዎች አሉ፡፡ ሆኖም በመጀመሪያ ዳግም መወለድ የእኛ ጉዳይ አለመሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ በሌላ አነጋገር ዳግም መወለድ የምግባሮች ብቻ ውጤት ሆኖ ሊመጣ የሚችል አንዳች ነገር አይደለም፡፡ 
ብዙ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ የተሳሳተ እሳቤ አላቸው፡፡ ዳግም እንደሚወለዱ እርግጠኞች እንደሆኑ ያምናሉ፡፡ እንዲህ የሚያምኑት ከሌሎች መካከል በተከታዮቹ ምክንያቶች ነው፡- አንዳንዶች ብዙ አዳዲስ ቤተክርስቲያናትን በመገንባት ደህንነትን ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ አንዳንዶች እጅግ ራቅ ባሉ ስፍራዎች ገና የኢየሱስ ቃል ባልደረሳቸው ሕዝቦች መካከል ሚሲዮናውያን ሆነው ክርስቶስን ለመስበክ ራሳቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሌሎችም ትዳር መመስረትን እምቢኝ ብለው የእግዚአብሄር ሥራ ነው ብለው የሚያምኑትን እየሰሩ ጉልበታቸውን ይፈጃሉ፡፡     
ይህ ብቻ አይደለም፤ ለቤተክርስቲያኖቻቸው በርካታ ገንዘብ የሚለግሱ ሰዎችም አሉ፡፡ ወይም ምናልባት በየቀኑ የቤተክርስቲያናቸውን ወለል ይጠርጋሉ፡፡ በአጠቃላይ ጊዜያቸውንና ንብረታቸውን ለቤተክርስቲያን ያውላሉ፡፡ እነዚህ ጥረቶች ሁሉ የሕይወትን አክሊል እንደሚያስገኝላቸው ያምናሉ፡፡ እግዚአብሄር ጥረቶቻቸውን እንደሚቀበልላቸውና ዳግም ይወለዱ ዘንድ እንደሚፈቅድላቸው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡   
ጉዳዩ ዳግም ለመወለድ የሚሹና ራሳቸውን የሰጡ በርካታ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ እነዚህ በየቦታው ይገኛሉ፡፡ አንድ ቀን እግዚአብሄር እንደሚባርካቸውና ዳግም ይወለዱ ዘንድ እንደሚፈቅድላቸው ተስፋ በማድረግ ተግተው ይሰራሉ፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማቶች፣ ሴሚናሪዎችና ሳናቶሪዬሞች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነርሱ ዳግም ስለመወለድ እውነቱን አለማወቃቸው የሚያሳዝን ነው፡፡   
ሁሉም የሚያስቡት ከምግባሮቻቸው አንጻር ነው፡- ‹‹ይህንን ያለ እንከን ባደርግ ዳግም እወለዳለሁ፡፡›› ዳግም ለመወለድ አስፈላጊ የሆነውን መሰረት እየገነቡ እንደሆነ በማመን ጥረቶቻቸውን በሙሉ በእነዚህ ሥራዎች ላይ ያውሉና ‹‹እኔም ልክ እንደ ሬቨረንድ ዌዝሊ አንድ ቀን ዳግመኛ እወለዳለሁ!›› ብለው ያስባሉ፡፡ ዮሐንስ 3፡8ን ካነበቡ በኋላ ጥቅሱ የዳግም ውልደት በረከት ከየት እንደሚመጣ ወይም ወዴት እንደሚሄድ ማንም ሊያውቅ አይችልም የሚል ነው በማለት ይተረጉሙታል፡፡  
ስለዚህ ኢየሱስ አንድ ቀን ዳግም እንዲወለዱ እንደሚፈቅድላቸው ተስፋ በማድረግ ጠንክረው ብቻ መስራት ይችላሉ፡፡ ‹‹በዚህ ሁኔታ ሙከራዬን ከቀጠልሁ አንድ ቀን ኢየሱስ ዳግም እንድወለድ ይፈቅድልኛል፡፡ ዳግም መወለዴን እንኳን ሳላውቅ ዳግም እወለዳለሁ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ዳግም ተወልጄ ከእነቅልፌ እነቃለሁ፡፡ ሰማይ እንደምገባም አውቃለሁ›› ብለው የሚያስቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ተስፋዎችና እምነት ምንኛ ፍሬ ቢስ ናቸው!   
በዚህ መንገድ መቼም ቢሆን ዳግም ልንወለድ አንችልም! ከሲጋራና ከመጠጥ ስለተላቀቅን ወይም ደግሞ ቤተክርስቲያን ስለሄድን ብቻ ዳግም ልንወለድ አንችልም፡፡ ኢየሱስ እንዳለው ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ለመግባት ‹‹ከውሃና ከመንፈስ መወለድ አለብን፡፡›› ውሃውና መንፈሱ ዳግም ለመወለድ የእግዚአብሄር ብቸኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ 
ሰው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም እስካልተወለደ ድረስ በኢየሱስ ፊት ጻድቅ ለመሆን የሚያደርጋቸው ጥረቶች በሙሉ ከንቱ ናቸው፡፡ ሰው መባዎችንና ስጦታዎችን በመስጠት ወይም ቀናዒ በመሆን ዳግም ሊወለድ አይችልም፡፡ ሰው ምናልባትም ዳግም የተወለደውንና ያልተወለደውን የሚያውቀው እግዚአብሄር ብቻ ስለሆነ እርሱ ዳግም መወለድ ወይም አለመወለዴን ማወቅ አልችልም ብሎ ያስብ ይሆናል፡፡  
በዚህ መንገድ ማሰብ መጽናናትን ይሰጥ ይሆናል፤ ነገር ግን ዳግመኛ መወለድ ከጠረጴዛ ስር ሊደበቅ አይችልም፡፡ ሰው ይህንን በእርግጠኝነት ራሱ ያውቀዋል፤ ሌሎችም እንደዚሁ ስሜቱ ይሰማቸዋል፡፡    
ምናልባት በአካላዊ መንገድ ስሜቱ አይሰማን ይሆናል፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ መንገድ በእርግጠኝነት ይታወቀናል፡፡ ከልብ ዳግመኛ የተወለዱት በእግዚአብሄር ቃል ማለትም በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ቃሎች አማካይነት ዳግም የተወለዱ አማኞች ናቸው፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ ያልተወለዱ ኒቆዲሞስ እንዳላስተዋለ ሁሉ ይህንን አያስተውሉትም፡፡   
ስለዚህ የእውነትን ቃሎች ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በኩል የመጣውን ቤዛነት ማድመጥ አለብን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስናደምጥና ስንማር በውስጡ ያለውን እውነት ማግኘት እንችላለን፡፡ ስለዚህ አእምሮዎቻችንን መክፈትና በጥንቃቄ ማድመጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡  
‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምጹንም ትሰማለህ፡፡ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፡፡ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው፡፡›› (ዮሐንስ 3፡8) 
ዳግም ያልተወለደ ሰው ይህን ምንባብ በሚያነብበት ጊዜ ‹‹አሃ! እኔ መቼ ዳግም እንደምወለድ ማወቅ እንደማልችል ኢየሱስ ተናግሮዋል!›› በማለት ያስባል፡፡ ሐሳቡ ምቾት ይሰጣል፡፡ ይህ ግን እውነት አይደለም፡፡ ነፋስ ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ አናውቅ ይሆናል፤ እግዚአብሄር ግን ሁሉን ያውቃል፡፡ 
ዳግም በተወለዱትም መካከል እንዲሁ በመጀመሪያ ላይ የማያስተውሉ አንዳንዶች አሉ፡፡ ይህ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ባለው ግለሰብ ልብ ውስጥ ወንጌሉ ማለትም በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ቤዛነትን የማግኛው ቃሎች አሉ፡፡ 
ይህ ዳግመኛ የመወለድ ምስክርነት ነው፡፡ ወንጌልን የሚሰሙ እንዲህ ያለ ግንዛቤ አላቸው፡- ‹‹ኦ! ሐጢያት የለብኝም፡፡ ስለዚህ ድኜ ዳግም ተወልጃለሁ፡፡›› የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሲያምኑና በልባቸው ውስጥ ሲቀበሉ ጻድቅ ማለትም የእግዚአብሄር ልጅ ይሆናሉ፡፡ 
አንድ ሰው ‹‹ዳግም ተወልደሃልን?›› ተብሎ ሲጠየቅ ‹‹ገና ነኝ›› ብሎ ይመልስ ይሆናል፡፡ ‹‹ታዲያ ድነሃልን?›› ‹‹አዎን እንደዳንሁ አምናለሁ፡፡›› ነገር ግን የተናገረው እርስ በርሱ የሚቃረን አባባል ነው፡፡ አይደለምን? እንደዚህ ያመነው አንድ ሰው ዳግም ሲወለድ በሥጋውም መለወጥ ይኖርበታል ብሎ ስላሰበ ነው፡፡  
እንደዚህ ያሉ ሰዎች ዳግም መወለድን ስር ነቀላዊ የሆነ የአኗኗር ለውጥ እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል፡፡ እውነቱ ግን እነዚህ ሰዎች ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድን ወንጌል ያልተረዱ መሆናቸው ነው፡፡  
ዳግም የመወለድን ትርጉም ያልተረዱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ በዚህ መታለል ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ተራ ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን መሪዎችም ጭምር ናቸው፡፡ እኛ ዳግም የተወለድን ለእነዚህ ሰዎች ከልባችን እናለቅስላቸዋለን፡፡ 
እኛ ይህን ያህል ካዘንን በሰማይ ያለው ኢየሱስ ምን ያህል ሕመም ይሰማው ይሆን? ሁላችንም በኢየሱስ የጥምቀትና የመስቀሉ ላይ ደም ወንጌል በማመን ዳግም እንወለድ፡፡
ዳግም መወለድ ማለትና መዳን ማለት ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሆኖም ይህን እውነት የማያውቁ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ዳግም መወለድ ማለት በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ሐጢያት ከውሃና ከመንፈስ በሆነው ወንጌል በማመን ነጽቶዋል ማለት ነው፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ በከፈለው መስዋዕትነት ማመን ጻድቅ መሆን ማለት ነው፡፡
ሰዎች ዳግም ከመወለዳቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ሐጢያተኞች ሲሆኑ ዳግም ከተወለዱ በኋላ ግን በገሃድ ሐጢያት የሌለባቸው አዲስ ሰው ይሆናሉ፡፡ በደህንነት ወንጌል በማመን የእግዚአብሄር ልጅ ሆነዋል፡፡ 
ዳግም መወለድ ማለት የኢየሱስን ጥምቀት ልብሶች መልበስ፣ በመስቀል ላይም አብሮ መሰቀልና በትንሳኤውም አብሮ መነሳት ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰው በጥምቀቱና በኢየሱስ መስቀል ቃሎች አማካይነት ጸድቋል ማለት ነው፡፡  
አንድ ሰው ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጀምሮ ሐጢያተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሰው ከውሃና ከመንፈስ የመወለድን እውነተኛ ወንጌል ሲሰማ ያን ጊዜ ዳግም ይወለድና ይጸድቃል፡፡ 
እንደዚህ ያለ ሰው ከውጪ ሲታይ የተለየ ሰው ላይመስል ይችላል፡፡ በውስጥ መንፈሱ ግን ዳግም ተወልዶዋል፡፡ ዳግም መወለድ ማለት ይህ ነው፡፡ ይህንን እውነት የሚያውቁት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከአስር ሺህ አንድ እንኳን አይሆኑም፡፡ እውነተኛውን የዳግም ውልደት ትርጉም የተረዱት በጣም ጥቂቶች ስለመሆናቸው ከእኔ ጋር ልትስማሙ ትችላላችሁን?  
በውሃና በመንፈስ የሚያምኑና ዳግም የተወለዱ ሰዎች በተጨባጭ ዳግም የተወለዱትን ከተራ ክርስቲያኖች መለየት ይችላሉ፡፡ 
 
 
ነፋሱን የሚቆጣጠረው ኢየሱስ ነው፡፡ 
 
ማን እንደዳነ ማወቅ የሚችለው ማነው?
ዳግም የተወለዱት ብቻ ናቸው፡፡ 

‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምጹንም ትሰማለህ፡፡ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፡፡ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው፡፡›› ኢየሱስ ሲናገር የነበረው ዳግም ውልደትን ስላላገኙ ሰዎች ነው፡፡ ዳግም የተወለዱት ስለ ዳግም ውልደት ያውቃሉ፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ይህንን አያውቅም ነበር፡፡ እግዚአብሄር ዳግም የተወለዱትን ያውቃል፡፡ ዳግም የተወለዱትም እንዲሁ ያውቃሉ፡፡   
ሆኖም ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ነፋስ ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ እንደማያውቁ ሁሉ ሰውም እንዴት ዳግም ሊወለድ እንደሚችል አያውቁም፡፡ 
ይህንን መረዳት ትችላላችሁን? ነፋሱን የሚያንቀሳቅሰው ማነው? እግዚአብሄር ነው፡፡ ነፋሱንስ የፈጠረው ማነው? አሁንም እግዚአብሄር ነው፡፡ የምድርን የአየር ጠባይ የሚቆጣጣረው፣ ነፋስንና ውሃን የሚያስተላልፈው ማነው? ሕይወት ላላቸው ነገሮች በሙሉ እስትንፋስን የሚሰጥስ ማነው? በሌላ አነጋገር በዚህ ዓለም ላይ ያለውን ሕይወት ሁሉ የፈጠረውና የሚያበዛው ማነው? ሌላ ማንም ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ኢየሱስም እግዚአብሄር ነው፡፡  
የውሃውን፣ የደሙንና የመንፈሱን የወንጌል ቃሎች ካላወቅን ዳግም ውልደትን ልናገኝ አንችልም፡፡ ሌሎችንም በመንፈሳዊ መልኩ ማስተማር አንችልም፡፡ ኢየሱስ አንድ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር ዳግም ሊወለድ እንደማይችል ነግሮናል፡፡   
እኛ ዳግም እንድንወለድ በሚያደርገን ብርቱ ወንጌል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡ መንፈስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ልቡናዎች ውስጥ ይገባና ያድራል፡፡  
ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ሐጢያት በሙሉ ለማስወገድ ተጠመቀ፡፡ የእነዚህን ሐጢያቶች ዋጋ ለመክፈልም በመስቀል ላይ ደማ፡፡ እርሱ በሰው ዘር ልቦች ውስጥ ዳግም የመወለድን ደህንነት አስርጾዋል፡፡ በዚህ ወንጌል ስናምን መንፈስ ወደ ነፍሳችን ይገባል፡፡ ዳግም የመወለድ ደህንነት ይህ ነው፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ አማካይነት ሐጢያቶች በሙሉ መንጻታቸውን ስናምን በትክክል ዳግም እንወለዳለን፡፡     
በዘፍጥረት 1፡2 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹ምድርም ባዶ ነበረች፤ አንዳችም አልነበረባትም፡፡ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ በውሃ ላይ ሰፍፎ ነበር፡፡›› የእግዚአብሄር መንፈስ በውሃ ላይ ሰፍፎ እንደነበር ተጽፎዋል፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ ከምድር ውጪ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡   
ይህ ማለት መንፈስ ወደ ሐጢያተኞች ልብ ሊገባ አይችልም ማለት ነው፡፡ ዳግም ያልተወለደ ሰው ልብ በሁከት ውስጥ ነው፡፡ በሐጢያት ጨለማም የተሞላ ነው፡፡ እግዚአብሄር ‹‹ብርሃን ይሁን አለ፡፡›› ከዚያም ብርሃን ሆነ፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር መንፈስ እንደዚህ ባለው ሰው ልብ ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡ 
እግዚአብሄር የሐጢያተኞችን ልብ ለማብራት የወንጌሉን ብርሃን ላከ፡፡ እግዚአብሄር ‹‹ብርሃን ይሁን አለ፡፡›› ብርሃንም ሆነ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ በሰዎች ልብ ውስጥ ማደር የሚችለው በዚህ ጊዜ ብቻ ነው፡፡  
ስለዚህ የእግዚአብሄር መንፈስ የሚበራው ከውሃና ከመንፈስ የሆነውን ወንጌል አምነው ዳግም በተወለዱት ልቦች ውስጥ ነው፡፡ ‹‹ዳግም የመወለዳቸው›› ትርጉም ይህ ነው፡፡ በልቦቻቸው ዳግም የተወለዱት ከውሃና ከመንፈስ የሆኑትን የደህንነት ቃሎች አድምጠው ስላመኑ ነው! 
አንድ ሰው ዳግም ሊወለድ የሚችለው እንዴት ነው? ኢየሱስ ለፈሪሳዊው ኒቆዲሞስ ሲያስረዳው፡- ‹‹ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ብሎ አስረድቶታል፡፡ ኒቆዲሞስም ሲመልስ፡- ‹‹እኛ ከውሃና ከመንፈስ የምንወለደው እንዴት ነው? እንደገና ወደ እናታችን ማህጸን በመግባት እንወለዳለንን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ በእርግጥም እርሱ ይህን የተረዳው ቃል በቃል ሲሆን የሰው ልጅ በትክክል እንዴት ዳግም ሊወለድ እንደሚችል አልተገነዘበም፡፡    
ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንተ መምህር ሆነህ ሳለህ ይህ ምን  ማለት እንደሆነ አታውቅምን?›› ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንደማይገባ እንደሚያየውም ነገረው፡፡ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ የነገረው ዳግም የመወለድን እውነት ነበር፡፡   
ዳግም ውልደትን ሳያገኙ በኢየሱስ የሚያምኑ መኖራቸው እውነት ነው፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች እንደ ኒቆዲሞስ ዳግም ያልተወለዱ ናቸው፡፡ 
ኒቆዲሞስ ልክ እንደ ዛሬዎቹ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉ በዚያን ወቅት የእሰራኤላውያን መንፈሳዊ መሪ ነበር፡፡፡ ልክ በዘመኑ ቋንቋ ከአንድ አገር የምክር ቤት አባል ጋር የሚነጻጸር ነበር፡፡ በሐይማኖታዊ መስፈርቶችም የዕብራውያን መምህር ነበር፡፡ እርሱ የአይሁዶች ሐይማኖታዊ መሪ ነበር፡፡ የተዋጣለት ሊቀ ሊቃውንትም ነበር፡፡  
በዚያን ዘመን በእስራኤል ዛሬ ካሉት ትምህርት ቤቶች ጋር የሚወዳደር ተቋም ስላልነበር ሰዎች ሁሉ ‹‹ከምሁራኑ›› ትምህርትን ለመቅሰም ወደ ቤተ መቅደስ ወይም ምኩራቦች ይሄዱ ነበር፡፡ የሕዝቡ አስተማሪዎች እነዚያ ምሁራኖች ነበሩ፡፡ ልክ እንደ ዛሬው ያን ጊዜም ብዙ የሐሰት አስተማሪዎች ነበሩ፡፡    
ዛሬም ዳግም ያልተወለዱ ብዙ የሐይማኖት መሪዎች፣ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ሰባኪያኖችና ዲያቆናት አሉ፡፡ ልክ እንደ ኒቆዲሞስም ዳግም የመወለድን እውነት አያውቁም፡፡ ብዙዎች ዳግም ለመወለድ ሁለተኛ ጊዜ ወደ እናታችን ማህጸን መግባት እንዳለብን ያስባሉ፡፡ ዳግም መወለድ እንዳለባቸው ቢያውቁም እንዴት ዳግም መወለድ እንደሚችሉ ግን አያውቁም፡፡ 
ከድንቁርናቸው የተነሳ በእጃቸው በመንካት እንዲያው የዝሆንን ማንነት ለመለየት እንደሚፍጨረጨር ዓይነ ስውር መመሪያቸው በግል ስሜቶቻቸውና ተሞክሮዎቻቸው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለ ዓለማዊ እሴቶች ይሰብካሉ፡፡ ብዙ ታማኝ ሰዎች ለዚህ በመገዛታቸው ዳግም ከመወለድ ተከልክለዋል፡፡    
ዳግም መወለድ ከምንሰራቸው በጎ ምግባሮች ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም፡፡ እኛ ዳግም መወለድ የምንችለው በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ባለን እምነት ብቻ ነው፡፡ ከሐጢያተኝነት ወደ ጻድቅነት ሊቀይረን የሚችለው ይህ የእግዚአብሄር ወንጌል ብቻ ነው፡፡ 
ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ተናገረ፡- ‹‹ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋቸው ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?›› ኢየሱስ በእርሱ ጥምቀት አማካይነት ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የሆነው ስርየት የመጠናቀቁን እውነት በነገራቸው ጊዜ አላመኑትም፡፡ እነርሱ ያላመኑት ምን ነበር? ደህንነታቸው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ መረጋገጡን አላመኑም፡፡ ስለ ‹‹ሰማያዊ ነገሮች›› ቢነግራቸው ሰዎች እንደማያምኑት በተናገረ ጊዜ ይህንን ማለቱ ነበር፡፡  
ኢየሱስ እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለማንጻት በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀና በመስቀል ላይም ሞተ፡፡ ከዚያም ሐጢያተኞች ዳግም ይወለዱ ዘንድ መንገዱን ለማዘጋጀት ከሙታን ተነሳ፡፡ 
ስለዚህ ከብሉይ ኪዳን በመጥቀስ ለኒቆዲሞስ ይህንን አብራራለት፡- ‹‹ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡›› (ዮሐንስ 3፡13-15) ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደሰቀለ ሁሉ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው ለመፍቀድ የሰው ልጅ መሰቀል አለበት፡፡   
ኢየሱስ ‹‹ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና›› ሲል ምን ማለቱ ነው? እርሱ ይህን ጥቅስ ከብሉይ ኪዳን የጠቀሰው የእርሱ ጥምቀትና ደም እንዴት የሰው ልጅን ከሐጢያት ቀንበር ነጻ እንደሚያወጣው ለማሳየት ነው፡፡ 
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለመሞትና ለመንጠልጠል በመጀመሪያ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያት መውሰድ ነበረበት፡፡ ኢየሱስ ሐጢያት አልባ ስለሆነ በመስቀል ላይ ሊሰቀል አይችልም፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ እንዲሰቀል በአጥማቂው ዮሐንስ መጠመቅና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ መውሰድ ነበረበት፡፡   
ሐጢያተኞችን በሙሉ ከኩነኔ ማዳን የሚችለው ሐጢያቶቻንን በራሱ ላይ ተሸክሞ ለእነዚያ ሐጢያቶች ዋጋ ሲከፍል ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ የሚገኘውን ደህንነት ሰጥቶናል፡፡  
ስለዚህ እነዚያ ኢየሱስ አዳኛቸው መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች የጥምቀቱን ልብስ ይለብሳሉ፡፡ ከእርሱም ጋር ይሞታሉ፡፡ ከእርሱም ጋር ዳግም ይወለዳሉ፡፡ ኒቆዲሞስም በኋላ ይህንን እውነት ተረዳ፡፡
 
 
እባቡ እንደተሰቀለ ሁሉ፡፡  
 
ኢየሱስ የተሰቀለው ለምንድነው?
በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ስለወሰደ ነው፡፡ 

ሙሴ በምድረ በዳ ከናስ የተሰራውን እባብ የሰቀለበትን ታሪክ ታውቃላችሁን? ታሪኩ በዘሁልቁ 21 ላይ በዝርዝር ይገኛል፡፡ ቃሉ እስራኤሎች ከግብጽ ከወጡ በኋላ በጣም ተስፋ ቆርጠው ስለነበር በሙሴ ላይ እንዳንጎረጎሩ ይናገራል፡፡   
ከዚህ የተነሳ በሕዝቡ መካከል ተናዳፊ እባቦችን ሰደደ፡፡ በየድንኳኖቻቸው ገብተው እየነደፉ ገደሉዋቸው፡፡ ከተነደፉ በኋላ አካላቸው ማበጥ በመጀመሩ ብዙዎች ሞቱ፡፡  
ሕዝቡ መሞት ሲጀምር መሪያቸው ሙሴ ወደ እግዚአብሄር ጸለየ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር ሆይ እባክህ አድነን፡፡›› እግዚአብሄርም ከናስ የእባብ ቅርጽ ሰርቶ በእንጨት ላይ እንዲሰቅለው አዘዘው፡፡ ማንም ወደተሰቀለው እባብ የተመለከተ ሁሉ እንደሚድን ነገረው፡፡ ሙሴ እንደተነገረው አደረገ፡፡ ለሕዝቡም የእግዚአብሄርን ቃሎች አወጀ፡፡ 
በእርሱ ቃሎች ያመነና ወደ ናሱ እባብ የተመለከተ ማንኛውም ሰው ተፈወሰ፡፡ ልክ እንደዚሁ እኛም በዲያብሎስ ከተነደፍንበት መርዝ መፈወስ ይኖርብናል፡፡ የእስራኤል ልጆች ሙሴን አዳመጡና በእንጨት ላይ የተሰቀለውን የናሱን እባብ በመመልከታቸው ተፈወሱ፡፡ 
እባቡ በእንጨት ላይ የመሰቀሉ መገለጥ በሰው ዘር ሐጢያቶች ሁሉ የመጣው ኩነኔ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ አማካይነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መጫኑን የሚገልጥ ነው፡፡ እርሱ በዓለም ላይ ያሉትን ሐጢያተኞች ሁሉ ቅጣት ለመክፈል ኩነኔውን በራሱ ላይ ተሸከመ፡፡ በዚህም የሐጢያቶቻችንን ቅጣት በሙሉ አስወገደ፡፡  
ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ከእባቡ መርዝ›› ከሰይጣን ፈተናዎች የተነሳ ሊሞቱ የተፈረደባቸውን ሰዎች ሁሉ ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ የሐጢያቶቻችንን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል፣ በእርሱ የሚያምኑትንም ለማዳን ከመነሳቱ በፊት መጠመቅና በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት፡፡   
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው ወደ ገሃነም እሳት ልንጣል የነበርነውን እኛን ሰዎች ለማዳን ነው፡፡ ስለሆነም እኛን ለማዳን ሲል በጥምቀቱ ሐጢያታችንን በሙሉ ወደ ራሱ ማስተላለፍና በመስቀል ላይም መሰቀል ነበረበት፡፡ በእርሱ ያመኑትን ለማዳን ከመነሳቱ በፊት መጠመቅና በመስቀል ላይ መሞት ነበረበት፡፡   
በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበሩት እስራኤሎች በዓላማ ላይ የተሰቀለውን እባብ አይተው እንደዳኑ ሁሉ ዛሬም በኢየሱስ የሚያምኑና እርሱ በጥምቀቱና በደሙ አማካይነት የሐጢያቶቻቸውን ዋጋ እንደከፈለላቸው እምነቱ ያላቸው ሁሉ መዳንና ዳግም መወለድ ይችላሉ፡፡ 
ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቁ፣ በመስቀል ላይ በመሞቱና ከሙታን በመነሳቱ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በቂ ክፍያ ከፍሎዋል፡፡ አሁን በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በምህረቱ አማካይነት በደህንነት በረከት ሊባረኩ ይችላሉ፡፡
‹‹ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው፡፡›› (ዮሐንስ 3፡13) ኢየሱስ ለሐጢያቶቻችን ካሳ ለመክፈል ተጠመቀና በመስቀል ላይም ደሙን አፈሰሰ፡፡ የሰማይንም ደጆች ከፈተልን፡፡ ኢየሱስ በዮሐንስ 14፡6 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡››  
ኢየሱስ የተጠመቀውና በመስቀል ላይ የተሰቀለው ለእኛ ለሰው ልጆች የመንግሥተ ሰማያትን በር ለመክፈት ስለሆነ ማንም በእርሱ ደህንነት የሚያምን ሁሉ ይድናል፡፡ ኢየሱስ ለሐጢያቶቻችን አንዴ ከፍሎልናል፡፡ ስለሆነም ማንም በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ እውነት የሚያምን ሁሉ መንግሥተ ሰማይ ይገባል፡፡ 
ኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አድኖናል፡፡ ዳግም መወለድ የሚመጣው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም እንደዚሁም እርሱ አምላክ የመሆኑን እውነት በማመን ነው፡፡ ‹‹ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ፡፡›› (ዮሐንስ 3፡14) ይህ ቁጥር ምን ማለት ነው? ኢየሱስ መሰቀል ያስፈለገው ለምንድነው? እንደ እኛ እርሱም ሐጢያትን ስለሰራ ነውን? እርሱ እንደ እኛ ደካማ ነበርን? እርሱም እንደ እኛ ያልተሟላ ነበርን? አይደለም፤ እርሱ እንደዚያ አልነበረም፡፡   
ታዲያ ሊሰቀል የተፈረደበት ለምንድነው? ይህ የሆነው እኛን ለማዳንና ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ካሳ ለመክፈል ነው፡፡ እርሱ የተጠመቀውና በመስቀል ላይም ደሙን ያፈሰሰው እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ነው፡፡  
የደህንነትና ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የመወለድ እውነት ይህ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀሉ ለሚያምኑት ሁሉ አዲስ ሕይወትን ሰጠ፡፡ ይህም ለሐጢያቶቻችን ካሳ ነበር፡፡  
 
 

የውሃውና የመንፈሱ ትርጉም፡፡ 

 
ውሃና መንፈስ ሲባል ምን ማለት ነው?
ውሃ ማለት የኢየሱስ ጥምቀት ማለት ሲሆን መንፈስ ማለት ደግሞ የእርሱ አምላክነት ነው፡፡ 

መጽሐፍ ቅዱስ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ባመንን ጊዜ ዳግም እንደተወለድን ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን ዳግም መወለድ የተገኘው የሐጢያቶቻችን ካሳ በሆነው በተጻፉት የእግዚአብሄር ቃሎች፣ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ወንጌል ብቻ ነው፡፡   
በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ‹‹ውሃ›› የሚያመላክተው የኢየሱስን ጥምቀት ነው፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) ‹‹መንፈስ›› ማለትም ኢየሱስ እግዚአብሄር ነው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ አማካይነት የሐጢያቶቻችንን ዋጋ ለመክፈል የሰውን ዘር ሥጋ ለበሰና ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ይህ ዳግም የመወለድ እውነት ነው፡፡   
ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ ወደ ራሱ ወሰደና በመስቀል ላይ በመሞት የሐጢያትን ደመወዝ ከፈለ፡፡ በመጠመቅና በመስቀል ላይ በመድማትም በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ አዳነ፡፡  
የኢየሱስ ጥምቀትና ሞት እኛን ከሐጢያቶቻችን ያዳኑን በመሆናቸው ደህንነትን እንደሚያመላክቱ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ የእግዚአብሄርን መንግሥት ሊያዩና ወደዚያ ሊገቡ የሚችሉት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የተወለዱ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ በውሃው፣ በደሙና በመስቀሉ ከሐጢያቶቻችን በሙሉ አዳነን፡፡ ይህን ታምናላችሁን?  
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመክፈል ወደ ምድር የመጣ ሰማያዊ ካህን ነው፡፡ እርሱ ተጠመቀ፣ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰና ከሙታንም ተነሳ፡፡ ከዚህ የተነሳ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ መድሃኒት ሆነላቸው፡፡ 
ኢየሱስ በዮሐንስ 10፡7 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ የበጎች በር ነኝ፡፡›› ኢየሱስ በሰማይ በር ቆሞዋል፡፡ በሩን ለእኛ የሚከፍትልን ማነው? እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ 
ኢየሱስ የእርሱን የደህንነት እውነት ሳያውቁ በእርሱ የሚያምኑትን ፊት ይነሳቸዋል፡፡ በእርሱ ጥምቀት፣ ደምና መንፈስ የማያምኑ ዳግም እንዲወለዱ አይፈቅድላቸውም፡፡ በተጻፈው የእርሱ ቃል ከማያምን፣ የእርሱን ቅድስና ለመቀበል እምቢተኛ ከሆነና እርሱን እንደ አምላክ ከማያውቀው ከማንኛውም ሰው ፊቱን ያዞራል፡፡  
የተጻፈው እውነት ኢየሱስ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ካሳ ለመክፈል ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ዓለም መምጣቱን፣ መጠመቁንና በመስቀል ላይ መሞቱን ይናገራል፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ የሞተው የእኛን ፍርድ ለመውሰድ ነው፡፡ ከተሰቀለም በኋላ በሦስተኛው ቀን ተነሳ፡፡ ይህንን እውነት ለማመን እምቢተኛ የሆነ ማንኛውም ሰው ወደ ውጭ ተጥሎ ይጠፋል፡፡ ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነው›› ተብሎ ተጽፎዋል፡፡ 
ሆኖም እነዚያ በእርሱ ጥምቀትና ደም አማካይነት በመቤዠት በረከት የሚያምኑና በልባቸው የተቀደሱ መንግሥተ ሰማያት መግባት ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ይህ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ዳግም የምንወለድበት ወንጌል ነው፡፡ ሰማያዊው ወንጌል ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ ነው፡፡ ዳግም ሊወለዱ የሚችሉት በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምኑ ብቻ ናቸው፡፡ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሐጢያት አልባ ናቸው፡፡ በትክክል ዳግም የተወለዱትም እነርሱ ናቸው፡፡  
ኒቆዲሞስ እውነቱን እንዳልተረዳ ሁሉ ዛሬም አብዛኛው ሕዝብ እውነተኛውን ወንጌል ሳያውቅ በኢየሱስ ያምናል፡፡ ኒቆዲሞስ በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት የነበረው አባል ነው፡፡ ነገር ግን እውነተኛውን ወንጌል ከኢየሱስ ሰማ፡፡ በኋላም ኢየሱስ ሲሰቀል ሬሳውን ለመቅበር መጣ፡፡ በዚያን ጊዜ ኒቆዲሞስ በሙሉ ልቡ አምኖ ነበር፡፡  
ዛሬም ስለ ኢየሱስ ውሃና መንፈስ የተነገረውን የማናውቅ በጣም ብዙ ነን፡፡ ከዚህም በላይ እውነተኛውን ወንጌል የመስማት ዕድል አግኝተው እንኳን እውነቱን ያልተቀበሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ የሚያሳዝን ነው፡፡  
ኢየሱስ ሁላችንም ዳግም እንድንወለድ አስችሎናል፡፡ ዳግም እንድንወለድ ያደረገን ምንድነው? ውሃው፣ ደሙና መንፈሱ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ሲጠመቅ ሐጢያቶቻችንን ወሰደና በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ከዚያም ከሙታን ተነሳ፡፡ 
በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉም ዳግም የመወለድን በረከት ሰጥቷል፡፡ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ ዳግም መወለድን የፈቀደ አዳኝ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሰማይን፣ ምድርንና በሁለቱ መካከል ያሉትን ነገሮች ሁሉ ከፈጠረው ከኢየሱስ ጋር ትሆኑ ዘንድ ጸልዩ፡፡  
በዮሐንስ 3፡16 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ፡፡›› በኢየሱስ በማመን ዘላለማዊ ሕይወትን አግኝተናል፡፡ የደህንነት ወንጌል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና ደም ካመንን፤ ኢየሱስም አዳኝና አምላክ መሆኑን ካመንን መዳን እንችላለን፡፡  
ነገር ግን በዚህ እውነት ካላመንን ለዘላለም ወደ ሲዖል እንወርዳለን፡፡ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ‹‹ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?›› ብሎ የተናገረውም ለዚህ ነው፡፡   
እግዚአብሄር ያደረገልን ምንድነው? በኢየሱስ በኩል ያገኘነው ደህንነት ዳግም እንድንወለድ ፈቀደልን፡፡ ኢየሱስ ከዓለም፣ ከዲያብሎስና ከዓለም ሐጢያቶች አዳነን፡፡ ኢየሱስ የዚህን ዓለም ሐጢያተኞች ከሐጢያት ፍርድ ለማዳን በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶችን በሙሉ ወሰደ፤ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ ከዚያም ከሙታን ተነሳ፡፡ 
በዚህ ደህንነት ማመን አለማመን የእኛ ምርጫ ነው፡፡ ዳግም የምንወለድበት ደህንነት የሚመጣው በኢየሱስ ጥምቀትና ደም አማካይነት የሚገኘውን ደህንነት በማመን ነው፡፡ 
እግዚአብሄር ሁለት በረከቶችን እንደሰጠን ተናግሮዋል፡፡ አንደኛው ጥቅል በረከት ሲሆን የተፈጥሮን ነገሮች ማለትም ጸሐይንና አየርን ያካትታል፡፡ ይህ ጥቅል በረከት የተባለበት ምክንያት ለሐጢያተኛውም ለጻድቁም ሁሉ የተሰጠ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ልዩ በረከት ምንድነው? ልዩ የሆነው በረከት ሐጢያተኞችን በሙሉ በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ከሚመጣው ሞት የሚያድነውና ከውሃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ ነው፡፡ 
ሌላው ደግሞ ልዩ በረከት ነው፡፡ ልዩ በረከት ምንድነው? ልዩው በረከት ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም መወለድ ነው፡፡ ይህም ሐጢያተኞችን በሙሉ በሐጢያታቸው ከመሞት የሚያድን ነው፡፡ 
 
 
ልዩው በረከት፡፡ 
 
የእግዚአብሄር ልዩው በረከት ምንድነው?
ይህ እግዚአብሄር በጥምቀቱ፣ በስቅለቱና በትንሳኤው እኛን ማዳኑ ነው፡፡ 

በዮሐንስ 3፡16 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡›› ይህ የእግዚአብሄር ልዩ በረከት ነው፡፡ ኢየሱስ የሰውን ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ ለእኛ በመጠመቅና በመሰቀልም ከሐጢያቶችን ሁሉ አነጻን፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መዳናችን የእግዚአብሄር ልዩ በረከት፤  እውነት ነው፡፡ 
ኢየሱስ እኛን ማዳኑ፣ ከሐጢያተኞች ወደ ጻድቃን መለወጡ እውነት ነው፡፡ ይህንን እውነት በማመን ብቻ የእግዚአብሄርን የተለየ በረከት ታገኛላችሁ፡፡ ይህንን ሁሉ ታምናላችሁን?   
በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ምንም ያህል በታማኝነት ብትኖሩም ይህንን ልዩ የእግዚአብሄር በረከት ከገፋችሁ እምነታችሁ ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡ 
እኔ  ሁልጊዜ በምሰብክበት ወቅት የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀሉ ላይ ደም ለመዳናችን መሰረታዊ ነገሮች መሆናቸውን ሳልጠቅስ አልፌ አላውቅም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለ ማንኛውም መጽሐፍ ‹‹የእግዚአብሄር ልዩ በረከት›› ማለት እኛ እየተነጋገርንበት ያለነው በኢየሱስ ዳግም መወለድ መሆኑን ሳይጠቅስ ያለፈ የለም፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በስቅለቱ አማካይነት የሆነውን የሐጢያተኞች መዳን በተሻለ መንገድ የሚገልጠው የእግዚአብሄር በረከት ነው፡፡   
የኢየሱስ ጥምቀትና የእርሱ በመስቀል ላይ መሞት የእግዚአብሄር ልዩ በረከቶች ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ያሉት የሐሰት ሰባኪዎች ስለዚህ የሚናገሩት ምንም ነገር የላቸውም፡፡ እነዚህ የሐሰት ሰባኪዎችም በሚያበራ የመላዕክት ልብስ ተሸፍነው የክርስትናን ስነ ሐይማኖታዊ ባህርይና ስነ ምግባር ሸክፈው ይመጣሉ፡፡ አዎን ይህ እውነት ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ልዩ በረከት ጋር የሚያገናኛቸው ምንም ነገር ከሌለ የሚሰሩት ተዓምራት፣ የሕሙማን ፈውስ ሁሉም ክፉ ነገሮች ናቸው፡፡ 
ለሐጢያተኞች የስርየትን ወንጌል የሰጠው የእግዚአብሄር ልዩ በረከት ነው፡፡ በዚህ የበረከት ወንጌልም እግዚአብሄር እኛ ዳግም እንድንወለድ ፈቅዶልናል፡፡ በጥምቀቱ፣ በደሙ በሞቱና በትንሳኤውም አዲስ ሰዎች አደረገን፡፡ ከሐጢያት የነጻን የእግዚአብሄር ልጆችም አደረገን፡፡  
በዚህ ታምናላችሁን? --አዎን-- በእውነት ተባርካችኋልን? --አዎን-- የኢየሱስ ጥምቀት፣ ደሙና መስቀሉ በውሃውና በመንፈሱ የተሰጡን የእግዚአብሄር ልዩ በረከቶች ናቸው፡፡ ይህ የልዩው በረከት ወንጌል ነው፡፡ በልዩው በረከት ስለዳንን ጌታ የተመሰገነ ይሁን፡፡ 
ዛሬ በርካታ ታማኝ ክርስቲያኖች የጥምቀት፣ የደምና በውሃና በመንፈስ ዳግም የመወለድ ወንጌል የሆነውን ይህንን የተለየ የእግዚአብሄር በረከት አለማወቃቸው ያሳዝናል፡፡ በገዛ ራሳቸው ቃለ እግዚአብሄርና ሐይማኖታዊ ምግባሮች መንገዶቹን ለማግኘት በዕውር ድንብር ይሞክራሉ፡፡ ምንኛ ደንቁረዋል! 
ክርስትና ለረጅም ጊዜ አብሮን ቆይቷል፡፡ ተሐድሶ ከመጣ አምስት መቶ አመታቶች ሆነውታል፡፡ ነገር ግን አሁንም በኮርያና በቀረው ዓለም ዳግም የመወለድን እውነትና የእግዚአብሄርን ልዩ በረከት የማያውቁ ብዙዎች አሉ፡፡ 
ሆኖም እኛ ያለነው አሁን የዚህ ዓለም ፍጻሜ በተቃረበበት ዘመን ላይ ስለሆነ እርሱ እውነትን ያውቁ ዘንድ እንደሚፈቅድላቸው ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምናለሁ፡፡ 
ሐጢያተኞች ጻድቃን እንዲሆኑና መንግሥተ ሰማይ እንዲገቡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበልና ዳግም መወለድ ይኖርባቸዋል፡፡ ብዙ ክርስቲያኖች ዳግም ለመወለድ ጠንክረው እየሞከሩ ነው፡፡    
ሆኖም ዳግም የመወለድን እውነተኛ ትርጉም ሳያውቁ የሚያምኑ ከሆነ እምነታቸው ከንቱ ነው፡፡ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ዳግም መወለድ ይኖርብናል ይላሉ፤ ነገር ግን ዳግም ስለመወለድ እውነት ፍንጩ እንኳን የላቸውም፡፡  
እነርሱ በታማኝነት ስለሚያምኑና እሳቱ በልባቸው ውስጥ ስለሚሰማቸው ዳግም መወለድ እንደሚችሉ ይገምታሉ፡፡ በግል ስሜቶች ወይም በሐይማኖታዊ ምግባሮች ላይ ተመርኩዞ ዳግም ለመወለድ መሞከር ወደ ተሳሳተ እምነት ሊመራ ይችላል፡፡  
 
 

ወደ እውነተኛ ዳግም ውልደት የሚመራን የእግዚአብሄር ቃል፡፡ 

 
በእምነትና በሐይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?
እምነት ማለት ኢየሱስ ሊያድነን ያደረገልንን ማመን ሲሆን ሐይማኖት በራስ አስተሳሰቦችና ምግባሮች ላይ መደገፍ ነው፡፡   

በ1ኛ ዮሐንስ 5፡4-8 ላይ በግልጽ እንደተጻፈው እኛ ዳግም መወለድ የምንችለው በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ስናምን ብቻ ነው፡፡ ዳግም መወለድ ካለብን ዳግም ልንወለድ የምንችለው በተጻፈው የእውነት ቃል፤ በእግዚአብሄር ቃል በማመን ብቻ መሆኑን በአእምሮዋችን ማስታወስ አለብን፡፡ ራዕዮች፣ በልሳን መናገር ወይም በስሜት ላይ የተመሰረቱ ልምምዶች በጭራሽ ዳግም ወደ መወለድ ሊያደርሱን አይችሉም፡፡  
በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ላይም ኢየሱስ ሲናገር ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት እንደማይችል ይናገራል፡፡ አንድ ሰው ዳግም መወለድ ካለበት በጥቅሉ በኢየሱስ ሁለት ጊዜ ማመን ይኖርበታል፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሰው ሐጢያቶቹን በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነት በመገንዘብ በሐይማኖታዊ መንገድ ኢየሱስን ማመን ይከጅላል፡፡ አንድ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሱስ ሲያምን የሚያምነው በእግዚአብሄር ሕግ አማካይነትና ምን ያህል ክፉ ሐጢያተኛ እንደሆነ በመገንዘብ ነው፡፡     
በአሁኑ ጊዜ ያሉት አብዛኞቹ ሐይማኖቶች እንደሚያምኑት በኢየሱስ ማመን አያስፈልገንም፡፡ ክርስትና ሐይማኖት አይደለም፡፡ ክርስትና በእምነት ዘላለማዊ ሕይወት የሚገኝበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ 
ኢየሱስን በሐይማኖት መልክ የሚያምን ማንም ሰው ባዶ እጁን ይቀራል፡፡ በሐጢያት፣ በሁከትና በባዶነት የተሞላ ልብ ይዞ ይቀራል፡፡ ይህ እውነት አይደለምን? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሱት ፈሪሳውያን ግብዝ ሆናችሁ መቅረት አትፈልጉም፡፡  
ዳግም መወለድ የማይፈለግ ሰው የለም፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ክርስትናን በሐይማኖት መልክ የሚያምን ከሆነ ሐጢያት የተሞላ ልብ ያለው ግብዝ ሆኖ ይቀራል፡፡ ዳግም የመወለድን እውነት ማወቅ አለብን፡፡   
ዳግም ሳይወለድ ክርስትናን በሐይማኖት መልክ የሚያምን ማንኛውም ሰው ልቡ በግራ መጋባትና በባዶነት የተሞላ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው በኢየሱስ አምኖ ዳግም ያልተወለደ ከሆነ እምነቱ የተሳሳተ ነው፡፡ ስለዚህ በሰው ሁሉ ፊት ቅዱስ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ነገር ግን የማይሳካለት ምስኪን ሆኖ ይቀራል፡፡ 
ክርስትናን በሐይማኖት መልክ ማመናችሁን እስከቀጠላችሁ ድረስ ሁልጊዜም ሐጢያተኛና ግብዝ ትሆናላችሁ፡፡ ዘመናችሁንም ሁሉ ለሐጢያቶቻችሁ እያለቀሳችሁ ትኖራላችሁ፡፡ ከሐጢያቶቻችሁ ነጻ መውጣት ከፈለጋችሁ ከውሃ፣ ከደምና ከመንፈስ በሆነው የተጻፈ የወንጌል እውነት ማመን ይኖርባችኋል፡፡   
 
 

የቤዛነትን ምስጢር በኢየሱስ ጥምቀት ውስጥ ሁሉ መፈለግ፡፡ 

 
ዳግም እንድንወለድ ያደረገን ምንድነው?
የኢየሱስ ጥምቀት፣ የመስቀል ላይ ሞቱና ትንሳኤው ናቸው፡፡  

መጽሐፍ ቅዱስ ማንም ሰው ፈጽሞ በማይለወጠው የእግዚአብሄር ቃል አማካይነት ዳግም ሊወለድ እንደሚችል ይነግረናል፡፡ አሁን የሐዋርያውን ጴጥሮስ ቃሎች ከ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 እንመልከት፡- ‹‹ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡›› 
የኢየሱስ ጥምቀት እኛን የሚያድነን ምሳሌ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦዋል፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ማወቅ ያለባቸው ስለ ራሳችን ጥምቀት ሳይሆን ስለ ኢየሱስ ጥምቀት ነው፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት ለእኛ ለሐጢያተኞቹ አዲስ ሕይወትን ይሰጠናል፡፡ እመኑት ዳግም ትወለዱና የደህንነት በረከት ታገኛላችሁ፡፡  
ደህንነት የሚገኘው በኢየሱስ ጥምቀት በማመን መሆኑን በመረዳት ልንድን፣ ጻድቅ ልንሆንና የዘላለምን ሕይወት ልናገኝ እንችላለን፡፡ በሌላ አነጋገር በእግዚአብሄር ቃሎች አማካይነት በደህንነት እውነት በምናምንበት ጊዜ ሐጢያቶቻችን ለዘላለም ይነጻሉ፡፡    
ዳግም መወለድ ማለት ለሁለተኛ ጊዜ መወለድ ማለት ነው፡፡ ብዙዎቻችን በተለምዶ የምንጀምረው በሐይማኖት መልክ በኢየሱስ በማመን ነው፡፡ ከዚያም እውነቱን ስንረዳ ዳግም እንወለዳለን፡፡ ‹‹እርሱም ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ሁሉ ያድናቸዋልና፡፡›› (ማቴዎስ 1፡21)
በኢየሱስ ስናምንና እርሱም ለሰው ዘር ምን እንዳደረገ ስንረዳ ከሐጢያቶቻችን በሙሉ እንነጻና አዲስ ሰው ሆነን ዳግም እንወለዳለን፡፡ በመጀመሪያ በሐይማኖት መልክ በኢየሱስ አመንን፡፡ ከዚያም ከውሃው፣ ከደሙና ከመንፈሱ ወንጌል ዳግም ስለመወለድ በሰማን ጊዜ እንደገና ተወለድን፡፡  
ዳግም እንድንወለድ የሚያደርገን እውነት ምንድነው? በመጀመሪያ የኢየሱስ ጥምቀት፣ ከዚያም በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ በመጨረሻም ከሙታን መነሳቱ ነው፡፡ ዳግም መወለድ ማለት ኢየሱስን አምላካችንና አዳኛችን አድርገን ማመን ማለት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰዎች እንዴት ዳግም እንደተወለዱ እንመልከት፡፡ 
 
 

በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረው የሐጢያት ካሳ፡ እጆችን የመጫንና ደምን የማቅረብ ስርዓት፡፡ 

 
በብሉይ ኪዳን ዳግም የመወለድ ወንጌል ምንድነው? በመጀመሪያ በዘሌዋውያን ምዕራፍ 1ንና ስለ ዳግም መወለድ ምን እንደሚል እናንብብ    
ዘሌዋውያን 1፡1-5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፡- ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡፡ ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሄር መባን ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ፡፡ መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ደንኳን ደጃፍ ያቀርበዋል፡፡ እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል፡፡ በሬውንም በእግዚአብሄር ፊት ያርደዋል፡፡ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፡፡ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል፡፡››
እግዚአብሄር በዘሌዋውያን ላይ እስራኤላውያን መስዋዕትን በማቅረብ እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር ሕብረትን መመስረት እንደቻሉ ይነግረናል፡፡ ይህ ሁላችንም ልናውቅውና ልንረዳው የሚገባን እውነት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ቃሎች እንከልሳቸው፡፡  
እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ አናገረው፡፡ ያናገረውም ስለ እስራኤላውያን የሐጢያት ስርየት ነበር፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሕጉን ያለ መታዘዝ ሐጢያቶችን በሰሩ ጊዜ ነውር የሌለበትን እንስሳ በእግዚአብሄር ፊት በማቅረብ ሐጢያቶቻቸውን ማስተሰረይ ችለው ነበር፡፡ 
እነዚህ የመስዋዕት እንስሶች እግዚአብሄር በዝርዝር የለያቸውና ነውር የሌለባቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ እግዚአብሄር በደነገገው ስርዓትም መቅረብ ነበረባቸው፡፡ የመስዋዕቱም ገጽታ እንደሚከተለው ነበር፡፡   
በብሉይ ኪዳን አንድ ሰው ሐጢያትን ቢሰራ በእግዚአብሄር ፊት ለሰራው ሐጢያት ስርየት የሚሆን መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ መስዋዕቱ ነውር የሌለበት ይሆናል፡፡ በመቀጠል ሐጢያተኛው እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ በመጫን ሐጢያቶቹን በሙሉ ወደ መስዋዕቱ ማስተላለፍ አለበት፡፡ 
መስዋዕቱ ከታረደም በኋላ ደሙ በመሰውያው ቀንዶች ላይ መቀባትና የቀረውም መሬት ላይ መፍሰስ ነበረበት፡፡ እግዚአብሄር የደህንነት በረከት አድርጎ ለሕዝቡ የሰጠውና በተቀደሰው ድንኳን ውስጥ የሚከናወነው ስርዓት ይህ ነበር፡፡ 
የእግዚአብሄር ሕጎችና ትዕዛዛቶች እነርሱ ‹‹ማድረግ የሚገባቸውን›› ወይም ‹‹ማድረግ የማይገባቸውን›› የሚያሳዩ 613 አንቀጾችን ይዘዋል፡፡ እግዚአብሄር ሕጉንና ትዕዛዛቱን ለእስራኤል ሕዝብ ሰጠ፡፡ ሕዝቡ የእግዚአብሄር ሕግና ትዕዛዛት ትክክል እንደሆኑ ቢያውቁም ሊኖሩባቸው አልቻሉም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የተወለዱት ከአዳም የወረሱዋቸውን አስራ ሁለት አይነት ሐጢያቶች ይዘው ነበርና፡፡  
ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት ትክክለኛ ነገር የማድረግ ችሎታ አጡ፡፡ እስራኤሎች ጻድቃን የመሆን ችሎታ አጡ፡፡ ከሐጢያት ነጻ ወጥተው ለመኖር አጥብቀው ቢሞክሩም ሐጢያቶችን ከመስራት ሊቆጠቡ አልቻሉም፡፡ ሐጢያተኞች ሆኖ መወለድና መሞት የሰው ዘር ሁሉ ዕጣ ፈንታ ነው፡፡
ነገር ግን እግዚአብሄር ወሰን በሌለው ምህረቱ ሐጢያቶቻቸውን ማስተሰረይ የሚችሉበትን የመስዋዕት ስርዓት ለሕዝቡ ሰጠ፡፡ የእስራኤል ሕዝብና የዓለም ሕዝብ በሙሉ ከሐጢያቶቻቸው መዳን ይችሉ ዘንድ በቅዱሱ ድንኳን ውስጥ የሚደረገውን ስርዓት አቀረበላቸው፡፡ በመስዋዕቱ ስርዓት አማካይነት ለሰው ዘር ሁሉ ጻድቅ ፍቅሩን ገለጠ፡፡ እርሱ ለዓለም የዘላለምን መንገድ አሳየ፡፡ 
እግዚአብሄር የመስዋዕት ስርዓቱን ለሕዝቡ ሰጠና መስዋዕቱን ያገለግል ዘንድ የሌዊን ቤት ሾመ፡፡ ከ12ቱ የእስራኤል ነገዶች መካከል ለእስራኤል ሕዝብ የመስዋዕት አገልጋይ ሆኖ የተሾመው የሌዊ ቤት ብቻ ነበር፡፡ 
ሙሴና አሮንም የሌዊ ቤት ነበሩ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተቀደሰው ድንኳን ውስጥ የሚቀርበውን መስዋዕት የሚያስተዳድሩ ሕጎችንና ስርዓቶችን መዝግቦዋል፡፡ ይህም እጆችን በመጫን የሚደረግ የስርየት ወንጌል ነው፡፡ 
ስለዚህ ሌዋውያን የሚያከናውኑትን የመስዋዕት ስርዓት በተጨባጭ ስናስተውል ዳግም ልንወለድ እንችላለን፡፡ በተቀደሰው ድንኳን ውስጥ የሚቀርበውን መስዋዕት በሚመለከት የእግዚአብሄርን ቃል ማጥናት የሚገባን ለዚህ ነው፡፡ ይህ የብሉይ ኪዳን እጅግ አስፈላጊው ክፍል ነው፡፡ በመጨረሻም ወደ አዲስ ኪዳን በመምጣት በውሃና በመንፈስ አማካይነት ዳግም የመወለድ በረከቶች አሉን፡፡  
 
 
የሐጢያት ስርየት በብሉይ ኪዳን፡፡ 
 
የእግዚአብሄር ባህርያት ምንድናቸው?
ፍትህና ፍቅር፡፡  

እግዚአብሄር ከሌዊ ነገድ የሆነውን ሙሴን ወደተቀደሰው መገናኛ ድንኳን ጠራውና ወንድሙን አሮንን ሊቀ ካህን አድርጎ ሾመው፡፡ የሕዝቡን ሐጢያቶች ወደ መስዋዕቱ የሚያስተላልፈው አሮን ነበር፡፡ 
በዘሌዋውያን 1፡2 ላይ እንደተጻፈው እግዚአብሄር ለሙሴ ያለው ይህንን ነው፡- ‹‹ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡፡ ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሄር መባን ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ፡፡›› እዚህ ላይ እግዚአብሄር ለመስዋዕት የሚቀርቡትን ቁርባኖች ዘርዝሮዋል፡፡ ከሕዝቡ ማናቸውም ለሐጢያቶቹ ስርየትን ማግኘት ከፈለገ ከመንጋው ወይፈን ወይም በግ ማቅረብ ነበረበት፡፡     
እግዚአብሄር እንዲህም ደግሞ ነገራቸው፡- ‹‹መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት እንዲሰምር በመገናኛው ደንኳን ደጃፍ ያቀርበዋል፡፡›› (ዘሌዋውያን 1፡3) 
እግዚአብሄር መስዋዕቱን የሚቀበለው በሐጢያቶቹ ምክንያት መሞት በነበረበት ሰው ሕይወት ፋንታ ነው፡፡ እስራኤላውያን እጆቻቸውን ለመስዋዕት በሚያቀርቡዋቸው እንስሶች ራሶች ላይ በመጫን ሐጢያቶቻቸውን ማስተላለፍ ይችሉ ነበር፡፡ ግለሰቡ ለመስዋዕት የሚሆኑትን እንስሶች ማቅረብ የነበረበት በገዛ ፈቃዱ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቁጥር 4 የሚለውን እንመልከት፡፡   
‹‹እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ ያስተሰርይለትም ዘንድ የሠመረ ይሆንለታል፡፡›› ቁርባኑ በእግዚአብሄር ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ አንድ ሐጢያተኛ እጁን በሚያቀርበው የሚቃጠል ቁርባን ራስ ላይ በመጫን ሐጢያቶቹን በሙሉ ወደ እንስሳው ራስ ላይ ያስተላለፋል፡፡ ስለዚህ ሐጢያቶቹን እንዲቀበልና ለሐጢያቶቹ ስርየትን እንዲለገሰው ሐጢያተኛው በእግዚአብሄር ፊት በቁርባኑ ራስ ላይ እጆቹን መጫን ነበረበት፡፡  
ከዚያም መስዋቱን ያቀረበው ግለሰብ እንስሳውን ያርደውና ደሙን በመሰውያው ቀንዶች ላይ ይቀባዋል፡፡ የቀረውንም ደም በመሰዊያው ፊት በመሬት ላይ ያፈስሰዋል፡፡ ለሐጢያቶቹ ዋጋ ለመክፈልና ከእነርሱም ነጻ ለመውጣት ባስቀመጣቸው ሕጎቹ መሰረት መስዋዕቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡  
በዘሌዋውያን 1፡5 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹በሬውንም በእግዚአብሄር ፊት ያርደዋል፡፡ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፡፡ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል፡፡›› በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሩ አጠገብ በአራቱም ማዕዘኖች አራት ቀንዶች ያሉት የሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያ ነበር፡፡ 
ሐጢያተኛው እጆቹን በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ በመጫን ሐጢያቶቹን በሙሉ ካስተላለፈ በኋላ ሐጢያተኛው መስዋዕቱን ማረድ፤ ካህኑም ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ላይ መርጨት ነበረበት፡፡ የመሰዊያው ቀንዶች የሚያመላክቱት የሐጢያቶችን ፍርድ ነው፡፡ ደሙን በእነዚህ ቀንዶች ላይ ማኖር ማለት እንስሳው በሐጢያተኛው ፋንታ የሐጢያቶችን ዋጋ ለመክፈል ደሙን ማፍሰስ ነበረበት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄርም በቀንዶቹ ላይ የተረጨውን ደም በተመለከተ ጊዜ የሐጢያተኛውን ሐጢያቶች አነጻ፡፡      
የሐጢያት ቁርባኑ መድማት የሚኖርበት ለምንድነው? ምክንያቱም ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት›› (ሮሜ 6፡23) ስለሆነና የሥጋ ሕይወት ያለውም በደም ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ በዕብራውያን ውስጥ ‹‹ደም ሳይፈስ ሰርየት የለም›› (ዕብራውያን 9፡22) ተብሎ ተጻፈ፡፡ በዚህም ከሐጢያቱ ቁርባን የሚፈስሰው ደም የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው የሚለውን የእግዚአብሄር ሕግ ፈጸመ፡፡ 
የቀረበው ደም መምጣት ያለበት ከሐጢያተኛው መሆኑ ተገቢ ነበር፡፡ ነገር ግን የሐጢያት ቁርባኑ ስርየት ይሆነው ዘንድ በእርሱ ምትክ ደማ፡፡ ያን ጊዜ ካህኑ የሐጢያት ደመወዝ እንደተከፈለ ለማሳየት ደሙን በመሰውያው ቀንዶች ላይ ይቀባዋል፡፡   
በአዲስ ኪዳን ራዕይ 20፡11-15ን ካነበብን ቀንዶቹ የሚያመለክቱት የፍርድ መጽሐፍን መሆኑን ማየት እንችላለን፡፡ ስለዚህ በቀንዶቹ ላይ ደም ማኖር ማለት በፍርድ መጽሐፍ ላይ ደምን ማኖር ነው፡፡ ይህም የሐጢያቶች ፍርድ እጆችን በመጫንና በሐጢያት ቁርባኑ ደም አማካይነት መፈጸሙን የሚመሰክር ነው፡፡   
 
 
ሐጢያቶች የተመዘገቡት በሁለት ቦታዎች ላይ ነው፡፡ 
 
የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በእግዚአብሄር ፊት በሁለት ቦታዎች ላይ ተመዝግበዋል፡፡ አንደኛው በልቦቻቸው ጽላቶች ላይ ሲሆን ሌላው በእግዚአብሄር ፊት በሚከፈተው የፍርድ መጽሐፍ ላይ ነው፡፡  
በኤርምያስ 17፡1 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹የይሁዳ ሐጢአት በብረት ብርዕና በተሾለ ዕብነ አልማዝ ተጽፎአል፡፡ በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ተቀርጾዋል፡፡››  
በዘሌዋውያን 17፡11 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና፡፡ በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተሰርያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት፡፡›› ደም የሥጋ ሕይወት ነው፡፡ የሐጢያቶቻችን ዋጋ ሊከፈል የሚችለውም በዚህ ደም ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በመሰዊያው ቀንዶች ላይ ደም ይረጭ ነበር፡፡ በሕጉ መሰረት ነገሮች ሁሉ በደም ይነጻሉ፤ ደም ሳይፈስም ስርየት የለም፡፡ (ዕብራውያን 9፡22)    
‹‹የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ይገፍፈዋል፡፡ በየብልቱም ይቆርጠዋል፡፡ የካህኑም የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ እሳት ያነዳሉ፡፡ በእሳቱም ላይ እንጨት ይደረድራሉ፡፡ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቆረጡትን ብልቶች፣ ራሱንም፣ ስቡንም  በመሰዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፡፡ የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውሃ ያጥባል፡፡ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መስዋዕት የእሳት ቁርባን አድርጎ በእግዚአብሄር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡›› (ዘሌዋውያን 1፡6-9)     
ያን ጊዜ ካህናቶቹ የሚቃጠሉትን ቁርባኖችን ይቆራረጡና በሚቃጠለው መሰዊያ ላይ ያኖሩዋቸዋል፡፡፡ ይህ ስርዓት ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት በሰሩ ጊዜ በዚያ መንገድ መሞት፣ መድማትና ወደ ሲዖል እሳቶች መጣል እንደነበረባቸው የሚያመላክት ነው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙ ዘንድ በሐጢያት ቁርባኑ በኩል ፍርድ ይተላለፋል፡፡      
የሚቃጠሉት ቁርባኖች መስዋዕት የእግዚአብሄር የጽድቅ ሕግ ፍርድ ስርዓት ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር ሁለቱንም ሕጎች ማለትም የጽድቅን ሕግና የፍቅርን ሕግ ለሰው ዘር ሁሉ ማስተሰርያ በሆነው ስርዓት ውስጥ አካተተ፡፡   
እግዚአብሄር ጻድቅ ስለሆነ እነርሱን መዳኘትና የሞት ውሳኔ መስጠት ነበረበት፡፡ ነገር ግን እርሱ ሕዝቦቹን ስለወደዳቸው ሐጢያቶቻቸውን ወደ ሐጢያት ቁርባኑ እንዲያስተላለፉ ፈቀደላቸው፡፡ በአዲስ ኪዳንም ጌታችን አብዝቶ ስለወደደን ለእኛ ለሐጢያተኞች የሐጢያት ቁርባን ይሆን ዘንድ ተጠመቀና ተሰቀለም፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ደመሰሰ፡፡   
 
 
በብሉይ ኪዳን በየቀኑ ለሚሰራ ሐጢያት የሚደረግ ስርየት፡፡ 
 
የብሉይ ኪዳን ነውር የሌለበት የሐጢያት ቁርባን የሚወክለው ማንን ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡
 
በዘሌዋውያን 4፡27 ላይ የተጻፈውን እንመልከት፡- ‹‹ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ሐጢአትን ሳያውቅ ቢሰራ፣ እግዚአብሄርም አትስራ ያለውን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ቢበድልም፣ ለእርሱም የሠራው ሐጢአት ቢታወቀው፣ ስለ ሠራው ሐጢአት ነውር የሌለበትን እንስት ፍየል ለቁርባን ያመጣል፡፡ እጁንም በሐጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፡፡ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የሐጢአትን መሥዋዕት ያርዳል፡፡ ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፡፡ ደሙንም ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሰዋል፡፡ ስቡም ሁሉ ከደህንነት መሥዋዕት ላይ እንደሚወስድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳል፡፡ ካህኑም ለእግዚአብሄር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፡፡ እርሱም ይቅር ይባላል፡፡››  (ዘሌዋውያን 4፡27-31) 
የአዳም ዘሮች፣ የእስራኤል ሕዝብና የዓለም ሕዝብ ሁሉ በዚህ ምድር ላይ የተወለዱት በሐጢያት ተሞልተው ነበር፡፡ ስለዚህ ልቦቻችን በሐጢያት ተሞልተዋል፡፡ በሰው ልብ ውስጥ ሁሉም አይነት ሐጢያቶች አሉ፡፡ ክፉ አስተሳሰቦች፣ ምንዝርና፣ ዝሙቶች፣ ነፍስ መግደል፣ ስርቆት፣ ስስትና፣ ስንፍና፡፡ 
አንድ ሐጢያተኛ በቀን ውስጥ የሰራቸውን ሐጢያቶች ለማስተሰረይ በሚፈልግበት ጊዜ ነውር የሌለበትን መስዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ይዞ መምጣት አለበት፡፡ ከዚያም ሐጢያቶቹን ለማስተላለፍ እጆቹን በእንስሳው ራስ ላይ መጫን፣ መስዋዕቱን ማረድና በእግዚአብሄር ፊት ያቀርብለት ዘንድ ደሙን ለካህኑ መስጠት አለበት፡፡ ከዚያም ካህኑ ሐጢያተኛው የሐጢያቶቹን ስርየት ያገኝ ዘንድ ቀሪውን የመስዋዕት ሥራ ያከናውናል፡፡  
የእግዚአብሄር ሕግና ትዕዛዛት ባይኖሩ ኖሮ ሰዎች ሐጢያት መስራታቸውን ወይም አለመስራታቸውን አያውቁም ነበር፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ሕግና ትዕዛዛት አማካይነት ራሳችንን ስንመለከት ሐጢያቶቻችንን እንገነዘባለን፡፡ ሐጢያቶቻችን የሚኮነኑት በራሳችን መለኪያዎች ሳይሆን በእግዚአብሄር ሕግና ትዕዛዛት ነው፡፡ 
ተራው የእስራኤል ሕዝብ ሐጢያትን የሚሰራው ፈልጎ ሳይሆን በልቡ ውስጥ ሁሉንም አይነት ሐጢያቶች ይዞ ስለተወለደ ነው፡፡ ሰው በድክመቶቹ ምክንያት የሚሰራቸው ሐጢያቶች መተላለፎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሐጢያት የሰውን መተላለፎችና በደሎች ሁሉ ያካትታል፡፡  
ሰብዓዊ ፍጡራን ሁሉ ጎዶሎ ፍጡራን ናቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝቦችም እንደዚሁ ጎዶሎ ስለነበሩ ሐጢያተኞች ነበሩ፡፡ ሐጢያቶችንም ሰርተዋል፡፡ የሰው መተላለፎችና በደሎች በሙሉ በሚከተለው መንገድ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ በአእምሮዋችን ውስጥ ክፉ አስተሳሰቦች ሲኖሩ ሐጢያቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ እነዚህን ሐጢያቶች ስንተገብራቸው ደግሞ መተላለፎች ተብለው ይጠራሉ፡፡ የዓለም ሐጢያቶች ሁለቱንም ያካትታሉ፡፡   
በብሉይ ኪዳን ሐጢያቶች በእጅ መጫን ወደ ሐጢያት ቁርባኑ ራስ ላይ ይተላለፉ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ሐጢያተኛው ሐጢያት አልባ ይሆናል፡፡ ስለዚህም በሐጢያቶቹ ምክንያት መሞት አያስፈልገውም፡፡ በመሆኑም የመስዋዕቱ ስርዓት የእግዚአብሄር ቅን ፍርድና ፍቅር ጥላ ነበር፡፡  
እግዚአብሄር ከአፈር ስለፈጠረን ከመጀመሪያውም አቧራ ነበርን፡፡ ደምን በመሰውያው ቀንዶች ላይ ማኖርና የቀረውንም ከመሰውያው በታች ማፍሰስ ማለት እስራኤሎች ለሐጢያቶቻቸው ካሳ ከፍለዋል፤ ሐጢያቶችንም ሁሉ ከልቦቻቸው ጽላቶች ላይ ሰርዞዋል ማለት ነበር፡፡  
‹‹ካህኑም ለእግዚአብሄር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡›› በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስቡ የሚያመላክተው መንፈስ ቅዱስን ነው፡፡ ስለዚህ ሐጢያቶቻችንን ለማስተሰረይ ይህንን እግዚአብሄር በወሰነው መንገድ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ እንደዚሁም የሐጢያቶቻችንን ስርየት እግዚአብሄር ተገቢ ነው ብሎ በወሰነው መንገድ በልቦቻችን ውስጥ መቀበል ይኖርብናል፡፡  
እግዚአብሄር የሐጢያት ቁርባኖች ጠቦት፣ ፍየል ወይም ጥጃ መሆን እንዳለባቸው ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው፡፡ የብሉይ ኪዳን የሐጢያት ቁርባኖች የተመረጡ ቁርባኖች ነበሩ፡፡ ጥጃ ንጹህ እንስሳ ነበር፡፡ የሐጢያት ቁርባኖች ነውር የሌለባቸው የሚሆኑበት ምክንያት ለሰው ዘር ሁሉ የሐጢያት መስዋዕት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለሚገልጡ ነበር፡፡  
የብሉይ ኪዳን ሰዎች ነውር በሌለበት የሐጢያት ቁርባን ራስ ላይ እጆቻቸውን በመጫን ሐጢያቶቻቸውን አስተላለፉ፡፡ ካህናትም ሐጢያቶቻቸውን ለመካስ መስዋዕቱን አገለገሉ፡፡ የእስራኤል ሕዝቦች የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙት በዚህ መልኩ ነበር፡፡ 
 
 

የስርየት ቀን ስርዓት፡፡ 

 
የእስራኤል ሕዝቦች በስርየት ቀን መስዋዕት ማቅረብ ያስፈለጋቸው ለምንድነው?
ምክንያቱም እስከሚሞቱ ድረስ ሐጢያት በመስራት ቀጠሉ፡፡ የዘወትር የሐጢያት ቁርባኖች በእግዚአብሄር ፊት ሊቀድሱዋቸው አልቻሉም፡፡  

ሆኖም ሐጢያት በሰሩ ጊዜ ሁሉ መስዋዕት ማቅረብ ስለነበረባቸው ሐጢያቶቻቸውን ለማስተሰረይ የሚያስፈልጉዋቸውን መስዋዕቶች በሙሉ ማቅረብ የሚቻላቸው አልነበረም፡፡ ስለዚህ ቀስ በቀስ ቸልተኞች ሆኑ፡፡ በየቀኑ ሐጢያቶቻቸውን ማስተሰረይ ማለቂያ የሌለው ተግባር መስሎ ስለታያቸው ይህንን ስርዓት ፈጽመው ማስወገድ እንዳለባቸው ተሰማቸው፡፡ 
ምንም ያህል ጠንክረን ብንሞክር ለሐጢያቶቻችን የሚበቃ መስዋዕትን ፈጽሞ ማቅረብ አንችልም፡፡ ስለዚህ ለሐጢያቶቻችን የሚሆነው እውነተኛው ካሳ እግዚአብሄር ባዘጋጀልን የደህንነት ሕግ ላይ ባለን ልባዊ በሆነው እምነታችን አማካይነት መሰጠት ይኖርበታል፡፡   
ምንም ያህል በእግዚአብሄር ሕግ ለመኖር ብንሞክር በድካሞቻችን ምክንያት ምን ያህል ጎዶሎዎችና ደካሞች እንደሆንን ብቻ እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ለእስራኤል ሕዝብ የዓመቱን ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ የሚያስተሰርዩበትን መንገድ ሰጣቸው፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡17-22) 
በዘሌዋውያን ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፡፡ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፡፡ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠ እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት ከሐጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፡፡ ታላቅ ሰንበት ይሆንላችኋል፡፡ ራሳችሁንም ታዋርዳላችሁ፡፡ የዘላለም ሥርዓት ነው፡፡›› (ዘሌዋውያን 16፡29-31) 
በዚህም ሊቀ ካህኑ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ሕዝቡ በዓመቱ ውስጥ ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች በሙሉ የስርየትን መስዋዕት ሲያቀርብ የእስራኤል ሕዝብ በዓመት አንድ ጊዜ የአእምሮ ሰላምን ያገኛል፡፡ ሐጢያቶቻቸው በመንጻታቸውም በዚያ ቀን አእምሮዋቸው ሰላም ይሆናል፡፡ 
ሊቀ ካህኑ አሮን የእስራኤል ሁሉ ወኪል ሆኖ በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን የስርየቱን መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ በዚህ ጊዜ ሌሎቹ ካህናቶች ወደ ቅዱሱ ድንኳን መግባት አይችሉም፡፡ እርሱና ቤተሰቦቹም ሐጢያት ስለሰሩ በመጀመሪያ አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ከማስተሰረዩ በፊት ለራሱና ለቤተሰቡ የስርየትን መስዋዕት ማቅረብ ነበረበት፡፡ 
እርሱ ለሕዝቡ መስዋዕትን የሚያቀርበው እንዲህ ነበር፡- ‹‹ሁለቱንም አውራ ፍየሎች ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሄር ፊት ያቆማቸዋል፡፡ አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፡፡ አንዱን ዕጣ ለእግዚአብሄር ሌላውንም ዕጣ ለሚለቀቅ፡፡ አሮንም የእግዚአብሄር ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያቀርባል፡፡ ስለ ሐጢአትም መስዋዕት ያደርገዋል፡፡ የመለቀቅም ዕጣ የሆነበትን ፍየል ያስተሰርይበት ዘንድ ለመለቀቅም ወደ ምድረ በዳ ይሰድደው ዘንድ በሕይወቱ በእግዚአብሄር ፊት ያቆመዋል፡፡›› (ዘሌዋውያን 16፡7-10)
አሮን ለራሱና ለቤተሰቡ ሐጢያት የስርየትን ስርዓት ከፈጸመ በኋላ ‹‹በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥላል፡፡›› አንዱ ዕጣ ለእግዚአብሄር ሲሆን ሌላው ደግሞ ለሚለቀቀው ማለትም ‹‹ለአዛዜል›› ነበር፡፡ 
በመጀመሪያ ከሁለቱ ፍየሎች አንዱ ለእግዚአብሄር ቀረበ፡፡ እዚህም ሊቀ ካህኑ ሕዝቦቹን በመወከል ሐጢያቶቻቸውን ወደ ፍየሉ ራስ ለማስተላለፍ እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ ጫነ፡፡  
ደሙ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ወዳለው የስርየት መክደኛ ይወሰድና ሰባት ጊዜ ተረጨ፡፡ የእስራኤል ልጆችም ባለፈው ዓመት ለሰሩዋቸው ሐጢያቶቻቸው ሁሉ ይቅርታን አገኙ፡፡ የእስራኤል ልጆች በሐጢያቶቻቸው ከመሞት ፋንታ ሊቀ ካህኑ ሐጢያቶችን በሐጢያት ቁርባኑ ራስ ላይ አስተላለፈና የእነርሱን ፍርድ እንዲወስድ ፈቀደ፡፡ ከዚያም አሮን በሕይወት ያለውን ሌላውን ፍየል በእግዚአብሄር ፊት ሰዋው፡፡ ለሕዝቡ የቀረበው መስዋዕት ያ ነበር፡፡ 
 
 
ለሕዝቡ፡፡  
 
አሮን በሕዝቡ ሁሉ ፊት እጆቹን በሁለተኛው ፍየል ራስ ላይ ጫነና በእግዚአብሄር ፊት ተናዘዘ፡፡ ‹‹አቤቱ የእስራኤል ሕዝብ ዝሙትን፣ ምንዝርናን፣ ስርቆትን ፈጽመዋል፡፡…በጣዖታት ፊት ሰግደዋል፡፡ ሰንበትን ቀድሰው አልጠበቁም፡፡ ስምህንም በከንቱ ጠርተዋል፡፡ የሕጎችህንና የትዕዛዛቶችህንም አንቀጾች በሙሉ ጥሰዋል፡፡›› በዚህም ዓመቱን በመሉ የተሰሩት የሕዝቡ ሐጢያቶች ወደ ሐጢያት ቁርባኑ ይተላለፉ ነበር፡፡ 
ዘሌዋውያን 16፡21ን እናንብብ፡- ‹‹አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፡፡ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፣ መተላለፋቸውንም ሁሉ፣ ሐጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፡፡ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፡፡ በተዘጋጀውም ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል፡፡›› በዚህም የሚለቀቀው ፍየል በምድረ በዳ ይቅበዘበዝና የእስራኤላውያንን ሐጢያቶች በራሱ ተሸክሞ ይሞታል፡፡ የሚለቀቀው ፍየል ማለትም ‹‹አዛዜል›› በዕብራይስጥ ‹‹ማውጣት›› ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት የሐጢያት ቁርባኑ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ምትክ በእግዚአብሄር ፊት ይባረራል ማለት ነው፡፡  
ስለዚህ የእስራኤላውያን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ ፍየሉ የተላለፉት በአሮን እጆችን የመጫን ስርዓት ነበር፡፡ በዚህ መንገድ እስራኤሎች ከሐጢያቶቻቸው ይቅርታን አግኝተዋል፡፡ ሊቀ ካህኑ በፍየሉ ላይ እጆቹን ሲጭን ሲመለከቱና ወደ ምድረ በዳ ሲጋዝ ሲያዩ በስርየቱ ስርዓት ያመኑ እስራኤሎች በሙሉ ለሐጢያቶቻቸው ስርየትን ስለ ማግኘታቸው እርግጠኞች ነበሩ፡፡ የብሉይ ኪዳን ስርዓቶች በሙሉ የአዲስ ኪዳን ‹ዳግም የመወለድ ወንጌል› ጥላ ነበሩ፡፡ 
በብሉይ ኪዳን እጆችን መጫንና የመስዋዕቱ ደም ከሐጢያት የሚዳንባቸው ወንጌል ነበሩ፡፡ ይህ በመሰረቱ በአዲስ ኪዳንም ያው ነው፡፡ 
 
 
በአዲስ ኪዳን ያለው የቤዛነት ወንጌል፡፡ 
 
በአዲስ ኪዳን የሕዝቡ ሐጢያቶች በሙሉ ስርየትን ያገኙት እንዴት ነበር? 
በማቴዎስ 1፡21-25 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹እርሱም ሕዝቡን ከሐጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፡፡ በነቢይም ከጌታ ዘንድ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው የሚል ነው፡፡ ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ እጮኛውንም ወሰደ፡፡ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፡፡ ስሙንም ኢየሱስ አለው፡፡››     
ጌታችን ኢየሱስ የሰውን ዘር ሁሉ ከሐጢያት ለማዳን በአማኑኤል ስም ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ስለዚህ ስሙ ኢየሱስ ተባለ፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ መጣ፡፡ የሰው ዘር አዳኝ ለመሆንም የሰብዓዊ ፍጡርን ሥጋ ለብሶ መጣ፡፡ ደህንነታችንንም አጠናቀቀና ከሐጢያት ለዘላለም ነጻ አወጣን፡፡   
 
 

ዳግም የመወለድ ወንጌል፡፡  

 
ኢየሱስ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጻ ያወጣን እንዴት ነበር? ይህንን ያደረገው በጥምቀቱ አማካይነት ነው፡፡ እስቲ ማቴዎስ 3፡13ን እንመልከት፡- 
‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር፡፡ ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናል አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› (ማቴዎስ 3፡13-17)
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው በዮርዳኖስ ወዳለው ወደ አጥማቂው ዮሐንስ መጣ፡፡ በእርሱም ተጠመቀና የሐጢያተኞችንም ሐጢያቶች ሁሉ ወሰደ፡፡ እንዲህ በማድረጉም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ፈጸመ፡፡ 
 
 

ኢየሱስ በዮርዳኖስ የተጠመቀው ለምን ነበር? 

 
በወንጌል ውስጥ የተገለጠው ምንድነው?
የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡  

አሁን ሰማያዊው ሊቀ ካህን ከሰው ዘር የመጨረሻ ሊቀ ካህን ጋር የተገናኘበትን ትዕይንት እንመልከት፡፡ እዚህ ላይ ለዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ስርየትን ባረጋገጠው ጥምቀት አማካይነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማየት እንችላለን፡፡ 
ኢየሱስን ያጠመቀው አጥማቂው ዮሐንስ ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ እጅግ ታላቅ ሰው ነበር፡፡ ኢየሱስ በማቴዎስ 11፡11 ላይ ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም›› በማለት መስክሮዋል፡፡ ሊቀ ካህኑ አሮን በስርየት ቀን እጆቹን በሐጢያት ቁርባኑ ላይ በጫነ ጊዜ የሕዝቡ ሐጢያቶች ስርየትን እንዳገኙ ሁሉ በአዲስ ኪዳንም ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ስርየትን አግኝተዋል፡፡    
ዳግም የመወለጃው ወንጌል ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ምሉዕ የሆነ የስርየት ወንጌል ነው፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ ጥምቀት በኩል የሆነው የቤዛነት ወንጌል የዓለምን ሕዝብ ሁሉ ያዳነ እግዚአብሄር ጽድቁን ለመፈጸም ያስቀመጠው ወንጌል ነው፡፡ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ለማስተሰረይ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ ተጠመቀ፡፡ 
‹‹ጽድቅን ሁሉ›› መፈጸም ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት እግዚአብሄር የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ አነጻቸው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለማንጻት ተጠመቀ፡፡ ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና፡፡›› (ሮሜ 1፡17)  
የእግዚአብሄር ጽድቅ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና በመስቀል ላይ በመሞት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ያነጻ ዘንድ አንድ ልጁን ወደዚህ ምድር ለመላክ በወሰነው ውሳኔው ውስጥ ታይቷል፡፡ 
በአዲስ ኪዳን የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠው በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ነው፡፡ እኛ ጻድቃን የሆንነው ኢየሱስ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ወንዝ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ስለወሰደ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ደህንነት በልባችን ስንቀበል የእግዚአብሄር ጽድቅ በእርግጥም ይፈጸማል፡፡ 
‹‹ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናል አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ፡፡ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፡፡ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፡፡ እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡›› (ማቴዎስ 3፡115-17)      
ይህ ምንባብ የልጁ ጥምቀት የደህንነትን ጽድቅ ሁሉ እንደፈጸመ እግዚአብሄር ራሱ መመስከሩን ይገልጣል፡፡ እግዚአብሄር ‹‹በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀው ኢየሱስ በእርግጥም ልጄ ነው›› እያለ ነው፡፡ ልጁ የተጠመቀው ለሰው ዘር ሁሉ ስርየትን ለመስጠት እንደሆነ እግዚአብሄር መሰከረ፡፡ ይህንን ያደረገው የተቀደሰው የልጁ የኢየሱስ ሥራ ከንቱ እንዳይሆን ነበር፡፡  
ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅና የዓለም ሐጢያተኞችም አዳኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ›› አለ፡፡ ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ መታዘዙና በጥምቀቱ አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ መውሰዱ እውነት ነው፡፡
ጥምቀት የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹መታጠብ፣ ማስተላለፍ፣ መቀበር›› ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ እርሱ ስለተላለፉ እኛ ማድረግ የሚኖርብን ነገር ቢኖር ከሐጢያቶቻችን እንድን ዘንድ በዚህ ወንጌል ማመን ነው፡፡ 
በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉት የደህንነት ትንቢቶች ሁሉ ፍጻሜ በአዲስ ኪዳን የተከናወነው በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ነበር፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉት ትንቢቶች በመጨረሻ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ግጣሞቻቸውን አግኝተዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ሕዝብ በዓመት አንድ ጊዜ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት እንዳገኙ ሁሉ በአዲስ ኪዳንም የሕዝቡ ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ ተላልፈው ለዘላለም ነጽተዋል፡፡  
ዘሌዋውያን 16፡29 የማቴዎስ 3፡15 ፍጻሜ ነው፡፡ ኢየሱስ የተጠመቀው የሰው ልጆችን ሐጢያት በሙሉ ለመውሰድ ነበር፡፡ ለጥምቀቱ ምሥጋና ይግባውና በእርሱ ዘላለማዊ የሐጢያት ይቅርታ የሚያምኑ ሁሉ ድነዋል፡፡ ሐጢያቶቻቸውም በሙሉ ከልቦቻቸው ጽላቶች ላይ ተደምስሰዋል፡፡ 
ምንም ያህል የተቀደሰ ሕይወት ብትኖሩም የኢየሱስን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱን እውነት ካልተገነዘባችሁና ካላመናችሁ ፈጽሞ ከሐጢያቶቻችሁ ልትነጹ አትችሉም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል የተፈጸመውና ሐጢያቶቻችን የተደመሰሱት በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ብቻ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እውነተኛ ደህንነት የተገኘው በሐጢያቶቻችን ሁሉ ቤዛነት ማለትም በኢየሱስ ጥምቀት ነው፡፡   
ይህንን እያሰባችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ይህንን ደህንነት በልባችሁ ውስጥ ትቀበላላችሁ? ወይስ አትቀበሉም? ይህ የሰው ቃል ሳይሆን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሞተው በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችሁን ሁሉ ስለወሰደ ነው፡፡ የኢየሱስ ስቅለት የጥምቀቱ ውጤት እንደነበር ትስማማላችሁን?  
በሮሜ 8፡3-4 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ከሥጋ የተነሳ ስለደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሄር የገዛ ልጁን በሐጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በሐጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና፡፡ እንደ መንፈስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕግ ትዕዛዝ ይፈጸም ዘንድ ሐጢአትን በሥጋ ኮነነ፡፡››  
እኛ ከሥጋ ድካም የተነሳ የእግዚአብሄርን ሕጎችና ትዕዛዛቶች መጠበቅ ስለማንችል ኢየሱስ የሥጋን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ አስወገዳቸው፡፡ ይህ የኢየሱስ ጥምቀት እውነት ነው፡፡ የኢየሱስ ጥምቀት የመስቀል ላይ  ሞቱን አስቀድሞ ወሰነ፡፡ ይህ የጥንቱ የእግዚአብሄር ወንጌል ጥበብ ነው፡፡ 
በኢየሱስ የመስቀል ላይ ሞት ብቻ ታምኑ የነበራችሁ ከሆናችሁ አሁኑኑ ተመለሱና በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት የደህንነትን ወንጌል በልባችሁ ውስጥ ተቀበሉ፡፡ በተጨባጭ የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የምትችሉት ያን ጊዜና ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ 
 
 
የጥንቱ ወንጌል፡፡ 
 
የጥንቱ ወንጌል ምንድነው?
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ 

የጥንቱ ወንጌል የሐጢያቶች ስርየት ወንጌል ነው፡፡ ይህ እግዚአብሄር የገለጠልን የኢየሱስ ጥምቀት፣ የሞቱና የትንሳኤው ወንጌል ነው፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ በመጠመቅ ሐጢያትን በአንድ ጊዜ አነጻ፡፡ በዚህ አማካይነትም ይህንን እውነት ለሚያምኑ ሁሉ ደህንነትን ሰጠ፡፡ በዚህ  ላይ ባለን እምነትም ወደፊት የምንሰራቸው ሐጢያቶቻችንም በሙሉ እንደዚሁ ተወግደዋል፡፡   
በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ደሙ የሚያምን ሁሉ ለዘላለም ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ድኖዋል፡፡ ታምናላችሁን? መልሳችሁ ‹‹አዎ! አምናለሁ›› ከሆነ በተጨባጭ ጻድቃን ትሆናላችሁ፡፡ 
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ የሆኑትን ኩነቶች በአጭሩ እናጠቃልላቸው፡፡ በዮሐንስ 1፡29 ላይ ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› ተብሎ ተጽፎዋል፡፡  
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ እንደነበር አጥማቂው ዮሐንስ መሰከረ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ ባጠመቀው ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወደ እርሱ አስተላልፎዋል፡፡ በተጨማሪም አጥማቂው ዮሐንስ ራሱ ኢየሱስን ስላጠመቀው ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› ብሎ መመስከር ቻለ፡፡ ኢየሱስ ተጠመቀና የዓለምን ሐጢያቶች ወሰደ፡፡  ይህም ዳግም የመወለጃው ወንጌል ነው፡፡         
 
‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ!›› (ዮሐንስ 1፡29) ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወሰደ፡፡ 
ከተወለዳችሁ ጀምሮ እስከ አስር ዓመታችሁ ድረስ የሰራችኋቸው ሐጢያቶች ከዓለም ሐጢያቶች ጋር ተጨምረዋል፡፡ እነዚያ ሐጢያቶችም ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ታምናላችሁን? --አዎን አምናለሁ--፡፡ ከ11 እስከ 20 ዓመት ዕድሜያችሁ ድረስ የሰራችኋቸው መተላለፎችስ? እነዚያም ሐጢያቶች ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን ታምናላችሁን? --አዎን አምናለሁ--፡፡ 
ወደፊት የምትሰሩዋቸውም ሐጢያቶች ከዓለም ሐጢያቶች መካከል መሆናቸውንስ ታውቃላችሁን? --አዎን እነርሱም እንደዚሁ ተጨምረዋል፡፡--፡፡ እንደዚያ ከሆነ እነርሱም ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል ማለት ነዋ? --አዎን ተላልፈዋል--፡፡ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ መተላለፋቸውን ታምናላችሁን? --አዎን እናምናለን--፡፡
ከዓለም ሐጢያቶችስ መዳን ትፈልጋላችሁን? መዳን የምትፈልጉ ከሆነ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ እመኑ፡፡ አንዴ ካመናችሁ ትድናላችሁ፡፡ ይህን ታምናላችሁን? ይህ ዳግም ከመወለድ የሚገኝ እውነተኛ ደህንነት ነው፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ደሙ ዳግም ለመወለድ የሚያበቃ እውነተኛ ወንጌል ነው፡፡ ለዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ከእግዚአብሄር የተሰጠ በረከት ነው፡፡      
በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ አማካይነት ዳግም በመወለድ ደህንነት ማመንና የእርሱን ፍቅር ቀና ብሎ መመልከት እውነተኛ እምነት መያዝና በእርግጠኝነትም ዳግም መወለድ ነው፡፡ እናንተ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ቃሎች መቀበል ብቻ ይኖርባችኋል፡፡   
 
 
ሐይማኖትና እምነት፡፡ 
 
ዳግም በተወለዱ ልቦች ውስጥ ምን ምስክር አለን?
ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱና በደሙ ማስወገዱን፡፡ 

የሐይማኖት ትርጉም ንጹህ የሆነውን የእግዚአብሄር ቃል ትቶ በራስ አስተሳሰብ በኢየሱስ ማመን ነው፡፡ ከሐጢያት መዳን ግን ከራስ አስተሳሰቦች የሚመነጭ አይደለም፡፡ እምነት ማለት የራስን አስተሳሰብ ክዶ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ቃሎች በሙሉ ማመን ማለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፈውን እንዳለ መውሰድና በውሃና በደም አማካይነት ደህንነትን መቀበል ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ነው፡፡ አንድ ሰው ሊድን የሚችለው የእውነተኛውን ወንጌል ጥበብ በልቡ በመቀበል ነው፡፡   
ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችን ሊሻገሩ አይችሉም፤ ደም ሳይፈስም ስርየት የለም፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወደ ራሱ አሻግሮዋል፡፡ ኢየሱስ እነርሱን ወደ መስቀል ከመውሰዱና ደሙን ለእኛ ከማፍሰሱ በፊት ሐጢያቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ተላልፈው ነበር፡፡ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ በወንጌል አማካይነት ዳግም በመወለድ ስናምን ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ነጻ እንሆናለን፡፡    
እውነተኛ እምነት ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን እንዳነጻን ማመን ማለት ነው፡፡ ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የተፈረደውን ፍርድ በመስቀል ላይ እንደወሰደው ማመን ነው፡፡ጻድቅ በሆነው የእግዚአብሄር ደህንነት ማመን ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንንም አብዝቶ ስለወደደን በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት አዳነን፡፡ በዚህ ወንጌል ስናምን ከፍርድ ነጻ ወጥተን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፤  በእግዚአብሄርም ፊት ጻድቃን እንሆናለን፡፡  
‹‹አቤቱ አምናለሁ፡፡ እኔ ደህንነት የማይገባኝ ብሆንም በኢየሱስ ጥምቀት፣ በስቅለቱና በትንሳኤው አምናለሁ፡፡›› ዳግም ለተወለድንበት የወንጌል በረከት ጌታን ማመስገን ይኖርብናል፡፡ በእውነተኛው ዳግም የመወለድ ወንጌል ማመን እውነተኛ እምነት ነው፡፡ 
ዳግም የምንወለድበት እውነት ይህ ነው፡- ‹‹እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡›› (ሮሜ 10፡17) ‹‹እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› (ዮሐንስ 8፡32) እውነቱን በትክክል ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ይህንን በሚመሰክሩት ውሃ፣ ደምና መንፈስ ማመን ይኖርብናል፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡5-8)
‹‹እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› እነዚህ ኢየሱስ ስለ ውሃውና ስለ ደሙ የተናገራቸው ቃሎች ናቸው፡፡ አርነት ወጥታችኋልን? እኛ ታማኞች ነን ወይስ ሐይማኖተኞች ነን? ኢየሱስ የሚፈልገው ከውሃና ከመንፈስ ዳግም በመወለድ ወንጌል ላይ እምነት ያላቸውን ሰዎች ብቻ ነው፡፡  
በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ደሙ የምታምኑ ከሆነ በልባችሁ ሐጢያት የሌለባችሁ ቅዱሳን ናችሁ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በኢየሱስ የምታምኑት የሐይማኖት ክፍል አድርጋችሁት ከሆነ አሁንም እየኖራችሁ ያላችሁት በሐጢያት ውስጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በኢየሱስ ደህንነት ሙሉ እምነት የላችሁምና፡፡ የሐይማኖት ሰዎች በየጊዜው በንስሐ በመጸለይ ከሐጢያቶቻቸው ለመዳን ይሞክራሉ፡፡    
ከዚህ የተነሳ እንደ እነዚህ አይነት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻቸው ሊድኑ አይችሉም፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ንስሐ ቢገቡ እንኳን በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ በሆነው ሞቱ አማካይነት የሚገኘውን የተሟላ የሐጢያት ስርየት መተካት አይችሉም፡፡ የወደፊቶቹን የዓለም ሐጢያቶች እንኳን ሳይቀር የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ   ባስወገደው የኢየሱስ ወንጌል በማመን እንዳን፡፡  
ደግሜ እነግራችኋለሁ፤ በየቀኑ ንስሐ መግባት ዳግም የምንወለድበትን ወንጌል በጭራሽ ሊተካው አይችልም፡፡ ክርስቲያኖች በሙሉ ዳግም ለመወለድ በሚያበቃው ወንጌል አማካይነት ስርየትን ለማግኘት አሁኑኑ ማመን ይገባቸዋል፡፡  
እውነተኛ ንስሐ ምንድነው? ወደ እግዚአብሄር መመለስ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደሰጠው የደህንነት ቃል መመለስና ቃሉንም እንደተጻፈው ማመን ማለት ነው፡፡ እኛን የሚያድነን ወንጌል የኢየሱስ ጥምቀት፣ ስቅለትና ትንሳኤ ወንጌል ነው፡፡ በዚህ ወንጌል ሙሉ በሙሉ ስናምን ያን ጊዜ እንድንና የዘላለምንም ሕይወት እናገኛለን፡፡  
ዳግም የምንወለድበት የወንጌል ጥበብ ይህ ነው፡፡ ይህም ዳግም እንድንወለድ በሚፈቅድልን በኢየሱስ ጥምቀት፣ በደሙና በእግዚአብሄር መንግስት ወንጌል ማመን ነው፡፡
ኢየሱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ዳግም መወለድ እንዳለብን  በነገረን ጊዜ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙ በማመን ዳግም መወለድ እንደሚገባን መናገሩ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባትና መኖር እንችላለን፡፡ በቃሉ ማመን ይኖርብናል፡፡ ለሐጢያቶቻችን ስርየት የሚመሰክሩት ሁለቱ ነገሮች የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ዳግም እንድንወለድ የሚፈቅዱልን ቃሎች ናቸው፡፡ 
አሁንስ ዳግም በመወለድ ወንጌልና በሐጢያቶቻችን ስርየት ታምናላችሁን? በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የሚኖረን እምነት ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ያድነናል፡፡ በዚህ እምነትም ዳግም መወለድ እንችላለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በደሙ በዓለም ውስጥ ያሉትን ሐጢያተኞች ሐጢያቶች በሙሉ እንዳነጻ የሚነግረን ከሆነ በዚህ አምነን ዳግም የማንወለደው ለምንድነው?     
እነዚያ ዳግም ለመወለዳችን ምስክሮች በሆኑት ሁለት ነገሮች በኢየሱስ ጥምቀትና በስቅለቱ የሚያምኑ ትክክል ዳግም የተወለዱ ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ልጅ የሚያምን ሰው በራሱ ምስክር አለው፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡3-10) በኢየሱስ ስታምኑ የውሃውን፣ የደሙንና የመንፈሱን ወንጌል መተው አይገባችሁም፡፡ 
የጦር አዛዡ ንዕማን ሙሉ በሙሉ ከለምጹ ለመፈወስ በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ሰባት ጊዜ እንደታጠበ ሁሉ (2ኛ ነገሥት ምዕራፍ 5) ኢየሱስም በዮርዳኖስ የዓለምን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ እንዳነጻና ከዚያ የተነሳም የዘላለም ሕይወት እንደሰጠን ማመን ይገባናል፡፡   
ኢየሱስ ስለወደደን ከዓለም ሐጢያቶች ሁሉ ድነን የሐጢያት ስርየት በሚያስገኘው ወንጌል በማመን የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንችላለን፡፡ ሁላችንም ዳግም ለመወለድ በሚያበቃው ወንጌል እንመንና የእግዚአብሄርን ደህንነት እናግኝ፡፡