Search

Проповіді

ርዕስ 11፡ የመገናኛው ድንኳን

[11-1] በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠው የሐጢያተኞች ደህንነት:: ‹‹ ዘጸዓት 27፡9-21 ››

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠው የሐጢያተኞች ደህንነት::
‹‹ ዘጸዓት 27፡9-21 ››
‹‹የማደርያውንም አደባባይ ሥራ፡፡ በደቡብ ወገን የጥሩ በፍታ መጋረጆች ይሁኑለት፡፡ የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፡፡ ከናስ የተሰሩ ሐያ ምሰሶችና ሐያ እግሮች ይሁኑለት፡፡ የምሰሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ፡፡ እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጆች ከናስ የተሰሩ ሐያ ምሰሶች ሐያም እግሮች ይሁኑ፡፡ በምዕራብም ወገን ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው ያላቸው መጋረጆች አስርም ምሰሶች አስርም እግሮች ይሁኑለት፡፡ በምሥራቅም ወገን የአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን፡፡ በአንድ ወገን የመጋረጆቹ ርዝመት አስራ አምስት ክንድ ይሁን፡፡ ምሰሶቹም ሦስት እግሮቹም ሦስት ይሁኑ፡፡ በሌላውም ወገን የመጋረጆቹ ርዝመት አሥራ አምስት ክንድ ይሆናል፡፡ ምሰሶቹም ሦስት እግሮቹም ሦስት ይሁኑ፡፡ ለአደባባዩም ደጅ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊም፣ ከቀይም ግምጃ ከጥሩም በፍታ በጥልፍ አሰራር የተሰራ ሐያ ክንድ መጋረጃ ይሆናል፡፡ ምሰሶቹም አራት እግሮቹም አራት ይሁኑ፡፡ በአደባባዩም ዙሪያ ላሉት ምሰሶች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ የብር ኩላቦች፣ የናስም እግሮች ይሁኑላቸው፡፡ የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ ስፋቱም አምሳ ክንድ ይሁን፤ የመጋረጃውም ከፍታ አምስት ክንድ ይሁን፤ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ እግሮቹም ከናስ የተሠሩ ይሁኑ፡፡ ለማገልገል ሁሉ የማደርያው ዕቃ ካስማዎቹም ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ የናስ ይሁኑ፡፡ አንተም መብራቱን ሁልጊዜ ያበሩት ዘንድ ለመብራት ተወቅጦ የተጠለለ ጥሩ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት ባለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሄር ፊት እንዲበራ ያሰናዱት በእሰራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘላለም ሥርዓት ይሁን፡፡››
 
 
በአራት ማዕዘን የተሰራው የመገናኛው ድንኳን አጥር ቁመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክንድ ከክርን እስከ ጣት ጫፍ የሚዘረጋ ሲሆን በዛሬው መለኪያ ወደ 45 ሳንቲ ሜትር አካባቢ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ አጥር አንድ መቶ ክንድ ነበር ማለት 45 ሜትር ሲሆን ወርዱ 50 ክንድ ነበር ማለት ደግሞ በግምት 22.5 ሜትር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሄር በእስራኤል ሕዝብ መካከል ያደረበት ቤት ይህ ነው፡፡
 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ በአጥር የታጠረ ነበር፡፡ 
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ ምሰሶች
 
በማናቸውም አጋጣሚ የመገናኛውን ድንኳን ምሳሌ ስዕል አይታችሁ ታውቃላችሁን? የመገናኛው ድንኳን በአደባባይና የእግዚአብሄር ቤት በሆነው በራሱ በመገናኛው ድንኳን የተከፈለ ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ቤተመቅደስ ተብሎ የሚጠራ አንድ አነስተኛ መዋቅር ነበር፡፡ ቤተ መቅደሱ በአራት የተለያዩ ሽፋኖች ተሸፍኖ ነበር፡፡ በጥሩ ጥልፍ በተሰራ የበፍታ፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና ቀይ ሽፋኖች ተሸፍኖ ነበር፡፡ ሌላው ደግሞ በፍየል ቁርበቶች፣ በቀይ በተነከረ የጠቦት ቁርበቶችና በአቆስጣ ቁርበቶች ተሸፍኖ ነበር፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የምሥራቅ ወገን በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ የተሸፈነው የመግቢያ በር አለ፡፡ አንድ ሰው ይህንን በር አልፎ ሲገባ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሰውያና የመታጠቢያውን ሰን ያያል፡፡ የመታጠቢያውን ሰን ስናልፍ ራሱን የመገናኛውን ድንኳን እናያለን፡፡ የመገናኛው ድንኳን በቅድስትና የእግዚአብሄር የምስክር ታቦት በሚገኝበት በቅድስተ ቅዱሳን ተከፍሎዋል፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ አጥር ከነጭ በፍታ የተሰሩ መጋረጃዎች የተንጠለጠሉባቸው 60 ምሰሶዎች ነበሩት፡፡ በሌላ በኩል የመገናኛው ድንኳን ራሱ በ48 ሳንቃዎችና በ9 ምሰሶዎች የተሰራ ነበር፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ንድፍ አማካይነት ምን እየነገረን እንደሆነ ማስተዋል እንችል ዘንድ ቢያንስ የመገናኛውን ድንኳን ውጫዊ ገጽታዎች በሚመለከት ጠቅለል ያለ አሳብ ሊኖረን ይገባል፡፡
 
እግዚአብሄር በ48 ሳንቃዎች በተሰራው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ አደረ፡፡ እግዚአብሄር ከመገናኛው ድንኳን በላይ በተገለጠው የደመና አምድ በቀን በእሳት አምድ ደግሞ በሌሊት ለእስራኤል ሕዝብ ሕልውናውን ገለጠ፡፡ እግዚአብሄር ራሱ ባደረበት በቤተመቅደሱ ውስጥም የእግዚአብሄር ክብር ስፍራውን ሞልቶት ነበር፡፡ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ የሕብስቱ ገበታ፣ መቅረዙና የዕጣኑ መሰውያ የነበሩ ሲሆን በቅድስተ ቅዱሳኑ ደግሞ የምስክሩ ታቦትና የስርየት መክደኛው ነበሩ፡፡ እነዚህ ለተራው የእስራኤል ሕዝብ የተከለከሉ ስፍራዎች መግባት የሚችሉት ካህናቶችና ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበሩ፡፡ እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹ይህም እንዲህ ተዘጋጅቶ ሳለ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፡፡ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፡፡ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስህተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፡፡›› ይህ በዛሬው ዘመን እርሱን እያገለገሉት ከእግዚአብሄር ጋር ሕይወታቸውን መኖር የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምን ወርቅ እምነት ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ይነግረናል፡፡
 
በሕብስቱ ገበታ ላይ የተቀመጠው ሕብስት ትርጉም ምንድነው? ትርጉሙ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እንግዲያውስ የዕጣኑ መሰውያ ምን ማለት ነው? እርሱ ስለ ጸሎት የሚናገር ነው፡፡ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የምስክሩ ታቦትና ከንጹህ ወርቅ ተሰርቶ ከታቦቱ በላይ የተቀመጠው የስርየት መክደኛ አለ፡፡ ከበላዩም ኪሩቤሎች ክንፎቻቸውን በመዘርጋት የስርየቱን መክደኛ በክንፎቻቸው ሸፍነውታል፡፡ እርስ በርሳቸውም እየተያዩ አቀርቅረው የስርየት መክደኛውን ይመለከታሉ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጸጋ የተለገሰበት የስርየት መክደኛው ስፍራ ነው፡፡ በምስክሩ ታቦት ውስጥ በሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች የተቀረጹት አስርቱ ትዕዛዛቶች፣ የለመለመችው የአሮን በትርና በመና የተሞላው ማሰሮ ተቀምጠውበታል፡፡ ታቦቱ በወርቅ ሽፋን (የስርየት መክደኛ) የተሸፈነ ሲሆን ከእርሱ በላይ ደግሞ ኪሩቤሎች ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ፡፡ 
 
 
የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙት የሚኖሩት የት ነው? 
 
የሐጢያት ስርየትን ያገኙት ሰዎች የሚኖሩት በቤተመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ቤተመቅደስ የተሰራው በ48 ሳንቀዎች ሲሆን ሁሉም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አስቡ፡፡ በ48 የወርቅ ልባጮች በተለበጡ ሳንቃዎች የተሰራውን ወርቃማ አጥር ስትመለከቱ እንዴት ብሩህ ሆኖ እንደሚያበራ ትመለከታላችሁ፡፡ የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍልና ዕቃዎቹ ሁሉ በዚህ መንገድ በወርቅ የተሰሩ ስለነበሩ ብሩህ ሆነው ያበሩ ነበር፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የውጪ አደባባይ ላይ ያሉት የሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያና የመታጠቢያው ሰን በሙሉ የተሰሩት ከናስ ነበር፡፡ የአደባባዩ አጥርም የተሰራው በብር ከተለበጡ ምሰሶዎችና ከጥሩ በፍታ ነበር፡፡ በንጽጽር በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ መቅረዙ የተሰራው ከወርቅ ነበር፡፡ የሕብስቱ ጠረጴዛም እንደዚሁ ከወርቅ የተሰራ ነበር፡፡ የቤተመቅደሱ ቁሳቁሶችና ባለ ሦስት ወገን ግድግዳዎቹ ሁሉ የተሰሩት ከንጹህ ወርቅ ስለነበር የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል ሁልጊዜም ብሩህ ሆኖ ያበራ ነበር፡፡
 
የቤተ መቅደሱ ውስጠኛው ክፍል በዚህ መንገድ ወርቃማ በሆነ ብርሃን ማብራቱ የዳኑት ጻድቃን የከበረውን የእምነት ሕይወታቸውን በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚኖሩ ይነግረናል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሚኖሩት ቅዱሳን በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንደሚገኘው ንጹህ ወርቅ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚኖሩት ሕይወት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ የእግዚአብሄርን ቃል የሚመገብ፣ ወደ እርሱ የሚጸልይና እርሱን የሚያመስግን፣ በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት የሚቀርብና በየቀኑም የእርሱን ጸጋ የሚጎናጸፍ የተባረከ ሕይወት ነው፡፡ ይህ ሁሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው የእምነት ሕይወት ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ይህንን የከበረ የእምነት ሕይወት መኖር የሚችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የዳኑ ጻድቃን ብቻ መሆናቸውን በልባችሁ ጽላት ላይ ልትጽፉት ይገባል፡፡
 
 
እግዚአብሄር የቤተ መቅደሱን ውስጥና ውጪ በግልጽ ከፋፍሎታል፡፡ 
 
አብዛኞቹ ቤቶች አጥር እንዳላቸው ሁሉ የመገናኛውም ድንኳን አደባባይ እንደዚሁ በ60 ምሰሶዎች የተሰራና በጥሩ ነጭ በፍታ መጋረጃዎች የተሸፈነ አጥር ነበረው፡፡ በአደባባዩ በስተ ምሥራቅ ሁሉም ያዩት ዘንድ 9 ሜትር ወርድ ያለው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተሰራ የመግቢያ በር ነበር፡፡
 
የመገናኛውን ድንኳን ስናጠና እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገው ብሩህ እምነት ምን እንደሆነ የዳኑት ሰዎች እምነት ምን ዓይነት እምነት እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይገባናል፡፡ የመገናኛው ድንኳን በተሰራባቸው ቁሳ ቁሶች አማካይነትም ጌታችን እንዴት እንዳዳነን ማየት አለብን፡፡ ይህ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለው ወርቃማውና ብሩህ እምነት ምን እንደሆነ ለማወቅ በመጀመሪያ የመታጠቢያውን ሰን የሚቃጠለውን መስዋዕት መሰውያ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ዙሪያ ያለውን አጥርና ለእነዚህ ያገለገሉትን ቁሳቁሶች በሙሉ በጥንቃቄ መመልከት ይኖርብናል፡፡ ይህንን ስናደርግ ወደሚያበራው ወርቃማና አንጸባራቂ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለመግባት ምን ዓይነት እምነት እንደሚያስፈልገን ማወቅ እንችላለን፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ምን አለ? የመታጠቢያው ሰንና የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበት መሰውያ ነበሩ፡፡ ይህ አደባባይ በ60 የእንጨት ምሰሶዎች የተከበበ ነበር፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች ላይ የአደባባዩ አጥር ሆነው እንዲያገለግሉ ከጥሩ በፍታ የተሰሩ መጋረጃዎች ነበሩባቸው፡፡ የዚህ አጥር ምሰሶዎች ጠንካራ ቢሆኑም በጣም ቀላል ከሆነው የዝግባ እንጨት የተሰሩ ነበሩ፡፡ ከዚህ እንጨት የተሰሩት ምሰሶዎች በግምት 2.25 ሜትር ከፍታ ያላቸው ሲሆን የተለመደ ቁመት ያላቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ከአደባባዩ አጥር በስተ ውጭ ሆነው የመገናኛውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ማየት የሚቻላቸው አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ከዚህ አጥር አጠገብ አንድ መውጣጫ ሆነ ተብሎ ቢቀመጥ የአደባባዩን ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡ የዚህ ዓይነት አጋዥ ከሌለ ግን ውስጡን ማየት አዳጋች ነው፡፡ ይህም እኛ በሰው ሰራሽ ጥረቶቻችን ፈጽሞ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግበት እንደማንችል ያሳየናል፡፡
 
በአደባባዩ የእንጨት ምሰሶዎች እግር ሥር የናስ መሰኪያ ቀለበቶች ያሉ ሲሆን ጫፎቻቸውም በብር ኩላቦች የተሸፈኑ ነበሩ፡፡ ምሰሶዎቹም በራሳቸው መቆም ስለማይችሉ የብር ዘንጎች ጎን ለጎን ካሉት ምሰሶዎች ጋር እርስ በርስ ተያይዘው ነበር፡፡ ምሰሶዎቹን በመስቀልያ አቅጣጫዎች በሚገባ ለመደገፍም በምሰሶዎቹ የብር ሽፋን ላይ የተያያዙት ሜንጦዎች ከናሱ ካስማዎች ጋር በገመዶች ታስረው ነበር፡፡ (ዘጸዓት 35፡18)
 
 

ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች ምን ነበሩ? 

 
የአደባባዩ ደጅ
 
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ ነበር፡፡ የመግቢያው በር ቁመት 2.25 ሜትር ወርዱም 9 ሜትር ነበር፡፡ ይህ በአራት ምሰሶዎች ላይ የተንጠለጠለ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይና ጥሩ በፍታ ሽፋን ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ለመግባት በሚሞክርበት ጊዜ የመግቢያውን በር በቀላሉ ሊያገኘው ይችላል፡፡
 
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ግምጃና ጥሩ በፍታ እግዚአብሄር ልጁ ኢየሱስ በሰራቸው በአራቱ ሥራዎቹ አማካይነት ከሐጢያቶቻችን እንደሚያድነን ይገልጣል፡፡ የመገናኛው ድንኳን አጥር 60 የእንጨት ምሰሶዎችና ጥሩው በፍታ እግዚአብሄር እናንተንና እኔን በልጁ በኢየሱስ አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ምን ዓይነት ዘዴ እንደሚጠቀም በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
 
በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን አደባባይ አማካይነት የደህንነትን ምስጢር ለእኛ በግልጽ እየገለጠልን ነው፡፡ ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉትን ቁሳቁሶች እንደገና እንመልከታቸው፡፡ እነዚህም ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና በጥሩ ጥልፍ የተሰራ በፍታ ናቸው፡፡ እነዚህ አራቱ ማጎች እኛ በኢየሱስ እምነን እንድን ዘንድ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች አስፈላጊ ባይሆኑ ኑሮ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በስፋት አይመዘግባቸውም ነበር፡፡
 
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች በሙሉ እግዚአብሄር እናንተንና እኔን ለማዳን ፈጽሞ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን የመግቢያው በር ያለ ምንም እንከን ከሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የመሰራቱ እውነት ሐጢያተኞችን በማዳን ረገድ ለእግዚአብሄር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አራት ማጎች የእግዚአብሄርን ፍጹም የሆነ ደህንነት የሚገልጡ ነበሩና፡፡ እግዚአብሄር እንዲሆን የወሰነው በዚህ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ምሳሌውን በሲና ተራራ ለሙሴ ያሳየውና የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር በትክክል እንዲሰራ የነገረው ለዚህ ነው፡፡
 
 

የሰማያዊው፣ የሐምራዊው፣ የቀዩ ማግና የጥሩው በፍታ ትርጉም ምንድነው? 

 
የቅድስቱ ስፍራ መግቢያ በር የተሰራው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ ሲሆን በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል ያለው መጋረጃም እንደዚሁ ከእነዚህ አራት ማጎች የተጠለፈ ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሊቀ ካህኑ ኤፉድና የደረት ኪስም እንደዚሁ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ታዲያ ሰማያዊው፣ ሐምራዊው፣ ቀዩ ማግና ጥሩው በፍታ ምን ይነግሩናል? ጌታችን እኛን ያድን ዘንድ እጅግ አስፈላጊ የሆኑት እነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩው በፍታ በትክከል ምን ይነግሩናል? ይህን ጉዳይ በሚገባ ለመመርመር በጣም እርግጠኞች መሆን ይገባናል፡፡
 
በመጀመሪያ ሰማያዊው መጋረጃ የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት ይነግረናል፡፡ ስለ ጥምቀት ፋይዳ የማያውቁ ሰማያዊው ማግ የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት የሚያመለክት ስለመሆኑ አያውቁም፡፡ ስለዚህ ዳግመኛ ያልተወለዱት በጥቅሉ የሰማያዊው ማግ ትርጉም ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር ራሱ ነው፤ ወደዚህ ምድርም የሰውን ሥጋ ለብሶ መጣ›› ማለት ነው ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ‹‹ሰማያዊው ማግ ቃሉ ማለት ነው›› ይላሉ፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሰማያዊው ማግ ‹‹ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ከመጣ በኋላ የዓለምን ሐጢያቶች የተቀበለበት የኢየሱስ ጥምቀት››› ማለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ሰማያዊው ማግ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን የውሃ ጥምቀት እንደሚያመለክት መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያሳየናል፡፡ ስለ መገናኛው ድንኳን የተጻፈውን ወንጌል ሳነብ ‹‹አሃ እግዚአብሄር በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ያለውን የእምነታችንን ጠቀሜታ ሊያሳየን ይፈልጋል›› ወደሚል መረዳት ደረስሁ፡፡
 
ሊቀ ካህኑ ቁርባኖችን በሚያቀርብበት ጊዜ የሚለብሰው መጎናጸፊያም እንደዚሁ ከሰማያዊ ማግ የተጠለፈ ነበር፡፡ ሊቀ ካህኑ በራሱ ላይ በሚያደርገው መጠምጠሚያ ላይ የወርቅ ምልክት ነበረበት፡፡ ምልክቱን ከመጠምጠሚያው ጋር የሚያያይዘው ማሰሪያም እንደዚሁ ሰማያዊ ነበር፡፡ በዚህ የወርቅ ምልክት ላይ ‹‹ቅድስና ለእግዚአብሄር›› የሚል ሐረግ ተቀርጾበታል፡፡ የወርቁን ምልክት ከሊቀ ካህኑ መጠምጠሚያ ጋር የሚያስረው ሰማያዊው ፈትል ለእግዚአብሄር ቅድስና የሚሰጠውን የኢየሱስን ጥምቀት በግልጥ የሚያሳይ እንደሆነ ማት እንችላለን፡፡
 
በዚህ መንገድ እግዚአብሄር የወርቁን ምልክት ከመጠምጠሚያው ጋር ባያያዘው በዚህ የሰማያዊ ፈትል አማካይነት ስለ እውነተኛው ደህንነታችን ይነግረናል፡፡ በሌላ አነጋገር ቅድስናን የሚሰጠን ፈትል ሰማያዊ ነው፤ ይህም የኢየሱስ ጥምቀት ነው፡፡ ሰማያዊው ቀለም በጥቅሉ ስለ ሰማያዊው ሰማይ የሚያስታውሰን ቢሆንም ሰማያዊ እግዚአብሄርን ብቻ የሚያመለክት አይደለም፡፡ ከሰማያዊው፣ ከሐምራዊው ከቀዩ ማግና ከጥሩው በፍታ አንጻር ሰማያዊው ማግ የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት የሚያመለክት መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ኢየሱስ በጥምቀቱ የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች ባይወስድ ኖሮ እኛ ምዕመናኖች ‹‹ቅድስናን ለእግዚአብሄር›› መስጠት አንችልም ነበር፡፡ በኢየሱስ ጥምቀት ባይሆን ኖሮ በእግዚአብሄር ፊት በቅድስና ባልተሸፈንን ነበር፡፡
 
የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ለሙሴ በታየው ምሳሌ መሰረት በሰማያዊ ግምጃ ይሰራ ዘንድ እግዚአብሄር የሰጠውን ትዕዛዝ መንፈሳዊ ትርጉም ታውቁታላችሁን? ወደ መገናኛው ድንኳን የሚመራው የአደባባዩ መግቢያ በር የሚያመለክተው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ካልሆነ በስተቀር ማንም መንግሥተ ሰማያት መግባት አይችልም፡፡ ኢየሱስን የሚያመለክተው የአደባባዩ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተሰራ ነበር፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ወደ ደህንነታችን የሚመራንን እውነት መግለጥ ፈልጎዋልና፡፡ ሐምራዊው ማግ ‹‹ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ መሆኑን›› የሚነግረንን መንፈስ ቅዱስን ያመላክታል፡፡ ቀዩ ማግ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን ያመለክታል፡፡ ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው ሰማያዊው ማግ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀት ያሳያል፡፡
 
ስለዚህ ሰማያዊው፣ ሐምራዊውና ቀዩ ማጎች ስለ ኢየሱስ ጥምቀት፣ ስለ እግዚአብሄር ሥጋ መልበስና በመስቀል ላይ ስለሆነው ሞቱ ይነግሩናል፡፡ በእነዚህ ሦስት ማጎች የተገለጡት የኢየሱስ ሥራዎች በቅድስና በየሆዋ ፊት የምንቀርብበትን እምነት ይሰጡናል፡፡ እግዚአብሄር የሆነው ኢየሱስ ራሱ የሰውን ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት በጥምቀቱ የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች በሙሉ በሰውነቱ በመሸከም ደሙን አፍስሶ የሐጢያቶችንና የእርግማኖችን ኩነኔ በሙሉ ወሰደ፡፡ የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ማግ ዋና መንፈሳዊ ትርጉም ይህ ነው፡፡
 
ምናልባት እስካሁን ድረስ ሰማያዊው ማግ እግዚአብሄርን ወይም ቃሉን የሚገልጥ እንደሆነ አድርጋችሁ ብቻ አስባችሁት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰማያዊው ማግ በትክክል የሚያመለክተው የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት እንደሆነ በግልጥ ማወቅ አለባችሁ፡፡ ኢየሱስ ወደ እርሱ የተሻገሩለትን ሐጢያቶች በሙሉ የተቀበለበት ጥምቀት በጣም አስፈላጊና ከእርሱ ሥራዎች መገንጠል መቻል የሌለበት ነው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳኑ የመገናኛው ድንኳን አማካይነት ጠቀሜታውን እየነገረን ነው፡፡
 
 

የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችንን የተሸከመበት መንገድ ነው፡፡ 

የኢየሱስ ጥምቀት ሐጢያቶቻችንን የተሸከመበት መንገድ ነው፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አጥር ምሰሶዎች ከግራር እንጨት የተሰሩ ነበሩ፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች እግሮች ሥር የናስ መሰኪያዎች ተደርገው ነበር፡፡ በጫፎቻቸው ላይም የብር ሽፋኖች ተደርገውባቸዋል፡፡ ይህ በመጀመሪያ ሐጢያተኞች ለሐጢያቶቻቸው መኮነን እንዳለባቸው ይነግረናል፡፡ ገና ያልተፈረደባቸውና ያልዳኑ በእግዚአብሄር ፊት ሲቀርቡ ለሐጢያቶቻቸው የዘላለም ቅጣትን ከመቀበል ሊሸሹ አይችሉም፡፡
 
እንዲህ ተብሎ ተጽፎዋል፡- ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፡፡›› (ሮሜ 6፡23) ሐጢያተኞች ለሰሩዋቸው ሐጢያቶች የእግዚአብሄርን አስፈሪ ፍርድ እንደሚቀበሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ ሐጢያተኞች ለሐጢያቶቻቸው አንድ ጊዜ በእግዚአብሄር መኮነንና ከዚያም የእርሱን ጸጋ በመጎናጸፍ እንደገና በሕይወት መኖር አለባቸው፡፡ ዳግመኛ መወለድ ማለት ይህ ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በራሱ ላይ መውሰዱን የሚያምነው የሰማያዊው ማግ እምነትና ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመኮነን ሐጢያተኞችን ሁሉ ማዳኑን የሚያምነው የቀዩ ማግ እምነት አንድ ጊዜ ለሐጢያቶቻችን ሞተን ዳግመኛ እንድንወለድ የሚያደርገን እምነት ነው፡፡ የዘላለም ኩነኔ የሚጠብቃቸው በአለማመናቸው ምክንያት በእምነት በፍርድ ውስጥ ማለፍ የማይችሉትን ብቻ እንደሆነ መረዳት አለባችሁ፡፡
 
የኢየሱስ ጥምቀት እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለማዳን ሐጢያቶቻችንን በሙሉ የተሸከመበት መንገድ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በራሱ ላይ ለመሸከም በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ኢየሱስ ራሱ አምላክ ነው፡፡ ነገር ግን እኛን ለማዳን የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ የሰው ዘር ወኪል በሆነው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅም የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ሥጋውን በመስቀል ላይ በመስጠትና ውሃና ደምን በማፍሰስ በሐጢያተኞች ፋንታ በይፋ ተኮነነ፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ኢየሱስ አዳኛችን ሆኖ ስለፈጸማቸው ሥራዎች በይፋ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር አማካይነት ኢየሱስ የሐጢያተኞች መድህን እንደሆነ በግልጽ እየነገረን ነው፡፡
 
በጥሩ ጥልፍ የተጠለፈው በፍታ በስፋት የተዘረዘረውንና እርስ በርሱ የሚስማማውን የብሉይና አዲስ ኪዳናትን ቃል ያመለክታል፡፡ ይህንን የተጠለፈ ጥሩ በፍታ ለመስራት እያንዳንዱ ክር ምን ያህል ተጠላልፎ ተሰርቶ ይሆን? በዚህ ጥሩ በፍታ አማካይነት እግዚአብሄር እንዴት እንዳዳነን በግልጽ እየነገረን ነው፡፡
 
ምንጣፎችን በምንመለከትበት ጊዜ የተለያዩ ማጎችን በአንድ ላይ በመፍተል እንደተሰሩ እናያለን፡፡ ልክ እንደዚሁ እግዚአብሄር እስራኤላውያንን ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና ጥሩ በፍታን በመፍተል የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር እንዲሰሩ ነገራቸው፡፡ ይህም በውሃው፣ (ጥምቀት) በደሙ (መስቀል) እና በመንፈስ ቅዱስ (ኢየሱስ አምላክ ነው) የመጣውና ባማረው የእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የተሰወረው ዋናው የደህንነት መግቢያ በራችን እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ባማረው የእግዚአብሄር ቃል ውስጥ በተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በማመንና ፍቅሩን በመልበስ አሁን በእምነት አማካይነት ሙሉ በሙሉ ድነናል፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ ያዳነን በደፈናው አይደለም፡፡ የመገናኛውን ድንኳን በምንመለከትበት ጊዜ ይህንን ማየት እንችላለን፡፡ ኢየሱስ በእርግጥም ሐጢያተኞችን ባማረ ሁኔታ አድኖዋል፡፡ የአጥሩን ምሰሶዎች ብቻ ስንመለከት እርሱ ምን ያህል ባማረ ሁኔታ እንዳዳነን ማየት እንችላለን፡፡ ከቁጥሮች ሁሉ የአጥሩ ምሰሶዎች ቁጥር ለምን 60 ሆነ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት 6 ቁጥር ሰውን ስለሚያመለክትና 3 ቁጥር ደግሞ እግዚአብሄርን ስለሚያመለክት ነው፡፡ በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ 666 የሚለው ምልክት ይታያል፡፡ ይህ ቁጥር የአውሬው ቁጥር እንደሆነና ጠቢብ የሆነ ሰው የዚህን ቁጥር ምስጢር እንደሚያወቅ እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡ ስለዚህ 666 የሚለው ቁጥር ሰው ልክ እንደ እግዚአብሄር ይሰራል ማለት ነው፡፡ የሰው ዘር ፍላጎት ምንድነው? ፍጹም መለኮታዊ ሕላዌ መሆን አይደለምን? በእርግጥ መለኮታዊ ሕላዌ መሆን የምንፈልግ ከሆንን በኢየሱስ በማመን ዳግመኛ መወለድና የእግዚአብሄር ልጆች መሆን አለብን፡፡ 60ዎቹ ምሰሶዎች ይህንን አንደምታ በሚገባ ያመለክታሉ፡፡
ሆኖም ሰዎች በማመን ፋንታ በራሳቸው ጥረቶች የዚህ መለኮታዊ ባህርይ ተካፋይ ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ ሰዎች ቃሉን እንደ ሰው ፍላጎት ዳግመኛ የተረጎሙበትና በራሳቸው ሰው ሰራሽ አስተሳሰቦች የካዱበት ምክንያት ይህ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እነርሱ እምነት የላቸውም፡፡ ያላቸው ነገር ቢኖር እግዚአብሄርን የሚቃወም ምኞት ብቻ ነው፡፡ በራሳቸው ምሉዓን እንዲሆኑና በራሳቸው ሥጋ ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ ከሚያስገድዳቸው ከዚህ የሥጋ ፍትወት የተነሳ ፍጻሜያቸው ከእግዚአብሄር በጣም መራቅ ሆንዋል፡፡
 
 
በመገናኛው ድንኳን ቁሳቁሶች ሁሉ ውስጥ የተገለጠው የደህንነት ቃል፡፡ 
 
ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያተኞችን ለማዳንና ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ስቦ ለማስገባት የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎችና ቁሳቁሶች በሙሉ አስፈላጊ ነበሩ፡፡ የመታጠቢያው ሰን አስፈላጊ ነበር፡፡ ምሰሶዎቹ፣ የናስ ኩላቦቹ፣ የብር ዘንጎቹ፣ ሜንጦዎቹና የብር ማሰሪያዎቹ አስፈላጊ ነበሩ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ውጭ የሚገኙ ዕቃዎች ነበሩ፡፡ ሐጢያተኛውን ወደ ጻድቅ ሰው ለመለወጥ ቁሳቁሶቻቸው በሙሉ አስፈላጊ ነበሩ፡፡
 
እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሐጢያተኛው ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ገብቶ እንዲኖር ለማስቻል አስፈላጊ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ መካከል እጅግ አስፈላጊው ሰማያዊው ማግ (የኢየሱስ ጥምቀት) ነበር፡፡ ሰማያዊው፣ ሐምራዊውና ቀዩ ማጎች የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ለመከለል ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እነዚህ ማጎች በእግዚአብሄር ስናምን ለእኛ አስፈላጊ የሆኑትን የኢየሱስን ሦስት ሥራዎች ያመለክታሉ፡፡ በመጀመሪያ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ሁለተኛ እግዚአብሄር አምላክ (መንፈስ) ነው፡፡ ሦስተኛ ኢየሱስ በዮሐንስ አማካይነት በዮርዳኖስ ወንዝ በራሱ ላይ የተቀበላቸውን ሐጢያቶች ኩነኔ በሙሉ ለመሸከም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ሐጢያተኞች እንዲድኑና ጻድቃን እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸው የእምነት ቅደም ተከተል ይህ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ጌታችን ምን ያህል ያማረ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እኛን እንደዚህ ጥሩ በፍታ ባማረ ሁኔታ ያዳነን አምላክ ራሱ እግዚአብሄር እንጂ ሌላ እንዳልሆነ በግልጽ መረዳት እንችላለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሄር 9 ሜትር ወርድ ባለው ጥሩ በፍታ ላይ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማጎችን በመፍተል የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር እንዲሰሩ እስራኤሎችን አዘዛቸው፡፡ ስለዚህ የመገናኛውን ድንኳን ከርቀት እንኳን ማየት የሚችል ማንኛውም ሰው የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር በቃሉ ማየት እንዲችል እግዚአብሄር ማረጋገጫን ሰጥቶዋል፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ምሰሶዎች ላይ ተንጠለጠለው ያማረ ነጭ በፍታ የእግዚአብሄርን ክብር ያሳያል፡፡ ስለዚህ ሐጢያተኞች የመገናኛውን ድንኳን ለመቅረብ መድፈር እንደማይችሉና ወደ አደባባዩ መግባት የሚችሉትም ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር በተጠለፉት ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማጎች በተገለጡት የኢየሱስ ሥራዎች በትክክል ሲያምኑ ብቻ እንደሆነ መረዳት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር በዚህ መንገድ ሐጢያተኞች ኢየሱስ ክርስቶስ ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ ደምስሶ በውሃው፣ በደሙና በመንፈስ ቅዱሱ አማካይነት ይድኑ ዘንድ አስችሎዋቸዋል፡፡
 
ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የመገናኛው ድንኳን የተሰራባቸው ቁሳቁሶች የአደባባዩን የመግቢያ በር ጨምሮ እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን ወደ ጻድቃንነት ይለውጣቸው ዘንድ ያስፈለገውን ያማረ ቃልም ያሳዩናል፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤሎች የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር እያንዳንዱ ሰው ሊያገኘው በሚችልበት መንገድ ሰፊ አድርገው እንዲሰሩት ስለነገራቸውና ይህም የመግቢያ በር በጥሩ በፍታ ላይ በተጠለፈ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማጎች ባማረ ሁኔታ የተሰራ ስለነበር እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን ወደ ጻድቅነት ሊለውጣቸው የሚችለውን ጠቃሚ ቃል ሁሉም በግልጥ ያስተውሉ ዘንድ አስችሎዋቸዋል፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር እንደ ግራር እንጨት የሆነውን እኛን በሰማያዊው ማግ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) በሐምራዊው ማግና (ኢየሱስ አምላክ ነው) በቀዩ ማግ (የመስቀሉ ደም) አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ሙሉ በሙሉ እንዳዳነን ይነግረናል፡፡ የእግዚአብሄር ቤት ወደሆነው ቤተ መቅደስ መግባት የሚችሉት በዚህ በግልጥ የሚያምኑ ብቻ እንዲሆኑ እግዚአብሄር ወስኖዋል፡፡
 
 
ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ አንደምታ አማካይነት እየነገረን ነው፡፡ 
 
ወርቃማውን የሚያበራ የእምነት ሕይወት መኖር ከመቻላችን በፊት አስቀድመን በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ መንጻት አለብን፡፡ እግዚአብሄር ራሱ ምሳሌውን ለሙሴ ያሳየው፣ ከዚያም በሙሴ አማካይነት የሰራውና የእስራኤል ልጆችም በዚህ የመገናኛው ድንኳን ተቋም አማካይነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት እንዲያገኙ ያደረገው ለዚህ ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ አሳልፎ ወደ ቤተ መቅደሱ የወሰደንን እምነት እናስታውሰው፡፡ እግዚአብሄር በመገናኛው ድንኳን አደባባይ አማካይነት ኢየሱስ በውሃው፣ በደሙና በመንፈስ ቅዱስ ያዳነን በመሆኑ እውነት ላይ ስላለን እምነት መናገሩን ቀጥሎዋል፡፡ የአደባባዩ መግቢያ በር በሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ የተሰራ መሆኑን ማመናችን፣ ሊቀ ካህኑም ለመስዋዕት በሚቀርበው ጠቦት ላይ እጆቹን የሚጭንና የዚህ መስዋዕታዊ ጠቦት ደምም የሚፈስስ መሆኑን ማመናችን፣ ሊቀ ካህኑ እጆቹንና እግሮቹን በመታጠቢያው ሰን ውስጥ የሚታጠብ መሆኑን ማመናችን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ወደ ቤተ መቅደሱ እንድንገባና በዚያም በክብር እንድንኖር የሚያስችለን ንጹህ ወርቅ የሆነው እምነታችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያለን እምነታችን ብቻ መሆኑን እንድናውቅ ይፈቅድልናል፡፡
 
ይህንን ሁሉ ዘመን በኢየሱስ ስታምኑ የከረማችሁት እንዲያው በአጋጣሚ ነበርን? ሰማያዊው ቀለም የሚያመለክተው ሰማያዊውን ሰማይ ብቻ እንደሆነ አምናችሁ ነበርን? በሐምራዊውና በቀዩ ቀለማቶች ላይ ያላችሁ እምነት የነገሥታት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በመስቀሉ ብቻ ያዳነን መሆኑን አውቃችሁ ስታምኑ ነበርን? እንደዚያ ከሆነ እውነተኛውን እምነት ለማግኘት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሁላችሁም የሰማያዊውን ቀለም እምነት ማለትም የኢየሱስን ጥምቀት በግልጽ አውቃችሁ እግዚአብሄር የሰጣችሁን ልኬት የሌለውን የደህንነት ጸጋ በመገንዘብ እንደምታምኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
 
እግዚአብሄር ያዳነን በደሙና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ብቻ አይደለም፡፡ ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለ ሰማያዊው፣ ስለ ሐምራዎውና ስለ ቀዩ ማጎች በግልጽ ነግሮናል፡፡ በእነዚህ ሦስት ማጎች አማካይነትም ኢየሱስ እንዴት እንዳዳነን በትክክል ነግሮናል፡፡ በመገናኛው ድንኳን አማካይነት አምላካችን የኢየሱስን የደህንነት ሥራዎች በዝርዝር አሳይቶናል፡፡ እግዚአብሄር ሙሴ የመገናኛውን ድንኳን እንዲሰራ ካዘዘው በኋላ በዚህ የመገናኛው ድንኳን አማካይነት በዚህ መንገድ እንደሚያድነን ተስፋ ሰጠ፡፡ በተስፋውም መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ሥጋ ለብሶ በመምጣት በዮርዳኖስ ወንዝ በውሃ ውስጥ ተጠምቆ (ሰማያዊ) ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያተኞችን በተጨባጭ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ አድኖዋቸዋል፡፡ ደህንነታችን ምን ያህል ያማረ፣ ምን ያህል ትክክለኛና እርግጠኛ ነው!
 
ወደ ቅድስቱ ስፍራ ስንገባ መቅረዙን፣ የሕብስቱን ገበታና የዕጣኑን መሰውያ እንመለከታለን፡፡ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመግባታችን በፊት ለልባችን ትፍስሐት የሚያመጣልንን የቃሉን እንጀራ እየተመገብን በብሩህ ወርቅ በሚያብለጨልጨው በዚህ ቅድስት ስፍራ ውስጥ ለጊዜው እንቆያለን፡፡ ይህ ምንኛ የተባረከ ነው? ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ከመግባታችን በፊት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ዳግመኛ በመወለድ ሙሉ በሙሉ የዳንን ሰዎች ሆነን በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንኖራለን፡፡ የሕይወትን እንጀራ የምትሰጠን የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ቅድስት ስፍራ ነች፡፡
 
በቅድስቱ ስፍራ ማለትም በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ መቅረዙ፣ የሕብስቱ ገበታና የዕጣኑ መሰውያ አሉ፡፡ ከአገዳው፣ ከቅርንጫፎቹ፣ ከጽዋዎቹ፣ ከጉብጉቦቹና ከአበቦቹ ጋር ከአንድ መክሊት ንጹህ ወርቅ ተቀጥቅጦ የተሰራው መቅረዝ እኛ ጻድቃን የሆንን ሰዎች ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ጋር መቆራኘት እንደሚገባን ይነግረናል፡፡
 
በሕብስቱ ገበታ ላይ እርሾ የሌለበት ሕብስት የሚቀመጥ ሲሆን የሚያመለክተውም ከዚህ የረከሰ ዓለም ክፉና ብልሹ ትምህርቶች ነጻ የሆነውን ንጹሁን የእግዚአብሄር ቃል ሕብስት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ማለትም የእግዚአብሄር ቤት እርሾ የሌለበትን ይህንን ንጹህ ቃል ትሰብካለች፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገርን ሳትሰራም በንጹህ እምነት ትኖራለች፡፡
ከቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ፊት ለፊት የዕጣኑ መሰውያ ተቀምጦዋል፡፡ የዕጣኑ መሰውያ ለእግዚአብሄር ጸሎት የሚቀርብበት ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባሉት ዕቃዎች አማካይነት በእርሱ ፊት በምንቀርብበት ጊዜ አንድነት፣ በንጹህ ቃሉም እምነትና ጸሎት ሊኖረን እንደሚገባ እየነገረን ነው፡፡ መጸለይ የሚችሉት ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር የሚያደምጠው የጻድቃንን ጸሎቶች ብቻ ነውና፡፡ (ኢሳይያስ 59፡1-2፤ያዕቆብ 5፡16) ሁሉም በእግዚአብሄር ፊት በትጋት ስለጸለዩ ብቻ ከእርሱ ጋር መገናኘት ይችላሉ ማለት አይደለም፡፡
 
ልክ እንደዚሁ ቅድስቱ ስፍራ በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖ መዳን ምን ያህል የከበረ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት ቁልፍ ቁሳቁሶች ማለትም ሰማያዊው ማግ፣ (ኢየሱስ መጠመቁ) ቀዩ ማግ (ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ በመስቀል ላይ መሞቱና የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ መሸከሙ) እና ሐምራዊው ማግ (ኢየሱስ አምላክ መሆኑ) ፈጽሞ ልናጣው የማይገባንን እምነት ያመለክታሉ፡፡ እነዚህ ሦስቱ እምነታችንን በሙሉ ያዋቅራሉ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅና በባህርይውም አምላክ መሆኑን፤ ያዳነንም እርሱ መሆኑን ስናምን ብቻ እግዚአብሄር ወደሚያድርበት አብረቅራቂ ስፍራ ወደሆነው ቅድስቱ ስፍራ መግባት እንችላለን፡፡ በእነዚህ ሦስት ማጎች በተገለጡት የኢየሱስ ሥራዎች የማናምን ከሆነ ምንም ያህል በኢየሱስ አጥብቀን ብናምንም በጭራሽ ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት አንችልም፡፡ ሁሉም ክርስቲያኖች ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት አይችሉም፡፡
 
 
የተሳሳተ እምነት ይዘው በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የሚቆዩ ሰዎች፡፡ 
 
ዛሬ እምነት እንዳላቸው ቢናገሩም ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት ያልቻሉ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በእውር ድንብር እምነታቸው ለመዳን የሚሞክሩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የዚህ ዓይነት ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ደም፤ እርሱ የነገሥታት ንጉሥና አምላክ ነው ብለው በማመን ብቻ መዳን እንደሚችሉ የሚያስቡ ሰዎች በትክክል የዚህ ዓይነት ሰዎች ናቸው፡፡ በደፈናው በኢየሱስ ያምናሉ፡፡ በኢየሱስ ደም ብቻ ስለሚያምኑ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰዊያ አጠገብ ቆመው ‹‹አቤቱ እኔ አሁንም ሐጢያተኛ ነኝ፤ አቤቱ ይቅር በለኝ፡፡ በእኔ ፋንታ ስለተሰቀልክልኝ ስለሞትህልኝ ምስጋናዬን ሁሉ አቀርብልሃለሁ፡፡ አቤቱ እወድሃለሁ›› እያሉ በዕውር ድንብር ይጸልያሉ፡፡
 
ይህን ጸሎት በማለዳ ከጸለዩ በኋላ ኑሮዋቸውን በመኖር ይቀጥላሉ፡፡ ከዚያም በምሽት እንደገና ወደሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ በየማለዳው፣ በየምሽቱና በየወሩ የሚያጨናንቁ ሰዎች ዳግመኛ ሊወለዱ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በራሳቸው አስተሳሰቦች መሰረት የተሳሳተ እምነት ውስጥ የተዘፈቁ ናቸው፡፡
 
እነርሱ በእሳት ነበልባል በሚንቀለቀለው መሰውያ ላይ መስዋዕታቸውን አቅርበው የእሳት ቁርባኖቻቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሥጋው በመሰውያው ነበልባል ስለሚቃጠል ሽታው የተጠበሰ ሥጋ ሆኖ ይናኛል፡፡ ነጭና ጥቁር ጢስም ይንቦለቦላል፡፡ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበት መሰውያ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን እንዲያስወግድ የምንጸልይበት ስፍራ ሳይሆን የእግዚአበሄርን አስፈሪ የሲዖል እሳት የሚያስታውሰን ስፍራ ነው፡፡
 
ሆኖም ሰዎች በየማለዳውና በየጠዋቱ ወደዚህ ስፍራ እየሄዱ ‹‹አቤቱ በድያለሁ፤ እባክህ ሐጢያቶቼን ሁሉ ይቅር በለኝ›› ይላሉ፡፡ ከዚያም ወደ ቤታቸው ተመልሰው የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ በተጨባጭ ያገኙ ይመስል በእርካታ ይሞላሉ፡፡ ‹‹♫ይቅር ተብያለሁ፤ ♫ሁላችንም ይቅር ተብለናል›› ብለው በደስታ ይዘምራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ስሜቶች ጊዜያዊ ብቻ ናቸው፡፡ ብዙም ሳይቆይ እንደገና ሐጢያት ይሰራሉ፡፡ ደግመውም በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ አጠገብ ቆመው ‹‹አቤቱ እኔ ሐጢያተኛ ነኝ›› በማለት ይናዘዛሉ፡፡ በየቀኑ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ ከወዲህ ወዲያ የሚቃብዙ በኢየሱስ ያላቸው እምነት ምንም ይሁን አሁንም ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቅዱስ ወደሆነው የእግዚአብሄር መንግሥት በጭራሽ አይገቡም፡፡
 
ታዲያ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት አግኝተው ወደ እግዚአብሄር ቅዱስ ስፍራ መግባት የሚችለው ማነው? እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የሰማያዊውን፣ ሐምራዊውንና ቀዩን ማግ ምስጢር አውቀው የሚያምኑበት ናቸው፡፡ በዚህ የሚያምኑ ወደ እርሱ የተሻገሩትን ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ በተቀበለው ኢየሱስ ሞት ባላቸው እምነት የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሰውያ በማለፍ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ሰን ላይ ታጥበው ሐጢያቶቻቸው በሙሉ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ እርሱ መሻገራቸውን በማስታወስ ወደ እርሱ መሻገራቸውን በማስታወስ ወደ ቅድስት ስፍራ መግባት የሚችሉ ናቸው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አምነው የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉ በእምነታቸው ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም እምነታቸው በእግዚአብሄር የተደገፈ ነውና፡፡
 
የሰማያዊው ማግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉም የኢየሱስ ጥምቀት መሆኑን ሁላችሁም እንደምትረዱና እንደምታምኑ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዛሬ በኢየሱስ እንደሚያምኑ የሚናገሩ አሉ፡፡ ነገር ግን የኢየሱስን ጥምቀት በሚያመለክተው ውሃ (ሰማያዊ ማግ) የሚያምኑ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይህ እጅግ የሚያሳዝን ክስተት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የጥምቀት እምነት ከክርስትና እምነታቸው ማውጣታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው አምላክ ለመሆንና በመስቀል ላይ ለመሞት ብቻ አይደለም፡፡ አሁንም ቢሆን ሁላችሁም በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ እምነት በማመንና እርሱን በማወቅ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት የምትችሉ ዕጩዎች እንድትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እጸልያለሁም፡፡
 
 
እኛ ባዳነን የእርሱ ትክክለኛ ቁም ነገር በሆነው የመገናኛው ድንኳን ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ በተገለጠው ጌታ ማመን አለብን፡፡ 
 
ጌታችን እናንተንና እኔን ሙሉ በሙሉ አድኖናል፡፡ የመገናኛውን ድንኳን በምንመለከትበት ጊዜ ጌታ እንዴት ባለ ድንቅ ዘዴ በተጨባጭ እንዳዳነን ማየት እንችላለን፡፡ ለዚህ በሚገባ አላመሰገንነውም፡፡ ጌታ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት ስላዳነን አመስጋኞች ልንሆን ይገባናል፡፡ በእነዚህ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ የሚያምን እምነት ስለሰጠንም ልናመሰግነው ይገባናል!
ሐጢያተኞች የእግዚአብሄርን ጸጋ ሳይለብሱና ለሐጢያቶቻቸውም በአስፈሪው ፍርዱ ውስጥ ሳያልፉ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ሊገቡ አይችሉም፡፡ ለሐጢያቶቹ ፍርድን ያልተቀበለ ሰው የመገናኛውን ድንኳን በር ከፍቶ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ሊገባ ይችላል? አይችልም! እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ወደ ቅድስቱ ስፍራ ሲገቡ ይገረሙና በቅጽበት ውስጥ በብርሃኑ ሐይል ይታወራሉ፡፡ ‹‹እዚህ ብሩህ ነው! ኦ አንዳች ነገር ማየት ያልቻልሁት ለምንድነው? ውጭ ሳለሁ ወደ ስፍራው ብገባ በቅድስቱ ስፍራ ያለውን እያንዳንዱን ነገር ማየት እችላለሁ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ ታዲያ ምንም ነገር ማየት ያልቻልሁት ለምንድነው? እዚህ ሁሉም ነገር ጨለማ የሆነው ለምንድነው? ከቅድስቱ ስፍራ ውጪ በነበርሁ ጊዜ በደምብ ማየት እችል ነበር፡፡…ቅድስቱ ስፍራ ብሩህ እንደሆነ ተነግሮኝ ነበር፡፡ ይህ ስፍራ እንዴት ይበልጥ ጨለማ ሆነ?›› መንፈሳዊ ዕውራን ስለሆኑ ማየት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና ቀዩ ማግ እምነት የላቸውምና፡፡ ከዚህ የተነሳ ሐጢያተኞች በጭራሽ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ሊገቡ አይችሉም፡፡
 
ጌታችን ለዘላለም በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ የመኖርን በረከት ሰጠን እንጂ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ እንድንታወር አላደረገንም፡፡ በእያንዳንዱ የመገናኛው ድንኳን ክልል በሚገኘው ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና በጥሩው በፍታ አማካይነት እግዚአብሄር የዳንበትን ዘዴ በትክክል ነግሮናል፡፡ በዚህ የትንቢት ቃል መሰረት በእርግጥም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል፡፡
 
ጌታችን በእርሱ የሚያብረቀርቅ ጸጋ ውስጥ ለዘላለም እንድንኖር እንጂ እንዳንታወር በውሃው፣ በደሙና በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት አድኖናል፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡4-8) እርሱ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ አማካይነት አድኖናል፡፡ ጌታችን ባማረው የእግዚአብሄር ቃል ተስፋ ሰጥቶናል፡፡ ይህንን ተስፋ በመፈጸምም እንዳዳነን ነግሮናል፡፡
 
እናንተና እኔ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጡት የኢየሱስ ያማሩ ሥራዎች እንደዳንን ታምናላችሁን? አዎ! የዳናችሁት በዘፈቀደ ብቻ ነውን? አይደለም! በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ሳናምን መዳን አንችልም፡፡
ሰማያዊው ማግ እግዚአብሄርን አያመለክትም፡፡ የሚያመለክተው የእያንዳንዱን በዓለም ላይ የሚኖር ሐጢያተኛ ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደበትን የኢየሱስን ጥምቀት ነው፡፡
 
የኢየሱስን ጥምቀት በሚያመለክተው ሰማያዊው ማግ ሳያምኑ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ አጠገብ መቆም ይቻላል፡፡ ሰዎች ከሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያ አጠገብ ወዳለው የመታጠቢያ ሰንም ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ወደሚኖርበት ቅድስት ስፍራ መግባት አይችሉም፡፡ የመገናኛውን ድንኳን በር ከፍተው ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የሚችሉት ሙሉ በሙሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሐጢያት ስርየትን ያገኙ እውነተኛ የእግዚአብሄር ልጆች ብቻ ናቸው፡፡ ሐጢያተኞች ግን ማንም ይሁኑ በጭራሽ ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት አይችሉም፡፡ ወደ ደህንነታችን ለመድረስ ምን ያህል ርቀን መግባት ይኖርብናል? የምንድነው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ስንገባ ሳይሆን እግዚአብሄር ወዳለበት ቅድስት ስፍራ ስንገባ ብቻ ነው፡፡
 
 
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው እምነትና ከመገናኛው ድንኳን ውጪ ባለው እምነት መካከል ያለው ልዩነት፡፡ 
 
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ ያሉት የሚቃጠል መስዋዕት መሰውያና የመታጠቢያው ሰን ሁሉም ከናስ የተሰሩ ነበሩ፡፡ አጥሩም ከእንጨት፣ ብርና ናስ የተሰራ ነበር፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ስንገባ ግን ቁሶቹ ሙሉ በሙሉ የተለዩ ናቸው፡፡ የመገናኛው ድንኳን ቁልፍ መለያ ‹‹ከወርቅ የተሰራ ቤት›› መሆኑ ነው፡፡ ባለ ሦስት ማዕዘኖቹ ግድግዳዎች ከ48 የግራር ሳንቃዎች የተሰሩና ሁሉም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡ የሕብስቱ ገበታና የዕጣኑ መሰውያም እንደዚሁ ከግራር እንጨት የተሰሩና በወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡ መቅረዙም ከአንድ መክሊት ወርቅ ተጠፍጥፎ የተሰራ ነበር፡፡ ስለዚህ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹህ ወርቅ የተሰሩ ወይም በንጹህ ወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡
 
በሌላ በኩል ከሳንቃዎቹ በታች ያሉት መሰኪያዎች የተሰሩት ከምን ነበር? ከብር የተሰሩ ነበሩ፡፡ ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አጥር ምሰሶዎች ሆነው የቆሙት መሰኪያዎች የተሰሩት ግን ከናስ ነበር፡፡ የአደባባዩ አጥር የተሰሩባቸው ምሰሶዎች ከእንጨት የተሰሩ ሲሆኑ የመገናኛው ድንኳን ሳንቃዎች ግን በወርቅ ከተለበጠ የግራር እንጨት የተሰሩ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ይሆኑ ዘንድ የቆሙት የአምስቱ ቋሚዎች መሰኪያዎች ከናስ የተሰሩ ነበሩ፡፡
 
ምንም እንኳን የመገናኛው ድንኳን ሳንቃዎች መሰኪያዎች (ኩላቦች) ከናስ የተሰሩ ቢሆኑም ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ቋሚዎች የተሰሩት መሰኪያዎች (ኩላቦች) ከፈሰሰ ናስ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ይህ ምን ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ወደ እግዚአብሄር ፊት የሚቀርብ ማንኛውም ሰው ለሐጢያቶቹ መኮነን አለበት ማለት ነው፡፡ የሞት ፍርድ ተፈርዶብን ሳለን ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምንችለው ታዲያ እንዴት ነው? እኛ ራሳችን ከሞትን በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ አንችልም፡፡
 
ለመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር አምስት ምሰሶዎች ላይ ባሉት መሰኪያዎች (ኩላቦች) ጥቅም ላይ በዋለው ናስ አማካይነት እግዚአብሄር ለሐጢያቶቻችን ብንኮነንም ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ በእኛ ምትክ ለእነዚህ ሐጢያቶች እንደተኮነነ ይነግረናል፡፡ ለሐጢያቶቻችን መኮነን የነበረብን እኛ ነበርን፡፡ ነገር ግን አንድ ሌላ ሰው በእኛ ምትክ ለሐጢያቶቻችን ሁሉ የመጣውን ኩነኔ ተሸከመ፡፡ በእኛ ፋንታ ሌላ አንድ ሰው ሞተልን፡፡ በእኛ ምትክ በይፋ የተኮነነውና የሞተው ሌላ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፡፡ 
 
በሰማያዊው ማግ የተገለጠው እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ አማካይነት ወደ እርሱ የተሻገሩትን ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ተቀብሎ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስላስወገደ ለሐጢያቶቻችን ምንም ኩነኔ እንደማይገጥመን የሚያምን እምነት ነው፡፡ በቀዩ ማግ የተገለጠው እምነት ኢየሱስ ደሙን በመስቀል ላይ ማፍሰሱን የሚያምን እምነት ነው፡፡ ይህ እምነት ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ ልንጋፈጠው የሚገባንን የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ በይፋ እንደተሸከመ ያምናል፡፡
 
ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የሚችሉት በጥምቀቱ በማመን ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ያሻገሩና ከእነዚህ ሁሉ ሐጢያቶች የተነሳም ኢየሱስ በሥጋው ሞት በመስቀል ላይ ደሙን እንዳፈሰሰ በማመን ለሐጢያቶቻቸው ሁሉ የተኮነኑ ብቻ ናቸው፡፡ የመገናኛው ድንኳን ኩላቦች ከናስ የተሰሩት ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱ አማካይነት በራሱ ላይ በወሰደው በክርስቶስ ደም ማመን አለብን፡፡
 
እግዚአብሄር ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት ይችሉ ዘንድ የወሰነላቸው እነርሱን ያዳናቸው ኢየሱስ ራሱ አምላክ (ሐምራዊ ማግ) መሆኑን የሚያምኑ፣ በኢየሱስ ጥምቀት (ሰማያዊ ማግ) የሚያምኑትንና ኢየሱስ በምትካቸው ለሐጢያቶቻቸው በይፋ የተኮነነ (ቀይ ማግ) በመሆኑ እውነት የሚያምኑትን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ወደ ቅድስቱ ስፍራ እንዲገቡ የፈቀደላቸው በኢየሱስ በማመን ለአንዴና ለመጨረሻ ለሐጢያቶቻቸው የተኮነኑትንና ኢየሱስ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንዳዳናቸው የሚያምኑትን ብቻ ነው፡፡
 
በመገናኛው ድንኳን የመግቢያ በር ላይ ባሉት ምሰሶዎች ላይ ያሉት መሰኪያዎች (ኩላቦች) ከናስ የተሰሩ ነበሩ፡፡ የናሶቹ ኩላቦች እግዚአብሄር የአዳም ዝርያዎች ሆነው የተወለዱት ሐጢያተኞች ማንም ይሁኑ የእርሱ ማደርያ ወደሆነው ቅድስቱ ስፍራ ይገቡ ዘንድ የሚፈቀድላቸው የሰማያዊው ማግ፣ (የኢየሱስ ጥምቀት) የቀዩ ማግ (ኢየሱስ በሐጢያተኞች ፋንታ በይፋ መኮነኑ) እና የሐምራዊው ማግ እምነት (ኢየሱስ ራሱ አምላክ መሆኑ) ሲኖራቸው ብቻ የመሆኑ መንፈሳዊ ትርጉም አላቸው፡፡ የመግቢያው በር ምሰሶዎች አምስቱ ኩላቦች በሙሉ የናስ በመሆናቸው በሮሜ 6፡23 ላይ እንደተጻፈው ‹‹የሐጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት›› መሆኑን ስለሚናገረው የእግዚአብሄር ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በውሃው፣ በደሙና በመንፈሱ ይቅር ብሎናል፡፡
 
 
በቃሉና በእግዚአብሄር ማመን አለብን፤ ቸል ማለት የለብንም፡፡ 
 
በኢየሱስ ማመን ማለት እናንተ ያለ ቅድመ ሁኔታ ድናችኋል ማለት አይደለም፡፡ ወደ ቤተክርስቲያናችሁ መሄድ ማለትም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዳግመኛ ተወልዳችኋል ማለት አይደለም፡፡ ጌታችን በዮሐንስ 3 ላይ የእግዚአብሄርን መንግሥት ማየትና ወደዚያ መግባት የሚችሉት ከውሃና ከመንፈስ የተወለዱ ብቻ እንደሆኑ ተናግሮዋል፡፡ ኢየሱስ የአይሁድ መሪና በእግዚአብሄር በታማኝነት ያምን ለነበረው ኒቆዲሞስ ‹‹አንተ የአይሁድ መምህር ነህ፤ ነገር ግን ዳግመኛ መወለድ እንዴት እንደሆነ አታውቅም›› በማለት በአጽንዖት ነገረው፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ዳግመኛ ሊወለዱ የሚችሉት በሰማያዊው ማግ፣ (ኢየሱስ ሲጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ በራሱ ላይ እንደወሰደ) በቀዩ ማግ (ኢየሱስ ለሐጢያታችን መሞቱ) እና በሐምራዊው ማግ (ኢየሱስ አዳኝ ራሱ አምላክና የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑ) ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በእያንዳንዱ የመገናኛው ድንኳን ክልል በሚገኘው ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግ አማካይነት ሐጢያተኞች በሙሉ ኢየሱስ የሐጢያተኞች መድህን መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡
 
ብዙ ሰዎች ዳግመኛ መወለድ ያልቻሉትና ዳግመኛ የመወለድን ቃል ያላወቁት በዚህ እውነት ሳያምኑ በኢየሱስ ብቻ በማመናቸው ነው፡፡ ጌታችን በኢየሱስ ብናምንም እንኳን ዳግመኛ ካልተወለድን የአብ መንግሥት ወደሆነው ቅድስት ስፍራ ፈጽሞ እንደማንገባና ትክክለኛ የሆነ የእምነት ሕይወትም እንደማንኖር በግልጽ ነግሮናል፡፡
 
በሰው ሰራሽ አስተሳሰቦቻችን ክርስቲያኖች ሁሉ እምነታቸው ምንም ይሁን ዳግመኛ ይወለዱ ዘንድ ቢፈቀድላቸው እንዴት ግሩም ይሆን ነበር ብለን እናስባለን፡፡ እንደዚያ አይደለምን? የሰውን ዘር ለማዳን ያደረጋቸውን ዝርዝር ነገሮች ሳናውቅ የኢየሱስን ስም በመጥራትና በእርሱ እምነት እንዳለን በመናገር ብቻ መዳን ብንችል ኖሮ ሰዎች በኢየሱስ ማመን በሚያስገርም ሁኔታ ቀላል እንደሆነ ይረዱ ነበር፡፡ አዲስ ክርስቲያን ባገኘን ቁጥር ‹‹♫እኔ ይቅር ተብያለሁ፤ ♫ሁላችንም ይቅር ተብለናል›› እያልን በመዘመር እግዚአብሄርን እናመሰግነው ነበር፡፡ ‹‹ብዙ አማኞች ስላሉ የመመስከሩ ፋይዳ ምንድነው? ነገሮች ባሉበት ሁኔታ ግሩም ናቸው፡፡ ይህ ድንቅ አይደለምን?›› ነገሩ በእርግጥም እንደዚህ ቢሆን ኖሮ ሰዎች ደህንነትን አቅልለው ያስቡት ነበር፡፡ ምክንያቱም የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና፡፡ በሚፈልጉት በማንኛውም መንገድ ቢኖሩም መዳናቸው አይቀርም፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ባለ ዕውር እምነት በፍጹም ዳግመኛ መወለድ እንደማንችል እግዚአብሄር ነግሮናል፡፡ በተቃራኒው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳያውቁ እንደዳኑ የሚናገሩ በሙሉ ዓመጽን እያደረጉ እንደሆነ ይነግረናል፡፡
 
 
ዳግመኛ የሚወለደው ሥጋችሁ ሳይሆን መንፈሳችሁ ነው፡፡ 
 
ኢየሱስ ሰው ሆኖ ወደዚህ ምድር በመምጣት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት አዳነን፡፡ የኢየሱስ የሥጋ አባት የነበረው ዮሴፍ አናጢ ነበር፡፡ (ማቴዎስ 13፡55) ኢየሱስም ለመጀመሪያዎቹ 29 ዓመታት ከአባቱ በታች አናጢ ሆኖ እየሰራ ቤተሰቡን ያግዝ ነበር፡፡ ነገር ግን 30 ዓመት ሲሆነው መለኮታዊ ሥራዎቹን ማለትም ይፋ የሆኑ አገልግሎቶቹን መጀመር ነበረበት፡፡
 
ኢየሱስ መለኮታዊና ሰብአዊ ተፈጥሮ ያለው እንደሆነ ሁሉ እኛም ዳግመኛ የተወለድን ጻድቃንም እንደዚሁ ሁለት የተለያዩ ተፈጥሮዎች አሉን፡፡ እኛ ሥጋና መንፈስ ነን፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው መንፈሱ ዳግመኛ ሳይወለድ በኢየሱስ እንደሚያምን የሚናገር ከሆነ ይህ ሰው ዳግመኛ አልተወለደም፡፡ ያም ማለት ዳግመኛ የተወለደ መንፈስ የለውም ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው መንፈሱ ዳግመኛ ሳይወለድ በኢየሱስ ሊያምን ቢሞክር ይህ ሰው ልክ እንደ ኒቆዲሞስ በሥጋ ዳግመኛ ለመወለድ የሚሞክር ዓይነት ሰው ነው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በባህርይው ራሱ አምላክ ቢሆንም ድካሞች የተሞላውንም የሰው ሥጋም ለብሶ ነበር፡፡ ስለዚህ ዳግመኛ ተወልደናል ስንል ዳግመኛ የተወለደው ሥጋችን ሳይሆን መንፈሳችን ነው ማለታችን ነው፡፡
 
በኢየሱስ እናምናለን የሚሉ ሁሉ በሆነ ደረጃ በእርግጥም ዳግመኛ ተወልደው ከሆነ እኔ ለጋሽ መጋቢ ተብዬ ለመታወቅ እሞክር ነበር፡፡ ለምን? በእውነት በማያምኑ ሰዎች በጣም ስለማልበሳጭ እውነትን ወደ ማወቅ ይመጣሉ በሚል ተስፋ ስብከቶቼን ጠንካራ አላደርጋቸውም ነበር፡፡ እኔ ሰዎች እንዴት በሥጋቸው ቅዱስ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያብራራ ጨዋ፣ የተከበረ፣ ለጋስ፣ ደግና አፍ የማያስከድን መጋቢ እሆን ነበር፡፡ ምስሌን በዚህ መንገድ ማሳመር እችላለሁ፡፡ ነገር ግን እንደዚያ አላደርግም፡፡ በአእምሮዋችሁ ውስጥ ‹‹ይህ መጋቢ የተቀደሰውንና የመሃሪውን ኢየሱስ ምስል ያንጸባርቃል›› የሚል አንደምታ የመትከል ችሎታ ስለሌለኝ አይደለም፡፡ ይህንን የማላደርገው የሰው ሥጋ መለወጥ ስለማይችልና በሥጋ ጥቂት ደግ፣ ለጋስና መሃሪ መሆን ማለት ይህ ሰው ዳግመኛ የተወለደ ጻድቅ ነው ማለት አይደለም፡፡ ማንም ሰው በሥጋ ዳግመኛ ሊወለድ አይችልም፡፡ በእግዚአብሄር ቃል በማመን መወለድ ያለበት መንፈስ ነው፡፡
 
በኢየሱስ ስታምኑ እውነትን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ‹‹እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› (ዮሐንስ 8፡32) ዳግመኛ እንድንወለድ የሚያደርገን፣ ነፍሳችንን ከሐጢያት ባርነት ነጻ የሚያወጣውና ጻድቃን ሆነን ዳግመኛ እንድንወለድ የሚያደርገን የእግዚአብሄር እውነት ብቻ ነው፡፡ ወደ ቅድስቱ ክፍል ገብተን እውነተኛ የእምነት ኑሮዋችንን የምንኖረውና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የስርየት መክደኛ መድረስ የምንችለው መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ስናውቅ፣ ስናምንና ስንሰብክ ብቻ ነው፡፡ ነፍሳችንን ዳግመኛ እንድትወለድ የሚያደርጋት የውሃውና መንፈሱ ወንጌል እውነት ነው፡፡ በዚህ ላይ ያለን እምነታችንም ለሐጢያቶቻችን ሁሉ ይቅርታን በመስጠት ከእግዚአብሄር ጋር በእምነት ክልል ውስጥ እንድንኖር ይፈቅድልናል፡፡ በልባችን ውስጥ ያለው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመንፈሳዊውና በሚያንጸባርቀው ክልል ውስጥ ዳግመኛ የተወለድን የእግዚአብሄር ልጆች ሆነን ከጌታ ጋር በደስታ እንድንኖር ያስችለናል፡፡
 
በዕውር ድንብር በኢየሱስ ማመን ትክክለኛ እምነት አይደለም፡፡ ከሰው ዕይታ አንጻር ሲታይ እኔ ብዙ ጉድለቶች አሉብኝ፡፡ ይህንን የምናገረው ከአንደበቴ አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር ሳደርግ ብዙ ጉድለቶች እንዳሉብኝ በትክክል ወደ መረዳት ደርሻለሁ፡፡ ለምሳሌ ተሳታፊ ቅዱሳኖችና አዳዲስ መጤዎች ቃሉን ተመችቶዋቸው እንዲሰሙ፣ በእግዚአብሄር ጸጋ ልባቸው እንዲነቃ፣ ዳግመኛ የመወለድን በረከት እንዲቀበሉና በአካልና በመንፈስ እርፍ ካሉ በኋላ በሰላም ወደየመጡበት እንዲመለሱ ለመጽሐፍ ቅዱስ ካምፕ በምዘጋጅበት ጊዜ ላስባቸው የተሳኑኝና አስቀድሜ ያልተዘጋጀሁባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ እገነዘባለሁ፡፡ ትንሽ ትኩረት በመስጠት ብቻ በቀላሉ ሊከወኑ የሚችሉ ነገሮች ብቅ የሚሉት የዝግጅቱ ጊዜ ሲያበቃና ካምፑ ሊጀመር ሲል ነው፡፡ ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሜ ያልተዘጋጀሁባቸው ለምንድነው በማለት ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ካምፕ ሳቅድ ትንሽ ትኩረት ባደርግና ጠንቃቃ ብሆን ቅዱሳንና አዳዲስ ነፍሳቶች ቃሉን በሚገባ ሰምተው መዳንና ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ይችሉ ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ በምሰራበት ጊዜ ጊዜ እንኳን የብቃት ችግር ስላለብኝ ውጤቶቹ ከጥረቶቼ ጋር የማይስማሙባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ እኔ ራሴ እጅግ ብዙ ጉድለቶች እንዳሉብኝ በሚገባ አውቃለሁ፡፡
 
‹‹ይህንን ማድረግ የማልችለው ለምንድነው? ስለዚህ ነገር ለምን አላሰብሁም? ማድረግ የሚኖርብኝ ነገር ቢኖር ትንሽ ትኩረት መስጠት ነበር፡፡ ሆኖም ይህንን ማድረግ ያልቻልሁት ለምንድነው?›› ወንጌልን በትክክል በማገለግልበት ጊዜ ብዙውን ጊዜ ጉድለቶቼን እገነዘባለሁ፡፡ ስለዚህ ራሴን በማወቅ ‹‹እኔ ማለት ይህ ነኝ፡፡ እኔ ይህን ያህል ብቁ አይደለሁም›› በማለት ጉድለቴን አምናለሁ፡፡ ይህንን የምናገረው ከአንደበቴ አይደለም፡፡ ትሁት ለመሆንም እያስመሰልሁ አይደለም፡፡ በእርግጥ እኔ ጥቃቅን ችግሮችን እንኳን በተገቢው መንገድ መፍታት የማልችል ነገር ግን በደፈናው የማልፍ ዓይነት ሰው ነኝ፡፡ ራሴን ስመለከት ብዙ ጉድለቶቼን አያለሁ፡፡
 
 

በሰማያዊው ማግ አማካይነት ቅድስናን እንቀበላለን፡፡ 

 
ሰዎች ስለ ራሳቸው ሲያስቡ ያለ አንዳች ስህተት ሁሉን በሚገባ መከወን እንደሚችሉ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን አንድ ችግር ሲገጥማቸው እውነተኛ ብቃታቸውና ጉድለቶቻቸው ቁልጭ ብለው ይገለጣሉ፡፡ በእርግጥም ብቃት እንደሌላቸውና ሐጢያትና ስህተት ከመስራት በቀር ሌላ ማድረግ እንደማይችሉ ይረዳሉ፡፡ ሰዎች ጥሩ ነገር እያደረጉ መሆኑ ሲሰማቸው እምነታቸው ጥሩ ስለሆነ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንደሚገቡ በማሰብ ራሳቸውን ያታልላሉ፡፡
 
ሥጋ ግን በፍጹም አይለወጥም፡፡ ጉድለቶች የሌሉበት ሥጋ የለም፡፡ ሥጋ ሁልጊዜም ይሳሳታል፡፡ ጉድለቶቹንም ይገልጣል፡፡ ሥጋችሁ ከፈጸመው አንዳች መልካም ነገር የተነሳ ወደ ጌታችን መንግሥት ልትገቡ እንደምትችሉ በአጋጣሚ እንኳን አስባችሁ ከሆነ ሥጋችሁ ጥሩ አድርጎ የከወነው ነገር ምንም ይሁን በእግዚአብሄር ፊት ከንቱ መሆኑን መረዳት አለባችሁ፡፡ ወደ ጌታ መንግሥት እንድንገባ የሚያስችለን ብቸኛው ነገር ጌታ እኛን ባዳነበት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የእውነት ቃል ላይ ያለን እምነት ነው፡፡ ጌታችን በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት ስላዳነን ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የምንችለው በዚህ በማመን ብቻ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት ባያድነን ኖሮ ሁላችንም በፍጹም ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት አንችልም ነበር፡፡ እምነታችን ምንም ያህል ብርቱ ቢሆን እዚያ መግባት አንችልም፡፡ ለምን? ምክንያቱም ነገሩ እንዲህ ቢሆን ኖሮ በሥጋ ላይ ያለን እምነታችን ወደዚያ መግባት ይችል ዘንድ ሁልጊዜም ጥሩ መሆን አለበት ማለት ይሆናልና፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት የምንችለው እምነታችን በየቀኑ መልካም ሲሆን ብቻ ከሆነ ደካማ ሥጋ የለበስን እኛ እምነታችንን በየቀኑ እንዴት መልካም ልናደርገውና ወደዚያ ልንገባ እንችላለን? በራሳችን የሐጢያት ስርየትን የምንቀበልበት ምንም መንገድ በሌለበትና ሐጢያት በምንሰራበት ጊዜ ሁሉም በየቀኑ የምንመለስበት እምነት በሌለን ሁኔታ ውስጥ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ለመግባት እምነታችንን በየቀኑ መልካም ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ገና ከመነሻው ሰውነታችን በጭራሽ ሐጢያት የማይሰራ ሰውነት መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን እንጸልያለን፤ እንጾማለንም፡፡ ነገር ግን ሰውነቱ ቅዱስ የሆነ ሰው ማነው? ይህንን ማድረግ የሚችል ማነው?
 
እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት ባያድነን ኖሮ ከመካከላችን መንግሥተ ሰማይ መግባት የሚችል አንድም ባልኖረ ነበር፡፡ እምነታችን በአንድ ወቅት ጥሩ የሚሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ የሚከስም ዓይነት ሰዎች ነን፡፡ እምነታችን ጥሩ ሆኖ ዳግመኛ ሲከስም እምነት አለን ወይስ የለንም በማለት እንወዛገባለን፡፡ በመጨረሻም መጀመሪያ የነበረንንም እምነት እንኳን እናጣዋለን፡፡ በመጨረሻም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢየሱስ ካመንን ከረጅም ጊዜ በኋላ ይበልጥ ሐጢያተኞች እንሆናለን፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እኛ ብቃት የሌለን ሐጢያተኞች በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው የደህንነት ዕቅዱ መሰረት ፍጹም አዳነን፡፡ የሐጢያቶቻችንንም ስርየት ሰጠን፡፡
 
ልክ እንደ ሊቀ ካህኑ በመጠምጠሚያችን ላይ ‹‹ቅድስና ለእግዚአብሄር›› የሚለውን ወርቃማ ምልክት መለጠፍ የምንችለው ይህ መረጃ ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ (ዘጸዓት 28፡36-38) ያን ጊዜ ክህነታችንን መፈጸም እንችላለን፡፡ እነዚያ የእርሱ ካህናቶች ሆነው እርሱን እያገለገሉ ‹‹ለእግዚአብሄር ያላቸውን ቅድስና›› ለሰዎች መመስከር የሚችሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ለመቀበላቸው በልባቸው ውስጥ ማስረጃው ያላቸው ናቸው፡፡
 
በሊቀ ካህኑ መጠምጠሚያ ላይ ወርቃማ ምልክት ተለጥፎዋል፡፡ ይህንን ወርቃማ ምልክት ከመጠምሚያው ጋር ያሰረው ሰማያዊ ፈትል ነበር፡፡ እግዚአብሄር መጠምጠሚያው በዚህ ሰማያዊ ፈትል ሊታሰር እንደሚገባው የተናገረው ለምንድነው? ጌታችን እኛን ለማዳን ወሳኝ ነገር አድርጎ የተመለከተው ነገር ቢኖር ይህ ሰማያዊ ማግ ነበር፡፡ ይህ ሰማያዊ ማግ የሚያመለክተው ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ለመውሰድ የተቀበለውን ጥምቀት ነው፡፡ ጌታ በብሉይ ኪዳን በሆነው የእጆች መጫን ስርዓት መሰረት በአዲስ ኪዳን በጥምቀቱ አማካይነት በራሱ ላይ በመውሰድ ሐጢያቶቻችንን ባይደመስስ ኖሮ ምንም ያህል በኢየሱስ በደምብ የምናምን ብንሆንም ከእግዚአብሄር ዘንድ ቅድስናን መቀበል አንችልም ነበር፡፡ ወርቃማው ምልክት ከመጠምጠሚያው ጋር በሰማያዊ ፈትል የታሰረው ለዚህ ነበር፡፡ ‹‹ቅድስና ለእግዚአብሄር›› የሚለውን ጽሁፍ በሊቀ ካህኑ ወርቃማ ምልክት ላይ የሚያዩ ሰዎች ሁሉ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት በመቀበል በእግዚአብሄር ፊት ቅዱስ መሆን እንደሚኖርባቸው ራሳቸውን ያስታውሳሉ፡፡ ይህም ሰዎች እንዴት በእግዚአብሄር ፊት ቅዱስ መሆን እንደሚችሉ ያስቡ ዘንድ ያደደርጋቸዋል፡፡
 
እኛም ደግሞ እንዴት ጻድቃን እንደሆንን ማስታወስ ይገባናል፡፡ እኛ ጻድቃን የሆንነው እንዴት ነው? ማቴዎስ 3፡15ን እናንብብ፡- ‹‹ኢየሱስም መልሶ [ለዮሐንስ] አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡ ያን ጊዜ ፈቀደለት፡፡›› ኢየሱስ ጥምቀትን በመጠመቅ ሁላችንንም ከሐጢያቶቻችን አድኖናል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በራሱ ላይ ስለወሰደ በዚህ የሚያምኑ ሐጢያት አልባ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ባይጠመቅ ኖሮ እንዴት ሐጢያት አልባ ነን ብለን ለመናገር እንደፍር ነበር? የሐጢያት ስርየትን የተቀበላችሁት ዓይኖቻችሁ ከልብ የሆኑ ዕንባዎችን ቋጥረው በመስቀል ላይ በሆነው የኢየሱስ ሞት በማመናችሁ ብቻ ነውን? ምንም ዓይነት ዝምድና ሳይኖራቸው በኢየሱስ ሞት ማዘን የሚከብዳቸው ብዙ ሰዎች የአያቶቻቸውን ሞት በማስታወስ ታመው በነበሩ ጊዜ የደረሱባቸውን ችግሮች በማሰብ ወይም ያሳለፉዋቸውን ችግሮችና መከራዎች በማስታወስ ከዓይኖቻቸው ዕንባዎችን ለማፍለቅ ይሞክራሉ፡፡ በዚህ መንገድ አስመስላችሁ ብታለቅሱ ወይም በኢየሱስ ስቅለት ከልባችሁ አዝናችሁ ብታለቅሱ ሐጢያቶቻችሁ በዚህ መንገድ በፍጹም ሊደመሰሱ አይችሉም፡፡
 
‹‹ቅድስና ለእግዚአብሄር›› የሚል ጽሁፍ የተጻፈበት ወርቃማ ምልክት ከሊቀ ካህኑ መጠምጠሚያ ጋር በሰማያዊ ፈትል እንደታሰረ ሁሉ ሐጢያቶቻችንን የሚደመስሰውና ቅዱሳን የሚያደርገንም የኢየሱስ ጥምቀት ነው፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ስለወሰደ የሆዋም ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በእርሱ ላይ ስላሸከመውና የዓለም ሐጢያቶች በሙሉም በጥምቀቱ አማካይነት ወደ ኢየሱስ ስለተሻገሩ ልባችን የሐጢያትን ስርየት ተቀብሎዋል፡፡ ልባችን ምንም ያህል ስሜት አልባ ሊሆን ቢችልም እኛም በድርጊቶቻችን ምንም ያህል ብቃት የሌለን ብንሆንም ጻድቃን ሆነናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጻፈው የሰማያዊ ማግ ቃልም ፈጽመን ድነናል፡፡ ሥጋችንን ስንመለከት ልንኮራ አንችልም፡፡ ነገር ግን በልባችን ውስጥ ባለው በዚህ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ እምነት የተነሳ ማለትም ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ በመስቀል ላይ ኩነኔያችን እንደተሸከመ በሚነግረን በዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል የተነሳ ስለ ወንጌል በድፍረትና ያለ ፍርሃት መናገር እንችላለን፡፡ በእምነታችን ጻድቃን ሆነን የምንኖረውና ይህንን ጻድቅ እምነት ለሰዎች የምንሰብከው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስላለን ነው፡፡
 
ስለ ጌታችን ጸጋ የሚበቃንን ያህል አላመሰገንንም፡፡ ደህንነታችን የመጣው እንዲያው በዘፈቀደ ስላልሆነ ለዚህ የበለጠ አመስጋኞች መሆን ይኖርብናል፡፡ እኛ የተቀበልነውን ደህንነት በትክክል ባያምንም እንኳን ማንም የሚቀበለው ዓይነት ርካሽ ደህንነት አይደለም፡፡ በራስ ስሜት ተነሳስቶ ‹‹ጌታ ጌታ›› ብሎ እግዚአብሄርን መጥራት ይህን የሚያደርግ ሰው ሁሉ የሚድን መሆኑን የሚያሳይ ነገር አይደለም፡፡ እኛ በልባችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያቶቻችን ለመወገዳቸውና ጌታም በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በድንቅ እንዳዳነን በልባችን ውስጥ መረጃው ስላለን ለዚህ ታላቅ መዳን አመስጋኞች ነን፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ በልቡ ውስጥ ይህ ምስክር እንዳለው ይነግረናል፡፡ (1ኛ ዮሐንስ 5፡10) በልባችን ውስጥ ምንም ምስክር ከሌለ እግዚአብሄርን ውሸታም እናደርገዋለን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ይህ አሳማኝ መረጃ ሊኖረን ይገባል፡፡ ከዚህ የተነሳ ‹‹ለመዳናችሁ ማስረጃ ስጡኝ፤ ሰዎች የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ሲያገኙ መንፈስ ቅዱስን እንደ ስጦታ ይቀበላሉ፡፡ ግልጽ የሆነ የመዳን ማረጋገጫም አለ ትላላችሁ፡፡ ይህንን ማስረጃ አሳዩኝ›› በማለት ከሚገዳደሩዋቸውና ከሚጠይቁዋቸው የምትሸሹበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ መረጃችሁን እንደሚከተለው በድፍረት ማሳየት ትችላላችሁ፡፡ ‹‹በውስጤ ኢየሱስ እኔን ሙሉ በሙሉ ያዳነበት የመንፈስና የውሃ ወንጌል አለኝ፡፡ እኔ በእርሱ ፈጽሜ ስለዳንሁ ሐጢያት የለብኝም፡፡››
 
በልባችሁ ውስጥ የመዳናችሁ ማስረጃ ከሌለ አልዳናችሁም፡፡ ሰዎች ምንም ያህል በትጋት በኢየሱስ ቢያምኑም ይህ በራሱ ደህንነታቸውን አይገልጥም፡፡ ይህ ምላሽ የማይሰጥ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሰው ለሚሰማው ስሜት ግድ የለሽ የሆነ ፍቅር ነው፡፡ እኛ የማንወደው ሰው የሚፈራ ልብ ያለው ከሆነ፣ ከእኛ አንድ ነገር የሚጠብቅ ከሆነ፣ ለመወደድ ሲል ሊሞት የተዘጋጀ በሚመስል ስሜት ፍቅርን ተጠምቶ ወደ እኛ የሚመለከት ከሆነ ይህ ማለት እኛም በምላሹ ይህንን ሰው መውደድ ይኖርብናል ማለት አይደለም፡፡ ልክ እንደዚሁ እግዚአብሄርም ልባቸው ስለ እርሱ ስለቃተተ ብቻ የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያላገኙትን በክንዶቹ አያቅፋቸውም፡፡ ሐጢያተኞች ለእግዚአብሄር ያላቸው በቀል አልባ ፍቅር የሚታወቀው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡
 
እግዚአብሄርን ስንወደው ቃሉን በእውነት በማመን ልንወደው ይገባናል፡፡ እኛ ለእርሱ ያለን ፍቅር የአንድ ወገን ፍቅር መሆን የለበትም፡፡ እኛ ለእርሱ ስላለን ፍቅር ልንነግረው ይገባናል፡፡ እርሱን ከመውደዳችን በፊትም እርሱ በእርግጥ ይወደን ወይም አይወደን እንደሆነ አስቀድመን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከልቡ ለማይወደን ሰው ፍቅራችንን ሁሉ ብንሰጠው ውሎ አድሮ የሚገጥመን ነገር የልብ ስብራት ነው፡፡
 
ጌታችን ስለ ሐጢያቶቻችን እንዳንኮነን ከሐጢያቶችን አድኖን በክብር ሸፍኖናል፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት እንድንገባና ከእግዚአብሄር ጋር እንድንኖር ፈቅዶልናል፡፡ በእግዚአብሄር ጸጋ አማካይነት የሐጢያት ስርየትን ማግኘት የሚያስችለንን ስጦታ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሄር ደህንነት ስፍር ቁጥር የሌላቸው መንፈሳዊ የሆኑ የሰማይ በረከቶችን አምጥቶልናል፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህን በረከቶች ሁሉ ከእርሱ እንድንቀበል ያስቻለን እግዚአብሄር የሰጠን ይህ ደህንነት ብቻ ነው፡፡
 
 
ኢየሱስ ራሱ ወደ እኛ ያመጣው ደህንነት፡፡ 
 
ጌታችን በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አድኖናል፡፡ ከሦስት የተለያዩ ማጎች የተሰራውን ደህንነት ሰጥቶናል፡፡ ይህ የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ማግ ደህንነት በእግዚአብሄር የተሰጠው ደህንነት ነው፡፡ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ገብተን በሕይወት እንድንኖር የሚያስችለን የደህንነት ስጦታ ይህ ነው፡፡ 
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እናንተንና እኔ ጻድቃን አድርጎናል፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እንድንገባና ንጹህ ሕይወትን እንድንኖር ፈቅዶልናል፡፡ ይህ እውነተኛው ወንጌል የእግዚአብሄርን መንፈሳዊ ቃል እንድንመገብና የእርሱን ጸጋ እንድንቀበል አስችሎናል፡፡ ወደ እግዚአብሄር የጸጋ ዙፋን ፊት ቀርበን እንድንጸልይም ፈቅዶልናል፡፡ እግዚአብሄር የለገሰንን የተትረፈረፈ ጸጋ መውሰድ የምንችልበትንም እምነት ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሄር በደህንነታችን ብቻ እነዚህን ታላላቅ በረከቶች የእኛ አድርጎዋቸዋል፡፡ ደህንነት ክቡር የሆነው ለዚህ ነው፡፡
 
ኢየሱስ የእምነት ቤቶቻችንን በዓለቱ ላይ እንድንገነባ ነግሮናል፡፡ (ማቴዎስ 7፡24) ይህ ዓለት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የተሰጠን ደህንነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ድነን ጻድቃን በመሆን የእምነት ሕይወታችንን መኖር አለብን፡፡ በመዳን የዘላለምን ሕይወት መደሰት በመዳን ሰማይ መግባት ይኖርብናል፡፡
 
የዚህ ዓለም የመጨረሻ ዘመን በእኛ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች በትክክለኛው ቃል ለመዳን ምክንያት አላቸው፡፡ ሰው የሰማያዊውን፣ የሐምራዊውንና የቀዩን ማግ እምነት ሳያውቅ እንዲያው በኢየሱስ በማመን ብቻ መዳን ይችላል፡፡ በዚህ መንገድ መዳን በቂ ስለሆነ ስለ እምነት ሕይወት መናገር አያስፈልግም የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡
 
እኔ ይህንን ደጋግሜ የተናገርሁት እግዚአብሄር ድጋፍ የሰጠውን የእምነት ሕይወታቸውን መኖር የሚችሉት በልባቸው የሐጢያት ስርየትን የተቀበሉ ብቻ ስለሆኑ ነው፡፡ የሐጢያትን ስርየት ያገኘው እያንዳንዱ ቅዱስ ሰው ልብ መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት የተቀደሰ መቅደስ ስለሆነ ዳግመኛ የተወለዱ ቅዱሳን ይህንን ቅድስናቸውን እንዳያረክሱት የእምነት ሕይወታቸውን መኖር አለባቸው፡፡
 
ጻድቃን ሕይወታቸውን የሚኖሩበት መንገድ ሐጢያተኞች ሕይወታቸውን ከሚኖሩበት መንገድ ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ ከእግዚአብሄር ዕይታ አንጻር የሐጢያተኞች አኗኗር ፈጽሞ ከእርሱ ደረጃ በታች ነው፡፡ ሕይወታቸው የተሞላው በግብዝነት ብቻ ነው፡፡ በሕጉ መሰረት ለመኖር አጥብቀው ይሞክራሉ፡፡ እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው፣ ሕይወታቸውን እንዴት መኖር እንዳለባቸው፣ እንዴት መናገር እንዳለባቸውና እንዴት መሳቅ እንደሚኖርባቸው የራሳቸውን መስፈርቶች አስቀምጠዋል፡፡
 
ይህ ግን ጻድቃን ከሚኖሩት የእምነት ሕይወት በጣም የራቀ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለጻድቃን ‹‹እግዚአብሄር አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ሐይልህ ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ›› በማለት በዝርዝር ነግሮዋቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ለጻድቃን የሰጣቸው የሕይወት ዘይቤ ይህ ነው፡፡ ለእኛ ለጻድቃኖች እግዚአብሄርን ከሙሉ ልባችን በመውደድና ፈቃዱንም በሙሉ ሐይላችንና ፈቃዳችን በመከተል ሕይወታችንን መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ባልንጀሮቻችንን ለማዳን በእርሱ ሥራዎች ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሐብቶች ማኖር አለብን፡፡ የክርስቲያኖች ሕይወት ይህ ነው፡፡
ዋናው ቁም ነገር እኛ ራሳችን ሐጢያት አለመስራታችን ነው በሚል እሳቤ ላይ ከሆነ ያለነው ዳግመኛ የተወለዱ ክርስቲያኖች የሚኖሩትን የታመነ ሕይወት መኖር አንችልም፡፡ እኔ ዳግመኛ ከመወለዴ በፊት በአንድ ወግ አጥባቂ የፕሪስባይቴርያን የእምነት ድርጅት ውስጥ በሕግ ላይ የተመሰረተ የእምነት ሕይወትን ስኖር ነበር፡፡ የሕይወትን ሕግ በሚመለከት በሚገባ ልጠብቀው ሞክሬያለሁ፡፡ በዚህ ዘመን ሰዎች ይህን አያደርጉም፡፡ እኔ ግን የሐይማኖት ሕይወቴን ለረጅም ጊዜ ስኖረው ስለነበር ሕጉን በቀን ተቀን ሕይወቴ ለመጠበቅ በጣም ትጉህ ነበርሁ፡፡ እኔ ሕጉን በሚገባ እታዘዝ ስለነበር በጌታ ቀን ሥራ ሰርቼ አላውቅም፡፡ ሰንበት ሊታወስና ቅዱስ ሆኖ ሊጠበቅ እንደሚገባ ስለሚያዝ በየእሁዱ መኪና ውስጥ እንኳን አልገባም ነበር፡፡ እናንተን እኔ እንደኖርሁት እንድትኖሩ ብጠይቃችሁ እንደዚህ ዓይነት ሕግ አጥባቂ ሕይወት መኖር አትችሉም ነበር፡፡ እኔ ዳግመኛ ከመወለዴ በፊት እኖር ነበረው ሕግ አጥባቂ ሕይወቴ ይህ ነበር፡፡ ነገር ግን የሐይማኖት ሕይወቴን ምንም ያህል በቅድስና ብኖረውም የዚህ ዓይነት ሕይወት ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የሌለውና ፈጽሞ የማይጠቅም ነበር፡፡
 
አንባቢዎች የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ማግ እምነት አላችሁን? የኢየሱስ ማዳን በእነዚህ ሦስት ማጎች ውስጥ ያለ በመሆኑ ወደ ቅድስቱ ስፍራ የምንገባው በእምነታችን ነው፡፡ የእኛ ደህንነት ከ2,000 ዓመታት በፊት ተፈጽሞዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አስቀድሞ ወስዶ ሲያበቃ በመስቀል ላይ ሞቶ የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ ተሸክሞዋል፡፡
 
 
ከሐጢያት መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ተዘጋጅቷል፡፡ 
 
ዳግመኛ ያልተወለዱ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በአደባባዩ መግቢያ በር በኩል አይገቡም፡፡ ነገር ግን በአጥር ይዘላሉ፡፡ ‹‹በአጥሩ ላይ ያለው ጥሩ በፍታ ለምን እንደዚህ ነጭ ሆነ? አድካሚ ነው፡፡ አንዳንድ ቀይና ሰማያዊ ቀለማቶችን መጨመር ነበረባቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ፋሽኑ ይህ ነው፡፡ ይህ አጥር ግን በጣም ነጭ ነው! እጅግ በጣም ያብረቀርቃል፡፡ ለምንስ ከፍ አለ? ከ2.25 ሜትር በላይ ነው፡፡ የእኔ ቁመት 2 ሜትር ላይ እንኳን አይደርስም፡፡ አጥሩ እንደዚህ ከፍ ያለ ሆኖ ሳለ እንዴት ወደ ውስጥ ልገባ እችላለሁ? መሰላል በመጠቀም መውጣት እችላለሁ›› ይላሉ፡፡
 
የዚህ ዓይነት ሰዎች በራሳቸው ተግባራት ለመግባት ይሞክራሉ፡፡ በስጦታዎቻቸው፣ በልግስና ሥራዎቻቸውና በትዕግስታቸው የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ አጥር መወጣጫ አድርገው ‹‹የሆነው ቢሆን ይህንን 2.25 ሜትር በእርግጠኝነት ልዘልለው እችላለሁ›› በማለት በአጥሩ ላይ ይዘላሉ፡፡ ዘለው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ከገቡ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሰውያ ይመለከታሉ፡፡ ከዚያም ዓይኖቻቸውን ከመሰውያው ላይ አንስተው ቅድስቱን ስፍራ ይመለከታሉ፡፡ የሚያዩት የመጀመሪያው ነገር ከፊት ለፊቱ የተቀመጠውን የመታጠቢያ ሰን ነው፡፡
 
የመገናኛው ድንኳን አደባባይ የአጥር ምሰሶዎቹ ከፍታ 2.25 ሜትር ሲሆን እግዚአብሄር የሚያድርበት የቅድስቱ ስፍራ ምሰሶዎችና የመከለያው ከፍታ 4.5 ሜትር ነው፡፡ ሰዎች በቂ ቁርጠኝነት ካላቸው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ መግባት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን 2.25 ሜትር ከፍታ ያለውን አጥር ዘለው ወደ መገናኛው ድንኳን አደባባይ ውስጥ ቢገቡም እግዚአብሄር ወደሚያድርበት ለመግባት ሲሞክሩ ግን 4.5 ሜትር ከፍታ ያላቸው ምሰሶዎችና የቅድስቱ ስፍራ መከለያ ይገጥማቸዋል፡፡ ሰዎች በጥረታቸው ከ2.25 ሜትር በላይ መዝለል ይችላሉ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ያስቀመጠውን 4.5 ሜትር መዝለል አይችሉም፡፡ ገደባቸው ይህ ነው፡፡
 
ይህ ማለት መጀመሪያ በኢየሱስ ስናምን ያመንነው እንደ ሐይማኖት አድርገን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በገዛ ውዴታቸው ኢየሱስን መድህናቸው አድርገው ሊያምኑና መድህኑ ኢየሱስም ከአራቱ ታላላቅ ሰዎች አንዱ እንደሆነ አድርገው ሊያምኑ ይችላሉ፡፡ የሰዎች እምነት ምንም ይሁን የመረጡት የራሳቸው የሆነ የእምነት መንገድ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ባለው እምነት አማካይነት ዳግመኛ ሊወለዱ አይችሉም፡፡
 
በትክክል ዳግመኛ ለመወለድ በእምነታቸው ሰማያዊውን፣ ሐምራዊውንና ቀዩን ማግ ማለፍ አለባቸው፡፡ ኢየሱስ አዳኛችንና የእውነት በር መሆኑንና በውሃውና በደሙም አማካይነት እንዳዳነን ስናምን በእግዚአብሄር ፊት ዳግመኛ እንወለዳለን፡፡ በሦስቱ ማጎች በተገለጡት የኢየሱስ ሥራዎች የሚያምነው እምነት የውሃው፣ የደሙና የመንፈሱ እምነት እንጂ ሌላ እምነት አይደለም፡፡ ሰዎች በሌላ ነገር ለማመን ነጻነት አላቸው፡፡ ነገር ግን እንደዚህ በማመን መዳን እንደሚችሉ ወይም በአያሌው እንደሚባረኩ የሚያረጋግጥ ትክክለኛ ማስረጃ ፈጽሞ የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ድጋፍና ታላቁን ጸጋ እንደዚሁም የአምላክን የደህንነት በረከቶች ማግኘት የምንችለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን ብቻ ነው፡፡ በዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማመኑ ዓላማ እኛን በእግዚአብሄር ጸጋ ለመሸፈን ነው፡፡
የመገናኛውን ድንኳን የምትመለከቱት በውስጡ ቤት ያለው አንድ ባለ አራት ማዕዘን ቅርጸ አደባባይ አድርጋችሁ ብቻ ነውን? ይህ ለእምነታችሁ አንዳች ጠቀሜታ አያመጣም፡፡ የመገናኛው ድንኳን ስለ አንድ ምሉዕ እምነት የሚነግረን ነው፡፡ ይህ እምነት በትክክል ምን እንደሆነም ማወቅ አለብን፡፡
 
የመገናኛውን ድንኳን በሚገባ የማታውቁት ከሆነ የመገናኛው ድንኳን ከፍታ እንደ አጥሩ ከፍታ 2.25 ሜትር ነው ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ነገሩ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ወደ አደባባዩ ስንገባ የመገናኛውን ድንኳን ከአጥሩ ውጪ ሆነን ብንመለከተው የመገናኛው ድንኳን ከአጥሩ በዕጥፍ ከፍ እንደሚል መመልከት እንችላለን፡፡ ይህም የመገናኛው ድንኳን ከአደባባዩ አጥር ከፍ ብሎ እንደቆመ ይነግረናል፡፡
 
በኢየሱስ በትክክል በማመን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት አግኝተው የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር አልፈው የገቡ በሚቃጠለው መስዋዕት መሰውያና በመታጠቢያው ሰን አጠገብ ትክክለኛውን እምነታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የሚችሉት ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ለመግባት ያለ ምንም ማመንታት ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡ በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ ያሉት ዕቃዎች ከቅድስቱ ስፍራ ውጭ ከሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ መለየት አለባቸው፡፡
 
ሰይጣን አብዝቶ የሚጠላው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? በቅድስቱ ስፍራ ውስጥና ውጭ የተሰመረውን የመለያ መስመር ይጸየፈዋል፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራው ውስጠኛውን ከውጪው በሚለዩት መካከል ስለሆነ ሰይጣን የዚህ ዓይነት መስመር መሰመሩን ስለሚጠላ ሰዎች ይህንን መስመር እንዳያሰምሩ ለመካልከል ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ይህ ይታወስ፡፡ እግዚአብሄር በግልጽ የሚሰራው ይህን የእምነት መለያ መስመር በሚያሰምሩት አማካይነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ይህንን ግልጽ የሆነ የመለያ መስመር ባሰመሩት ሰዎች ስለሚደሰት ብሩህ በሆነው እምነታቸው በቅድስቱ ስፍራ ውስጥ መኖር ይችሉ ዘንድ በረከቶቹን ይለግሳቸዋል፡፡
 
ሰዎች የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ያገኙ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ያሉት ዕቃዎችና ለእነርሱ አገልግሎት ጥቅም ላይ የዋሉት ቁሳቁሶች በሙሉ በእግዚአብሄር የተዘጋጁና አስቀድመው የተሰናዱ ናቸው፡፡ በዚህ አምናችሁ ወደ ቅድስቱ ስፍራ ስትገቡ እግዚአብሄር የላቀ ጸጋንና በረከቶችን ይሰጣችኋል፡፡
 
 
የስርየት መክደኛው የደህንነት ጸጋ የሚሰጥበት ስፍራ ነው፡፡ 
 
የኪዳኑ ታቦት
 
በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሁለት ኪሩቤሎች ክንፎቻቸውን ዘርግተው የምስክሩን ታቦት የሸፈነውን መክደኛ ይመለከታሉ፡፡ በሁለቱ ኪሩቤሎች መካከል ያለው ክፍት ቦታ የስርየት መክደኛ ተብሎ ይጠራል፡፡ የስርየት መክደኛው እግዚአብሄር ጸጋውን በእኛ ላይ የሚለግስበት ስፍራ ነው፡፡ ሊቀ ካህኑ ለእስራኤል ሕዝብ የሆነውን የመስዋዕቱን ደም በዚህ የስርየት መክደኛ ላይ ሰባት ጊዜ ስለሚረጭ የምስክሩ ታቦት መሸፈኛ በደም ተበክሎዋል፡፡ እግዚአብሄር በዚህ መንገድ ወደ ስርየት መክደኛው ይወርድና ምህረቱን ለእስራኤል ሕዝብ ይለግሳል፡፡ በዚህ ለሚያምኑ የእግዚአብሄር በረከቶች፣ ጥበቃና ምሪት ይጀምራል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሄር እውነተኛ ሕዝብና ወደ ቅድስቱ ስፍራ የመግባት ፈቃድ ያላቸው ይሆናሉ፡፡
 
በዚህ ዓለም ላይ ከሚገኙት ብዙ ክርስቲያኖች መካከል እምነታቸው ወደ ቅድስቱ ስፍራ እንዲገቡ የፈቀደላቸው አንዳንዶች አሉ፡፡ ሌሎች ግን ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት የሚያስችላቸው የዚህ ዓይነት እምነት የላቸውም፡፡ እናንተ ምን ዓይነት እምነት አላችሁ? ይህን ግልጽ የሆነ የደህንነት መስመር አስምሮ ወደ እግዚአብሄር ቅድስት ስፍራ የሚገባ እምነት ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሄር በአያሌው የሚባርከን ይህንን ማድረግ ስንችል ብቻ ነው፡፡
 
ነገር ግን የዚህ ዓይነት እምነት ማግኘት ያን ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ሰዎች ይህንን ግልጽ የሆነ የደህንነት መስመር ሲያሰምሩ ሰይጣን ስለማይወድ ሁልጊዜም ይህንን መስመር ሊያደበዝዘው ይሞክራል፡፡ ‹‹በዚህ መንገድ ማመን አይኖርባችሁም፡፡ እንደዚህ አይታመንም፡፡ በዚህ ነገር ላይ ብዙ ትኩረት የምታደርጉትና ራሳችሁን የምትደጋግሙት ለምንድነው? ቀለል አድርጋችሁ ተመልከቱት፡፡ ከሕዝቡ ጋር ተስማሙ፡፡›› ሰይጣን እነዚህን ነገሮች በመናገር ይህንን ግልጽ የሆነ የደህንነት መስመር ለማደብዘዝ ይሞክራል፡፡ ሰይጣን የሥጋ ድካሞቻችንንም በመግለጥ ወደ ችግር ሊለውጣቸው ይሞክራል፡፡ ከእግዚአብሄር ሊለዩን የሚሞክሩትን የሰይጣን አሳሳች ቃሎች ትሰማላችሁን? ወይስ በየቀኑ ስለ ደህንነታችሁ ራሳችሁን እያስታወሳችሁ፣ ከቤተክርስቲያን ጋር እየተባበራችሁ፣ የእግዚአብሄርን ቃል እየተከተላችሁ፣ የጸሎት ሕይወትን እየመራችሁና እግዚአብሄር የለገሳችሁን ጸጋ እየተቀበላችሁ ሕይወታችሁን ትኖራላችሁ?
 
የሐጢያቶቻቸውን ስርየት የተቀበሉ በቻሉት መጠን ሁልጊዜም ስለ ደህንነታቸው ማሰላሰል እንደሚወዱ የታወቀ ነው፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ደጋግመው ማሰላሰል ይወዳሉ፡፡ ወንጌልን ማሰላሰል ለእናንተ ጥሩና አስፈላጊም ነው፡፡ ይህንን አትወዱትምን? ‹‹አሁንም ስለ ደህንነታችን የሚነገረው ያው ታሪክ ነውን? የታሪኩ መዋቅርና መቼት የተለየ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አሁንም ያው የጥንቱ ታሪክ ነው፡፡ በጣም ሰልችቶኛል!››
 
እንዲህ የሚል ሰው ይኖራልን? እኔ በየቀኑ ስለ ራሴ ተመሳሳይ ታሪክ ብናገር ከንፈር የሚመጠጥልኝ ሰው እሆናለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን በየቀኑ ስለ ደህንነታችን ማሰላሰል እንደሚገባን የሚናገር ከሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ? ብሉይና አዲስ ኪዳናት ስለ ውሃውና ስለ መንፈሱ ወንጌል የሚነግሩን ከሆነ በእግዚአብሄር ፊት ክፉው ነገር ሰዎች ከዚህ ሌላ አንዳች ነገር መስበካቸው ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በሙሉ ስለ ውሃውና ስለ መንፈሱ ወንጌል ይናገራል፡፡ ‹‹ደህንነት፣ የእምነት ሕይወት፣ መንፈሳዊ አኗኗር፣ ሰይጣንን መዋጋት፣ ሰማይ፣ ክብር፣ ጸጋ፣ በረከት፣ ትንሳኤ፣ የዘላለም ሕይወት፣ ተስፋና መንፈስ ቅዱስ፡፡›› እነዚህ ሁሉ ቁልፍ የቅዱሳን እሳቤዎች ከዚህ እውነተኛ ወንጌል ጋር የተቆራኙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ነገሮች ውጭ ሌላ ነገር መናገር ኑፋቄና የሐሰት ትምህርት ነው፡፡ የሐሰት ትምህርቶች ተመሳሳይ ቢሆኑም በፍሬ ነገራቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ በስተ ውጪ ተመሳሳይ የሚመስሉ በስተ ውስጥ ግን ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል የተለዩ ወንጌሎች ከሐሰት ሐይማኖቶች የፈለቁ አስመሳይ ወንጌሎች ናቸው፡፡
 
የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ከሐሰት ሐይማኖቶች የሚፈልቁትን አሳች ቃሎች ሳይሆን የእግዚአብሄርን ቃል በየቀኑ ለዓለም የምታሰራጭ መሆንዋ ምንኛ ያማረ ነው? እኛ ከእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ጋር መቀላቀላችንና የእግዚአብሄርን ንጹህ ቃል ሰምተን ማመናችን በረከት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ሁልጊዜም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስበክ ቅዱሳን በየቀኑ የእግዚአብሄርን ጸጋ እንዲያስቡ፣ ወደ እርሱ እንዲጸልዩ፣ እርሱን እንዲያከብሩና ክፉ ነገርን የማያደርግ ሕይወት እንዲኖሩ ታስችላቸዋለች፡፡ የሐጢያትን ስርየት እንድትቀበሉ የሚፈቅድላችሁን የእውነት ቃል እንደገና ሰምታችሁ በማመናችሁ ደስተኞች አይደላችሁምን? እኔም ደግሞ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
 
እኔ ከዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል ውጭ ሌላ አንዳች ነገር እንድሰብክ ብገደድ ክፉኛ እጎዳለሁ፡፡ የደህንነትን ቃል ሳይሆን ሌላ ሰው ሰራሽ ትምህርቶችን እንዳሰራጭ ብገደድ እሸሻለሁ፡፡ ይህንን የማደርገው ሌላ ምንም የምናገረው ነገር ስለሌለኝ አይደለም፡፡ ልናገርባቸው የምችልባቸው ሌሎች በርካታ በሰው ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች አሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ አስፈላጊ አይደሉም፡፡ ዳግመኛ ለተወለድነውም በእርሾ የረከሱ ትምህርቶች ናቸው፡፡
 
የከበረው የእግዚአብሄር ቃል ራሱ አምላክ የሆነው ኢየሱስ እኛን ያዳነበት ይህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ብቻ ነው፡፡ ይህንን ወንጌል ደጋግመን ስናኝከው ጣፋጭነቱ አያልቅም፡፡ ብዙ ልነግራችሁ የምችላቸው ብዙ ሌሎች ታሪኮች አሉ፡፡ እጅግ የምወደው ግን እኛን ስላዳነን የውሃና የመንፈስ ወንጌል ስናገር ነው፡፡ ያን ጊዜ በጣም እደሰታለሁ፡፡ ስለዚህ ደህንነት ስናገር እጅግ ደስተኛ ሰው እሆናለሁ፡፡ የቀድሞ ትዝታዎችን በማሰብ ጌታ እንዴት እንዳዳነኝ ለራሴ የማስታውሰውና እርሱን እንደገና የማመሰግነው፣ የደህንነትንም ሕብስት ዳግመኛ መመገብ የምችለው በዚህ ጊዜ ነውና፡፡
 
እናንተም ይህንን የደህንነት ቃል ስትሰሙ እጅግ እንደምትወዱት አምናለሁ፡፡ ምናልባት በየቀኑ ተመሳሳይ ታሪክ ነው ብላችሁ ታንጎራጉሩ ይሆናል፡፡ በውስጣችሁ ግን ‹‹አሁን እንደገና ስሰማው የተሸለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ በመጀመሪያ ያን ያህል የሚስብ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በመስማት ስቀጥል እንዲህ ያለ ሊደመጥ የሚገባው ሌላ ታሪክ እንደሌለ ማየት ችያለሁ፡፡ የዛሬው ታሪክ በመጠኑም ቢሆን የተለየ ነው ብዬ አስቤ ነበር፡፡ ድምዳሜው ግን እንደገና ያው ታሪክ እንደሆነ ነግሮኛል፡፡ ቢሆንም አሁንም ደስተኛ ነኝ›› ብላችሁ ታስባላችሁ፡፡ የልባችሁ ስሜት ይህ እንደሆነ አስባለሁ፡፡
 
ወንድሞችና እህቶች እኔ እዚህ እየሰበክሁ ያለሁት የኢየሱስን ቃል ነው፡፡ ሰባኪዎች የኢየሱስን ቃል መስበክ አለባቸው፡፡ ኢየሱስ በተጻፈው በውሃውና በመንፈሱ ቃል አማካይነት ያደረገውን መስበክ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን እያደረገችው ያለው ነገር ነው፡፡ እኛ አሁን በቤተክርስቲያን ውስጥ የእምነትን ሕይወት እየመራን ነው፡፡ ወደ ቅድስቱ ስፍራ መግባት፣ ከአንድ መክሊት የተጠፈጠፈ ወርቅ ከተሰራውና ሰባት ቅርንጫፎች ካሉት መቅረዝ በሚወጣው ብርሃን ማብራት፣ በንጹህ ወርቅ በተሰራው ቤት ውስጥ ሕብስትን መብላት፣ በዕጣኑ መሰውያ አጠገብ ሆኖ መጸለይ፣ ወደ እግዚአብሄር መቅደስ መግባት፣ ለእርሱ መስገድና በወርቁ ቤት ውስጥ መኖር የእምነት ሕይወታችን ነው፡፡
 
እናንተና እኔ በእግዚአብሄር የተሰጠንን ይህንን የእምነት ሕይወት እየኖርን ነው፡፡ በዚህ የእግዚአብሄር ወርቃማ ቤት ውስጥ መኖር ማለት የሐጢያት ስርየትን መቀበልና ትክክለኛውን የእምነት ሕይወት መኖር ማለት ነው፡፡ ‹‹ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል፡፡›› (1ኛ ቆሮንቶስ 4፡16) ነፍሳችን በመገናኛው ድንኳን ላይ ባሉት በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ላይ ባላት እምነት እንደ ወርቅ በሚያብረቀርቀው የእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ትኖራለች፡፡
 
ከሐጢያቶቻችንና ከኩነኔ ሁሉ ስላዳነን ለዘላለም እግዚአብሄርን አመሰግነዋለሁ፡፡ ሐሌሉያ!