Search

Поширені запитання щодо Християнської Віри

Запитання 1: Народження знову з води та Духа

1-32. በአንተ አባባል መሠረት ኢየሱስ ያለፉትን፣ አሁን ያሉትንና ወደፊት ኃጢአቶችን በሙሉ ቀድሞውኑም አስወግዶዋል ካልን፤ በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል በማመን ኃጢአቶቹ በሙሉ ቀድሞውኑ የታጠቡ እንደሆነ በማሰብ ያለ ማቋረጥ ኃጢአትን የሚሠራ ሰው የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዴት ይሆናል? ይህ ሰው ሌላ ሰው ቢገድል እንኳን በኢየሱስ አማካይነት ለዚህ አይነቱ ኃጢአትም እንኳን ማስተስረያ እንዳገኘ ሊያስብ ይችላል። ስለዚህ ኢየሱስ ወደፊት የሚሠራቸውን እነዚህን ኃጢአቶች ቀድሞውኑም እንዳስወገደለት በማመን ያለ ምንም ማመንታት ኃጢአት በመሥራት ይቀጥላል። እባክህ እነዚህን ነገሮች አብራራልኝ።

በመጀመሪያ ስለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ጥያቄዎችን ስላነሳህ አመሰግንሃለሁ። ያነሳሃቸው ጥያቄዎች ብዙ ክርስቲያኖች ዳግም ከመወለዳቸው በፊት የጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ናቸው። ዳግም የተወለዱ ሰዎች ፍጹም በሆነው ወንጌል መዳን አግኝተው ያለማቋረጥ ኃጢአት ይሠራሉ ብለህ እንደምትጨነቅ አውቃለሁ። ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች አንተ የምትጨነቅለትን እንደዚህ ያለውን ሕይወት እንደማይኖሩ፣ በምትኩ የጽድቅ ሕይወትን እንደሚመርጡ ልነግርህ እፈልጋለሁ።
በመጀመሪያ ስለዚህ ነገር ልታስብ ይገባሃል። በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ካለ እንደዚያ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን የተቀደሱ ፍሬዎችን ታፈራለህ። በሌላ በኩል መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ከሌለ ምንም ያህል ጠንክረህ ብትሞክርም አንዳች የመንፈስ ፍሬዎችን ማፍራት አትችልም። ሰው በኢየሱስ ቢያምንም እንኳን በልቡ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከሌለው እንዴት የመንፈስን ፍሬዎች ማፍራት ይቻለዋል? ይህ የማይቻል ነው። ጌታ ክፉ ዛፍ በፍጹም መልካም ፍሬዎችን ሊያፈራ እንደማይችል ተናግሮዋል (ማቴዎስ 7፡17-18)።
አሁን ይህንን ጥያቄ ልጠይቅህና መልሱንም ልሰጥህ እፈልጋለሁ። አንተ በኢየሱስ ታምናለህ፣ ነገር ግን ሕይወትህን የምትኖረው በእርግጥ አለማዊ ኃጢአቶችን አሸንፈህ ነው? አለማዊ ኃጢአቶችን እያሸነፍህ፣ ጌታን አብዝተህ እያገለገልህና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለሌሎች በማቅረብ እነርሱ ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ እንዲድኑ እያደረግህ፣ ጻድቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆነህ እየኖርህ ነውን? በውኑ በኢየሱስ ካመንህ በኋላ ቅንጣት መጠን ያለው ኃጢአት እንኳን የሌለብህ ጻድቅ ሰው ሆነሃልን? ለእነዚህ ጥያቄዎች “አዎ” የሚል መልስ እንድትሰጥ የሚያስችልህ ብቸኛው እምነትና ወንጌል ጌታ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስጥ የመሰከረለት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው።
በኢየሱስ ካመንን በኋላ እንኳን በዓለም ላይ ኃጢአት መሥራት እንቀጥላለን። ሆኖም ጌታችን ከዓለም ኃጢአቶች በሙሉ እኛን ለማዳን በዮሐንስ ተጠምቆ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶዋል። ስለዚህ ጌታ ለእኛ የጽድቅ ሥራን ሠርቶልናል፤ እኛም ኃጢአቶቻችንን ባስወገደው በእግዚአብሔር ጽድቅ፣ በጌታ ጥምቀትና ደም ላይ ባለን እምነት አማካይነት ከኃጢአቶቻችን ድነናል።
እንደገና አንዳንድ ጥያቄዎችን ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ከሕሊናህ ኃጢአቶች ነጻ ነህን? በኢየሱስ ካመንህ በኋላ እንኳን፣ በእርሱ ከማመንህ በፊት እንደነበርከው ሁሉ ኃጢአተኛ አልነበርህምን? ይህ እውነት ከሆነ ለዚህ ምክንያቱ ምናልባትም ስለ ውሃውና ስለ መንፈሱ ወንጌል አለማወቅህ ነው። ስለዚህ በልብህ ውስጥ መንፈስ ባለመኖሩ በሥጋ ውስጥ ከሚገኙ ችግሮችና ውዥንብሮች ጋር ተጋፍጠሃል። ምንም ያህል የታመንህ ምዕመን ብትሆንም ከሥጋ አስተሳሰቦች ማምለጥ የምትችለው ልብህን ባዶ በማድረግና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመቀበል ብቻ ነው። የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነት የመሆኑን ሐቅ ለመረዳት ሥጋዊ አስተሳሰቦችን መጣልና ወደተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል መመለስ ይገባሃል።
በዚህ ዓለም ላይ ጌታን በአንደበታቸው ቢጠሩትም ጌታ የደነገገውን የመዳን ሕግ በፈለጉት በማንኛውም መንገድ የሚለውጡ ብዙ ሰዎች አሉ። አንተ ከእነዚህ አይነት ሰዎች አንዱ ከሆንህ ጌታ በመጨረሻው ቀን ይተውሃል። ይህ በዚህ ዓለም ባለ በማንኛውም ሰው ላይ እንዳይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። እጸልያለሁ አንተ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ብቻ ሊያድንህ የሚችል ብቸኛው ነገር እንደሆነ የሚያምን እንደዚያ አይነት ሰው እንዳትሆን፤ እንዲሁም ጥያቄዎችህን የጠየቅኸው ቀሪውን የሕይወት ዘመንህን ከኃጢአት ተላቀህ ለመኖር ካለህ ፍላጎት የተነሳ የሆነ ሰው እንዳትሆን እጸልያለሁ።
ሆኖም አስተሳሰቦችህ “ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል” (ሮሜ 8፡7) የሥጋ አስተሳሰቦች ናቸው። ጳውሎስ እንዲህ ይላል፦ “በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም” (ሮሜ 8፡8)። በእርግጥ እግዚአብሔርን የሚያስደስት እምነት እንዲኖርህ ከፈለግህ በጌታ አስደናቂ ሥራ ማመን ይገባሃል። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በማርያም በኩል ወደዚህ ዓለም መጣ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጥምቁ ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የሰውን ዘር ኃጢአቶች ወሰደ፣ በዚህም የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሁሉ ፈጸመ።
የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ማከናወን የሚችለው ማን ይመስልሃል ጻድቅ ሰው ወይስ ኃጢአተኛ? ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት ከኃጢአቱ ሙሉ በሙሉ ስላልነጻ አሁንም ድረስ በኃጢአት ውስጥ ነው። ስለዚህ ይህንን ሰው የሚጠብቀው ብቸኛው ነገር ለኃጢአቶቹ የሚቀበለው ፍርድ ነው። እግዚአብሔር ኃጢአተኞች ወደ መንግሥቱ እንዲገቡ አይፈቅድም፣ ምክንያቱም “አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና” (መዝሙረ ዳዊት 5፡4)። እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ወደ እርሱ መጥቶ ከእርሱ አንድ ነገር ቢጠይቀው የኃጢአተኛውን ጸሎቶች አይሰማም፣ ምክንያቱም “በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች” (ኢሳይያስ 59፡2)። የኃጢአት ደመወዝ ሞት ስለሆነ ኃጢአተኛ ሲዖል መውረዱ የተረጋገጠ ነው።
የጽድቅ ሥራዎችን መሥራት የሚችሉት ቅዱስ የሆኑና በልቦቻቸው ውስጥ ኃጢአት የሌለባቸው ጻድቃን ሰዎች ብቻ ናቸው። በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል ካመኑ በኋላ ኃጢአት በሌለባቸው ጻድቃን ልቦች ውስጥ ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ በበዓለ ሐምሳ ቀን እንዲህ አለ፦ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል) እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ” (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)።
ይህ ምንባብ እያለ ያለው እውነተኛ እምነት እንዲኖርህና በእምነትም ከኃጢአቶችህ ሁሉ ሙሉ በሙሉ መንጻት ከፈለግህ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ሞቱ ማመን ይገባሃል ነው። እንዲህ ያለው እምነት “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ” ያስችልሃል፣ ይህም ማለት በእርሱ የጽድቅ ምግባሮች በማመን ከኃጢአቶችህ ሁሉ ሙሉ በሙሉ መንጻት ትችላለህ ማለት ነው። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በእርሱ ጥምቀትና መስቀል እምነት ላላቸው ዳግም የተወለዱ ምዕመናን የጥምቀት ሥርዓትን አከናውነዋል። ኢየሱስ ሰውን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ደቀ መዛሙርቱን አዞዋቸዋል (ማቴዎስ 28፡19)።
ከዚህም በላይ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፦ “የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም” (ሮሜ 8፡9)። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለጻድቃን የሰጠው የእርሱ ልጆች መሆናቸውን ለማተም ነው። መንፈስ ቅዱስ በፍጹም በኃጢአተኞች ውስጥ አይኖርም፣ ምክንያቱም እነርሱ ኃጢአት አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን አይወድም፣ የሚመርጠው ቅድስናን (ከኃጢአት መለየትን) ነው። መንፈስ ቅዱስ ጻድቃንን በጽድቅ መንገድ ይመራቸዋል፣ የአብንም ፈቃድ እንዲከተሉ ይመራቸዋል። ታዲያ የአብ ፈቃድ ምንድነው? የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በየአገሩ ላሉ ሰዎች ማሰራጨትና እነርሱን ኃጢአት የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ማድረግ ነው።
የጻድቃንና የኃጢአተኞች ሥጋ እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ ኃጢአትን ይሠራል። ሆኖም ጌታ በጥምቀቱና በደሙ ሰዎች በሥጋቸውና በልባቸው የሚሠሩትን ኃጢአቶች በሙሉ የማስወገዱን የጽድቅ ሥራ ሠርቷል። ኢየሱስ የፈጸመው የእግዚአብሔር ጽድቅ ይህ ነው። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ተጽፎዋል፦ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና” (ሮሜ 1፡17)። በእግዚአብሔር ጽድቅ በማመን ከኃጢአቶቹ ሁሉ ሙሉ በሙሉ የተነጻ ሰው ‘ከኃጢአትና ከሞት ሕግ’ አሸንፎ የእርሱን ጽድቅ ይከተላል። ይህ የሚቻለው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ላይ በሚመጣና በሚኖር መንፈስ ቅዱስ አማካይነት ብቻ ነው።
የጻድቅ ሰው ያለፉት፣ አሁን ያሉትና የወደፊት ኃጢአቶች በሙሉ ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀበት ጊዜ ወደ እርሱ ተላልፈዋል። የጻድቃን ሥጋም እንደዚሁ ከኢየሱስ ጋር ሞቷል። አንድ ሰው በዚህ ሲያምን ከኢየሱስ ሞት ጋር አንድ ይሆናል። ይህም ለእነርሱ ኃጢአቶች ሁሉ ፍርድ ይሆናል (ሮሜ ምዕራፍ 6)።
ስለዚህ የአንድ ጻድቅ ሰው ሥጋ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ያለ ማቋረጥ ኃጢአት ቢሠራም መንፈስን መከተል ይችል ዘንድ በልቡ ውስጥ የሚኖረው መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል። አንድ ጻድቅ ሰው መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ስለሚኖር መንፈስ ቅዱስን ይከተላል፣ የእግዚአብሔርንም ሥራ ይሠራል።
በሐዋርያት ዘመንም እንኳን፣ ብዙ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ የሚገዙ ዳግም የተወለዱ ሰዎችን ሕይወት ለመጨነቅ የደፈሩበት ድፍረት ምክንያት፣ እነዚህን ዳግም የተወለዱ ሰዎችን ያለ ምክንያት ይወቅሷቸው ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ሐዋርያት የሰበኩትን የውሃውንና የመንፈሱን እውነተኛ ወንጌል እንደ ሥጋዊ ተፈጥሯዊ አስተሳሰብ በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል። ስለዚህ ሐዋርያው ጰውሎስ ለእነዚህ ሰዎች እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን?” (ሮሜ 6፡1-2) ጨምሮም “በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ” (ሮሜ 7፡25)።
በመጨረሻ የጻድቃን ሥጋ አሁንም ድረስ ጎዶሎ ነው፣ በየጊዜው ኃጢአት ከመሥራት በቀር ምርጫ የለውም፤ ነገር ግን እነርሱ አሁንም መንፈስ ቅዱስን በመከተል ወንጌልን በመላው አለም ይሰብካሉ። ጻድቃን ልቦቻቸው በጸጋው ስር ስላሉ በመንፈስ ይመላለሳሉ። “እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም። ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ” (ሮሜ 6፡15-16)።
እውነተኛ አበቦች ከሰው ሰራሽ አበቦች በጣም የተለዩ እንደሆኑ ሁሉ በጻድቅ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ባለቤትና በኃጢአተኛ ልብ ውስጥ ያለው ባለቤት እርስ በርሳቸው የተለያዩ ናቸው። በጻድቅ ሰው ልብ ውስጥ ያለው ባለቤት መንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ሰውየው በመንፈስ መመላለስና በሕይወቱ ውስጥም እግዚአብሔርን የሚያስደስተውን የጽድቅን እውነት መከተል ይችላል። በሌላ በኩል ኃጢአተኛ በውስጡ ያለው ባለቤት ኃጢአት ራሱ ስለሆነ ኃጢአትን ከመከተል ውጪ ምርጫ የለውም። ኃጢአተኛ በብዙ ኃጢአቶቹ ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ስለሌለው የተቀደሰ ሕይወትን መኖር አይችልም።
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች የተቀደሰ ሕይወትን መኖር አይችሉም የሚለው ግምት ከሥጋ ግብታዊ እሳቤዎች የመነጨ ስህተት ነው። እግዚአብሔር እነርሱን እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃቸዋል፦ “እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ” (ይሁዳ 1፡10)። ዛሬ ብዙዎች የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነተኛ ወንጌል መሆኑን ቢያውቁም የጻድቃኖችን ሕይወት አይረዱም፣ ምክንያቱም ወንጌሉን ሙሉ በሙሉ ስላላወቁትና በልባቸው ስላልተቀበሉት ነው።
ዳግም የተወለዱ ቅዱሳን የሚሠሩትን የጽድቅ ሥራዎች በሚመለከት ምን ታስባለህ? እነርሱ ወንጌልን በመላው ዓለም ለማስፋፋት የሚደረጉ በጎ ሥራዎች ላይ ያላቸውን ክቡር ነገሮች ሁሉ፣ እንዲሁም ራሳቸውንም ጭምር ሕያው መሥዋዕቶች አድርገው አቅርበዋል። በአንተ እሳቤዎች መሰረት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናኖች ሆን ብለው በወንጌል ሽፋን ኃጢአት እንደሚሠሩ የምታስበው ለምንድነው?
ጻድቃን በእውነት ብርሃንና በእግዚአብሔር ጽድቅ መካከል በእምነት በጎ ሥራዎችን ይሠራሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያደርጉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተወልደዋል። ኃጢአተኞች በሙሉ ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ኃጢአቶቻቸውን ሁሉ ወዳስወገደበት ወንጌል እንዲመለሱ ተስፋ እናደርጋለን።
አዎ ልባዊ ምኞታችን አንተም በእውነት ከልብህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከኃጢአቶችህ ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንድትነጻና እስከ መጨረሻው ቀን ድረስም ያለ ኃጢአት ሆነህ ጌታን እንድትጠብቅ ነው።