Search

শিক্ষা

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 3-2] ከሐጢያቶች መዳን የሚገኘው በእምነት ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ሮሜ 3፡1-31 ››

‹‹ ሮሜ 3፡1-31 ››
‹‹እንግዲህ አይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው፡፡ አስቀድሞ የእግዚአብሄር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው፡፡ ታዲያ ምንድር ነው? የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፡፡ በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሄር እውነተኛ ይሁን፡፡ ነገር ግን አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ቁጣን የሚያመጣ እግዚአብሄር አመጸኛ ነውን? እንደ ሰው ልማድ እላለሁ እንዲህ አይሁን፡፡ እንዲህ ቢሆን እግዚአብሄር እንዴት በዓለም ይፈርዳል? በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሄር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ሐጢያተኛ ገና ይፈረድብኛል? ስለምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና፤ አንዳንዱም እንዲህ እንድንል ይናገራሉና፡፡ የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው፡፡ እንግዲህ ምን ይሁን? ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፡፡ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከሐጢአት በታች እንዲሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ እግዚአብሄርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉም ተሳስተዋል፤ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፡፡ ቸርነትን የሚያደርግ የለም፤ አንድ ስንኳ የለም፡፡ ጉሮሮአቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፡፡ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፡፡ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፡፡ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፡፡ እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፡፡ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፡፡ የሰላምንም መንገድ አያውቁም፡፡ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሄርን መፍራት የለም፡፡
አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሄር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፡፡ ይህም የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፡፡ ሐጢያት በሕግ ይታወቃልና፡፡ አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሄር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፡፡ እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ልዩነት የለምና ሁሉ ሐጢአትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡ እርሱንም እግዚአብሄር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሰርያ አድርጎ አቆመው፡፡ ይህም በፊት የተደረገውን ሐጢያት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡ ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል፡፡ በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፡፡ በእምነት ሕግ ነው እንጂ፡፡ ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና፡፡ ወይስ እግዚአብሄር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸደቅ አምላክ አንድ ስለሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው፡፡ እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ፡፡››
 
 

የሰዎች አለማመን የእግዚአብሄርን ደህንነት ሊያስቀረው አይችልም፡፡

 
ሐዋርያው ጳውሎስ የሕጉ ፍጻሜና የእግዚአብሄር ጸጋ ቤዛነት የተሰጡን በእምነት እንጂ በምግባሮቻችን እንዳልሆነ ይናገራል፡፡ ከሐጢያቶቻችን ድነን በእግዚአብሄር ማዳን ጻድቃን ሆነናል፡፡ ‹‹እንግዲህ አይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው፡፡ አስቀድሞ የእግዚአብሄር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው፡፡ ታዲያ ምንድር ነው? የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፡፡›› (ሮሜ 3፡1-4)
 
የአይሁድ ጥቅሙ የእግዚአብሄር ቃል ለእነርሱ መሰጠቱ ነው፡፡ የእርሱን ቃል ከአያቶቻቸው እየሰሙ ኖሩ፡፡ እግዚአብሄር ቃሉን ስለሰጣቸውና በእነርሱ በኩልም ስለተላለፈ ከአሕዛቦች የተሻሉ እንደሆኑ አሰቡ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ከሐጢያቶቻቸው ያዳናቸውን ኢየሱስን ባለማመናቸው አይሁዶችን እንደተዋቸው ይናገራል፡፡
 
ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፡፡›› የሰዎች አለማመን የእግዚአብሄርን ማዳን ሊያስቀረው አይችልም፡፡ ‹‹የእግዚአብሄር ታማኝነት›› ማለት ‹‹የእግዚአብሄር እውነተኛነት›› ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ የእግዚአብሄር እውነተኛነትና ከሐጢያቶች መዳን አይሁዶች ባያምኑበትም እንኳን ዋጋ ሊያጣ አይችልም ማለቱ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚያምነውን ሁሉ እንደሚያድን የሰጠው የቃሉ ተስፋ ባያምኑበት እንኳን አይሰረዝም፡፡
 
አይሁዶች ባያምኑ አሕዛቦች ያምናሉ፡፡ እግዚአብሄር የሚያምን ሁሉ ከሐጢያቶቹ እንደሚድን ተናግሮዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር አይሁዶችን የተዋቸው እግዚአብሄር ቃሉን ቢሰጣቸውም የእውነት ቃል በእግዚአብሄር ተስፋ መሰረት እንደተፈጸመ ባለማመናቸው ነው፡፡
 
የሐዋርያው ጳውሎስ ማረጋገጫ እንደሚከተለው ነው፡፡ እግዚአብሄር የደህንነትን ስጦታ ለሰዎች ሁሉ ሰጥቶዋል፡፡ እግዚአብሄርም ይህንን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተስፋ እንደሰጠና አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ዓለም በመላክ እንደፈጸመው ተናግሮዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በተናገረው የተስፋ ቃል መሰረት የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሄር ልጅ በመሆን ተባርኮዋል፡፡ ምንም ያህል ብዙ ሰዎች ባያምኑም የእግዚአብሄር በረከቶች አይሰረዙም፡፡
 
 

በእውነት የሚያምን ሰው ሁሉ የእርሱን ታላቅ ፍቅር መቀበል ይችላል፡፡

 
የእውነትን ቃል ሰምቶ በእርሱ የሚያምን ሰው የእግዚአብሄርን ታላቅ ፍቅር ይቀበላል፡፡ የማያምኑ ሰዎች ግን እግዚአብሄር ውሸታም ነው ይላሉ፡፡ እግዚአብሄር ተስፋውን መፈጸሙ እርግጥ ነው፡፡ የማያምኑ ሰዎች ግን በሐጢያቶች ስርየት ጸጋ ስለማያምኑ ከእግዚአብሄር ደህንነት ተገልለዋል፡፡
 
ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን? እንዲህ አይሁን፡፡›› እግዚአብሄር አንድ ጊዜ ተስፋ ከሰጠ በኋላ የደህንነት ስጦታውንና ክብሩን ለሰዎች ሁሉ ሰጥቷል፡፡
 
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ስጦታ ምንድነው ይላል? መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሄር አብ የሚወደውን ልጁን በመላክ በልጁ በኩል በሆነው የሐጢያት ስርየት የሚያምኑ ሰዎች ልጆቹ የሚሆኑበትን ጸጋ እንደሰጣቸው ይናገራል፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ለሰዎች ሁሉ የእርሱ ልጆች የሚሆኑበትን ክብርና በጽድቁም አማካይነት ከሐጢያት መዳንን ሊሰጣቸው አቀደ፡፡ ይህንንም በታማኝነት ፈጸመ፡፡ ስለዚህ አማኞች በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ተባርከዋል፡፡ የማያምኑ ግን በቃሉ መሰረት ተፈርዶባቸዋል፡፡
 
የማያምኑ ሰዎች ወደ ሲዖል መውረዳቸው በጣም ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ ላይ ባለን እምነት መዳን እንችል ዘንድ ሕግን ደነገገ፡፡ ሰዎች ባያምኑም የእግዚአብሄር ታማኝነት በፍጹም እንደማይቀርም ተናግሮዋል፡፡ የእግዚአብሄርን የማዳን ታማኝነት በመቀበል ተባርከናል፡፡ ‹‹በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሄር እውነተኛ ይሁን፡፡›› (ሮሜ 3፡4)
 
ሰው ሁሉ ውሸተኛ ነው፡፡ ‹‹በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ውሸተኛ ከሆነ እግዚአብሄር እውነተኛ ይሁን፡፡›› እግዚአብሄር የሚባርኩትን እንደሚባርክ የሚረገሙትን ደግሞ እንደሚረግም አስቀድሞ ተስፋ እንደሰጠ ተናግሮዋል፡፡ የሚያምኑትን መባረክ የማያምኑትን ደግሞ መርገም የእግዚአብሄር ሥራ ነው፡፡ ‹‹ሰው ሁሉ ውሸተኛ እግዚአብሄር እውነተኛ ይሁን›› ይላል፡፡
 
‹‹በቃልህ ትጸድቅ ዘንድ ወደ ፍርድ በገባህም ጊዜ ትረታ ዘንድ፡፡›› እርሱ ሰዎች በቃሉ መሰረት እንደሚያድናቸው ተናግሮዋል፡፡ ቃል ሥጋ ሆኖ በመካከላችን በማደር አድኖናል፡፡ ስለዚህ ጌታ በቃሎቹ አማካይነት አጸደቀን፡፡
 
ጌታ ሰይጣንን በተጻፈው ቃል አሸነፈው፡፡ ጌታ ቃል የገባውን ስለፈጸመ በራሱ በሰይጣንና በመንፈሳዊ ፍጡራን ሁሉ ፊት ጻድቅና እውነተኛ ነው፡፡ ሰዎች ግን እውነተኞች አይደሉም፡፡ ደካሞች በሚሆኑበት ጊዜ ባህሪዎቻቸው ወዲያውኑ ይለወጣሉ፡፡ በአንጻሩ እግዚአብሄር ፈጽሞ ተስፋዎቹን ጥሶ አያውቅም፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ እምነታችን በእግዚአብሄር ቃል ላይ መመስረት እንዳለበት ይናገራል፡፡
 
 
አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ያስረዳል፡፡
 
ሮሜ 3፡5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ነገር ግን አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ቁጣን የሚያመጣ እግዚአብሄር አመጸኛ ነውን? እንደ ሰው ልማድ እላለሁ እንዲህ አይሁን፡፡›› ሰዎች ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው፡፡ የእነርሱ ዓመጽ የእግዚአብሄርን የደህንነት ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን? ሐጢያቶቻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዱ ከሆኑ ምን እንላለን?
 
በእኛ ሐጢያቶችና ዓመጻ ምክንያት የእግዚአብሄር ጽድቅ ይበልጥ ይገለጣል፡፡ እግዚአብሄርም በእርግጥ እውነተኛ ነው፡፡ እርሱ በቃሉ ሊያድነን ቃል የገባና የገባውንም ቃል የፈጸመ የደህንነት ጌታ፣ አዳኝና እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በድካሞቻችን አማካይነት ቢገለጥ ምን እንላለን? እኛ እስከምንሞት ድረስ ሐጢያት ስለምንሰራ ድካሞቻችን አብዝተው የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይገልጣሉ፡፡
 
እግዘአብሄር የፍቅር ጌታ መሆኑን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይህንን የምናውቀው ከድካሞቻችን ነን፡፡ እኛ እስከ መጨረሻዋ የሕይወታችን ቀን ድረስ ሐጢያት ስለምንሰራ የእግዚአብሄር ፍቅር በእኛ ውስጥ ይገለጣል፡፡ ጌታ የዓለምን ሐጢያቶች ለአንዴና ለመጨረሻ እንደደመሰሰ ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያት ያላደረጉ ጥሩ ሰዎችን ብቻ የሚወድድ ቢሆን ኖሮ ፍቅሩ እንከን ያለበት ይሆን ነበር፡፡ እግዚአብሄር ፈጽሞ መወደድ የማንችለውን እኛን ሐጢያተኞችን የተቀበለውና ከእኛ ጋር የተስማማው ከእውነተኛ ፍቅሩ የተነሳ ነው፡፡
 
እኛ ሰዎች ዓመጸኞች እስከሆንን ድረስ እግዚአብሄርን ክደነዋል፡፡ በእርሱ አናምንም፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት የሚወደድ ነገር የለንም፡፡ ሐጢያተኞች ክፉ ነገርን ብቻ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከሐጢያቶቻችንና ከበደሎቻችን ሁሉ ያዳነን ኢየሱስ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፍቅር ፈጸመ፡፡
 
ሰዎች ሐጢያት ሰርተው በሰይጣን ማታለያ ሲዖል ለመወረድ በታጩ ጊዜ ከሰይጣን ጨለማና እርግማኖች ያድነን ዘንድ አንድያ ልጁን የላከው ከጽድቁና ከፍቅሩ የተነሳ ነበር፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጸጋ ነው፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹ነገር ግን አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን?›› በማለት ተቃራኒ አሳብ ያቀርባል፡፡ ጳውሎስ እኛ ሰዎች በእርሱ ፊት ሐጢያትን እንጂ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ማድረግ እንደማንችል ክፋታችንም የእግዚአብሄርን ጽድቅ እንደሚያስረዳ ይናገራል፡፡ አዎ ይህ እውነት ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ክፉዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ግን ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ አድኖዋቸዋል፡፡
 
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ ድነናል፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ ሰዎች ጻድቅ ሊሆኑ እንደማይችሉና በሐጢያቶች ወጥመድ እንደተጠመዱ ይናገራል፡፡ ጌታ እንዲህ ያሉትን ሐጢያተኞች አዳነና ወደዳቸው፡፡ እኛ በየቀኑ ሐጢያት መስራትን ማቆም ስለማንችል የእርሱ ፍጹም ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የዳንነው በኢየሱስ ፍጹም ፍቅር፣ በነጻ ጸጋውና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሆነው የደህንነት ስጦታ ብቻ ነው፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ በእግዚአብሄር ጽድቅ በመዳኑ ዕዳ እንዳለበት ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያተኞችን ሁሉ ለማዳን ያደረገው ነገር ጽድቁን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ውስጥ ተገልጦዋል፡፡ መዳናችን እግዚአብሄር ለእኛ ባደረገው የጽድቅ ሥራ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ ስለዚህ ሐጢያተኞች በእምነት ከሐጢያቻቸው ሁሉ ድነዋል፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች መንግሥተ ሰማይ ይገቡ ዘንድ ጥሩ መሆን እንደሚገባቸው ያስባሉ፡፡
 
ጳውሎስ ሆነ ብለን ክፉ ነገሮች እንናድርግ ማለቱ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሳይቀበሉ ሰናይ ምግባሮችን ለማድረግ በመሞከራቸው ምክንያት መጨረሻው ሲዖል መውረድ ይሆናል፡፡ ወደ ሲዖል ከመውረድ ለመዳን ይለወጡ ዘንድ ንስሐ መግባትና እግዚአብሄር በሰጣቸው ደህንነት ማመን አለባቸው፡፡
 
በእግዚአብሄር ፊት መልካም ስነ ምግባሮችን ማድረግ የሚችል ማነው? ማንም የለም፡፡ ታዲያ ሐጢያተኛ ከእርሱ/ከእርስዋ ሐጢያቶች መላቀቅ የሚችለው እንዴት ነው? እርሱ/እርስዋ የራሱን/የራስዋን አስተሳሰቦች መለወጥ አለባቸው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በእምነት እንደዳነ ተናግሮዋል፡፡ ነገር ግን ሰዎች ምን ያስባሉ? ሰዎች ጥሩ ነገሮች በማድረግ መዳን እንደሚችሉ ያስባሉ፡፡ በኢየሱስ በማመን ከሐጢያቶቻቸው የዳኑና ፍጹም የሆነ የሐጢያቶች ስርየት ያገኙ ሰዎች የሚመኩት በእግዚአብሄር ጽድቅ ብቻ ነው፡፡ እርሱን ከፍ ያደርጉታል፡፡
ነገር ግን ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች በኢየሱስ ቢያምኑም ጥሩ ምግባሮችን በማድረግ መንግሥተ ሰማይ መግባት እንደሚችሉና ጥሩ ምግባሮችን ባያደርጉ ወደ ሲዖል እንደሚወርዱ ያስባሉ፡፡ እምነታቸው ትክክል አይደለም፡፡ የሐዋርያው ጳውሎስ እምነት ዳግም የተወለደ ሰው ከያዘው እምነት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች በኢየሱስ እንደሚያምኑ ቢያስቡም እምነታቸው የተሳሳተ ነው፡፡ ምክንያቱም በእምነታቸው ላይ ሰናይ ምግባሮቻቸውን ለማከል ይሞክራሉና፡፡ የዳንነው በእምነታችን ላይ ሰናይ ምግባሮቻችንን በማከል ሳይሆን የእግዚአብሄር ጽድቅ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ነው፡፡
 
 
ጻድቅ ሆነ ብሎ ሐጢያት አይሰራም፡፡
 
‹‹ነገር ግን አመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚያስረዳ ከሆነ ምን እንላለን?›› መጽሐፍ ቅዱስ ዓመጻችን የእግዚአብሄርን ጽድቅና ፍቅሩን ብቻ እንደሚያስረዳ ይናገራል፡፡ ‹‹በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሄር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ሐጢያተኛ ገና ይፈረድብኛል? ስለምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና፤ አንዳንዱም እንዲህ እንድንል ይናገራሉና፡፡ የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው፡፡›› (ሮሜ 3፡7-8) የማያምኑ ሰዎች ስሞች በፍርድ መጽሐፍ ላይ ተጽፎዋል፡፡ እነርሱም ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡ ስለዚህ ይለወጡ ዘንድ ንስሐ መግባትና በውሃውና በደሙ የተፈጸመውን ወንጌል ማመን አለባቸው፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ቁጣን የሚያመጣ እግዚአብሄር አመጸኛ ነውን? እንደ ሰው ልማድ እላለሁ እንዲህ አይሁን፡፡›› ሰዎች ‹‹እግዚአብሄር በማያምኑ ሰዎች ላይ ቁጣን የሚያመጣና ኢየሱስ አስቀድሞም ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንዳዳናቸው ባለማመናቸው ሲዖል የሚወረውራቸው መሆኑ ዓመጸኝነት አይደለምን?›› በማለት ይከራከራሉ፡፡
 
ሮሜ 3፡7 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሄር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ሐጢያተኛ ገና ይፈረድብኛል?›› ይህን ጊዜ ሰዎች ‹‹ምን? የሐጢያቶችን ስርየት ስላገኘህ ሆነ ብለህ ሐጢያት ትሰራለህን?›› ይሉ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንደዚህ የሚያደርጉ ሰዎች የእግዚአብሄርን ማዳን የማያውቁና በፍቅሩም የማያምኑ ሰዎች እንደሆኑ ይናገራል፡፡
 
ስለዚህ ጳውሎስ የእግዚአብሄር እውነተኛነት በእኛ ዓመጸኝነትና ውሸት በዕዳ ሳይያዝ ለክብሩ እንደሚልቅ ይናገራል፡፡ ሰዎች ግን ‹‹ያለ ሥራ በእምነት እንዳዳናችሁ የምታምኑ ከሆነ ብዙ ሐጢያቶችን ልትሰሩ ትችላላችሁ›› በማለት በራሳቸው አስተሳሰቦች ጳውሎስን ተቀናቅነውታል፡፡ ሰዎች ሐጢያት የሚሰሩት የሐጢያት ፈቃድ ስላላቸው መሆኑ እውነት አይደለም፡፡ ሐጢያተኞች ሆነው ስለተወለዱ ሐጢያት መስራትን ማስወገድ አይችሉም፡፡ የአፕል ዛፍ የአፕል ፍሬዎችን ማፍራቱ ተፈጥሮው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሐጢያተኛ ሆኖ የተወለደ ሰውም ሐጢያት በመስራት መቀጠሉ ተፈጥሮአዊ እንደሆነ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ያሉ ሐጢያተኞችን በጽድቁ አዳናቸው፡፡ እነርሱ መዳን የሚችሉት የጌታን ማዳን በመቀበል ብቻ ነው፡፡
 
‹‹ስለምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና፤ አንዳንዱም እንዲህ እንድንል ይናገራሉና፡፡ የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው፡፡›› (ሮሜ 3፡8) በሐሰተኛ አስተማሪዎች የተታለሉ ሰዎች በኢየሱስ እናምናለን እያሉ እንደዚህ ያስባሉ፡፡ የሮሜ መልዕክት ከ2,000 ዓመታት በፊት የተጻፈው በሐዋርያው ጳውሎስ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ብዙ ሰዎች ልክ የዛሬዎቹ አላማኒዎች እንደሚያስቡት በዚህ መንገድ አስበው ነበር፡፡ ሐሰተኛ ምዕመናኖች በጳውሎሰ ዘመን የነበሩት የማያምኑ ሰዎች እንዳሰቡት ‹‹የሐጢያቶችን ስርየት ከተቀበላችሁ፣ ሐጢያት አልባ ከሆናችሁና ወደፊት የምትሰሩዋቸው ሐጢያቶችም ይቅር እንደተባሉ ካወቃችሁ ሆነ ብላችሁ ተጨማሪ ሐጢያት ትሰራላችሁን?›› ብለው ያስቡ ነበር፡፡
 
የማያምኑ ሰዎች ድርጊት እምነት የለሽ በሆኑት የሥጋ አሳቦች ላይ የተመረኮዙ ናቸው፡፡ እነርሱ ሐሰተኛ ከሆኑት የሥጋ አስተሳሰቦች የተነሳ የእግዚአብሄርን ደህንነት እውነት መረዳት አይችሉም፡፡ ጻድቃኖችም የሐጢያቶችን ስርየት ከተቀበሉ በኋላ አሁንም እንደሚሰሩ እርግጥ ነው፡፡ ነገር ግን ገደብ አለ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሐጢያተኞች ሐጢያት በመስራት የሚቀጥሉት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ከመወለዳቸው በፊት ሐጢያት እያደረጉ መሆናቸውን ስለማይገነዘቡና ሐጢያት መሆኑንም ስለማያውቁ ነው፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃን ሆነ ብለው ሐጢያት እንደማይሰሩ ይናገራል፡፡ ምክንያቱም እነርሱ በእግዚአብሄር አገዛዝ ሥር ናቸውና፡፡
 
አንዳንድ ሰዎች ለሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብለውት ነበር፡፡ ‹‹እግዚአብሄር ከሐጢያቶችህ ሁሉ ስላዳነህ መልካም እንዲመጣ ክፉን አታደርግምን? የእግዚአብሄር ጽድቅ አብዝቶ ይገለጥ ዘንድ ብዙ ክፉ ምግባሮችን ብታደርግ ይሻላል፡፡›› ጳውሎስም ፍርዳችሁ ቅን ነው አላቸው፡፡ ይህንን ሲል ተፈርዶባቸው ወደ ሲዖል መውረዳቸው ትክክል ነው ማለቱ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም የተደገፉት በራሳቸው ምግባሮች ላይ እንጂ በእምነት ላይ አይደለም፡፡
 
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ በፍጹም ዋጋ ቢስ አይሆንም፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን?›› እነርሱ በእግዚአብሄር ደህንነት ስላላመኑ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ማዳን ዋጋ ቢስ ያደርገዋልን? ሰዎች የሚድኑት ሲያምኑ ነው፡፡ የማያምኑ ከሆኑ ግን የሐጢያቶች ስርየትን ጸጋ ያጣሉ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ጸንቶ ይቆማል፡፡ ገባችሁ? ወደ ሲዖል የሚነጉዱ ሰዎች ሲዖል ለመውረድ ፈቅደዋል፡፡ ምክንያቱም ማመን አልመረጡምና፡፡ የእግዚአብሄር ሥራዎችና ከሐጢያት የመዳን ጸጋ በፍጹም ዋጋ ቢስ አይሆኑም፡፡ ጸንተው ይቆማሉ፡፡
 
የጌታ ማዳን በሕግ ሥራዎች ላይ የተመረኮዙ የሰው ጥረቶች ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ አማኞች በእግዚአብሄር እውነት መሰረት ይድናሉ፡፡ የማያምኑ ሰዎች ግን ወደ ሲዖል ይወርዳሉ፡፡ ምክንያቱም እውነትን ስለሚንቁ አይድኑምና፡፡ እግዚአብሄር ‹‹የእንቅፋት ድንጋይንና የማሰናከያን ዓለት›› (ኢሳይያስ 8፡14) ላከ፡፡ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ምንም ያህል ክፉ ቢሆንም ጻድቅ ሆንዋል፡፡ የዘላለም ሕይወትም አለው፡፡ በኢየሱስ የማያምን ሰው ምንም ያህል ጥሩ ሰው ቢሆንም ከሐጢያት ደመወዝ የተነሳ ወደ ሲዖል ይወርዳል፡፡ ኢየሱስ በሐጢያቶች ይቅርታ ለማያምኑ ሰዎች የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት ነው፡፡
 
 
ሐጢያት ያለበት ጻድቅ ሰው የለም፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ ጥሩ ሰዎች እንደሆኑ ለሚያስመስሉ ሰዎች ደህንነት ስለሚያስገኘው እምነት ይናገራል፡፡ ስለዚህ ሰዎች የሮሜን መጽሐፍ ስለ እምነት የሚናገር የእግዚአብሄር ቃል አድርገው ይመለከቱታል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ጻድቃን አድርገው ስለሚሰይሙ ሰዎች ግራ ይጋባሉ፡፡ በእርግጥም ሐጢያቶቻቸው በሙሉ ይቅር ስለተባሉ ጻድቃን ናቸው፡፡ ‹‹ኢየሱስ ታማኝ ነው›› ማለት ‹‹ሐጢያተኞችን በታማኝነት ከሐጢያቶቻቸው አድኖዋቸዋል›› ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ‹‹የዳኑ›› ሐጢያተኞች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት የዚህ አይነት ሰዎች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ሰው ከሐጢያት ከዳነ በኋላ እንዴት ገናም ሐጢያተኛ ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ ካዳነን ድነናል፡፡ ኢየሱስ ካላዳነን ሐጢያተኞች ነን፡፡ በደህንነት ውስጥ ‹‹መሃል ሰፋሪ›› የለም፡፡
 
ሐጢያት ያለበት ጻድቅ ሰው አለን? ሐጢያት ያለበት ጻድቅ ሰው የለም፡፡ አንድ ሰው ሐጢያት ካለበት ሐጢያተኛ ነው፡፡ በኢየሱስ ካመነ ግን ጻድቅና ሐጢያት አልባ ነው፡፡ በየቀኑ የምንሰራቸውንና ወደፊት የምናደርጋቸውን ሐጢያቶች ችግር የምንቀርፈው እንዴት ነው? ሰዎች የተለመዱ ሐጢያተኞች እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ ምክንያቱም በየቀኑ ሐጢያት ይሰራሉና፡፡ እስኪሞቱ ድረስም ሐጢያት መስራታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ የወደፊት ሐጢያቶችን ጨምሮ የዓለምን ሐጢያቶች በዮርዳኖስ ወንዝ እንደወሰደና እንደተሰቀለ በሚናገረው ወንጌል በማመናችን ጻድቃን ሆነናል፡፡
 
‹‹ሐጢያት ያለበት ጻድቅ ሰው›› የሚለው አባባል ትርጉም አይሰጥም፡፡ ሰው ዕዳዎቹን ሁሉ አስቀድሞ ከፍሎ ሳለ ገናም ባለ ዕዳ ስለ መሆን ማሰብ ምክንያታዊ ነውን? በአንድ ወቅት ብዙ ገንዘብ የነበረው ሰው ነበር ብለን እናስብ፡፡ የሰውየው ልጅ ግን እያደገ ሲሄድ በየቀኑ በከተማው ውስጥ ከሚገኙ የገበያ ማዕከሎች ሁሉ ከረሜላዎችን በዱቤ የመግዛት መጥፎ ልማድ ውስጥ ወደቀ፡፡ ሆኖም ባለጠጋው አባቱ ልጁ ዕድሜውን ሙሉ ካጠራቀማቸው ዕዳዎች የሚበልጥ በቂ ገንዘብ አስቀድሞ ለእያንዳንዱ የገበያ ማዕከል ከፍሎ ስለነበር እስኪሞት ድረስ በየቀኑ ገንዘብ ሳይከፍል ከረሜላዎችን በመብላት ቢደሰትም በፍጹም ባለ ዕዳ ሊሆን አይችልም፡፡
 
ጌታ ሐጢያቶቻችንን ለዘላለም በዮርዳኖስ ወንዝ በወሰደበት ጽድቁ አድኖናል፡፡ እርሱ ሁላችንንም ፈጽሞ አድኖናል፡፡ ስለዚህ ምንም ያህል ደካሞች ብንሆንም ዳግመኛ ፈጽሞ ሐጢያተኞች አንሆንም፡፡ እግዚአብሄር እርሱ ያደረገውን ካልካድን ጻድቃን እንደሆንን ተናግሮዋል፡፡
 
 
ሰዎች በሥጋዊ አሳቦች ወንጌልን ሊያምኑም ሆነ ዳግም ሊወለዱ አይችሉም፡፡
 
ራሳቸውን ‹‹የዳኑ›› ሐጢያተኞች አድርገው የሚሰይሙ ክርስቲያኖች የሚያስቡት ሥጋዊ አሳብ ነው፡፡ ስለ መንፈስ ማሰብ በእግዚአብሄር ቃል ማመን ነው፡፡ የሥጋ አሳብ የሰው አሳብ ነው፡፡ ሥጋ ሐጢያት ከመስራት አይቆጠብም፡፡ ነገር ግን እኛ በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል በማመን ጻድቃን መሆን እንችላለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሐጢያትን ለመስራት ባለ መሞከር ፈጽሞ ጻድቃን መሆንና መቀደስ እንደማንችል ይናገራል፡፡
አንድ ሰው በኢየሱስ ካመነ በኋላ ዳግመኛ ፈጽሞ ሐጢያት የማይሰራ ቅዱስ ሰው በመሆን መንግሥተ ሰማይ መግባት ይችላልን? ወይስ ይህ የሚቻለው አንድ ጊዜ ለዘላለም በተሰጠው ደህንነት ብቻ ነው? ሐጢያተኞች የሐጢያቶች ስርየት በሚያስገኘው ጸጋ በእርግጥ ጻድቃን እንዲሆኑ ተደርገዋልን? በሥጋ አሳብ ጻድቃን መሆን አይቻላችሁም፡፡ ሥጋ በፍጹም ጻድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ ሥጋ በሚራብበት ጊዜ ሁሉ ሁሌም የሚበላው ነገር ይፈልጋል፡፡
 
ሥጋ ፍትወቶችና ፍላጎቶች ስላሉት ሊቀደስ አይችልም፡፡ በዚህ ምክንያት ጻድቃን የምንሆነው በውሃውና በኢየሱስ ደም በማመን ብቻ ነው፡፡ ዳግመኛ ሐጢያት ባለመስራትና ራሳችን እንደ በረዶ ንጹህ አድርገን በማንጻት መንግሥተ ሰማይ መግባት እንችላለንን? የሥጋ ፍትወትና መሻቶች ያሉት ሰው ሐጢያትን በመራቅ ለመቀደስ መሞከሩ ትምክህታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ የማይቻል ነው፡፡
 
ሰዎች ስለ እምነት የሚያስቡት በሥጋ አእምሮ ስለሆነ በወንጌል ሊያምኑም ሆነ ዳግም ሊወለዱ አይችሉም፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው፡፡›› (ዮሐንስ 3፡6)
 
በሥጋ አሳብ ጻድቅ መሆን አይቻልም፡፡ ምንም አጥብቃችሁ ንስሐ የገባችሁና እስከ ዛሬም ድረስ በኢየሱስ ያመናችሁ ብትሆኑም ነገ ሐጢያት ስለምትሰሩ እናንተም የማይቻል እንደሆን ታስቡ ይሆናል፡፡ ‹‹አሁን እንኳን ሐጢያት በመስራት ላይ እያለሁ እንዴት ያለ ሐጢያት ነኝ ማለት እችላለሁ?›› ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ ሥጋ እንደሚያደርገው በሥጋ የምታስቡ ከሆነ ጻድቅ መሆን ይቻላችኋልን? በሥጋ መቀደስ አይቻልም፡፡
 
 
ሆኖም እግዚአብሄር ጻድቃን ሊያደርገን ይችላል፡፡
 
ሰው ባይችልም እግዚአብሄር ግን ፈጽሞ ሊያድነን ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ሕሊናችንን ሊያነጻ፣ ጻድቃን እንደሆንንና እርሱም አባታችንና አዳኛችን ስለመሆኑ እንድንመሰክር ሊያደርገን ይችላል፡፡ እምነት የሚጀምረው እውነተኛውን ቃል በልባችሁ በማመን መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ ጻድቃን የሆንነው እውነተኛውን ቃል በልባችን በማመናችን ነው፡፡ በሥጋ ሥራዎች ፈጽሞ ጻድቃን መሆን አንችልም፡፡
 
ነገር ግን ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች በራሳቸው አስተሳሰቦች የተቆለፉ ስለሆኑ ራሳቸውን ከራሳቸው አስተሳሰቦች ነጻ ማድረግ አይችሉም፡፡ በሥጋ አእምሮ ስለሚያስቡ ጻድቃን ስለመሆናቸው በፍጹም አይናገሩም፡፡ በአንጻሩ ጻድቃን ነን ማለት የምንችልበት እምነት የሚጀምረው የእግዚአብሄርን ቃል እውነት በማወቅ ነው፡፡ በእርግጥ ዳግም መወለድ የምትፈልጉ ከሆናችሁ በእርግጠኝነት ዳግም መወለድ የምትችሉት ያለ ማወላወል ዳግም በተወለደ ሰው አማካይነት እውነተኛውን ቃል በመስማት ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ዳግም በተወለደ ቅዱስ ሰው ውስጥ ያለው መንፈስ ከእውነት ጋር በመስራት ይደሰታል፡፡ ‹‹የእግዚአብሄርን ጥልቅ ነገር ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና፡፡›› (1ኛ ቆሮንቶስ 2፡10) ሰዎች በጻድቁ በኩል የሚመጣውን ቃል ሲሰሙ ዳግም ይወለዳሉ፡፡ ምክንያቱም መንፈስ ዳግም በተወለደው ጻድቅ ሰው ውስጥ ያድራልና፡፡ ይህንን በአእምሮዋችሁ እንድትይዙት እፈልጋለሁ፡፡ ዳግም የመወለድን ጸጋ ማግኘት ከፈለጋችሁ ዳግም ከተወለደ ጻድቅ ሰው ጋር ልትገናኙ ይገባችኋል፡፡
 
አብርሃም እስማኤልንና ይስሐቅን ወለደ፡፡ እስማኤል ከገረዲቱ የተወለደ ነበር፡፡ ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ እስማኤል 14 ዓመት ሆኖት ነበር፡፡ እስማኤል ከጨዋይቱ የተወለደውን ይስሐቅን አሳደደው፡፡ በትክክል የወራሽነት መብት ያለው ማን ነበር? የወራሽነት መብት የነበረው ከጨዋይቱ ሣራ የተወለደው ይስሐቅ ነበር፡፡
 
ምንም እንኳን እስማኤል ከይስሐቅ በዕድሜ የሚበልጥና በሥጋም ጠንካራ የነበረ ቢሆንም ይስሐቅ የወራሽነት መብት ነበረው፡፡ ይህም ተረጋግጦለታል፡፡ ለምን? ይስሐቅ የተወለደው በእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ በሰው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ እምነት በአሸዋ ላይ የተገነባን ግምብ ይመስላል፡፡ ሰዎች ዳግም መወለድ የሚችሉት የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ተምረው ሲያምኑበት ብቻ ነው፡፡
 
‹‹እንግዲህ ምን ይሁን? ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፡፡ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከሐጢአት በታች እንዲሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ጻደቅ የለም አንድ ስንኳ፤›› (ሮሜ 3፡9-10) እነዚህ ምንባቦች ምን ይላሉ? ምንባቦቹ የሚያመለክቱት ሰዎች ዳግም ከመወለዳቸው በፊት ያለውን ሁኔታ ነው ወይስ ዳግም ከተወለዱ በኋላ ያላቸውን ሁኔታ? ሁላችንም ዳግም ከመወለዳችን በፊት ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ ‹‹ጻድቅ የለም›› የሚለው አባባል ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች ከመደምሰሱ በፊት ያለውን የሰዎችን ሁኔታ የሚጠቁም ነው፡፡ ሰው በኢየሱስ ሳያምን ከቶውኑም ጻድቅ ሊሆን አይችልም፡፡
‹‹ቅድስና በሒደት›› የሚለው ቃል የመጣው ጣዖትን ከሚያመልኩ የአሕዛብ ሃይማኖቶች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፡፡›› ሰው ራሱን በማሰልጠን እንዴት ሊቀደስ ይችላል? ሰው በራሱ/በራስዋ ጻድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ በራሱ ጻድቅ የሚሆን ወይም ጻድቅ የሆነ ሰው የለም፡፡ በራሱ/በራስዋ ጥረቶች ሐጢያት አልባ የሆነ ማንም የለም፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው በእግዚአብሄር ቃል በማመን ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹አስተዋይም የለም፡፡ እግዚአብሄርንም የሚፈልግ የለም፡፡›› (ሮሜ 3፡11)
 
 
ሁሉ ተሳስተዋል፡፡
 
‹‹ሁሉ ተሳስተዋል፡፡ በአንድነትም ማይጠቅሙ ሆነዋል፡፡›› (ሮሜ 3፡12) ሰው በእግዚአብሄር ፊት የሚጠቅም ፍጡር ነው፡፡ ገና ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት የማይጠቅሙ ናቸው፡፡ እነርሱ ሁላቸውም በእግዚአብሄር የተፈጠሩ መሆናቸውን ረስተው ዝናብ ስላላዘነበላቸው አኩርፈው ከእግዚአብሄር ጋር ለመጣላትና እርሱን ለመራገም ጣቶቻቸውን ወደ ሰማይ አይቀስሩምን?
 
‹‹ሁሉ ተሳስተዋል፡፡ በአንድነትም ማይጠቅሙ ሆነዋል›› ይላል፡፡ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ሰው እንዴት እግዚአብሄርን ሊያከብር ይችላል? የሐጢያት ችግሮቻቸውን መቅረፍ የማይችሉ ሐጢያተኞች ጌታን እንዴት ሊያመሰግኑ ይችላሉ? ሐጢያተኛ እንዴት ጌታን ሊያመሰግን ይችላል? ሐጢያተኞች እግዚአብሄርን ማክበር አይችሉም፡፡
 
በዚህ ዘመን የምስጋና አገልግሎቶች በዝተዋል፡፡ ሐጢያተኞች በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ያሉ ጥቅሶችን በመጥቀስ ለወንጌል መዝሙሮች ግጥሞችን ይጽፋሉ፡፡ ‹‹በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ በረከት፣ ውዳሴ፣ ክብርና ሐይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፡፡›› (ዮሐንስ ራዕይ 5፡13) በእርግጥ ጌታ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን ማመስገን የሚችሉት ጻድቃን ብቻ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር የሐጢያተኞችን ምስጋና በደስታ የሚቀበል ይመስላችኋልን? የሐጢያተኞች ምስጋና ልክ እንደ ቃየን መስዋዕት ነው፡፡ ውዳሴዎቻቸው ከንቱ ናቸው፡፡ ጌታን ያመሰገኑ ቢመስላቸውም የተዘመሩት ለባዶው ሰማይ ነው፡፡ ለምን? እግዚአብሄር በእነርሱ አይደሰትባቸውምና፡፡ እግዚአብሄር የሐጢያተኞችን ጸሎቶች ፈጽሞ አይሰማም፡፡ (ኢሳይያስ 59፡1-2)
 
መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ እንደተሳሳቱና በአንድነትም የማይጠቅሙ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ‹‹ሁሉ ተሳስተዋል›› የሚሉት ቃሎች የእግዚአብሄርን ቃሎች የእግዚአብሄርን ቃል ትተው የራሳቸውን አስተሳሰቦች አመኑ ማለት ነው፡፡ እውነተኛ ብያኔ የሚገኘው ከእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ዳኛውም እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ሰዎች መፍረድ አይችሉም፡፡ ‹‹ሁሉ ተሳስተዋል›› የሚሉት ቃሎች ወደ ራሳቸው አስተሳሰቦች ተመልሰዋል ማለት ነው፡፡ እነርሱ ሁልጊዜም ‹‹የማስበው በዚህ መንገድ ነው፡፡ የማምነውም እንዲህ ነው›› የሚሉ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ አስተሳሰቦቻቸውን የማይተዉ ሰዎች ለአስተሳሰቦቻቸው ነጻነትን ስለሚሰጡ ወደ እግዚአብሄር ቃል አይመለሱም፡፡
 
ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች የራሳቸው ዳኞች እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የተጻፈው ነገር ለእነርሱ ጠቃሚ አይደለም፡፡ አስተሳሰቦቻቸውን የሙጥኝ ብለው ይዘው ‹‹እንደዚህ አስባለሁ፡፡ በዚህ መንገድ አምናለሁ፡፡ ያ እኔ ከማስበው ጋር የሚስማማ አይደለም›› በማለት እውነት ወይም ውሸት ስለመሆኑ በተስማሙበት ሁኔታ ይፈርዳሉ፡፡ እውነትን እንዴት ሊያገኙ ይችላሉ? እግዚአብሄር ሰዎች ሁሉ ወደገዛ አስተሳሰቦቻቸው እንደተመለሱ ይናገራል፡፡ እኛ መመለስ ያለብን ወደ እግዚአብሄር ነው፡፡ በትክክለኛው መንገድ መዳን ይኖርብናል፡፡ በእውነተኛው ቃል ፊት ሊፈረድብን ይገባል፡፡ እንግዲያውስ ጽድቅ ምንድነው?
 
 
በእግዚአብሄር ቃል ዳግም መወለድ አለብን፡፡
 
ጽድቅ እውነት የሆነው የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ‹‹መለኪያ በትርን›› የሚያመለክት ቀኖና ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል መስፈርት ወይም መለኪያ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ ‹‹በመጀመሪያው ቃል ነበረ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡1) ከእግዚአብሄር አብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብሮ ማን ነበር? እርሱ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ ቃሉ እግዚአብሄር ነው፡፡ ቃሉ አምላካችን የሆነው አዳኛችንና የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
 
ቃል በመጀመሪያ ከእግዚአብሄር ጋር እንደነበር ተጽፎዋል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ማን ነበር? ቃል ነበር፡፡ ስለዚህ ቃሉ አዳኛችንና አምላካችን ኢየሱስ ነው፡፡ የእርሱን ባህርይ በትክክል የሚወክለው ቃሉ ነው፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር ቃል ከእኛ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ ምክንያቱም ቃል እግዚአብሄር ነውና፡፡ ሰዎች በራሳቸው ሥጋዊ አስተሳሰቦች የእግዚአብሄርን ቃል ለመረዳት መሞከራቸው ድንቁርናቸውን ያሳያል፡፡
 
ስለዚህ እግዚአብሄር በቃሉና በእምነት ጸንቶ የሚቆምን ሰው ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ጸንቶ የሚቆም ሰው ታማኝና በእግዚአብሄርም ፊት የሚጠቅም ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ያለውን ሰው ይባርከዋል፡፡
 
ሰው መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ይችላልን? ከእግዚአብሄር የሆነው ቃል ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ ይላል፡፡ ነገር ግን አንዳንዶች ‹‹መልካም የሚያደርግ ሰው የሚኖር ይመስለኛል›› ብለው ያስባሉ፡፡ እንዲያውም ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ግብዝነትን ይተውናሉ፡፡ ዳግም ከመወለዳችን በፊት ጽድቅ እንደሌለን ማወቅ አለብን፡፡
 
ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ያምጻሉ፡፡ አንዱ ቅዱስ፣ መልካምና መሃሪ ነኝ በሚል ማስመሰል ሌላውን እግዚአብሄርንም ሳይቀር ያጭበረብራል፡፡ መልካም መስሎ መታየት ለእነርሱ እግዚአብሄርን መገዳደር ነው፡፡ መልካም እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ዳግም ሳይወለዱና በእርሱ ፍቅርና ጽድቅ ሳያምኑ መልካም መስሎ መታየት እግዚአብሄርን መቃወምና በእርሱ እውነት ላይ ማመጽ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር የሚፈርድባቸው ያመረሩ ሐጢያተኞችን ብቻ ይመስላችኋልን? ዳግም ያልተወለደ ሰው ክርስቲያን ቢሆንም እንኳን ከእግዚአብሄር ቁጣ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ስለዚህ ግብዝነት የተሞላበትን የሕይወት መንገድ ትታችሁ የእግዚአብሄርን ቃል ስሙ፡፡ ዳግም ተወለዱ፡፡ ያን ጊዜ ከእግዚአብሄር ቁጣ ማምለጥ ትችላላችሁ፡፡
 
ዳግም ባልተወለዱት መካከል መልካም ለመሆን በምኞት የተሞላ ክፉ ሰው አይታችሁ ታውቃችሁን? ሰዎች መልካም በመሆን ምኞት የተሞሉ ናቸው፡፡ ይህንን ማን አስተማራቸው? ሰይጣን አስተማራቸው፡፡ ሰው ከመነሻው በፍጹም መልካም መሆን አይችልም፡፡ ሰው መልካም ሕይወትን መኖር የሚችለው ሐጢያቶቹ በሙሉ ሲደመሰሱለት ነው፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ሆነ ብለን ክፉን እንድናደርግ ይነግረናልን? አይነግረንም፡፡ እግዚአብሄር የሚነግረን የሐጢያቶችን ስርየት እንድንቀበል ነው፡፡ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ከመወለዳችን በፊት በሐጢያት የተበከልንና ሲዖል ለመውረድ የታጨን ነንና፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንም እንድን ዘንድ የእርሱን እውነተኛ ቃል እንድንቀበል ይፈልጋል፡፡
 
 
ሰይጣን በማያምኑ ሰዎች በኩል ሁልጊዜም ውሸትን ይናገራል፡፡
 
‹‹ጉሮሮአቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፡፡ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፡፡ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፡፡ አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፡፡ እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፡፡ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፡፡ የሰላምንም መንገድ አያውቁም፡፡ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሄርን መፍራት የለም፡፡›› (ሮሜ 3፡13-18)
 
‹‹በመላሳቸውም ሸንግለዋል፡፡›› ሰዎች ሁሉ በመሸንገል የተካኑ ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ስለ ሰይጣን እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፡፡›› (ዮሐንስ 8፡44) ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ሁሉ ‹‹እኔ እውነትን እናገራለሁ፡፡ ይህ እውነት ነው›› ይላሉ፡፡ አባባላቸው ግን በሙሉ ውሸት ነው፡፡
 
አባባሎቻቸው ትክክል እንደሆኑ አበክረው የሚናገሩ ሰዎች ውሸታሞች ናቸው፡፡ አጭበርባሪዎች ሌሎችን ለማጭበርበር ሲሞክሩ ‹‹እኔ ውሸታምና አጭበርባሪ ነኝ›› ሲሉ አይታችሁ ታውቃላችሁን? የሚናገሩት ሁሉ እውነት እንደሆነ አድርገው ይናገራሉ፡፡ በሚያሳምን መልኩ ‹‹አንድ ነገር ልንገርህ፡፡ ገንዘብህን በዚህ ላይ ብታፈስስ ብዙ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ፡፡ አንድ ሚሊዮን ዶላር ብታፈስስ ከዋናህ በላይ ማግኘት ትችላለህ፡፡ በሁለት ዓመታት ውስጥም አስር ሚሊዮን ዶላር ትሰበስባለህ፡፡ ይህ እጹብ ድንቅ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ገንዘብህን መጠቀም ትፈልጋለህን?›› ይላሉ፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ሁልጊዜም በመላሳቸው ይሸነግላሉ፡፡
 
ሰይጣን ውሸትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፡፡ ዳግም ያልተወለደ ሰባኪ ሁልጊዜም ውሸትን ይናገራል፡፡ ሰው ከፍተኛ መጠን ያለው አስራት ቢሰጥ ባለጠጋ ሊሆን ይችላል የሚል ምንባብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለን? ሰዎች ሽማግሌዎች ለመሆን የሚሞክሩት ለምንድነው? እነርሱ ሽማግሌዎች ለመሆን የሚሞክሩት እግዚአብሄር ምድራዊ በረከቶችን እንደሚሰጣቸው እንዲያምኑ ስለተነዱ ነው፡፡ ሽማግሌዎች ቢሆኑ የብልጥግና ጸጋ ሊኖራቸው እንደሚችል ስለሚያምኑ ተታልለዋል፡፡ በሽንገላ ወጥመድ ተይዘዋል፡፡
 
እንዲህ ባለ ውሸት ተሸንግላችሁ ሽማግሌ ሆናችሁ ታውቃላችሁን? ብዙ ሰዎች ሽማግሌዎች ከሆኑ በኋላ እንደ ለማኞች ኖረዋል፡፡ በዙሪያ ያሉትን ብዙዎቹን አውቃለሁ፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ሐሰተኛ ነቢያቶች ሐብታሞችን የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች አድርገው ይሾማሉ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ሽማግሌዎቹ ለቤተክርስቲያኖቻቸው ከፍተኛ መዋጮዎችን እንዲያደርጉ ይፈልጋሉና፡፡ አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ የሌላቸውን ሰዎች ሽማግሌዎች አድርገው ይሾማሉ፡፡ ምክንያቱም እውር ተከታዮቻቸው እንዲሆኑ ይፈልጋሉና፡፡
 
‹‹ሰው ሽማግሌ ከሆነ በሐብት ይባረካል›› የሚለው የተለመደ አባባል ውሸት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ የሚል ነገር የለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄር ባሮች የብልጥግና ጸጋ ሳይሆን ስደት እንደሚገጥማቸው ይናገራል፡፡ ጌታ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡›› (ማቴዎስ 6፡33)
 
መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ›› ይላል፡፡ ሰዎች በእርግጥም የእባብ መርዝ አለባቸው፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ሰዎች ለጻድቁ ምን ይሉታል? ጻድቁን ይረግሙታል፡፡ ልክ እንደ እባብም ይናገሩታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፡፡ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፡፡ የሰላምንም መንገድ አያውቁም፡፡ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሄርን መፍራት የለም፡፡››
 
 
የሕጉ ዓላማ ምንድነው?
 
‹‹እንደ ተጻፈ›› የሚለው ምንባብ ጥቅሱ የተወሰደው ከብሉይ ኪዳን መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ብሉይ ኪዳንን ብዙ ጊዜ ጠቀሶታል፡፡ እርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፡፡ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው ይገኛል፡፡ የሰላምንም መንገድ አያውቁም፡፡ በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሄርን መፍራት የለም፡፡›› ዳግም የመወለድን መንገድ ሳያውቁ ወደ ሲዖል ለሚወርዱ ሰዎች አዝናለሁ፡፡
 
ሮሜ 3፡19 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሄር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፡፡›› እግዚአብሄር በሕጉ መሰረት ቁጣውን ይገልጣል፡፡ ጳውሎስ ‹‹ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን›› ያለበት ምክንያት እግዚአብሄርን ሕግን የሰጠው ዳግም ላልተወለዱ፣ ሐጢያትን ለማያውቁ፣ ሐጢያትን ሐጢያት እንደሆነ ለማይቆጥሩ ሰዎችና በሕይወታቸውም ሕግን ፈጸሞ ጠብቀው የማያውቁ ሐጢያተኞችን ለማሳወቅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሕግን የሰጠን እንድንጠብቀው አይደለም፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር ሕጉን እንደሻረው ተናግሮዋልን? አልተናገረም፡፡ እርሱ በሙሴ በኩል ሕጉን የሰጠን ሐጢያቶቻችንን እንድናውቅ ነው፡፡ ሕጉን የሰጠን እንድንጠብቀው አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ሕግ ሚና ምንኛ ሐጢያተኞች እንደሆንን ያስተምረናል፡፡
 
 
በሕግ ሥራዎች ማንም ሊጸድቅ አይችልም፡፡
 
ሮሜ 3፡20 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፡፡ ሐጢያት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› ዳግም የተወለዱ ክርስቲያኖች ሥጋ የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራዎች እንደማይጸድቅ ያውቃሉ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስና የእግዚአብሄር ባሮች በሙሉ ‹‹የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ አይጸድቅም›› ይላሉ፡፡ ሕግን የሚጠብቅ ሰው የለም፡፡ ወደፊትም የሚጠብቅ ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የሕግን ሥራዎች በመስራት ፈጽሞ መጽደቅ እንደማንችል መናዘዝ አለብን፡፡ ምግባሮቻችን ጻድቃን ሊያደርጉን አይችሉም፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን አውቆ አምኖበታል፡፡ ሕግን በመጠበቅ መጽደቅ እንችላለንን? ሕጉ ሊያጸድቀን ይችላልን? ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ በኢየሱስ ካመንን በኋላ ሥጋችን መልካም ሥራዎችን በመስራት ለጽድቅ ተለውጦ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ብሎ ማመን ትክክል ነው ብላችሁ ታስባላችሁን? ይህ እውነት አይደለም፡፡ ውሸት ነው፡፡ ሰው ቀስ በቀስ ወደ መጽደቅ እየተለወጠ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት ውሸት ነው፡፡ ምክንያቱም በምግባሮቻቸው የእግዚአብሄርን ቃል መጠበቅ እንደሚገባቸው ያስባሉና፡፡ ይህም ሕጉን ለመጠበቅ እንዲሞክሩና በየቀኑም ይቅርታን ለማግኘት እንዲጸልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የመጀመሪያውን ቁልፍ ትክክለኛ ቦታ ላይ ባለመትከላቸው ነው፡፡ ሕጉ ሐጢያተኞች መሆናችንን ያሳውቀናል፡፡ ሐጢያተኞች ሕጉን ለመጠበቅ ጥረቶችን የሚያደርጉት ከድንቁርናቸው፣ ከደህንነት እውነት ጋር ከማይጣጣሙትና ከሥጋ ከመነጩት አስተሳሰቦቻቸው የተነሳ ነው፡፡ ይህ ቦታውን የሳተ እምነት ነው፡፡
 
በሒደት እንጸድቃለን የሚለው የቅድስና ትምህርት በዓለም ላይ በሚገኙ ሌሎች አለማዊ ሃይማኖቶች ውስጥም ይገኛል፡፡ የቡድሃ ሃይማኖትም ልክ እንደ ክርስትናው በሒደት የመቀደስ ትምህርት ሁሉ ተመሳሳይ የሆነ ኒርቫና የሚል ትምህርት አለው፡፡ ብዙ ሰዎች ሥጋቸው በይበልጥ ሊቀደስ እንደሚችልና ውሎ አድሮም መንግሥተ ሰማይ ሊገቡ እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ እውነቱ ግን ጌታ መንፈሳችንን ለአንዴና ለመጨረሻ የቀደሰው መሆኑ ነው፡፡
 
ጻድቃን የሆኑ ሰዎችም ቢሆኑ በሥጋ ሊቀደሱ አይችሉም፡፡ መንፈስ የሌላቸው ሰዎችም ሊቀደሱ አይችሉም፡፡ መልካም ምግባሮችን ለማድረግ አብዝተው በሞከሩ መጠን ይበልጥ ያመረሩ ሐጢያተኞች ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም በልቦቻቸው ውስጥ ሐጢያት አለና፡፡ ውስጣቸው በሐጢያት የተሞላ ስለሆነ ከውጭ ራሳቸውን ለማንጻት ምንም ያህል በርትተው ቢሞክሩም ከውስጣቸው ቆሻሻ የሆነ ነገር ይወጣና ያቆሽሻቸዋል፡፡ የሐጢያተኛ እውነተኛ ኑሮ ይህ ነው፡፡
 
ይህ ሁኔታ የሐጢያቶችን ስርየት ካገኙት ጋር የሚቃረን ነው፡፡ እነርሱ በሥጋቸው ሐጢያት ከመስራት ባይቆጠቡም ንጹህ ሕይወትን ይኖራሉ፡፡ በሐጢያት ተበክለው የተወለዱ ሐጢያተኞች ሐጢያትን በመላው ሕይወታቸው ላይ ያሰራጫሉ፡፡ ምክንያቱም ሐጢያት ያለ እነርሱ ፈቃድ ከውስጣቸው ይወጣልና፡፡ እነርሱ ሐጢያቶቻቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ሊያስወግድላቸው የሚችል የፈውስ ክትባት ከማግኘት በቀር ምርጫ የላቸውም፡፡ ክትባቱም የእግዚአብሄር እውነት ወንጌል ነው፡፡ የሐጢያቶችን ስርየት የሚሰጠው ቃል በመስማት ከሐጢያቶቻቸው መዳን ይችላሉ፡፡ ዳግም የመወለጃውን ቃል በማድመጥ የሐጢያቶችን ስርየት እንድትቀበሉ እፈልጋለሁ፡፡
 
ሙሉ በሙሉ በሕግ መኖር የሚችል ማነው? ዳግም ቢወለድም ፈጽሞ በሕጉ መኖር የሚችል ማነው? ማንም የለም፡፡ በሮሜ እንዲህ ተጽፎዋል፡- ‹‹ሐጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡›› ይህ በጣም ቀላል ነው፡፡ አዳምና ሄዋን በንጽህናው ዘመን በሰይጣን ተታልለው ለሐጢያት ተሸጡ፡፡ ሐጢያትም የእግዚአብሄርን ቃል ወደማያውቁት ዘሮቻቸው ተላለፈ፡፡ ሐጢያትን ቢወርሱም ሐጢያተኞች ሆነው እንደተወለዱ አላወቁም፡፡
 
ከአብርሃምና ከያዕቆብ ዘመን በኋላ አባታቸው አብርሃም በእምነት ቢጸድቅም እስራኤሎች እምነትንና የሐጢያት ኑሮዋቸውን ረሱ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻቸውን እንዲያውቁ ሕግን ሰጣቸው፡፡ በተስፋው በማመንም የሐጢያቶችን ስርየት እንዲቀበሉ ፈለገ፡፡ ይህንን ታምናላችሁን?
 
 
አሁን ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦዋል፡፡
 
ሮሜ 3፡21 እንዲህ የላል፡- ‹‹አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሄር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፡፡›› ሐዋርያው ጳውሎስ የእግዚአብሄር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦዋል ይላል፡፡ ‹‹በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት›› የሚሉት ቃሎች ብሉይ ኪዳንን ይጠቁማሉ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመስዋዕት ስርዓቱ ውስጥ የተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ወንጌሉ በሐጢያት መስዋዕት አማካይነት የሐጢያቶችን ስርየት ወደ መቀበል የሚመራንን ጽድቅ ይገልጣል፡፡
 
ሮሜ 3፡22 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ልዩነት የለምና፡፡›› እምነታችን ልባችን ውስጥ ነው፡፡ የእምነት ጀማሪና ፈጻሚ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ዕብራውያን 12፡2 እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእምነታችንን ጀማሪ ፈጻሚ ተመልክተን፡፡›› የእምነት ጀማሪና ፈጻሚ ኢየሱስ ነው፡፡ እኛም በእውነተኛው ቃል ማለትም በእግዚአብሄር እናምናለን፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ለመዳንና በእምነት ለመኖር ዳግም ከተወለዱ አገልጋዮች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛ ቃሎች መማርና ማመን አለብን፡፡ በልባችን በኢየሱስ ማመን አለብን፡፡
 
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ልዩነት የለምና፡፡›› ስለዚህ እውነተኛውን ቃል በልባችን በማመንና ፍጹም የሆነ የደህንነት ማረጋገጫም እንዳለን በአፋችን በመመስከር ጸድቀናል፡፡ በእምነት እንጂ በራሳችን ምግባሮች መዳን አንችልም፡፡ ምስጋናን የምንሰጠው ለእግዚአብሄርና ለአምላክ ቤተክርስቲያን ብቻ ነው፡፡
 
ሐጢያቶቻችሁ በሙሉ ተደምስሰው ሳሉ በምግባሮቻችሁ ታስራችሁ ታውቃላችሁን? እግዚአብሄርን በልባችሁ የምታምኑ ከሆነ ሥጋችሁ ደካማ ቢሆንም ጻድቃን ናችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ‹‹ጻድቃን ናችሁ›› በማለት በልባችሁ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሄር ቃል ይመሰክራል፡፡ ምክንያቱም ቃሉን በምንሰማበት ጊዜ እውነተኛውን ቃል እንድናስተውል ይመራናልና፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ከሰማችሁ በኋላ በእምነት ድናችኋልን?
 
‹‹እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሄር ጽድቅ ነው፡፡ ልዩነት የለምና፡፡›› እውነት የሆነውን የእግዚአብሄር ቃል የተማረና ያመነ ሰው ሁሉ ከሐጢያቶቹ ሁሉ መዳን ይችላል፡፡
 
 
ኢየሱስ ከዓለም ጅማሬ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያሉትን ሐጢያቶች በሙሉ አንጽቶዋል፡፡
 
ሮሜ 3፡23-25 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሁሉ ሐጢአትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡ እርሱንም እግዚአብሄር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሰርያ አድርጎ አቆመው፡፡ ይህም በፊት የተደረገውን ሐጢያት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡››
 
መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ሐጢያትን እንደሰሩና የእግዚአብሄርም ክብር እንደጎደላቸው ይናገራል፡፡ ሐጢያተኞች ወደ ሲዖል ሲወርዱ እኛ ግን በእርሱ ጸጋና ፍቅር የሐጢያቶች ይቅርታ አግኝተን በነጻ ጸድቀናል፡፡ ወደ እግዚአብሄር ክብር ደርሰን ጸድቀናል፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሰርያ አድርጎ አቆመው፡፡
 
ቁጥር 25 እና 26 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እርሱንም እግዚአብሄር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተሰርያ አድርጎ አቆመው፡፡ ይህም በፊት የተደረገውን ሐጢያት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡›› እዚህ ላይ ‹‹አቆመው›› የሚለው ቃል እግዚአብሄር ለመላው ዓለም የሐጢያቶች ስርየት ይሆን ዘንድ ልጁን ኢየሱስን ማስተሰርያ አደረገው ማለት ነው፡፡
 
ኢየሱስ በጥምቀቱ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ ኢየሱስ አልፋ ዖሜጋ ነው፡፡ እስቲ ስለ ዓለም መጀመሪያና መጨረሻ እናስብ፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን ባነጻው እምነት ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ካሉት ሐጢያቶቻችን አድኖናል፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስን እውነትን በማመን የሚገኝ ማስተሰርያ አድርጎ አቆመው፡፡ ‹‹ይህም በፊት የተደረገውን ሐጢያት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው›› የሚሉትን ቃሎች የተረዳሁት በወንጌል ካመንሁ በኋላ ነበር፡፡
 
ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ እንዳነጻ በሚናገረው ቃል ስናምን ሐጢያቶቻችን በሙሉ ይወገዳሉ፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻም የሐጢያቶችን ስርየት አግኝተናል፡፡ ሥጋችን ግን አሁንም ሐጢያት መስራቱን ቀጥሎዋል፡፡ ሥጋ ከድካሞቻችን የተነሳ ሐጢያት ይሰራል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄር በፉት የተደረገውን ሐጢአት ትቶታል፡፡›› ሥጋ አሁንና ወደፊት የሚሰራቸው ሐጢያቶች እንኳን ከእግዚአብሄር እይታ አንጻር በፊት የተደረጉ ናቸው፡፡
 
ለምን? እግዚአብሄር የኢየሱስን ጥምቀት የደህንነታችን መሰረታዊ መነሻ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ አሁን በእግዚአብሄር ምልከታ ያለፉ ሐጢያቶች ናቸው፡፡ ምክንያቱም የሐጢያቶች ስርየት ለአንዴና ለመጨረሻ በኢየሱስ ተከናውነዋልና፡፡ የአሁኖቹ ሐጢያቶች ቀድሞውኑም ተደምስሰዋል፡፡ ‹‹እግዚአብሄር በፊት የተደረጉትን ሐጢያቶች ትቶዋቸዋል›› የሚሉት ቃሎች ‹‹እርሱ አስቀድሞ የዓለምን የሐጢያቶች ደመወዝ ከፍሎዋል›› ማለት ናቸው፡፡ የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድሞ በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል ይቅር ተብለዋል፡፡
 
ስለዚህ እግዚአብሄር ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተሰሩትን ሐጢያቶች በሙሉ አስቀድሞ ደምስሶዋቸዋል፡፡ ስለዚህ ሐጢያቶች በሙሉ በእግዚአብሄር እይታ በፊት የተደረጉ ናቸው፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች በፊቱንም በእግዚአብሄር ልጅ የተደመሰሱ ሐጢያቶችን ይሰራሉ፡፡ ኢየሱስ በ2002 አ.ም የሚሰሩትን ሐጢያቶች ከ2,000 ዓመታት በፊት አስቀድሞ አስወግዶዋቸዋል፡፡ ይህንን ተረድታችሁታልን?
 
እግዚአብሄር የእናንተንና የእኔን ጨምሮ የዓለምን ሐጢያቶች አስቀድሞ አስወግዶዋል፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አያችሁን? ካልገባችሁ ወንጌልን ለሌሎች ሰዎች በምትሰብኩበት ጊዜ ግራ ልትጋቡ ትችላላችሁ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር በፊት የተደረጉትን ሐጢያቶች ትቶዋቸዋል›› የሚሉት ቃሎች እግዚአብሄር ቀድሞውኑም ከ2,000 ዓመታት በፊት ስላስወገዳቸው ሐጢያቶችን ሁሉ ረስቶዋቸዋል ማለት ናቸው፡፡ ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ስለተጠመቀና ስለተሰቀለ የሰዎች ሁሉ ሐጢያቶች ቀድሞውኑም ተፈርዶባቸዋል፡፡ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጥቶ ሰዎችን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ፈጽሞ ስላጸደቃቸው እግዚአብሄር ሐጢያቶችን ሁሉ ትቶዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች በሰሩዋቸውና እርሱ በደመሰሳቸው ሐጢያቶች ላይ ክስ አያቀርብም፡፡ እርሱ ፍርድን የሚሰጠው ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል ባለማመናቸው ነው፡፡
 
ሐዋርያው ጳውሎስ ምን ማለቱ ነው እንደሆነ ገብቶዋችኋልን? ይህ ለእኛ መዳንን ላገኘነው ሰዎች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ዳግም ያልተወለዱ ይህንን ቸል በማለታቸው ወደ ሲዖል ይወርዳሉ፡፡ ቃሉን መስማትና በትክክል ማወቅ አለብን፡፡ ይህ ለራሳችሁ እምነትና ወንጌልን ለሌሎች በምትሰብኩበት ጊዜ ይጠቅማችኋል፡፡
 
 
ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው?
 
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህም በፊት የተደረገውን ሐጢአት በእግዚአብሄር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡›› እግዚአብሄር በፊት የተሰሩት ሐጢያቶች ቀድሞውኑም እንደተደመሰሱ ያስተምረናል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር ኢየሱስን ማስተሰርያ አድርጎ አቁሞታልና፡፡ ስለዚህ በእምነት ጸድቀናል፡፡
 
ቁጥር 26 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡›› ‹‹አሁን በዚህ ዘመን›› ዓለም እንዳይጠፋ እግዚአብሄር ለዓለም የዘላለምን ሕይወት ሰጠ፡፡ አሁን በዚህ ዘመን እግዚአብሄር ጽድቁን ያሳይና ቃል የገባውን ይፈጽም ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው፡፡ እግዚአብሄር ጽድቁን አሳየ፡፡ እግዚአብሄር በሚያድነው እውነት አማካይነት ፍቅሩን ሊያሳየን አንድያ ልጁን ልኮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል ፈቀደ፡፡
 
ጌታ አዳኛቸው ሆኖ ወደ ሐጢያተኞች መጣ፡፡ ‹‹ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፡፡›› እግዚአብሄር ጻድቅ ነው፡፡ የዓለምንም ሐጢያት ለአንዴና ለመጨረሻ አስወግዶዋል፡፡ በልባችን በኢየሱስ ስላመንን ሐጢያት የለብንም፡፡ ኢየሱስን በእውነት የሚያምኑ ሰዎች ሐጢያት የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም እርሱ አንጽቶዋቸዋልና፡፡ ወደፊት ከሚሰሩዋቸው ሐጢያቶችም ሳይቀር አድኖዋቸዋል፡፡ የሚያድነን ኢየሱስ ያደረገውን በልባችን ማመናችን ነው፡፡ በእርሱ ደህንነት ላይ ባለን እምነት ውስጥ ምግባሮቻችን 0.1% እንኳን ቦታ የላቸውም፡፡
 
ሮሜ 3፡27-31 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል፡፡ በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፡፡ በእምነት ሕግ ነው እንጂ፡፡ ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና፡፡ ወይስ እግዚአብሄር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸደቅ አምላክ አንድ ስለሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው፡፡ እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ፡፡››
 
‹‹ሕግን እናጸናለን›› የሚሉት ቃሎች በምግባሮቻችን መዳን እንደማንችል የሚያሳዩ ናቸው፡፡ እኛ እንከን ያለብንና ደካሞች ስለሆንን በሕጉ ፊት ወደ ሲዖል መውረድ ነበረብን፡፡ ነገር ግን በቃሉ ስላዳነን የእግዚአብሄር ቃል አጸደቀን፡፡ ፍጹማንም አደረገን፡፡ ጌታ ከሐጢያቶቻችን ከዳንን በኋላ እንኳን ሥጋችን አሁንም ድረስ እንከን እንዳለበት ይናገራል፡፡ ወደ እግዚአብሄር መቅረብ የምንችለው ኢየሱስ እዳዳነን በማመን ነው፡፡
 
‹‹ትምክህት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል፡፡ በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፡፡ በእምነት ሕግ ነው እንጂ፡፡›› እግዚአብሄር ያጸናውን ሕግና ሕጉም በመንግሥቱ ውስጥ ዘላለማዊ እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ እግዚአብሄር ‹‹በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፡፡ በእምነት ሕግ ነው እንጂ›› ይላል፡፡ ይህንን አስተዋላችሁትን? እግዚአብሄር ከዓለም ሐጢያቶች በሙሉ አድኖናል፡፡ በእውነት ላይ ተመርኩዘን ስናምን እንድናለን፡፡ የሕግ ሥራዎች ሊያድኑን እንደማይችሉ ማስታወስ ይኖርብናል፡፡
 
እግዚአብሄር በሐዋርያው ጳውሎስ በኩል በሮሜ ምዕራፍ 3 ላይ ስለ እምነት ሕግ ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- ‹‹የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሄርን ታማኝነት ያስቀራልን?›› (ሮሜ 3፡3) አማኞች በእምነት ጸንተው ይቆማሉ፡፡ የማያምኑ ሰዎች ግን ይወድቃሉ፡፡ የእውነትን ወንጌል ሙሉ በሙሉ የማያምኑ ሰዎች በኢየሱስ እንደሚያምኑ ቢያስቡም ሲዖል ይወርዳሉ፡፡
 
 
እግዚአብሄር ሁላችንንም ከሐጢያቶቻችን ፈጽሞ አድኖናል፡፡
 
እግዚአብሄር ሕጉን ያጸናው በራሳቸው አስተሳሰቦች ላይ ተመርኩዘው የሚያምኑ ሰዎች በእምነት ሕግ እንዲደናቀፉ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁላችንንም ፈጽሞ ከሐጢያቶቻችን አድኖናል፡፡ ሮሜ ምዕራፍ 3 ስለ እምነት ሕግ ይናገራል፡፡ በእውነተኛው ቃል በማመን ድነናል፡፡ መንግሥተ ሰማይንም በእምነት እንወርሳለን፡፡ ሰላምም ይሆንልናል፡፡ የማያምኑ ሰዎች ሰላም ሊኖራቸው አይችልም፡፡ በፋንታው ሲዖል ይወርዳሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? በመጀመሪያ የእግዚአብሄርን እውነት ቃል ስላልተቀበሉ በእግዚአብሄር የእውነት ሕግ መሰረት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ደህንነት የሚመጣው ከእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ የዳንነው እውነትን በማወቅና ጌታ ያደረገውን በልቦቻችን በማመን ነው፡፡
 
ይህንን እምነትና በምድር ላይ ያለችውን ቤተክርስቲያኑን የሰጠንን ጌታ አመሰግናለሁ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ የነበረውን አይነት እውነት፣ እምነትና ቃል ስለሰጠንና የሐጢያቶች ስርየት ምስጢርን ለቤተክርስቲያኑ ስለገለጠላት ጌታን አመሰግናለሁ፡፡ ከውስጥ ከልቤ አመሰግነዋለሁ፡፡
 
በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ ስላዳነን ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ይህ እምነትና የእርሱ ቤተክርስቲያን ባይኖሩ ኖሮ ወደ ሲዖል ከመውረድ በቀር ምርጫ አይኖረንም ነበር፡፡ በተፈጥሮዋችን ፈጽሞ መዳን የማንችል ሐጢያተኞች ነበርን፡፡ ነገር ግን በልባችን አምነን ጸደቅን፡፡ በልባችን አምነን የጸደቅን በአፋችንም መስክረን የዳንን የእርሱ ልጆች ሆነናል፡፤ (ሮሜ 10፡10)