Search

শিক্ষা

ርዕስ 11፡ የመገናኛው ድንኳን

[11-24] ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት የብር እግሮች መንፈሳዊ ትርጉም፡፡ ‹‹ዘጸዓት 26፡15-30››

ለመገናኛው ድንኳን ጥቅም ላይ የዋሉት የብር እግሮች መንፈሳዊ ትርጉም፡፡
‹‹ዘጸዓት 26፡15-30›› 
‹‹ለማደርያውም የሚቆሙትን ሳንቆች ከግራር እንጨት አድርግ፡፡ የሳንቃው ሁሉ ርዝመቱ አሥር ክንድ ወርዱም አንድ ተኩል ይሁን፡፡ ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለማደርያው ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አድርግ፡፡ ለማደርያውም በደቡብ ወገን ሀያ ሳንቆችን አድርግ፡፡ ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ፡፡ ለማደርያውም ለሁለተኛው ወገን በሰሜን በኩል ሀያ ሳንቆች፤ ለእነርሱም አርባ የብር እግሮች ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሁኑ፡፡ ለማደርያውም በምዕራቡ ወገን በስተኋላ ስድስት ሳንቆችን አድርግ፡፡ ለማደርያውም ለሁለቱ ማዕዘን በስተኋላ ሁለት ሳንቆችን አድርግ፡፡ ከታችም እስከ ላይ እስከ አንደኛው ቀለበት ድረስ አንዱ ሳንቃ ድርብ ይሁን፤ እንዲሁም ለሁለቱ ይሁን፤ እነርሱም ለሁለቱ ማዕዘን ይሆናሉ፡፡ ስምንት ሳንቆችና አሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፤ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ፡፡ ከግራርም እንጨት በማደርያው በአንድ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች፤ በማደርያውም በሁለተኛው ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወርያዎች፤ በማደርያውም በስተኋላ በምዕራብ ወገን ላሉት ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎች አድርግ፡፡ መካከለኛው መወርወሪያ በሳንቆች መካከል ከዳር እስከ ዳር ይለፍ፡፡ ሳንቆቹንም በወርቅ ለብጣቸው፡፡ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ ሥራቸው፤ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለብጣቸው፡፡ ማደርያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም፡፡›› 


እግዚአብሄር የሚያድርበት የመገናኛው ድንኳን ሳንቆች በሙሉ በወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር የመገናኛው ድንኳን እያንዳንዱ ሳንቃ ቀጥ ብሎ እንዲቆም ሙሴን ሁለት የብር እግሮች እንዲሠራ አዘዘው፡፡ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ሁለት የብር እግሮችን የማቆሙ መንፈሳዊ ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወርቅ የሚያመለክተው በጊዜ ሒደት የማይቀየረውን እምነት ነው፡፡ እነዚህ የብር እግሮች በዚህ ወርቅ ከተለበጡት ሳንቆች በታች የመደረጋቸው ትርጉም እግዚአብሄር ለደህንነታችን ዋስትና ይሆኑ ዘንድ ሁለት ስጦታዎችን የሰጠን መሆኑ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ በመጠመቅና ደሙን በማፍሰስ ከሐጢያት መዳናችንን ፈጽሞታል ማለት ነው፡፡ 
የእግዚአብሄር ሕዝብና የመንግሥቱ አባል እንድንሆን የሚያስችለንን ይህንን እንደ ንጹህ ወርቅ የሆነውን እምነት እንቀበል ዘንድ ፈጽሞ አስፈላጊ ያደረገው ነገር በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ደሙ የሚያምነው እምነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመደምሰስ የሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለእኛ እጅግ የሚያስፈለገን የእምነት ስጦታ ነው፡፡ እኛ በየቀኑ ሐጢያት ስለምንሠራና ለሲዖል የታጨን ስለሆንን በራሳችን ጥረቶች፣ ጉልበት ወይም ፈቃድ ሐጢያቶቻችንን ማስወገድ አንችልም፡፡
እኛ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመደምሰስ በራሳችን ብርታት በመደገፍ ፋንታ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ብቻ ማመን አለብን፡፡ ከሐጢያቶቻችን መዳን የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ጌታ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት የደህንነትን ስጦታ እንደሰጠን በምስጋና ማመናችን ተገቢ ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ የወንጌል ክፍሎች በተዘጋጀው የደህንነት ስጦታ ስናምን እግዚአብሄር ይህንን እምነታችንን አይቶ የእርሱ ፍጹማን ሕዝቦች ያደርገናል፡፡ ስለዚህ አሁንም ድረስ በልባችሁ ውስጥ አንዳች ሐጢያት ካለባችሁ እግዚአብሄር እኛን ለማዳን ስጦታው አድርጎ በሰጠን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሙሉ ሙሉ መዳን ይኖርባችኋል፡፡
በዚህ ዓለም ላይ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሄር ሕዝብ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝብ ለመሆን በቅድሚያ የእግዚአብሄርን ቃል ብርሃን በራሳችን ላይ በማብራት በዚያ መሠረት ራሳችን መመርመር ይገባናል፡፡ ያን ጊዜ ለሐጢያቶቻችን የምንኮነን ብንሆንም ሁላችንም የምንቃወመው ምንም ነገር የሌለን ሐጢያተኞች መሆናችንን እንገዘነባለን፡፡ እኛ ሁልጊዜም በእግዚአብሄር ሕግ ላይ ሐጢያት እንሠራለን፡፡ እውነተኛው ማንነታችን ይህ ስለሆነ ፍርዳችንን እየጠበቅን በዓመጽና በሐጢያት የሞላውን ሕይወታችንን ከመኖር በቀር ምርጫ የለንም፡፡ የእግዚአብሄር ሕዝብ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? እኛ የእርሱ ሕዝብ እንሆን ዘንድ እግዚአብሄር የሰጠንን ሁለቱን የደህንነት ስጦታዎች መቀበል እንደሚያስፈልገን ወደ መረዳት መጥተናል፡፡
ለእኛ ጌታ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ የደመሰሰ አዳኝ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድነውናል፡፡ እነዚህ ሁለት ፍሬ ነገሮች ለደህንነታችን አስፈላጊ ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ እውነት ሳያምን ማንም የእግዚአብሄር ሕዝብ ሊሆን አይችልም፡፡
እግዚአብሄር በሰጠን በእነዚህ በሁለቱ የደህንነት ስጦታዎች አማካይነት በተክክል የእርሱ ሕዝብ መሆን እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄር ለጆች መሆናችን ከበጎ ምግባሮቻችን ጋር የሚያያይዘው ምንም ነገር የለም፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሁሉና ከሐጢያት ኩነኔያችን ሁሉ መዳናችንና ነጻ መውጣታችን ሙሉ በሙሉ የተቻለው በኢየሱስ ጥምቀትና ባፈሰሰው ደሙ አማካይነት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የእግዚአብሄር ልጆች የሆንነው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ነው፡፡ እንደ ንጹህ ወርቅ የሆነው እምነታችን የተገነባው እነዚህን የእግዚአብሄር ስጦታዎች በመቀበል ላይ ነው፡፡
የመገናኛው ድንኳን ሲሠራ እግዚአብሄር ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ሁለት የብር እግሮችን አደረገ፡፡ ይህ እውነት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በመውሰድ፣ እነዚህን ሐጢያቶች በመስቀል ላይ ተሸክሞ በመሞት የሐጢያት ኩነኔን እንደደተሸከመ ይናገራል፡፡ ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደሙ ትክክለኛ የሐጢያቶች ስርየት ስጦታዎች ናቸው፡
በዚህ ዘመን የምንኖር እናንተና እኔ ሐጢያተኛውን ማንነታችንን ማወቅ አለብን፡፡ ራሳቸውን በእግዚአብሄር ፊት የሚያውቁ ሰዎች ጌታ በትክክል ወደዚህ ምድር መጥቶ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅና በመስቀለ ላይ በመሞት ከሐጢያቶቻቸውና ከኩነኔያቸው ሁሉ እንዳዳናቸው መገንዘብ አለባቸው፡፡ በደህንነት ስጦታ አምነን ልክ እንደዚህ የሐጢያቶቻችንን ስርየት ስንቀበል በፊቱ የእግዚአብሄር ልጆች እንሆናለን፡፡ ከሐጢያት የዳንነው ጌታ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙ ስላዳነን ነው፡፡ እንዲህ ባያደርግ ኖሮ በራሳችንን ጥረት ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ፈጽሞ ከሐጢያት ነጻ ማድረግ አንችልም ነበር፡፡ ስለዚህ እናንተና እኔ የእግዚአብሄር ሕዝብና ጻድቃን የሆንነው 100 በመቶ በእግዚአብሄር ጸጋ እንደሆነ ከማመንና ከመመስከር በቀር ልናደርገው የምንችለው ነገር የለም፡፡
ከመገናኛው ድንኳን ሳንቃዎች በተሠሩት የብር እግሮች የሐጢያቶቻችን ስርየት በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት የተፈጸመ ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሄር ስጦታ ነው፡፡ እኛ ሙሉ በሙሉ በእምነት መዳን የቻልነው እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ የደህንነትን ጸጋ ስለሰጠን ነው፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሄርን የደህንነት ለመቀበል ብቁ የሚሆኑት በመንፈስ ድሆች የሆኑና ስለ ሐጢያቶቻቸው ለሲዖል የታጩ በመሆናቸው ስለ ራሳቸው የሚተክዙ ብቻ ናቸው፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው እውነት እግዚአብሄር አብ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል የሚያምኑ የእግዚአብሄር ልጆች ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ መዳን ይችላሉ፡፡ በእግዚአብሄር በረከቶች ሁሉ መደሰት የሚችሉት በጌታ የተሰጠውን የደህንነት ስጦታ የሚቀበሉ ብቻ ናቸው፡፡ እዚህ ብቃት ላይ መድረስ የሚችሉት ስለ ሐጢያቶቻቸው ለሲዖል የታጩ መሆናቸውን የሚያውቁና የእግዚአብሄርን ምህረት የሚለምኑ ብቻ ናቸው፡፡ ነገሩ በእርግጥም እንደዚህ ነው፡፡
ከሐጢያቶቻችን ሁሉ የዳንነው እግዚአብሄር በሰጠን የደህንነት ስጦታ ነው፡፡ ኤፌሶን 2፡8 ‹‹በጸጋ ድናችኋልና›› የሚለው ለዚህ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች የሆንነውም በዚህ የደህንነት ስጦታ ስላመንን ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ የምንኮራበት ምን ነገር አለን? ኩራታችንን አርቀን ያዳነን እግዚአብሄር እንጂ ራሳችን አለመሆናችንን በመመስከር እግዚአብሄርን ብቻ ማመስገን ይገባናል፡፡
በእውነት ለመናገር እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ባያድነን ኖሮ በጭራሽ ከሐጢያቶቻችን መዳን አንችልም ነበር፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ ውስጥ ያለው እውነት ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ሥልጣን የተሠራ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ተወልዶ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ (ማቴዎስ 3፡13-17) ለአንዴና ለመጨረሻ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የመውሰዱን፣ በመስቀል ላይ የመሞቱንና ዳግመኛም ከሙታን የመነሳቱን የደህነነት እውነትም ይገልጣል፡፡ እግዚአብሄር እኛን ያዳነበት ጸጋ እጅግ ፍጹም ስለሆነ በስጋ ጎዶሎዎችና በሐጢያት የተሞላነውን እኛን በእምነት ፍጹማን በማድረግ የእግዚአብሄር መንግሥት ዓምዶች አድርጎ ሊያቆመንና የመንግሥቱ ሕዝቦች አድርጎ ሊለውጠን ከበቂም በላይ ነው፡፡
 

በኢየሱስ እያመናችሁ አሁንም ድረስ በትክክል ማን እንደሆናችሁ አታውቁምን? 

በዚህ ዘመን በኬብል ወይም በሳተላይት የሚተላለፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህ ጣቢያዎች በቀን ለ24 ሰዓታት ስለሚተላለፉ የራሳቸውን ልዩ መርሃ ግብሮች ይዘው ያለ ማቋረጥ ይተላለፋሉ፡፡ ተመልካቾቻቸውንም ያዝናናሉ፡፡ ከእነዚህ ጣቢያዎች መካከል በንግዱ ዘርፍ እጅግ የተዋጣላቸው ልዩ ጣቢያዎች ከሁሉም በላይ ለጎልማሶች የሚተላለፉ ጣቢያዎች ናቸው፡፡ ጣቢያዎችን በመቀያየር ብቻ ሁሉም ዓይነት ልቅ የሆኑ የወሲብ ድርጊቶች የሚታዩባቸውና ለጎልማሶች የተዘጋጁ ብዙ የዚህ ዓይነት ጣቢያዎች አሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ ብዙዎቹ የዚህ ዘመን ሰዎች እንደዚህ ባሉ ልቅ የወሲብ ድርጊት የሚያሳዩ ፊልሞች ውስጥ ራሳቸውን አስጥመዋል፡፡ ከሁሉ የከፋው ደግሞ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊውን ባህሪያቸውን እንደ ሐጢየቶች አድርገው የማይቆጥሩት መሆኑ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር የሚፈልቁት ዝሙት፣ ምንዝርናና ልቅነት በግልጥ ሐጢያቶች እንደሆኑ ይጠቁማል፡፡ (ማርቆስ 7፡21-23) ታዲያ ሁላችንም በሐጢያት የተሞላን አይደለንምን? እግዚአብሄር ለእኛ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች በሐጢያት የተሞሉ እንደሆኑ፣ የሐጢያት ደመወዝ ሞት እንደሆነና ሐጢያትም ሲያድግ ሞትን እንደሚወልድ በተደጋጋሚ ነግሮናል፡፡ ነገር ግን ይህንን በእርግጠኝነት እናምነዋለን? እንዴት ነው? ዓይኖቻችንን በመጨፈንና ጆሮዎቻችንን በመድፈን ለእኛ ውስብስብ ከሆኑብን የሐጢያት ባህሪዎች ማምለጥ እንችላለን? በአእምሮዋችን እሳቤዎችና አስተሳሰቦች ሁሉንም ዓይነት ሐጢያቶች ከመሥራት በስተቀር ማድረግ የምንችለው ነገር የለም፡፡ እንደዚህ ካሉት ሐጢያቶች መራቅ እንዳለብን ምንም ያህል አብዝተን ለራሳችን ብንናገር፣ ይህንንም ለማድረግ ምንም ያህል ጠንክረን ብንሞክር ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ ስጋችን እንዲህ ያለ በመሆኑ ስጋዊ ሐጢያት የማይሠሩ ፍጹም ቅዱሳን መሆን ጨርሶ አለመቻል ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ከሐጢያት ጋር በተጨባጭ ፍቅር ስለያዘን ከእርሱ የመራቅ ፍላጎቱም የለንም፡፡ የሰው ዘር ስጋና ልብ ሁልጊዜም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች በጣም የራቁ ናቸው፡፡ ከዚህም በላይ እነርሱ ወደ ሐጢያት መቅረብ የሚፈልጉ ከመሆናቸውም በላይ ታላላቅ ሐጢያቶችንም እንኳን መሥራት እንደሚሹ የታወቀ ሐቅ ነው፡፡
እያንዳንዳችን የሐጢያትና የበደሎች ቁስለኞች ነን፡፡ ስለዚህ በመሠረታዊው ተፈጥሮዋችን ተበላሽተናል፡፡ ፍንጥቅ ብለው የሚጠፉት ብልሹነቶቻችን ለረጅም ጊዜ በትዝታዎቻችን ውስጥ ተቀርቅረው ስለቀሩ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉት ቅሪቶች አእምሮዋችንን ይበጠብጡታል፡፡ ይህ የሆነው የእያንዳንዱ ሰው ልብ በመሠረታዊ ተፈጥሮው የሐጢያት ቁስለኛ ስለሆነ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ባህሪዎቻችን የሐጢያት ጥርቅሞች መሆናቸውን በእግዚአብሄር ፊት ማመን አለብን፡፡ በእግዚአበሄር የጽድቅ ፍርድ ለሲዖል የታጨን መሆናችንን ተገንዝበን መዳናችንን ከእርሱ መለመን ጠቢብነት ነው፡፡ ናፖሊዮን ቦናፖርት ‹‹አይቻልም የሚለው ቃል በሞኞች መዝገበ ቃላት ውስጥ ብቻ የሚገኝ ቃል ነው›› አላለምን? ብዙ ክርስቲያኖች በራሳቸው ጥረት ሐጢያት መሥራትን ፈጽመው ማስወገድ የሚችሉ ይመስል በራሳቸው ጽድቅ ለመኩራራት ይሞክራሉ፡፡ ይህ ግን እግዚአብሄርን መገዳደር ነው፡፡ እንዲህ ያለ የዕብሪት እምነት የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለመቀበል እምቢተኞች የሆኑና እርሱ የሰጣቸውንም የደህንነት ፍቅር የናቁ ክፉዎች ያደርጋቸዋል፡፡
ራሳችሁን እንደ መልካም ሰው አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁን? በማናቸውም ሁኔታዎችና በማናቸውም መልክ አንዳች ዓመጸኝነትን ፈጽሞ መታገስ የማይችል ጠንካራ የፍትሃዊነት ስሜት እንዳላችሁ ታስባላችሁን? በየቀኑ የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት በልባችሁ ስለምትጠብቁና በሕይወታችሁ ውስጥም ልትታዘዙዋቸውና ልትተገብሩዋቸው ስለምትሞክሩ በመጠኑም ቢሆን በእግዚአብሄር ጻድቅ እንደሆናችሁ ታስባላችሁን? አንድ ሰው እግዚአብሄር የሰጠውን የደህንነት ስጦታና ጸጋ ባያውቅና ልቡ አሁንም ድረስ በሐጢያት ተሞልቶ እያለ ጻድቅ የሆነ ይመስል ሊንቀባረር ቢሞክር እያደረገ ያለው ነገር በረከሰው የሰብዓዊ ፍጡር ጽድቅ ጻድቅ ለመሆን እያስመሰለ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ሰዎች መልካምነት የእግዚአብሄር ቤት ዓምዶች እንዲሆኑ አያስችላቸውም፡፡ ስለዚህ የማይረቡ ቁስለኞች ናቸው፡፡
በምሥራቅ እስያ አገሮች ብዙዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ የኮንፊሺየስን ትምህርቶች ስለሚማሩ እነዚህን ትምህርቶች በተግባር ለመግለጥ በብዙ ይጥራሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራቡ ዓለም የሐይማኖቱን ሜዳ የተቆጣጠረረው የካቶሊክ ወይም የፕሮቴስታንት ሐይማኖት በመሆኑ ብዙ ምዕራባውያን የእግዚአብሄርን ሕግ ለመጠበቅ ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ምንጫቸው ከየትም ይሁን ከምሥራቅ ይሁን ወይም ከምዕራብ በእግዚአብሄር ፊት ቀርበው እውነተኛው ማንነታቸው ሲገለጥ በኮንፊሺየስ ትምህርቶች መሠረት ለመኖር የሚሞክሩትና በእግዚአብሄር ትዕዛዛቶች መሠረት ለመኖር የሚሹት የሐጢያት ጥርቅሞችና የክፉ አድራጊ ዘሮች ናቸው፡፡ ሰብዓዊ ፍጡራን ዓመጸኞች፣ በእንከኖች የተሞሉና ከአፈርና ከቆሻሻ የተሠሩ የሐጢያት ማከማቻዎች ናቸው፡፡ በጎ ምግባሮቻቸው ለመታወቅ የተደረጉ ሳይሆኑ ከእውነተኛ ልባቸው የፈለቁና ለሠሩዋቸው በጎ ምግባሮች አንዳች ምስጋና መቀበል የማይመቻቸው በጎ ሰዎች የሚመስሉ እንኳን መሠረታዊ ነገራቸው በእግዚአብሄር ፊት ሲታዩ የሐጢያት ማከማቻዎችና የክፉ አድራጊ ዘሮች ከመሆናቸው እውነታ ማምለጥ አይችሉም፡፡ የሰውን ዘር ጽድቅ ማቀንቀን በእግዚአብሄር ፊት ትልቅ ሐጢያት ስለሆነ ሰዎች ቅጣታቸውን ተረድተው የእግዚአብሄር ፍቅር የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እስካልተቀበሉ ድረስ ከሐጢያት ኩነኔ ማምለጥ አይችሉም፡፡ የሰው ዘር ጥረቶች በእግዚአበሄር ፊት ወደ ምንም ዓይነት ቸርነት አይለወጡም፡፡ የአቧራ ያክል እንኳን ዋጋ የላቸውም፡፡ የሰው ዘር ፈቃድ በእርሱ ፊት የረከሰ ነው፡፡ የሰው ዘር መሰረታዊ ተፈጥሮ ከቆሻሻ፣ ከእንጨትና ከናስ የተፈጠረ ነው፡፡ ሰብዓዊ ፍጡራን በቅድሚያ በወርቅ እስካልተለበጡ ድረስ በእግዚአብሄር ቤት ደጃፍ ላይ ሊቆም የማይችል እንጨት ዓይነት ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ከተሠጠው ጸጋ ውጪ የእግዚአብሄርን የእሳት ፍርድ መቋቋም ከማይችለው ናስ የሚበልጡ አይደሉም፡፡ መሲሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በእጆች መጫን አማካይነት በመጠመቁና እስከ ሞት ድረስ ደሙን በማፍሰሱ የደህንነት ስጦታ የማናምን ከሆንን ሐጢያተኞች ሆነን እንቀራለን፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ሰዎች መሆናቸውን የማያውቁና ለመዳንም የእግዚአብሄርን ስጦታ ያልተቀበሉ በእርግጥም ያሳዝናሉ፡፡
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከማወቃችን በፊት የሕይወት መለኪያችን የሰው ዘር ጽድቅ ነበር፡፡ የእግዚአብሄርን የደህንነት ስጦታ ሳላውቅና በቃሉ ሳላምን በፊት እኔም እንደዚያ ነበርሁ፡፡ በእርግጥ የራሴ የሆነ ጽድቅ አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን ራሴን ጨዋ እንደሆንሁ አድርጌ አስብ ነበር፡፡ ስለዚህ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ የፍትህ መጓደልን በመቃወም ከማልችላቸው ሰዎች ጋር እንኳን እጣላ ነበር፡፡ የእኔ መፈክር የጽድቅ ሕይወት መኖር የሚል ነበር፡፡ ምክንያቱም የተወለድሁት አንዴ የምሞተውም አንዴ ነበርና፡፡ አሳቤ ‹‹ከመብላት በስተቀር አንዳች ነገር ሳይሠሩ እንደዚህ ዓይነት የማይረባ ሕይወት ከመኖር መሞት ይሻለኛል፡፡ ሕይወት ማለት ይህ ከሆነ አሁን ብሞት ወይም ሌላ 50 ዓመት ብኖር የሚያመጣው ልዩነት የለም፡፡ እንደዚህ ሆኖ መኖር አሰልቺና አስጠሊታ ነው፡፡ ያለ ትርጉምና ያለ ዓላማ መኖርና በሕይወት ውስጥ ምንም ትልቅ ዓላማ ሳይኖር አንዳች ጽድቅ የሆነ ነገር ማድረግ ሳይችሉ መኖር በራሱ ሲዖል ነው፡፡ ታዲያ ሲዖል ማለት ሌላ ምንድነው? ለሰው እስከሚሞትበት ቀን ድረስ እየበላና ሆዱን እየሞላ ብቻ እንደ አሳማ መኖር የውርደት ሲዖል ነው›› የሚል ነበር፡፡ ስለዚህ ራሴን በእግዚአብሄር ፊት ማየት ስለተሳነኝ በራስ ጽድቅ የተሞላሁ ነበርሁ፡፡ በመሆኑም ከሌሎቹ ይልቅ ስለ ራሴ ጥሩ አስብና በጽድቅ ለመኖርም እጥር ነበር፡፡
ነገር ግን እኔ በእግዚአብሄር ጽድቅ ፊት ከተራ የሐጢያት ማከማቻ የተሻልሁ አልነበርሁም፡፡ እኔ እግዚአብሄር እንዲጠበቁ ካዘዛቸው አስርት ትዕዛዛት ወይም ከ613 ሕጎች አንዱን እንኳን መጠበቅ ያልቻልሁ ሰው ነበርሁ፡፡ እነዚህን ሕጎች የመጠበቅ ፈቃድ ያለኝ የመሆኑ እውነት በራሱ እኔ ከሐጢያት በስተቀር አንዳች ነገር ፈጽሞ ማድረግ የማልችል መሆኔን ‹‹አንተ እግዚአብሄርን በመቃወም ሐጢያት የምትሠራ ሰው ነህ›› ብሎ በሚነግረኝ በእግዚአብሄር ቃልና በራሱ በእግዚአብሄር ላይ የማመጽ የዓመጽ ድርጊት ነበር፡፡ የሰው ዘር ጽድቅ ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ዓመጽ ብቻ ነው፡፡ በልቅነትና በብልሹነት ጎርፍ ውስጥ እግዚአብሄርንና የእርሱን ሕግ ያጣው ይህ የአሁኑ ዘመን የጥፋተኝነት ስሜት የማይሰማው የመጨረሻው ዘመን ነው፡፡ ይህ ማለት ስጋችን በተደጋጋሚ እንዲህ ባሉ ብልሹና ልቅ ሐጢያቶች ተወጥሮ ስለተያዘ በሕይወታችን እነዚህን ሐጢያቶች በእርግጥም እንፈጽማቸዋለን ማለት ነው፡፡ እንዲያውም ስጋችን ሁልጊዜም በእነዚህ መግለጫ በሌላቸው ሐጢያቶች ስለሚጎተት በውስጡ አንዳች ጥሩ ነገር አይገኝበትም፡፡
 

እኛ ዓመጸኞችና በሐጢያት የተሞላን ነበርን፡፡ አሁን ግን ጌታ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከሐጢያቶቻችን ሁሉ በማዳን የራሱ ሕዝብ አድርጎናል፡፡

እኛ ሁላችን ዓመጸኞች ነበርን፡፡ ነገር ግን ጌታ በደህንነት ስጦታ አማካይነት እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አድኖናል፡፡ ርዝመቱ 4.5 ሜትር ወርዱ 67.5 ሳ.ሜ የሆነው የቅድስተ ቅዱሳኑ እያንዳንዱ ሳንቃ በወርቅ ከተለበጠ የግራር እንጨት ተሠርቶ የቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳዎች ሆኖ ቆሞዋል፡፡ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ሳንቃውን ለመደገፍ ሲባል ሁለት የብር እግሮች ይኖራሉ፡፡ እዚህ ላይ የብሩ እግሮች እግዚአብሄር እናንተንና እኔን ሙሉ በሙሉ በራሱ እንዳዳነን ይገልጣሉ፡፡
እውነቱ እግዚአብሄር እኛን ያዳነን ከፍቅሩ የተነሳ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ፍቅር ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጣ፤ ሐጢያቶቻችንን ለመውሰድ ተጠመቀ፤ በመስቀል ላይ በመሞትም የሐጢያቶቻችንን ኩነኔ ተሸከመ፤ በዚህም ከዓለም ሐጢያቶችና ኩነኔ ሁሉ አዳነን፡፡ እርሱ በሰጠን የደህንነት ስጦታ በማመን ዳግመኛ ተወልደናል፡፡ ጌታ የሰጠን ይህ የደህንነት ስጦታ ልክ እንደ ወርቅ የማይበሰብስ ስለሆነ ለዘላለም የማይለወጥ ነው፡፡
ጌታ የሰጠን ደህንነት ከኢየሱስ ጥምቀትና ደም የተገኘ ነው፡፡ ይህም ሙሉ በሙሉ በግልጥ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ደምስሶታል፡፡ እናንተና እኔ በአእምሮዋችን፣ በአስተሳሰቦቻችንና በተጨባጭ በምናደርጋቸው ምግባሮች ከምንሠራቸው ሐጢያቶች ሙሉ በሙሉ ነጻ መውጣት የቻልነው ጌታ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ስላዳነን ነው፡፡ እግዚአብሄር በልባችን ውስጥ የሰጠንን የደህንነት ስጦታ በማመን የእርሱ ክቡር ቅዱሳን ሆነናል፡፡ እግዚአብሄር ምሰሶዎችም ግድግዳዎችም በሆኑት የመገናኛው ድንኳን ሳንቆች አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ደህንነት እየነገረን ነው፡፡ እግዚአብሄር በሳንቆቹ የብር እግሮች አማካይነትም እኛ የእርሱ ልጆች የሆንነው 100 በመቶ በእርሱ ጸጋና ስጦታ እንደሆነ እየነገረን ነው፡፡
በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ላይ ያለንን እምነት ብናስወግድ በውስጣችን የሚቀር አንዳች ነገር አይኖርም፡፡ ሁላችንም ለሐጢያት ለመኮነን የታጨን ነበርን፡፡ እኛ የሐጢያት ደመወዝ ሞት መሆኑን በሚያውጀው የእግዚአብሄር ሕግ መሰረት እርግጠኛ በሆነው ሞታችን ፊት ለመንቀጥቀጥ የታጨን ተራ ሟቾች የነበርንና የሚጠብቀንን የጽድቅ እሳት ፍርድ በማወቅ ስናለቅስ የነበርን ሰዎች ነበርን፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያለንን እምነት ካስወገድን ከንቱዎች የምንሆነው ለዚህ ነው፡፡ አሁን እየኖርን ያለነው በሐጢያት በተሞላ ዘመን ውስጥ ስለሆነ ዕድላችን የእሳት ፍርድን መጠባበቅ ብቻ እንደነበር ፈጽሞ መርሳት የለብንም፡፡ እኛ እንዲህ ያለን ሟቾች ነበርን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ደህንነት ስለሰጠን ጸጋውን በሙላት ለገሰን፡፡ መሲሁ ወደዚህ ምድር መጥቶ በዮሐንስ በመጠመቅ ደሙን አፍስሶ በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ ዳግመኛም ከሙታን ተነሳ፡፡ በዚህም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ፣ ከዓመጻችን ሁሉና ከኩነኔያችን ሁሉ አዳነን፡፡ አሁን እኛ በዚህ የውሃና የደም ፍጹም ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻችን ስለዳንን በእምነታችን እግዚአብሄርን ማመስገን እንችላለን፡፡
በስጋችን ብቁዓን ባንሆንም ሠራተኞቻችን፣ አገልጋዮቻችንና እኔ ይህንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል በመላው እየሰበክን ነው፡፡ ይህ ዘመን የተበላሸ ዘመን ቢሆንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስለምናምን ከማናቸውም ሐጢያት ነጻ ሆነን ጌታን በንጽህና ማገልገል ችለናል፡፡ ይህንን አእምሮ የያዝነው ከእኛ ጉልበት የተነሳ ሳይሆን እኛን በደህንነት ጸጋው በማልበስ ቅድስናን ስለሰጠን ነው፡፡ ይህንን የደህንነት ሐይል የለበስነው ጌታ ከሐጢያትና ከኩነኔ ፈጽሞ ስላዳነን ነው፡፡ ጌታን በንጽህና ማገልገል የቻልነውም ሙሉ በሙሉ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ጌታ በውሃና በመንፈስ ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ስላዳነን ደካሞች ብንሆንም ከእንግዲህ ወዲያ በሐጢያቶቻችን፣ በድካሞቻችንና በኩነኔ ሳንታሰር እርሱን ልናገለግለው እንደምንችል አምናለሁ፡፡
በእርግጥ በጌታ ጸጋ ባይሆን ኖሮ ወንጌልን በመላው ዓለም መስበክ አንችልም ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ጸጋ ባይሆን ኖሮ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመላው ዓለም ማሰራጨትና ይህንን ወንጌል በንጽህና ማገልገል ፈጽሞ የሚቻል ነገር አልነበረም፡፡ እናንተና እኔ ወንጌልን እየደገፍንና እያገለገልን ሕይወታችንን መኖር የቻልነው 100 በመቶ እግዚአብሄር በሰጠን ደህንነት ጸጋ ነው፡፡ እኛ በእምነት የእግዚአብሄር መቅደስ ዓምዶችና የመንግሥቱ ሕዝቦች ሆነናል፡፡ ጌታ እንደ ወርቅ የሆነውን እምነት ስለሰጠን አሁን በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ እንኖራለን፡፡ ዓለም በሐጢያት እየተጥለቀለቀና እየሰጠመ ባለበት በዚህ ዘመን አብዛኛው ሕዝብ እግዚአብሄርን እየረሳ ወይም እየሰደበ ባለበት በዚህ ዘመን እኛ በንጹህ ውሃ ታጥበን ነጽተናል፡፡ ጥሩ ውሃ መጠጣትና ጌታን በንጽህና ማገልገልም ችለናል፡፡ እኔ ለዚህ በረከት ምንኛ በሰፊው አመስጋኝ እንደሆንሁ ቃላቶች መግለጥ አይችሉም፡፡
በእምነት ጻድቃን የሆንነው በእርግጥም በዚህ መንገድ ነው፡፡ እንዴት ጻድቃን ልንሆን ቻልን፣ በውስጣችን በጎነት የሌለ ሆኖ ሳለ ራሳችንን እንዴት ጻድቃን ብለን መጥራት ቻልን? እንደ እናንተና እንደ እኔ ያሉ ሐጢያተኛ ፍጡራን እንዴት ሐጢያት አልባ ሆኑ? በስጋችሁ ጽድቅ፣ ሐጢያት አልባና ጻድቅ መሆን ይቻላችኋልን? የስጋችሁ አስተሳሰቦች፣ የራሳችሁ ጥረቶችና ምግባሮቻችሁ-- ከእነዚህ ማናቸውም እናንተን ሐጢያት አልባ ወደ መሆን ሊቀይሩዋችሁና ጻድቃን ሊያደርጉዋችሁ ይችላሉን? ጻድቃን መሆን የቻላችሁት በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው የእግዚአብሄር ደህንነት በማመናችሁ አይደለምን? በመሲሁ በተፈጸመውና በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ በተገለጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አማካይነት በተገኘው ደህንነታችሁ ሳታምኑ ጻድቃን መሆን ትችላላችሁን? በፍጹም እንደዚያ መሆን አትችሉም ነበር! በቀዩ ማግ በማመን ብቻ ፈጽሞ ጻድቃን መሆን አንችልም፡፡
አዳኛችንና መሲሃችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ፋንታ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ለመደምሰስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት በሕይወት ዘመናችን የሠራናቸውን ሐጢያቶች በሙሉ ጨምሮ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ስለተሸከመ በእምነት ጻድቃን ሆነናል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ መሥዋዕት ሐጢያተኞች ወይም ሊቀ ካህኑ በራሱ ላይ እጆቻቸውን ሲጭኑበት ሐጢያትን እንደሚሸከም ሁሉ በአዲስ ኪዳን ዘመንም ኢየሱስ ክርስቶስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ወደ እርሱ የተሻገሩለትን የዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ተቀብሎዋል፡፡ ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በተጨባጭ ወስዶዋል፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ዮሐንስም ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ› (ዮሐንስ 1፡29) ብሎ መስክሮለታል፡፡ ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ የሕይወቱን ቀጣይ ሦስት ዓመታቶች ለእኛ ደህንነት በመኖር ወደ መስቀል ሄዶ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ስጋውን ለእግዚአብሄር በመስጠት ሐጢያቶቻችንንና ኩነኔን ሁሉ አስወግዶ አዲስ ሕይወትን ሰጠን፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በዝምታ አሳልፎ የሰጠውና በሮማውያን ወታደሮች በተሰቀለ ጊዜ እጆቹና እግሮቹ የተቸነከሩት ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በመውሰዱ ነው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በልቡ ውስጥ ያለውን ደሙን ሁሉ አፈሰሰ፡፡ ‹‹ተፈጸመ!›› (ዮሐንስ 19፡30) በማለትም በደህንነታችን ላይ የመጨረሻውን ምዕራፍ አኖረ፡፡ በዚህ መንገድ ከሞተ በኋላ በሦስት ቀናት ውስጥ ዳግመኛ ከሙታን ተነስቶ ወደ መንግሥተ ሰማይ በማረግ የዘላለምን ሕይወት ሰጠንና አዳኛችን ሆነ፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በመሸከሙ በመስቀሉ፣ በትንሳኤውና በዕርገቱ ፍጹም የሆነ አዳኛችን ሆነ፡፡
 


በመስቀሉ ደም ብቻና እያደገ በሚሄድ ቅድስና ማመን ፈጽሞ ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችሁ አላዳናችሁም፡፡ 


ክርስቲያኖች ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ብቻ በማመን ፈጽመው ከሐጢያቶቻቸው ሊድኑ አይችሉም፡፡ ሰዎች በዓይኖቻቸውና በድርጊቶቻቸው በየቀኑ ሐጢያት ስለሚሠሩ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም በማመን ብቻ ሐጢያቶቻቸውን መደምሰስ አይችሉም፡፡ በዚህ ዘመን በሰዎች ሕይወት ውስጥ ከሚፈጸሙት እጅግ ድብቅ ሐጢያቶች አንዱ ልቅ የጾታ ግንኙነት ነው፡፡ ልቅና አሳፋሪ የጾታ ግንኙነት ባህል ዓለምን እንዳጥለቀለቀው ሁሉ ይህ ሐጢያት በስጋችን ውስጥ ተተክሎዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳናመነዝር ያዝዛል፡፡ ነገር ግን ዛሬ የምናየው ተጨባጭ ነገር ብዙ ሰዎች ከከበቡዋቸው ሁኔዎች የተነሳ ባይፈልጉትም ይህንን ሐጢያት ይሠራሉ፡፡ የፍትወት አሳቦችን ማሰብ ብቻውን ምንዝርናን መፈጸም እንደሆነ እግዚአብሄር ይናገራል፡፡ ነገር ግን ዓይኖቻችን በየቀኑ የሚያዩት ሁሉ አሳፋሪ ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች በየደቂቃውና በየሰከንዱ እነዚህን ልቅ ሐጢያቶች ይፈጽማሉ፡፡ ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ እንዴት ሊቀደሱና ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገቡ ይችላሉ? እንዴትስ ጸድቃን ሊሆኑ ይችላሉ? ለረጅም ጊዜ ራሳቸውን በመግታትና ባረጁ ጊዜ በመጠኑም ቢሆን በመቀደስ ልባቸው ጻድቅ ይሆናልን? ጠባያቸው ይበልጥ ልዝብ ይሆናልን? ይበልጥ ታጋሾች ይሆናሉን? በእርግጥም አይሆኑም! የሚሆነው የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡
ሰዎች ሲያረጁ ቁጡዎችና ቅብጥብጦች ይሆናሉ፡፡ በእርጅና ወቅት የሆርሞን ለውጦችም ይከሰታሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ታጋሾች የነበሩት እንኳን ቁጣቸውን ማለዘብና ቅብጥብነታቸውን መግታት ይከብዳቸዋል፡፡ ስለ ሌሎች ከማሰብ ይልቅም ስለ ራሳቸው አብዝተው ያስባሉ፡፡ አካላዊ ተግባሮቻቸው እየደከሙ ሲሄዱ ራሳቸውን የማቆየቱ ደመ ነፍሳቸው ይጠነክራል፡፡ ስለዚህ ስናረጅ ልክ እንደ ሕጻን ልጅ እንሆናለን፡፡ እንዲህ የሚል አባባል አለ፤ ሕጻን ሳለ በአራት እግሩ ሲድህ የነበረ በልጅነቱ በሁለት እግሮቹ ይቆማል፡፡ ሲያረጅ በሦስት እግሩ ይራመዳል፡፡ ይህ አባባል ሰዎችን የሚመለከት አባባል ነው፡፡ ሁሉም ሰው እንደዚሁ ነው፡፡
በክርስትና ትምህርቶች መካከል ‹‹እያደገ የሚሄድ የቅድስና ትምህርት›› ተብሎ የሚጠራ ትምህርት አለ፡፡ ይህ ትምህርት ክርስቲያኖች በመስቀል ላይ የሆነውን የኢየሱስ ሞት ለረጅም ጊዜ ካመኑበት፣ በየጊዜው የንስሐ ጸሎቶችን ከጸለዩና ጌታን በየቀኑ የሚያገለግሉ ከሆኑ ቀስ በቀስ ቅዱስ ይሆናሉ ብሎ ያስተምራል፡፡ ኢየሱስን ማመን ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ዘመን እያለፈ በሄደ ቁጥር ከሐጢያት ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውና ምግባሮቹም የተቀደሱ ዓይነት እንሆናለን፤ ወደ ሞት በምንቀርብበት ወቅት ሙሉ በሙሉ የተቀደስን ሰለሆንን ፈጽሞ ሒያት አልባ እንሆናለን ይላሉ፡፡ ይህ ትምህርት በየጊዜው የንስሐ ጸሎቶችን ስለምንጸልይ ልብሶቻችን እንደሚታጠቡ ሁሉ በየቀኑ ከሐጢያቶቻችን እንታጠባለን፤ ስለዚህ በመጨረሻ ስንሞት ፈጽሞ ጻድቅ እንደሆነ ሰው ሆነን በእግዚአብሄር ፊት እንቀርባለን ብሎ ያስተምራል፡፡ እንዲህ የሚያምኑ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ይህ ግን በሰው ሰራሽ አስተሳሰቦች የረቀቀ መላ ምታዊ ግምት ብቻ ነው፡፡
ሮሜ 5፡19 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ሐጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ፡፡›› ምንባቡ ሁላችንም በአንዱ ሰው መታዘዝ ሐጢያት አልባ እንደሆንን ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በግሉ ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ እናንተና እኔ ማድረግ ያልቻልነውን አደረገ፡፡ ኢየሱስ እናንተና እኔ ራሳችንን ከሐጢያት ነጻ ማውጣት እንደማንችል በሚገባ በማወቁ በእኛ ፋንታ ሐጢያቶቻችንን አስወገደ፡፡ ይህ ደግሞ እናንተም ሆናችሁ እኔ መቼም ልናደርገው የማንችለው ነገር ነው፡፡ እርሱ ወደዚህ ምድር በመምጣት፣ በመጠመቅ፣ በመሰቀልና ዳግመኛም ከሙታን በመነሳት እናንተንና እኔን አዳነን፡፡ ለአንዴና ለዘላለምም ከሐጢያቶቻችን ሁሉ አነጻን፡፡ 
ኢየሱስ ክርስቶስ በሐጢያቶች ስርየት ለሕዝቡ ደህንነትን መስጠት የቻለው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመታዘዙ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መሲህ ሆኖ የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመታዘዝ በጥምቀቱ፣ በመስቀሉና በትንሳኤው የደህነነትን ጸጋ ሰጠን፡፡ ኢየሱስ አንዲህ የደህንነትን ስጦታ ለእኛ በመስጠት የሐጢያት ስርየትን ፈጽሞ አጠናቀቀ፡፡ አሁን እኛ በእምነት ይህንን የደህንነት ጸጋ ለብሰናል፡፡ ምክንያቱም በራሳችን ሥራዎች ወይም ትሩፋቶች ፈጽሞ ሊከናወን የማይችለውን ከሐጢያት መዳናችንን ጌታ ፈጽሞታልና፡፡
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀት በማመን ፋንታ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ብቻ በማመን በራሳቸው ምግባሮች ለመቀደስ ይሞክራሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የወሰደ ቢሆንም ሰዎች አሁንም በዚህ እውነት አያምኑም፡፡ ማቴዎስ ምዕራፍ 3 ኢየሱስ የአገልገሎት ሕይወቱን ሲጀምር ያደረገው የመጀመሪያው ነገር ቢኖር ከዮሐንስ ጥምቀትን መቀበል እንደነበር ይነግረናል፡፡ ይህ በአራቱም የወንጌል ጸሐፊዎች የተመሰከረለት እውነት ነው፡፡
ኢየሱስ የሰው ዘር ወኪልና ከሴቶች ከተወለዱት ሁሉ እጅግ በሚበልጠው በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችንን ወሰደ፡፡ ነገር ግን ይህንን እውነት ችላ የሚሉና የማያምኑበት በጣም ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በጥምቀቱ ሳያምኑ በኢየሱስ ያምናሉ፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ያፈሰሰውን ደም ብቻ በግለት ያመሰግናሉ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞቱ አዝነው ስሜቶቻቸውን በማነሳሳት በምስጋናቸው ውስጥ ሁሉንም ዓይነት ጫጫታ በማስገባት ‹‹♫በደሙ ውስጥ ግሩም ሐይል አለ፤ ♪በበጉ ክቡር ደም ውስጥ ሐይል ድንቅን የሚያደርግ ሐይል አለ!♫›› እያሉ ይጮሃሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በራሳቸው ስሜቶች ጥንካሬና ጉልበት ግለው ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን አብዝተው ባደረጉ ቁጥር መጨረሻቸው ሐጢያቶችን ማከማቸትና ይበልጥ ግብዞች መሆን ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን ስንመጣ ሁለቱ የኢየሱስ የጸጋ አገልግሎቶች ፈጽመው አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነርሱ ምንድናቸው? ከእነርሱ አንደኛው ኢየሱስ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን መውሰዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ የዓለምን ሐጢያቶች በመስቀል ላይ በመሸከምና በዚያም በመሞት የሐጢያቶቻችንን ደመወዝ መክፈሉ ነው፡፡ በእነዚህ በሁለቱ የኢየሱስ የጸጋ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ የሚያምን ሰው በእርግጠኝነት ጻድቅ ይሆናል፡፡ በሁለቱ ወሳኝ የደህንነት ስጦታዎቹ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ደሙ ያለን እምነት በእግዚአበሄር ቤት ውስጥ በጽናት እንድንቆም ያደርገናል፡፡ እኛ በእግዚአብሄር ጸጋ በትክክል እንከን አልባ ሕዝብ ሆነናል፡፡ በኢየሱስ በተሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ለዘላለም እንደ ንጹህ ወርቅ የማይለወጠውን እምነት ተቀብለናል፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው በዚህ የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ፍጹም የሆነውን የሐጢያት ስርየት ደህንነት ተቀብለናል፡፡
 
 
የሥነ መለኮት ዕውቀት እስካሁን ድረስና የውሃና የመንፈስ ወንጌል ዘመን፡፡ 

በ313 ዓ.ም የሚላን ሕግ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ የዘመኑ ክርስትና የጥንቱን የቤተክርስቲያን ዘመን አግልሎ የኢየሱስን ጥምቀት በማስወገድ የመስቀሉን ወንጌል ሲያሰራጭ ነበር፡፡ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን ጀምሮ ክርስትና አዲሱ የሮም ሐይማኖት ሆኖ በሕግ እስከተደነገገበት 313 ዓ.ም ድረስ ክርስትና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሲሰብክ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የሮም ካቶሊከ ቤተክርስቲያን የሐይማኖቱን ትዕይንት ተቆጣጠረች፡፡ ከዚያም ከ14ኛው ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ ሁሉን ነገር በሰው ሰራሽ አስተሳሰቦች ላይ የሚያነጣጥርና የሰብዓዊነትን መታደስ የሚሻ ባህል ብቅ ማለት ጀመረ፡፡ በመጀመሪያ በአንዳንድ የበለጠጉ የሰሜን ጣልያን ጠቅላይ ግዛቶች ተስፋፋ፡፡ ይህም ሕዳሴ ተብሎ ተጠራ፡፡
በ16ኛው ምዕተ ዓመት በጣልያን የጀመረው የዚህ በሰው ላይ የሚያነጣጥር ባህል ዱካ በምዕራቡ ዓለም መስፋፋት በመጀመሩ በሰብዓዊነት ላይ ያነጣጠረ ሰው ሰራሽ ፍልስፍናን ያጠኑ ምሁራን ነገረ መለኮትን ማጥናት ጀመሩ፡፡ በራሳቸው ጭንቅላት መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጎም የክርስትና ትምህርቶችን መገንባት ጀመሩ፡፡ ነገር ግን እውነትን ባለማወቃቸው መጽሐፍ ቅዱስን በትክክልና በሙላት መረዳት አልቻሉም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጣም ብዙ አስቸጋሪ ምንባቦች ያሉ በመሆናቸው ዓለማው ዕውቀታቸወን ከፍልስፍና አመለካከቶቻቸው ጋር በማቆራኘት የራሳቸውን የክርስትና ትምህርቶች ፈበረኩ፡፡ ሉተራውያንነት፣ ካልቪናዊነት፣ አርሜኒያዊነት፣ አዲስ ነገረ መለኮት ወግ አጥባቂነት፣ ቀና አስተሳሰባዊነት፣ ነቃሽ ነገረ መለኮት፣ ረቂቅ ነገረ መለኮት፣ በጥቁሮች ላይ ያተኮረ ነገረ መለኮት፣ ክህደት ላይ ያነጣጠረ ነገረ መለኮትና ወ.ዘ.ተረፈ ከዚህ ውስጥ ብቅ ያሉት ከዚህ የተነሳ ነው፡፡
የክርስትና ታሪክ በጣም ረጅም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በተጨባጭ ያን ያህል ረጅም አይደለም፡፡ ከጥንቷ የክርሰቲያን ቤተክርስቲያን ዘመን ጊዜ አንስቶ ለ300 ዓመታት ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ችለው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ፈጥኖ የክርስትና የጨለማ ዘመን በሆነው በመካከለኛው ዘመን ተተካ፡፡ በዚህ ዘመን ለተራ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ በመታረድ ሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ነበር፡፡ የቃለ እግዚአብሄር ዕውቀት ነፋስ በ1700 መንፈስ ጀመረ፡፡ ከዚያም የክርስትና የቃለ እግዚአብሄር ዕውቀቶቹ ብሩህና ሕያው ሆነው ሲያድጉ በ1800ዎቹና በ1900ዎቹ ያበበ መሰለ፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በራሳቸው ልምምዶች ላይ ተመሥርተው በእግዚአብሄር በማመን ረቂቅ በሆኑ ትምህርቶች ተጠልፈው ወድቀዋል፡፡
ይህ ግን እውነት ነውን? በዚህ መንገድ ስታምኑ ሐጢያቶቻችሁ በእርግጥ ይወገዳሉን? እናንተ በየቀኑ ሐጢያትን ትሠራላችሁ፡፡ እናንተ በየቀኑ በልቦቻችሁ፣ በአስተሳሰቦቻችሁ፣ በድርጊቶቻችሁና በድካሞቻችሁ ሐጢያትን ትሠራላችሁ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመን ብቻ ከእነዚህ ሐጢያቶች ነጻ መሆን ትችላላችሁን? ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱ ሐጢያቶቻችንን መሸከሙ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን በመስቀሉ ደም በማመን ብቻ ሐጢያቶቻቸው እንደተወገዱላቸው የሚያምኑና በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶቻቸውን የሚጸልዩ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን የንስሐ ጸሎቶች በማቅረብ የልባችሁና የሕሊናችሁ ሐጢያቶች ነጽተዋልን? ይህ የማይቻል ነው፡፡
እናንተ ክርስቲያኖች ከሆናችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ በዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶቻችንን የወሰደ የመሆኑን ይህንን የደህንነት ዕውቀት ማወቅና ማመን አለባችሁ፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ አሁንም ይህንን እውነትና ላለማወቅና በእርሱም ላለማመን ስትሉ ብቻ ችላ ትሉታላችሁን? እንደዚያ ከሆነ ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ ከልባችሁ ስለማመን መናገር አትችሉም፡፡ ነገሩ እንደዚህ ከሆነ በኢየሱስ ላይ የማላገጥና ስሙን የማዋረድንና የመናቅን ሐጢያት እየሠራችሁ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በገዛ ፈቃዳችሁ የኢየሱስን ስም የመስደብ ሐጢያት እየሠራችሁና በእግዚአብሄር ላይ እያላገጣችሁ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ለማስወገድ ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ ከዚህ የአመጣጡ ዓላማ ጋር በተስማማ መልኩም ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመውሰድ ተጠመቀ፡፡ የዓለምን ሐጢያቶች በመቀበል በመስቀል ላይ የእነዚያን ሐጢያቶች ኩነኔ ሁሉ ተሸከመ፡፡
ሆኖም ይህ ሰማያዊ እውነት እያለ ብዙ ሰዎች አሁንም ድረስ በዚህ የኢየሱስ ክርስቶስ ደህንነት አያምኑም፡፡ ከዚህ የተነሳ በእግዚአብሄር ላይ ይቅር የማይባለውን ሐጢያት ይሠራሉ፡፡ የኢየሱስን ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ከተፈጸመው ከዚህ የደህንነት ዕቅድ በማስወጣት ትክክል በሚመስላቸው በማናቸውም መንገድ ስለሚያምኑ ፈጽሞ የደህንነትን ጸጋ አይለብሱም፡፡ እነዚህ ሁሉ እውነቶች እያሉ ብዙ ሰዎች በተጻፈው እውነት ማለትም ኢየሱስ ሐጢያቶቻቸውን ሁሉ የደመሰሰላቸው መሆኑን አያምኑም፡፡ በፋንታው የራሳቸውን አስተሳሰቦች በመከተል ማመን በሚፈለጉዋቸው በማናቸውም የተዛቡ እውነቶች ያምናሉ፡፡ በዚህ ዘመን ሐጢያቶቻቸው በመስቀሉ ደም በማመን ብቻ ሊደመሰሱላቸው እንደሚችሉ በማመን የሰዎች ልቦች በተሳሳቱ ትምህርቶች በማመን ደንድነዋል፡፡
ነገር ግን በእግዚአብሄር የታቀደው የደህንነት ምላሽ እንደሚከተለው ነው፤ በኢየሱስ ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ ሞቱና በትንሳኤው በማመን ዘላለማዊ የሐጢያት ስርየት ይገኛል፡፡ ነገር ግን የእርሱን ጥምቀት ከዚህ የደህንነት እውነት በመነጠል የሚያምኑና ቀጣዩ ቀመር የማይለወጥ ሕግ መሆኑን በተሳሳተ መንገድ የሚያምኑ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ‹‹ኢየሱስ (መስቀሉና ትንሳኤው)+የንስሐ ጸሎቶች+መልካም ምግባሮች = እያደገ በሚሄድ ቅድስና አማካይነት የተሰጠ ደህንነት፡፡›› በዚህ መንገድ የሚያምኑ ሰዎች በአንደበታቸው የሐጢያታቸውን ስርየት እንደተቀበሉ ይናገራሉ፤ ነገር ግን እውነቱ ልቦቻቸው በተጨባጭ አሁንም ድረስ መፍትሄ ባጡ የሐጢያት ክምሮች የተሞሉ መሆናቸው ነው፡፡
በኢየሱስ መስቀል ብቻ የሚያምኑ መጨረሻቸው ብዙ ሐጢያቶችን መሥራት እንደሆነ ግልጥ ነው፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ ሐጢያቶቻችሁን በሙሉ እንደደመሰሰ በሚናገረው በዚህ እውነት እንዳለ ማመን ሲገባችሁ በኢየሱስ እናምናለን እያላችሁ በእነዚህ ሰው ሰራሽ የሐሰት ትምህርቶች የምታምኑት ለምንድነው? ከግራር እንጨት የተሠራው የመገናኛው ድንኳን እያንዳንዱ ሳንቃ ሁለት ማጋጠሚያዎች ከእነርሱም በታች ደግሞ ሳንቃዎቹን አጥብቀው የሚይዙ ሁለት የብር እግሮች የመኖራቸውን እውነታ መረዳት አለባችሁ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል (ኢየሱስ የተቀበለው ጥምቀትና የመስቀሉ ደም) ፍጹም እውነት ነው፡፡
የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ከፍተን ወደ አደባባዩ ስንገባ በመጀመሪያ የምናየው የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠውያና ከዚያም የናሱን የመታጠቢያ ሰን ነው፡፡ የሚቃጠለው መሥዋዕት መሠውያ ምን ዓይነት ስፍራ ነው? የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች የሚቀርቡበት ስፍራ ነው፡፡ የእስራኤሎችን ሐጢያቶች የተሸከሙት የመሥዋዕት እንስሶች ለእነዚያ ሐጢያቶች የሚኮነኑበት ስፍራ ነው፡፡ የመታጠቢያው ሰን ምን ዓይነት ስፍራ ነው? ሰውነት የሚታጠብበትና የሚነጻበት ስፍራ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በሐጢያት የረከሱ ልቦች ታጥበው የሚነጹበት ስፍራ ነው፡፡ የመገናኛውን ድንኳን ከፍተን ወደ እግዚአብሄር ቤት መግባት የምንችለው በእምነት በዚህ ሒደት ውስጥ በምናልፍበት በዚህ ጊዜ ብቻ እንጂ ከዚያ ቀደም ብሎ አይደለም፡፡
የመገናኛው ድንኳን መጋረጃ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ የተሠራ ነበር፡፡ ጥሩ በፍታ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ማግን በጥልፍ ሥራ በመሥራት የተሠራ ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሄር መንግሥት መግባት የምንችለው በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ በተገለጡት የኢየሱስ አገልግሎቶች ስናምን ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ የሰማያዊው፣ የሐምራዊውና የቀዩ ማግ ፍጻሜ ሆነ፡፡ ሰማያዊው ማግ ኢየሱስ የተቀበለውን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ ሐምራዊው ማግ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ አምላክ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ቀዩ ማግ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ የሐጢያቶቻችንን ሁሉ ኩነኔ መሸከሙን ይነግረናል፡፡
አሁንም ድረስ በልቦቻችሁ ውስጥ ሐጢያት አለ? በሌላ አነጋገር በልባችሁ ማዕከል ውስጥ ሐጢያት አለ? አሁንም በኢየሱስ እያመናችሁ እንኳን በልቦቻችሁ ውስጥ ሐጢያት ካለባችሁ እምነታችሁ ከባድ ችግር እንዳለበት ግልጥ ነው፡፡ ሕሊናዎቻችሁ ያልነጹትና ሐጢያት ያለባችሁ በኢየሱስ የምታምኑት ከሐይማኖት ጉዳይ ጋር ብቻ አያይዛችሁ ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ በተገለጠው እውነት አማካይነት እግዚአብሄርን በማመን ሕሊናችሁን ንጹህ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ስለ ኢየሱስ ያላችሁ የተሳሳተ ዕውቀት በፈጠረባችሁ ብዥታ አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች መሆናችሁን መረዳት የመቻላችሁ እውነት በራሱ በጣም አስደሳች ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም ሐጢያት እንዳለባቸው በእውነት የሚረዱ ለዚህ ሐጢያት ለሲዖል የታጩ ከመሆን ውጪ ማምለጥ እንደማይችሉ ይገነዘባሉ፡፡ ይህንን ሲያደርጉም በመጨረሻ በመንፈስ ድሆች ስለሚሆኑ የእውነተኛውን ደህንነት ቃል መስማት ይችላሉ፡፡
ከእግዚአብሄር ዘንድ የሐጢያት ስርየትን መቀበል የምትፈልጉ ከሆነ ልቦቻችሁ ዝግጁ መሆን አለባቸው፡፡ ልቦቻቸው በእግዚአብሄር ፊት ዝግጁ የሆኑላቸው ሰዎች ‹‹አቤቱ የሐጢያት ስርየትን መቀበል እፈልጋለሁ፡፡ ለረጅም ጊዜ በኢየሱስ አምኜያለሁ፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ ሐጢያት አለብኝ፡፡ የሐጢያት ደመወዝ ሞት ስለሆነ ወደ ሲዖል ከመጣል አላመልጥም›› በማለት ያምናሉ፡፡ በእግዚአብሄር ፊትም ሙሉ በሙሉ ሐጢያተኞች መሆናቸውን ይገነዘባሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የሚረዱና የእግዚአብሄር ቃል በእርግጥም እንደሚናገረው በትክክል የሚፈጸም መሆኑን የሚያምኑ ሰዎች ልባቸው ዝግጁ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል ይሰማሉ፡፡ ቃሉንም በራሳቸው ዓይኖች ያያሉ፡፡ እንዲህ በማድረግም ‹‹አሃ በተሳሳተ መንገድ ሳምን ቆይቻለሁ፤ በርካታ ሰዎች አሁንም በተሳሳተ መንገድ እያመኑ ነው›› ወደሚል ግንዛቤ ይመጣሉ፡፡ ሌሎች ምንም ቢናገሩም ሆነ ቢያደርጉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያት ስርየታቸውን ይቀበላሉ፡፡
በዚህ ዓለም ላይ በተሳሳተ እምነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ያህል ብዙ እንደሆኑና ብዙዎችም በተሳሳተ መንገድ ላይ እየተጓዙ መሆናቸውን ሳስብ ልቤ ክፉኛ ያዝናል፡፡ ወንድሞችና እህቶች ጌታ እኛን ከሐጢያቶቻችን ያዳነበት ወንጌል የተፈጸመው ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ነው፡፡ ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ በጥምቀቱ በመውሰድ የሐጢያትን ኩነኔ ሁሉ በመስቀሉ ደም ተሸክሞ አዳነን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በጥሩው በፍታ የሚያምነውን እምነት በመስጠት እንዳዳነን ያለ ምንም ማመንታት ማመን አለብን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናንተንና እኔን በዚህ መንገድ ያዳነን ለመሆኑ እውነት አመስጋኝ ነኝ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን እናንተና እኔ ሁልጊዜም ሰላም አለን፡፡ ልቦቻችንም ፈጽሞ አይናወጡም፡፡
 


ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ የዳኑ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን እምነታቸወን መደገፍ አለባቸው፡፡

 
ይህ ዓለም ዳግመኛ የተወለዱትን ሰዎች ልቦች ማናወጥና ማርከስ በሚችሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ክፉ ትምህርቶች የተሞላ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ሲል አስጠንቅቆናል፡- ‹‹ተጠንቀቁ፤ ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ፡፡› (ማርቆስ 8፡15) አንድ ጊዜ ብቻ ተደምጠው የሰዎችን ልብ ያረከሱት እንደዚህ ያሉ እርሾ ያለባቸው ትምህርቶች ምን ያህል እንደሆኑ መቁጠር እንኳን አንችልም፡፡ ይህ ዓለም እንዴት በልቅ ወሲብ እንደተጥለቀለቀ መገንዘብ አለብን፡፡ እኛ የምናምን በምን ዓይነት ዘመን ላይ እየኖርን እንዳለን በትክክል ማወቅና እምነታችንን መከላከል አለበን፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ባለው ሐጢያተኛ ዓለም ውስጥ ብንኖርም በልቦቻችን ውስጥ ጌታ እኛን ከሐጢያት ያዳነበት ሊጠቃ የማይችል እውነት አለ፡፡ የማይለወጠው ደህንታችን የሚመሰክረው የምስክርነት ቃል የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ በእውነት ላይ በዓለም የማይናወጥና የማይጎተት እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡
ከዚህ ዓለም የሚመነጭ ማንኛውም ነገር እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን በሰይጣን ውሸቶች የተሞላ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጻድቃን ዓለምን እንደሚያሸንፉ ነግሮናል፡፡ ጻድቃን ዲያብሎስን ድል የሚነሱትና ዓለምን የሚያሸንፉት በማይለወጠው የደህንነት እውነት ላይ ባላቸው እምነት ነው፡፡ ብቁዓን ባንሆንም ልቦቻችን፣ አስተሳሰቦቻችንና አካሎቻችን አሁንም ድረስ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ ናቸው፡፡ በእምነትም በደህንነት ወንጌል ላይ በጽናት ተተክለዋል፡፡ ጌታ እኛን ፈጽሞ ባዳነበት በውሃውና በደሙ ወንጌል ላይ በጽናት እንቆማለን፡፡
ለመገናኛው ድንኳን እንደ ምሰሶዎችም ግድግዳዎችም ሆነው የቆሙ የግራር እንጨት ሳንቆች በወርቅ የተለበጡ ነበሩ፡፡ ሳንቆቹ በብር እግሮች ላይ የቆሙ በመሆናቸው በጥብቅ ስለተተከሉ አይናወጡም፡፡ ልክ እንደዚሁ ከውሃውና ከመንፈሱ ዳግመኛ የተወለድን ሰዎች የያዝነው እምነት ለዘላለም የማይለወጥ ነው፡፡ በወርቅ ቅጠልያ የተለበጡት ከግራር እንጨት የተሠሩት ሳንቆች እንደማይለወጡ ሁሉ እንደ ንጹህ ወርቅ የሆነው እምነታችንም አይለወጥም፡፡ ለእናንተና ለእኔ በእሳት የሚቃጠለው የግራር እንጨት ሙሉ በሙሉ መዳን የሚችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ የተነሳ እግዚአብሄርን አብዝተን እናመሰግነዋለን፡፡ ሐጢያት በዚህ ዓለም ላይ ምንም ያህል ቢበዛም ቢያንስ እኛ ጻድቃኖች ነቁጥ የሌለባቸው ሕሊናዎችና በልባችን ውስጥ እንደ ወርቅ የሚያበራ እምነት አለን፡፡ ጌታ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ በመንግሥቱ ውስጥም ሆነን እንኳን ሁላችንም ይህንን እውነት እናወድሳለን፡፡ ያዳነንን ጌታና ይህንን እምነት የሰጠንን አምላክ ለዘላለም እናመሰግነዋለን፡፡
በእግዚአብሄር ፊት ያለን እውነተኛ እምነት በዓለት ላይ የተገነባ ስለሆነ በማናቸውም ሁኔታዎች አይናወጥም፡፡ ስለዚህ በጌታ ፊት እስከምንቆምበት ቀን ድረስ በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ምንም ነገር ቢገጥመን ልቦቻችንን በእምነት እንከላከላለን፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለው እያንዳንዱ ነገር ቢወድም እንኳን፣ ይህ ዓለም በሐጢያት እየሰጠመ ቢሆንም እንኳን፣ ይህ ዓለም ከጥንቶቹ ሰዶምና ገሞራ የከፋ ቢሆንም ይህንን ዓለም አንከተልም፡፡ ነገር ግን ሳንናወጥ በእግዚአብሄር እናምናለን፡፡ የእርሱን ጽድቅ እንከተላለን፡፡ እነዚህን ሁለት የደህንነት ጸጋዎች (የኢየሱስን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ሞቱን) እውነተኛ የእግዚአብሄር ጸጋዎች የሚያሰራጩትን ሥራዎች በመሥራት እንቀጥላለን፡፡
በዚህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እንዴት ወደ ማመን እንደመጣን ሳስብ በእግዚአብሄር ጸጋ ፈጽሞ እገረማለሁ፡፡ ይህንን ወንጌል ወደ ማወቅና ወደ ማመኑ በመምጣታችንና የእግዚአብሄርን መልካም ሥራዎች ወደ መሥራት በመድረሳችን ወሰን የለሽ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በነጻ የተሰጠን የእግዚአብሄር ጸጋ በመሆኑ ለጌታችን ልንሰጠው የምንችለው ነገር ቢኖር በእምነታችን ማመስገንና እርሱ ዳግመኛ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ የዚህን ወንጌል እውነት ማሰራጨት ነው፡፡
ይህንን እውነት ስለሰጠን እግዚአብሄርን አመሰግነዋለሁ፡፡