Search

খ্রীষ্টীয় বিশ্বাসের উপরে যে প্রশ্নগুলি প্রায়শই করা হয়ে থাকে

বিষয় ৩: প্রকাশিত বাক্য

3-7. የአውሬው ምልክት ምንድነው? 

በመከራው ዘመን ወቅት ጸረ ክርስቶስ ሁሉንም በእርሱ ቁጥጥር ሥር ለማድረግ በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክቱን እንዲቀበሉ ያስገድዳል፡፡ ይህ ምልክት የአውሬው ምልክት ነው፡፡ ጸረ ክርስቶስ ሰዎችን የእርሱ ባሮች ለማድረግ ምልክቱን እንዲቀበሉ ይጠይቃል፡፡ የሰዎችን ሕይወት በእርሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ የፖለቲካ ዓላማውን በማስፈጸም ይቀጥላል፡፡ ሰዎች የአውሬው ምርኮኞች መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ከሌላቸው ምንም ነገር እንዳይገዙና እንዳይሸጡ ይከለክላቸዋል፡፡ ይህ ምልክት የአውሬው ስም ወይም የእርሱ ቁጥር ነው፡፡ አውሬው በዚህ ዓለም ላይ ሲገለጥ ሕዝቡ የስሙን ወይም የቁጥሩን ይህንን ምልክት እንዲቀበል ይገደዳል፡፡ 
በዚህ ምልክት ላይ ያለው የአውሬው ቁጥር ሲቆጠር 666 ነው፡፡ ይህ ማለት ጸረ ክርስቶስ የሆነው አውሬው ራሱን አምላክ አድርጎ ያውጃል፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ አምላክ ለመሆን እየሞከረ ያለውን የሰው ፍጡር ዕብሪት ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይህንን ምልክት በቀኝ እጁ ወይም በግምባሩ የሚቀበል ማንኛውም ሰው አውሬውን ጸረ ክርስቶስ እንደ አምላክ ያገለግላል፤ ያመልክማል፡፡ 
ዓለም በሰባቱ መለከቶች መቅሰፍቶች ከፍተኛ ችግሮች ሲገጥመው ጸረ ክርስቶስ የሰይጣንን ሥልጣን ተሞልቶ መላውን ዓለም በታላቅ ጉልበት በራሱ አገዛዝ ሥር ያደርገዋል፡፡ ለሞቱ ከሆነው ቁስሎቹ ራሱን ፈውሶ እሳትን ከሰማይ እስከ ማውረድ ድረስ ተዓምራቶችን በማድረግ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖረው እያንዳንዱ ሰው እንዲከተለው ያደርጋል፡፡ ጀግኖች ብቅ የሚሉት በመከራ ዘመን ስለሆነ ሥልጣኑን ከሰይጣን የሚቀበለው ሰው የሆነው ጸረ ክርስቶስ ዓለም የገጠመውን አዳጋች ችግሮች በታላቅ ሥልጣኑ በማቃለል መላው የዓለም ሕዝብ እንደ አምላክ እንዲያከብረው ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ሰዎች ጸረ ክርስቶስን እንደ አምላክ እንዲያመልኩት ሲያደርግ ብዙዎች እርሱ እንደ አምላክ አድርገው ይሰግዱለታል፡፡ 
ስለሆነም ጸረ ክርስቶስ ከምድር በሚወጣው ሌላ አውሬ እርዳታ የመጨረሻዎቹን ሥራዎቹን ይሰራል፡፡ ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ለጸረ ክርስቶስ ምስልን እንዲያደርጉ ሰዎችን ያስገድዳል፡፡ በሰይጣን ሥልጣን ለዚህ የአውሬ ምስል እስትንፋስ ይሰጠውና እንዲናገር ያደርገዋል፡፡ ለአውሬው ምስል የማይሰግዱትንም ሁሉ ይገድላል፡፡ ሰው ሁሉ በቀኝ እጁ ወይም በግምባሩ ምልክቱን የማይቀበል ማንኛውንም ሰው ምንም ነገር እንዳይገዛ ወይም እንዳይሸጥ ያደርጋል፡፡ 
የአውሬውን ምልክት መቀበል ማለት ለእርሱ ማጎብደድና የእርሱ ባርያ መሆን ማለት ነው፡፡ ምልክቱ ተቀባይነት የሚያገኘው በግዴታ ሳይሆን በግላዊና አመዛዛኝ በሆነ ውሳኔ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ይህንን ምልክት ሳይቀበል ምንም ነገር መግዛት ወይም መሸጥ አይችልም፡፡ ወይም ኑሮውን ሊኖር አይችልም፡፡ የሐጢያት ስርየትን ያልተቀበሉ የዓለም ሕዝቦች በሙሉ ከአውሬው ጎን ይቆማሉ፡፡ መጨረሻቸውም ለእርሱ ማጎብደድ ይሆናል፡፡ 
በዚህ ሁኔታ ለአውሬው የሚያጎበድዱና ምልክቱን የሚቀበሉ ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር አብረው በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባህር ውስጥ ይጣላሉ፡፡ ገና ዳግመኛ ያልተወለዱ የስም ክርስቲያኖች  በልባቸው ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለማይኖር በመጨረሻ ለሰይጣን ያጎበድዱና በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክቱን ይቀበላሉ፡፡ እርሱንም አምላክ አድርገው ይሰግዱለታል፡፡ በዚህ ጊዜ ምልክቱን ለመቀበል አውሬው የሚጠይቀውን ጥያቄ መቋቋምና ጸረ ክርስቶስን በእምነት ተዋግተው ማሸነፍ የሚችሉት የሐጢያት ስርየትን የተቀበሉና በልባቸው ውስጥም መንፈስ ቅዱስ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡