Search

សំណួរញឹកញាប់អំពីសេចក្តីជំនឿរបស់គ្រីស្ទបរិស័ទ

ប្រធានបទទី១៖ ការបានកើតជាថ្មី ដោយទឹក និងព្រះវិញ្ញាណ

1-2. ኢየሱስ ማነው? 

በዘፍጥረት 1፡3 እና በዮሐንስ 1፡1-3 ላይ እንደተጠቀሰው እርሱ ፈጣሪ፣ እውነተኛ አምላክ፣ ሐጢያተኞችን ሁሉ ከዓለም ሐጢያቶች ያዳነ፣ የዩኒቨርስ ሁሉ አምላክ ነው፡፡ ‹‹እርሱ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሄር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም›› (ፊልጵስዩስ 2፡6) ‹‹ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ፡፡ ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም፡፡›› (ዮሐንስ 1፡2-3) ኢየሱስ የፍጥረት አምላክ የዩኒቨርስ ጌታ ነው፡፡  
ሆኖም ብዙ ሰዎች በሥጋ ወደዚህ ዓለም በመጣው በኢየሱስ ፍቅርና ደህንነት ባለማመን መዳን አቅቶዋቸዋል፡፡ ነገር ግን ሌሎች ብዙዎች ደህንነትን ተቀብለው የእግዚአብሄር ሕዝብ ሆነዋል፡፡ በእርሱ በማመንም የዘላለምን ሕይወት አትርፈዋል፡፡ ጻድቃንም ሆነዋል፡፡