Search

សំណួរញឹកញាប់អំពីសេចក្តីជំនឿរបស់គ្រីស្ទបរិស័ទ

ប្រធានបទទី២៖ ព្រះវិញ្ញាណបរិសុទ្ធ

2-9. መንፈስ ቅዱስ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስጥ እንዴት የተለያየ ሆኖ ይገለጣል? 

መንፈስ ቅዱስ ጊዜው ምንም ይሑን ያው እግዚአብሄር ነው፡፡ ስለዚህ ስለ እርሱ በብሉይ ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብናነብ መለኮታዊ ባህርይው አይለወጥም፡፡ ሆኖም በእግዚአብሄር ችሮታ የሰውን ዘር ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስጥ በተለየ ሁኔታ መስራቱ እውነት ነው፡፡ 
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ቃሎቹን እንዲናገሩ፣ ፈቀዱን በድንቆች አማካይነት እንዲያሳዩና የእርሱን ስራ እንዲሰሩ በተለዩ ዘዴዎች መንፈስ ቅዱስን በእግዚአብሄር ሰዎች ላይ አፈሰሰ፡፡ ለምሳሌ የእግዚአብሄር መንፈስ በፈራጁ ሳምሶን ላይ ወረደና በእርሱ አማካይነት ብዙ ብርቱ ሥራዎችን ሰራ፡፡ (መሳፍንት 13፡25፤14፡19) በሌላ አነጋገር በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ በተመረጡ ሰዎች ላይ ብቻ ወረደ፡፡ 
ሆኖም በአዲስ ኪዳን ዘመን እግዚአብሄር በዓለ ሃምሳን የመንፈስ ቅዱስ መምጣት የመጀመሪያ መነሻ አድርጎ በመወሰን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምን እምነታቸው አማካይነት የሐጢያቶችን ይቅርታ ላገኙ ቅዱሳን ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ሰደደ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር ፈቀደ፡፡ 
ስለዚህ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ሐዋርያት በመጀመሪያው በዓለ ሃምሳ በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኋላ በወንጌል እውነት በማመን ሐጢያቶቻቸው ይቅር የተባሉ ጻድቃን በሙሉ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 2፡38) ጴጥሮስ አህዛብና ሮማዊ መቶ አለቃ ወደነበረው ወደ ቆርኔሌዎስ ቤት ገባና የኢየሱስን ጥምቀትና የመስቀል ላይ ደሙን ወንጌል ሰበከ፡፡ ጴጥሮስ ወንጌልን እየተናገረ ሳለ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ ወረደ፡፡ (የሐዋርያት ሥራ 10፡34-45) ይህም አንድ ሰው ኢየሱስ የፈጸመውን የኢየሱስ ጥምቀትና የመስቀል ደሙን ወንጌል ሲሰማና ሲያምን በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስን እንደ ስጦታ እንደሚቀበል ያረጋግጣል፡፡ 
እግዚአብሄር በእውነተኛው ወንጌል በማመን የሐጢያቶቻቸውን ሁሉ ይቅርታ ባገኙ ጻድቃን ሁሉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ እንዲኖር አደረገ፡፡ በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመምራትን ሚና ተጫወተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ለእግዚአብሄር ጽድቅ ይመሰክርና ለዚያም ዋስትና ሆኖ ይቆማል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ማለት ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ደሙ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ይቅር አለ ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስም የደህንነት ወንጌል ዋስትና ሆኖ ይቆምና ሁሉም ሰው በዚህ እንዲያምን ያግዛል፡፡