Search

ခရစ်ယာန်ယုံကြည်မှုနှင့်ပတ်သက်သောမေးခွန်းများ

ဘာသာ ၁ - ရေနှင့်ဝိညာဥ်တော်အားဖြင့် ဒုတိယမွေးဖွားခြင်း

1-24. የዮሐንስ ንስሐ ጥምቀት ምንድነው?

መጥምቁ ዮሐንስ ከኢየሱስ 6 ወራት በፊት የተወለደ የእግዚአብሔር ባርያ ነበር፣ እርሱም በሚልክያስ መጽሐፍ ውስጥ በብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነቢይ እንደሚሆን የተተነበየለት ነው።
“ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባርያዬን የሙሴ ሕግ አስቡ። እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ። መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል” (ሚልክያ 4፡4-6)።
ኢየሱስ በተወለደ ጊዜም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን የኪዳን ቃሎች ትተው ለእንግዳ አማልክቶች ይሰግዱ ነበር። እውርና ነውር ያለባቸውን እንስሶች መሥዋዕቶች አድርገው ያቀርቡ ነበረ፣ የእግዚአብሔርንም መቅደስ የንግድ ስፍራ አድርገውት ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት ተተንብዮለታል። ሕጉ ሰዎች ምን ያህል ኃጢአተኞች እንደሆኑ በማሳየት የኃጢአትን ዕውቀት ሰጥቶዋቸዋል (ሮሜ 3፡20)። ማንም ሰው በሕጉ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው አንድ ትዕዛዝ እንኳን ባይኖር በእርግጥ ኃጢአት ነው።
በብሉይ ኪዳን ከሕጉ አንቀጾች አንዳቸውን የተላለፈ ኃጢአተኛ በመገናኛው ድንኳን ፊት የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል። ኃጢአቶቹን ወደ እርሱ ለማስተላለፍ በኃጢአት መሥዋዕቱ ራስ ላይ እጆቹን ይጭናል፣ የኃጢአት ቁርባኑን በማረድም ኃጢአት የሌለበት ሰው በመሆን እንደገና ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቃል። 
ከዚያም ካህኑ ከደሙ የተወሰነውን ይወስድና በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠውያ ቀንዶች ላይ ይቀባዋል፤ የቀረውንም ደም ሁሉ ከመሠውያው በታች ያፈስሰዋል።
ሆኖም የእስራኤል ሕዝብ በየቀኑ በርካታ መሥዋዕቶችን ቢያቀርቡም ከሁሉም ኃጢአቶቻቸው መዳን አልቻሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር የዘላለም ሥርዓት የሆነውን የስርየት ቀን አደረገላቸው። እግዚአብሔር በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን ዓመታዊ ኃጢአቶቻቸውን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግደው በዚህ ጊዜ ነበር። በዚያ ቀን ሊቀ ካህኑ አሮን ሁለት ፍየሎችን ወስዶ ዕጣ ይጥልባቸዋል፤ አንዱ ለይሖዋ ሌላው ደግሞ ለሚለቀቅ ፍየል ይሆናል። ከዚያም ለይሖዋ በተመረጠው ፍየል ራስ ላይ እጆቹን በመጫን የእስራኤልን ሕዝብ ዓመታዊ ኃጢአቶች በሙሉ በእርሱ ላይ ያኖራል። አሮንም ያርደውና ደሙን ወስዶ በስርየት መክደኛው ላይና ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
ቅድስቱን ቦታው ማስተሰረይ ከፈጸመ በኋላ ሌላውን እንስሳ ያቀርባል። በሕያው ፍየሉ ራስ ላይ እጆቹን በመጫንም የእስራኤሎችን ዓመታዊ ኃጢአቶች በሙሉ ይናዘዝበታል። በዚህ ዘዴ ዓመታዊ ኃጢአቶቻቸው በሙሉ ወደ ፍየል ይተላለፋሉ፣ በተዘጋጀው ሰው እጅም ወደ ምድረ በዳ ይሰደዳል። እስራኤሎችም በዚህ መንገድ ከዓመታዊ ኃጢአቶቻቸው ይድኑ ነበር።
ሆኖም በብሉይ ኪዳን ሕግ መሠረት የቀረበው መሥዋዕት ያለ ማቋረጥ ዓመት በዓመት መሥዋዕቶችን ያቀረቡትን ፍጹማን ሊያደርጋቸው አልቻለም። ይህ ሊመጡ ያሉ (የመሲሁ የጽድቅ ምግባሮች) በጎ ነገሮች ጥላ ብቻ ነበር (ዕብራውያን 10፡1)። የእስራኤል ሕዝብ አዳኙን ኢየሱስ ክርስቶስን አልጠበቁም። በፋንታው በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉትን የነቢያቶች ቃሎች ትተው የኃጢአተኛውን ዓለም እንግዳ አማልክቶች አመለኩ።
ስለዚህ እግዚአብሔር የእስራኤሎችን ልብ ለማደስ፣ ወደ እርሱ ለመመለስና ልባቸውም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲቀበል ለማዘጋጀት መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚልክ ተነበየ። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ከማጥመቁ በፊት በይሁዳ ምድረ በዳ ለእስራኤል ሕዝብ የንስሐ ጥምቀት ሰጠ።
መጥምቁ ዮሐንስ እነርሱን በውሃ ያጠምቅ የነበረው አላማ እነርሱ ኢየሱስን እንዲጠብቁና እንዲያምኑበት ለመምራት ነበር። እርሱ አዳኙ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድ በእጆች መጫን መንገድ በእርሱ እንደሚጠመቅና እነርሱን ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ ለማዳን እንደሚሰቀል አስተማረ። እርሱ ኢየሱስ እንደሚመጣና ያለፉትን ያልተሟሉ መሥዋዕቶችን አልጥሎ በሥጋው የዘላለም መሥዋዕት እንደሚያቀርብ ተናግሮዋል፤ የእስራኤል ሕዝብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ባለው የመሥዋዕት ሥርዓት መሠረት ነውር የሌለበትን የኃጢአት መሥዋዕት በማቅረብ፣ እጆቻቸውን በእርሱ ላይ በመጫንና በማረድ እንደዳኑ ሁሉ እርሱም በጥምቀት አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ እንደሚወስድ ተናገረ።
ብዙ እስራኤላውያን ኃጢአቶቻቸውን ተናዘውና ንስሐ ገብተው በእርሱ ተጠምቀዋል። “ንስሐ” ማለት “አእምሮን ወደ ጌታ መመለስ” ማለት ነው። እነርሱ የብሉይ ኪዳንን ሕግ በማስታወስ ወደ ዮሐንስ መጥተው እስከሚሞቱ ድረስ ኃጢአቶችን ከመሥራት በቀር ምንም ማድረግ ያልቻሉ ተስፋ ቢስ ኃጢአተኞች እንደነበሩ ተናዘዙ። በሕጉ መሠረትም በመልካም ምግባሮቻቸው መንግሥተ ሰማይ መግባት እንደማይችሉም ተናዝዘው ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ በመደምሰስ የመንግሥተ ሰማይን በር ሰፊ አድርጎ ወደሚከፍትላቸው ኢየሱስ ክርስቶስ አእምሮዋቸውን መለሱ።
መጥምቁ ዮሐንስ ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠው ጥምቀት የሚከተለው ነበር፤ በሕይወታቸው ምን ያህል ኃጢአት እንደሠሩ እንዲናዘዙ፣ ንስሐ እንዲገቡና ከኃጢአቶቻቸው ሁሉ ሊያድናቸው እንደሆነ ኢየሱስን ክርስቶስን እንዲመለከቱ ፈቀደላቸው። እውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንስሐ ይህ ነው። 
ስለዚህ ዮሐንስ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል” (ማቴዎስ 3፡11)።
መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ እንደሚወስድና (ዮሐንስ 1፡29) ለእነርሱ ተካፋይ ሆኖ እንደሚሞት በመመስከር የሕዝቦቹን አእምሮ ወደ ኢየሱስ መለሰ። በዚህም ኢየሱስ ራሱ ዮሐንስን የጽድቅን መንገድ ሊያሳየን እንደመጣ መሰከረ (ማቴዎስ 21፡32)።