Search

ခရစ်ယာန်ယုံကြည်မှုနှင့်ပတ်သက်သောမေးခွန်းများ

ဘာသာ ၁ - ရေနှင့်ဝိညာဥ်တော်အားဖြင့် ဒုတိယမွေးဖွားခြင်း

1-29. በኢየሱስ ማመን እንዳዳነኝ እርግጠኛ ነበርሁ፡፡ በልቤ ውስጥ ባሉት አመኔታዎችም ሰላም ነበርሁ፡፡ አሁን ግን በመልዕክቶችህ ግራ ተጋብቻለሁ፡፡ ለመዳን የእርሱን ጥምቀት ከመስቀሉ ጋር አብሬ ማመን ይገባኛልን?    

በኢየሱስ ጥምቀት የማታምን ከሆንህ በልብህ ውስጥ ሐጢያት መኖሩ እርግጥ ነው፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ሐጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን እውነትም በእኛ ውስጥ የለም፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 1፡8) በኢየሱስ ጥምቀት ባለማመንህ ምክንያት በእርግጥም ሐጢያት እያለብህ እንኳን ሐጢያት የለብኝም የምትል ከሆነ የራስህን ሕሊና እያታለልህ ነው፡፡ እውነት በውስጥህ የሌለ ለመሆኑም ማስረጃ ነው፡፡ የደህንነት ማረጋገጫ ከልባችን የሚወጣው በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል በማመን የሐጢያቶቻችንን ስርየትና የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ስንቀበል ነው፡፡  
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹…ሌላ ወንጌል…›› (ገላትያ 1፡7) ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ሊያድነን የሚችለው ሐዋርያት ከኢየሱስ የተቀበሉትና ለሰዎች የሰበኩት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ ሐዋርያት የሰበኩትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ካላመንን በእርግጥም አሁንም ድረስ በውስጣችን ሐጢያት አለብን፡፡  
አሁንም ድረስ በውስጣችን ሐጢያት እያለብን በደህንነት ማረጋገጫ መኖር የምንችለው እንዴት ነው? ገና ዳግም ያልተወለዱ ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ፊት ጥሩ ሆነው ሲታዩ ስለ ደህንነታቸው በሙሉ ደስታና አመኔታ እርግጠኞች ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ከበድ ያሉ ሐጢያቶችን በሚሰሩበት ጊዜ በልባቸው ውስጥ ባለው የሐጢያት ሸክም የተነሳ ድፍረት አጥተው ይፈራሉ፡፡ ይህ በእግዚአብሄር ላይ ሳይሆን በራሳቸው አስተሳሰቦችና ስሜቶች ላይ የተመሰረተ አስመሳይ ደህንነት ነው፡፡ ቀስ በቀስ ለመቀደስና በቀላሉ የሚናወጡ ደህንነቶቻቸውን ለመጠበቅ ሲሉ በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን ለማድረግ ያዘነብላሉ፡፡   
በዚህ የሐሰት ደህንነት የሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሄርን በየቀኑ ይቅርታ በመጠየቅና በምግባሮቻቸውም ሕጉን በመጠበቅ ቅዱስ ሕይወትን የሚኖሩ ከሆኑ በመጨረሻ አንድ ቀን ፈጽመው እንደሚድኑ ያምናሉ፡፡ ሆኖም በእርሱ ጥምቀት ላይ ባለ እምነት አማካይነት ሐጢያቶቻቸውን በኢየሱስ ላይ ካላኖሩ አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች ናቸው፡፡
እግዚአብሄር ያዘጋጀው ደህንነት ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ በተጠመቀው ጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ እንደወሰደና በመስቀል ላይ እንደደመሰሳቸው የሚነግረን ፍጹም ደህንነት ነው፡፡     
ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ አለ፡- ‹‹በሐጢአታችን ብንናዘዝ ሐጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመጻም ሁሉ ኪያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው፡፡›› (1ኛ ዮሐንስ 1፡9) ሐጢያቶቻችን በሙሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ይቅር ባይባሉ ኖሮ በእርሱ ብናምንና በሐጢያቶቻችን ምክንያት ሲዖል ለመውረድ ታጨን መሆናችንን ብናውቅም አሁንም ድረስ ሐጢያተኞች መሆናችንን በጌታ ፊት መናዘዝ ይኖርብን ነበር፡፡ እውነተኛ የሐጢያት ኑዛዜ ይህ ነው፡፡ ሐጢያቱ ምንም ያህል ትንሽ ቢሆንም ሐጢያት ያለ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ሊነጻ አይችልም፡፡ በዚህ መንገድ ስንናዘዝ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ አንድ ጊዜ ያስወግድና ጻድቃን ያደርገናል፡፡ 
የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 6፡2) በኢየሱስ ጥምቀትና መስቀል የሚያምን ማንኛውም ሰው ከሐጢያቶቹ ሁሉ ይድናል፡፡ ጻድቅ ይሆናል፡፡ ጌታ በማንኛውም ጊዜ ቢመጣ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ሁሌም ዝግጁ እንደሆነ ጠንካራ እምነት ይኖረዋል፡፡ ከእውነተኛው ወንጌል ውጭ በትምህርቶችና በስነ መለኮቶች የሚያምን ማንኛውም እምነት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ሊያድነን አይችልም፡፡ እነዚያ ዲያብሎስ በሰዎች አሳቦች ውስጥ ያስቀመጣቸው ብልጣ ብልጥ ማታለያዎች ናቸው፡፡ ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መመለስና በልብህ እውነተኛውን የሐጢያቶች ደህንነት መቀበል ይገባሃል፡፡ ይህም እርሱንና ስራውን መውደድ ነው፡፡