Search

मसीही विश्वास पर पूछे गए ज्यादातर प्रश्न

विषय ४: हमारी किताब के पाठकों की ओर से ज्यादातर पूछे गए प्रश्न

4-3. ጥምቀት ማለት ‹‹ሐጢያቶችን ማስተላለፍ›› ነው ብለሃል፡፡ ለዚያ አንዳች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አለ?

ኢየሱስ እንዲህ አለ፡- ‹‹አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና፡፡›› (ማቴዎስ 3፡15) እዚህ ላይ በጥንት ግሪክ ‹‹ጽድቅ ሁሉ›› ማለት ‹ዲካዮሱኔ› ማለት ሲሆን ትርጓሜውም እጅግ ያማረ ሁኔታ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ኢየሱስ የሰውን ዘር በሙሉ እጅግ ተገቢ በሆነ መንገድ አዳነ ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ በሕጉ ውስጥ ባለው የመስዋዕት ስርዓት መሠረት ኢየሱስ ራሱን የሐጢያት ቁርባን አድርጎ ለማቅረብ ምን ማድረግ እንደሚገባው ማሰብ ያስፈልገናል፡፡ እርሱ ሕጉን ለመፈጸም እንጂ ሕጉን ለማፍረስ አልመጣም፡፡ እርሱ በማቴዎስ 5፡17 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም፡፡›› 
  
ስለዚህ ሊቀ ካህኑ አሮን በስርየት ቀን እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ በመጫን የእስራኤላውያንን ዓመታዊ ሐጢያቶች በሙሉ እንዳስተላለፈ ሁሉ ኢየሱስም በእጆች መጫን መልክ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን መቀበልና የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ መውሰዱ አስፈላጊ ነበር፡፡ ይህም የዘላለም ቃል ኪዳን ነበር፡፡ (ዘሌዋውያን 16፡34)
ወልድ ኢየሱስ የአብን የዘላለም ቃል ኪዳን ለመጠበቅ የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘርና የዓለም እጅግ ታላቁ ሰው በሆነው የሰው ዘር ወኪል በአጥማቂው ዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ (ሉቃስ 1፡5፤ ማቴዎስ 11፡11) አጥማቂው ዮሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ በመጫን የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ማስተላለፍ ነበረበት፡፡ ምክንያቱም እርሱ የሰው ዘር ወኪል ሆኖ ምድራዊ ሊቀ ካህን ነበርና፡፡ 
ዮሐንስ 1፡6-8 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከእግዚአብሄር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ፡፡ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ብርሃን አልነበረም፡፡›› ኢሳይያስ 53፡6ም እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ፡፡›› እግዚአብሄር መልዕክተኛው የሆነውን አጥማቂውን ዮሐንስ ከኢየሱስ ስድስት ወር ቀደም አድርጎ የላከው ለዚህ ነው፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀው ማግስት እንዲህ አለ፡- ‹‹እነሆ የዓለምን ሐጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ፡፡›› (ዮሐንስ 1፡29) 
በብሉይ ኪዳን ለሐጢያተኞች ስርየት ለመስጠት ነውር የሌለበት መስዋዕት፣ እጆችን መጫንና ደሙን ለመውሰድም መስዋዕቱን ማረድ አስፈልጓል፡፡ ስለዚህ ቅዱስና ሐጢያት የሌለበት የእግዚአብሄር ልጅ ለሆነው ኢየሱስ በእግዚአብሄር ኪዳን መሠረት ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም በእጆች መጫን መልክ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን መቀበልና መሰቀል ተገቢ ነበር፡፡ 
ቅዱሳት መጻህፍት በሙሉ የተጻፉት በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በመሆኑ በስጋ አስተሳሰቦቻችን ብቻ ልናስተውላቸው አንችልም፡፡ ስለዚህ መንፈሳዊ ትርጉም የሆነውን የተደበቀ ትርጉም በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ማግኘት አለብን፡፡ ስለዚህ ጳውሎስ ‹‹ፊደል ይገድላል፤ መንፈስ ግን ሕይወትን ይሠጣል›› አለ፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 3፡6) እርሱ በፊደል መሠረት ማመን እንደሌለብን ነገር ግን ከፊደሎቹ በስተ ጀርባ የተደበቀውን መንፈሳዊ ትርጉም መረዳት ይገባናል ማለቱ ነው፡፡
ኢሳይያስ 34፡16 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእግዚአብሄር መጽሐፍ ፈልጉ፤ አንብቡም፤ አፌ አዝዞአልና፤ መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና፤ ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፤ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም፡፡››   
እግዚአብሄር እንዲህ አላለም፡- ‹‹ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ተቀበለ፡፡›› ሆኖም ይህንኑ እውነት በቅዱሳት መጽሐፍት ሁሉ ውስጥ ተናገረና በውስጣቸው መንፈስ ቅዱስ ከሌለባቸው ዕውራን ሰወረው፡፡ ‹‹እማማ›› ስንል እርስዋ ወለደችኝ፤ እስከ አሁን ድረስም አሳደገችኝ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹እማማ›› የሚለው ቃል ቃል ብቻ ቢሆንም ብዙ ድብቅ ትርጉሞች አሉት፡፡ ልክ እንደዚያ ‹‹ጽድቅ ሁሉ›› የሚለውም ኢየሱስ በእግዚአብሄር ሕግ መሠረት ሐጢያቶችን ሁሉ እጅግ ተገቢ ና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ተሸከመ የሚል መንፈሳዊ ትርጉም አለው፡፡ይህንን የተደበቀ መንፈሳዊ ትርጉም ማስተዋል ይኖርብናል፡፡
ሰዎች እርሱ ሐጢያቶቻችንን በመሉ በመስቀል ላይ ወሰደ የሚሉ ከሆነ ቃል በቃል አንደዚያ የሚል ጥቅስ አለ ይህ መልስ እንደሚረዳህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡