Search

တရားဟောချက်များ

ርዕስ 1፡ ሐጢያት

[1-1] ለመዳን አስቀድመን ስለ ኃጢአቶቻችን ማወቅ አለብን (ማርቆስ 7፡8-9፣ 20-23)

ለመዳን አስቀድመን ስለ ኃጢአቶቻችን ማወቅ አለብን (ማርቆስ 7፡8-9፣ 20-23)
 
(ማርቆስ 7፡8-9)
“የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ። እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።”
 
(ማርቆስ 7፡20-23)
“እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና። ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።” 
 
 
በመጀመሪያ ኃጢአት ምን እንደሆነ ለማብራራት እወዳለሁ። በእግዚአብሔር የተብራሩ ኃጢአቶች አሉ፣ በሰው የተብራሩም ኃጢአቶች አሉ። በግሪክ ኃጢአት ማለት ‘ኢላማን መሳት’ ማለት ነው። ይህ ማለት ትክክል የሆነን ነገር አለማድረግ ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛቶች በትክክል የማንታዘዝ ከሆነ ኃጢአት ነው። በመጀመሪያ በሰው ዘር የተብራሩ ኃጢአቶችን እንመልከት።
 
ኃጢአት ምንድን ነው?
የእግዚአብሔርን ትዕዛዛቶች አለመታዘዝ ነው።
 
ኃጢአትን በሕሊናችን መሠረት እንለካዋለን። በሌላ አገላለጽ፣ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በደል አይደለም፣ ነገር ግን በአንድ ሰው ዳራ፣ ልብ እና ህሊና መሠረት ይፈረድበታል።
በእያንዳንዱ ግለሰብ ነው የሚፈረደው። ስለዚህ፣ ተመሳሳይ እርምጃ በእያንዳንዱ ሰው መስፈርቶች ላይ በመመርኮዝ እንደ ኃጢአት ሊቆጠር ወይም ላይሆን ይችላል። ለዚህም ነው እግዚአብሔር 613 የሕጉ አንቀጾች ለፍርድ መመዘኛነት እንዲውሉ የሰጠን።
ከዚህ በታች ያለው ገላጭ ስዕል የሰውን ዘር ኃጢአት ያብራራል።
 
ብሄራዊ ሕግ፣ የዜጎች ሕግ
የሰው ሕሊና
የእግዚአብሔር ሕግ
ግብረገብነት፣ ማህበራዊ ደንቦች
 
 
ስለዚህ በሕሊናችን ላይ ተመስርተን በጭራሽ መለኪያዎችን መደንገግ አይገባንም።
የኅሊናችን ኃጢአት እግዚአብሔር ኃጢአት ብሎ ከገለጸው ጋር የሚስማማ አይደለም። ስለዚህ ሕሊናችንን ማዳመጥ የለብንም፣ ይልቁንም የኃጢአትን መመዘኛዎች በእግዚአብሔር ትእዛዛት ላይ መመሥረት አለብን።
እያንዳንዳችን ኃጢአት ምን እንደሆነ የራሳችን እሳቤ አለን። አንዳንዶች ኃጢአትን የራሳቸው ጉድለቶች አድርገው ሲመለከቱት፣ ሌሎች ደግሞ በተዛባ ባህርይ ላይ የተመሰረተ ነገር እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል።
ለምሳሌ በኮርያ፣ ልጆች የወላጆቻቸውን መቃብሮች በሣር መሸፈን፣ ሣሩን መቁረጥ እና እነርሱ እስኪሞቱ ድረስ መቃብሮቹን በደምብ መንከባከብ ግዴታቸው እንደሆነ ይቆጥራሉ። ነገር ግን በፓፑዋ ኒው ጊኒ ውስጥ ባለው አንድ ጥንታዊ ነገድ፣ የሞቱ ወላጆቻቸውን የሚያከብሩት ሬሳውን ከቤተሰብ አባላት ጋር በመጋራትና በመመገብ ነው። (ሬሳውን ከመብላታቸው በፊት ይቅቀሉት እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም።) ሬሳው በትሎች እንዳይበላ መከላከላቸው እንደሆነ ይመስላል። እነዚህ ባህሎች ሰው ስለ ኃጢአት ያለው እሳቤዎች በሰፊው የተለያየ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
መልካምም ሆነ ኃጢአትም እንዲሁ ነው። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አለመታዘዝ እንደሆነ ይነግረናል። “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ። እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል” (የማርቆስ ወንጌል 7፡8-9)። እግዚአብሔር በውጭ እንዴት እንደምንታይ አይጠነክርም። እርሱ የልቦቻችንን ጥልቅ ይመለከታል።
 
 
የሰው መስፈርት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ነው
 
በጣም አሳሳቢው ኃጢአት ምንድነው?
የእግዚአብሔርን ቃል መናቅ ነው።
 
በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ምን እንደሆነ ልንገራችሁ። ኃጢአት በእርሱ ፈቃድ ከመኖር መጉደል ነው። ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቃል አለማመን ነው። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንደናቁትና በራሳቸው ትውፊታዊ ትምህርቶች ላይ ይበልጥ ጠቀሜታ እንዳኖሩት ፈሪሳውያን መኖር ኃጢአት እንደሆነ እግዚአብሔር ተናገረ። ኢየሱስ ፈሪሳውያኖችን እንደ ግብዞች ቆጠራቸው።
“የምታምኑት የትኛውን አምላክ ነው? በእውነት እኔን ትፈራላችሁ እና ታከብራላችሁ? ስለ ስሜም ትመካለህ፥ ነገር ግን በእውነት ታከብረኛለህን?” ሰዎች ውጫዊውን ገጽታ ብቻ ይመለከታሉ እናም የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ይላሉ። እና በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ነው። በጣም ከባድ የሆነው ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ማለት ነው። ይህንን ታውቃላችሁን? ከኃጢአቶች ሁሉ እጅግ አሳሳቢው ኃጢያት ያ ነው።
ድክመቶቻችን ጥፋቶች ብቻ ናቸው፣ መተላለፍ ብቻ ናቸው። ፍጹማን ባለመሆናችን ምክንያት የምንሠራቸው ስህተቶችና የምንሰራው በደል መሰረታዊ ኃጢአት ሳይሆኑ ጉድለቶች ናቸው። እግዚአብሔር ኃጢአቶችን ከስህተቶች ለይቶዋቸዋል። የእርሱን ቃል የሚንቁ ሰዎች ስህተቶች ባይኖሩባቸውም እንኳን ኃጢአተኞች ናቸው። እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ኃጢአተኞች ናቸው። ኢየሱስ ፈሪሳውያንን የወቀሳቸው ለዚህ ነው።
ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ኦሪት ዘዳግም ድረስ ያሉትን መጽሐፎች በያዘው ፔንታቱክ ውስጥ ምን እንደምናደርግና ምን ማድረግ እንደሌለብን የሚነግሩን ትዕዛዛቶች አሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ ትእዛዙ ናቸው። እነርሱን በጭራሽ 100% ልንጠብቃቸው አንችልም፣ ነገር ግን የእርሱ ትዕዛዛት መሆናቸውን መቀበል አለብን። ከመጀመሪያ ለእኛ ሰጥቶናል፣ እና የእግዚአብሔር ቃል አድርገን ልንቀበላቸው ይገባናል።
“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐንስ 1፡1)። ከዚያም እንዲህ አለ፦ “ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ” (ዘፍጥረት 1፡3)። እርሱ እያንዳንዱን ነገር ፈጠረ። እግዚአብሔርም ሕጉን አቋቋመ።
“ቃልም ሥጋ ሆነ ተመልቶ በእኛ አደረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ” (ዮሐንስ 1፡1፣ 14)። እግዚአብሔር ራሱን የሚገልጥልን እንዴት ነው? ራሱን የሚገልጥልን በትዕዛዛቶቹ በኩል ነው። እግዚአብሔር ቃል ነው፣ ራሱንም በትዕዛዛቶቹ በኩል ይገልጣል። እግዚአብሔር መንፈስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ምን ብለን እንጠራዋለን? የእግዚአብሔር ቃል ብለን እንጠራዋለን።
እዚህ ላይ እንዲህ ተብሎዋል፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ።” በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ 613 አንቀጾች አሉ። ይህንን አድርግ ያንን ግን አታድርግ፤ ወላጆችህን አክብር፣ ወዘተ። በኦሪት ዘሌዋውያን ውስጥ ሴቶች እንዲህ ማድረግ አለባቸው እና ወንዶች እንዲህ ማድረግ አለባቸው እና የቤት እንስሳ ወደ ጉድጓድ ውስጥ ሲወድቅ ምን ማድረግ እንዳለበት፣ ወዘተ። በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ 613 እንደዚህ ያሉ አንቀጾች አሉ።
ነገር ግን እነዚህ የሰው ቃሎች ስላልሆኑ ደጋግመን ልናስብባቸው ይገባናል። አምላክን መታዘዝ አለብን እና ሁሉንም የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ባንችል እንኳን ቢያንስ እነርሱን እውቅና ልንሰጣቸው ይገባል።
ትክክል ያልሆነ አንድ በእግዚአብሔር ቃል እንኳን አለ? ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ተዉት። ከእግዚአብሔር ትዕዛዛቶች ይልቅ የሰዎችን ወግ ያዙ። ከእግዚአብሔር ቃሎች ይልቅ የሽማግሌዎቻቸው ቃሎች ይበልጥ ክብደት ነበራቸው። ኢየሱስ በተወለደ ጊዜም እንዲሁ ነበር። ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ማለቱ በኢየሱስ ዘንድ በእጅጉ አልተወደደም።
እግዚአብሔር እርሱ እውነት እንደሆነ፣ እርሱ አምላክ እንደሆነ፣ ኃጢአቶቻችንን በእርሱ ፊት ምን እንደሆኑ ሊያስተምረንና ቅድስናውን ሊያሳየን የሕጉን 613 አንቀጾች ሰጠን። ስለዚህ ሁላችንም ከእርሱ በፊት ኃጢአተኞች ስለሆንን፣ ለእኛ ባለው ፍቅር ከእግዚአብሔር የተላከውን ኢየሱስን ማመን አለብን በእምነትም መኖር አለብን።
የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ጎን የሚተው፣ እና የማያምኑ ኃጢአተኞች ናቸው። የእርሱን ቃል መጠበቅ ያልቻሉ ሰዎችም እንደዚሁ ኃጢአተኞች ናቸው፣ ነገር ግን የእርሱን ቃል መናቅ አሳሳቢ ኃጢአት ነው። መጨረሻቸው ገሃነም ውስጥ የሚገቡት እነሱ ናቸው። በእርሱ ቃል አለማመን በእርሱ ፊት ኃጢአትን መሥራት ነው።
 
 

እግዚአብሔር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት

 
እግዚአብሔር ለምን ሕጉን ሰጠን?
ኃጢአታችንን እና ለእነሱ የሚደርስብንን ቅጣት እንድንገነዘብ ለማድረግ
 
እግዚአብሔር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት ምንድነው? ኃጢአቶቻችንን ተገንዝበን ወደ እርሱ እቅፍ እንድንመለስ ነው። ኃጢአቶቻችንን እንድንገነዘብና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ቤዛነትን እንድናገኝ የሕጉን 613 አንቀጾች ሰጠን። እግዚአብሔር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት ይህ ነው።
ሮሜ 3፡20 እንዲህ ይላል፦ “በሕጉ የኃጢአት እውቀት ነው።” ስለዚህ እግዚአብሔር ሕጉን ለእኛ የሰጠበት ምክንያት በእርሱ እንድንኖር ሊያስገድደን አልነበረም።
ታዲያ ከእግዚአብሔር ሕግ የምናገኘው እውቀት ምንድነው? እኛ ሕጉን በሙላቱ ለመጠበቅ በጣም ደካሞችና በፊቱም ኃጢአተኞች መሆናችንን ነው። ታዲያ ከ613ቱ የእግዚአብሔር ሕግ ትእዛዛት የምንገነዘበው ምንድነው? የራሳችንን ጉድለቶች እና በእግዚአብሔር ሕግ መኖር የማንችልበትን ሁኔታ እንገነዘባለን። እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረቶች በእርሱ ፊት አቅመ ቢስ ፍጡራን መሆናችንን እንገነዘባለን። በእርሱ ፊት ኃጢአተኞች መሆናችንን እንገነዘባለን፣ እንዲሁም በሕጉ መሠረት የሁላችንም መጨረሻ ገሃነም መሆን እንዳለበት እንረዳለን።
ኃጢአቶቻችንንና በሕጉ ለመኖር አቅመ ቢስነታችንን ስንገነዘብ ምን እናደርጋለን? ፍጹማን ለመሆን እንሞክራለን? አይደለም። ማድረግ ያለብን ነገር ኃጢአተኞች መሆናችንን መቀበል፣ በኢየሱስ ማመን፣ በእርሱ የውሃና የመንፈስ ማዳን በኩል ቤዛነትን ማግኘት፣ እና እርሱን ማመስገን ነው።
እግዚአብሔር ሕጉን የሰጠን ያለ ኢየሱስ ከገሃነም መዳን እንደማንችል እናውቅ ዘንድ ኃጢአቶቻችንን እንድንገነዘብና ለእነዚያ ኃጢአቶችም የሚገቡንን ቅጣቶች እንድንገነዘብ ለማድረግ ነው። ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ብናምን ቤዛነትን እናገኛለን። እግዚአብሔር ሕጉን የሰጠን እኛን ለማዳን ነው።
እርሱ ሕጉን የሰጠን እኛ ምን ያህል ፍጹም ኃጢአተኞች እንደሆንን እንድንገነዘብ ለማድረግና ነፍሳችንን ከዚህ ኃጢአት ለማዳን ነው። እርሱ ሕጉን ሰጠንና እኛን ለማዳን ኢየሱስን ላከው። እርሱ የራሱን ልጅ ላከ፣ በጥምቀቱ በኩል ኃጢአታችንን እንዲወስድ። እኛም በኢየሱስ በማመን መዳን እንችላለን።
ተስፋ የለሽ ኃጢአተኞች መሆናችንን ልንገነዘብ እና ከኃጢአት ነፃ እንድንወጣ፣ ልጆቹ እንድንሆን እና ክብርን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ በኢየሱስ ማመን አለብን።
የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት አለብን። ጅማሬዎች ሁሉ ከእርሱ ናቸውና። እኛም በቃሉ እንጀምር እና የቤዛነት እውነትን በእግዚአብሔር ቃል ልንረዳ ይገባናል። እንደ ቃሉ ማሰብና መፍረድ አለብን። ትክክለኛውና እውነተኛው እምነት ይህ ነው።
 
 
በሰው ዘር ልብ ውስጥ ያለው ምንድነው?
 
በእግዚአብሔር ፊት ምን ማድረግ አለብን?
ኃጢአቶቻችንን አምነን መቀበልና እግዚአብሔር እንዲያድነን መጠየቅ አለብን።
 
እምነት መጀመር ያለበት በእግዚአብሔር ቃል ነው፣ እኛም በቃሉ አማካይነት በእግዚአብሔር ማመን ይገባናል። ካላመንን ስህተት ላይ እንወድቃለን። ያም የተሳሳተና እውነተኛ ያልሆነ እምነት ይሆናል።
ፈሪሳውያን እና ጸሐፍት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እጃቸውን ሳይታጠቡ ዳቦ ሲበሉ ባዩ ጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ቢመለከቱት ሊገሥጹአቸው አይችሉም ነበር። ቃሉ ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሁሉ ሊያረክሰው እንደማይችል ይነግረናል፣ ምክንያቱም ወደ ሆዱ ይገባል እንጂ ወደ ልቡ አይገባም።
በማርቆስ 7፡20-23 እንዲህ ተባለ፦ “እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና። ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።” ኢየሱስ ሰዎች ከኃጢአት ጋር ስለተወለዱ ኃጢአተኞች እንደሆኑ ተናገረ።
ይህ ምን ማለት እንደሆነ ይገባችኋልን? እኛ ኃጢአተኞች ሆነን የተወለድነው ሁላችንም የአዳም ዘሮች ስለሆንን ነው። ነገር ግን እውነቱን ማየት አልቻልንም ምክንያቱም የጌታ ቃሎችን በሙሉ አልተቀበልናቸውም፣ አላመንናቸውም። በሰው ልብ ውስጥ ምን አለ?
በማርቆስ 7፡21-22ን እንመልከት። “ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና።” እነዚህም ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣሉ እና እርሱን ወይም እርስዋን እንዲሁም ሌሎችን ያረክሳሉ።
በመዝሙረ ዳዊት እንዲህ ተጽፎዋል፦ “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥ ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?” (መዝሙረ ዳዊት 8፡3-4)።
ጌታ የሚጎበኘን ለምንድነው? እርሱ የሚጎበኘን ስለሚወደን። እርሱ ፈጠረን፣ ወደደን፣ ለኃጢአተኞችም አዘነን። እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ደምስሶ ሕዝቡ አደረገን። “ጌታ ሆይ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ ምን ያህል ጥሩ ነው፥ ክብርህን ከሰማይ በላይ ያደረገ ማነው!” (መዝሙረ ዳዊት 8፡1) ንጉሥ ዳዊት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህንን መዝሙር የዘመረው እግዚአብሔር የኃጢአተኞች አዳኝ እንደሚሆን በተረዳ ጊዜ ነበር።
በአዲስ ኪዳንም ሐዋርያው ጳውሎስ ተመሳሳይ ነገር ተናገረ። እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረታት የእርሱ ልጆች መሆን መቻላችን እንደዚህ ያለ አስገራሚ ነገር ነው። የሚፈጸመው ለእኛ ባለው ርኅራኄ ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነው።
ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ሕግ ለመኖር መሞከር በአንድ በኩል እርሱን መገዳደር ነው። ከድንቁርናችን የሚመነጭም የዕብሪት አሳብ ነው። ሕጉን ለመጠበቅ እና ለመጸለይ በሚታገልበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ፍቅር ውጪ መኖር ትክክል አይደለም። በሕግ በኩል ኃጢአተኞች መሆናችንን እንድንገነዘብና በውሃና በደም (በመንፈስ) ቤዛነት እንድናምን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
የእርሱ ቃል በማርቆስ 7፡20-23 እንዲህ ተጽፎዋል፦ “እርሱም አለ፦ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፦ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።”
ኢየሱስ ሰዎችን የሚያረክሱት ከእነርሱ ውስጥ የሚወጡት በውስጥ ያሉት ኃጢአቶች እንደሆኑ ተናግሮዋል። እግዚአብሔር የሰጠን ምግብ ሊያረክሰን አይችልም። ሁሉም ፈጠራዎች ንጹህ ናቸው፣ ነገር ግን ከአንድ ሰው የሚወጡት ነገሮች ብቻ ናቸው፣ ማለትም፣ ኃጢአቱ፣ ያረክሰዋል። ሁላችንም የአዳም ዘር ሆነን ተወልደናል። ታዲያ የምንወለደው እንዴት ነው? አስራ ሁለት ኃጢአቶችን ይዘን እንወለዳለን።
ታዲያ ያለ ኃጢአት መኖር እንችላለን? ከኃጢአት ጋር ስለተወለድን ኃጢአት በመስራት እንቀጥላለን። ሕጉን ስለምናውቅ ኃጢአት መስራት ማቆም እንችላለን? በትዕዛዛቶቹ መኖር እንችላለን? አንችልም።
አብዝተን በሞከርን ቁጥር እየከበደን ይሄዳል። ገደቦቻችንን ማወቅና መተው ይገባናል። ያን ጊዜ ትሁት በሆኑ ልቦች የሚያድነንን የኢየሱስን ጥምቀትና ደም መቀበል እንችላለን።
ሁሉም 613 የእግዚአብሔር ሕግ አንቀጾች ትክክል እና ፍትሃዊ ናቸው። ሰው ግን በእናቱ ማህጸን ውስጥ ከተጸነሰ ጊዜ ጀምሮ ኃጢአተኛ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል መሆኑን ስንገነዘብ፣ ነገር ግን በራሳችን ጻድቃን መሆን የማንችል ኃጢአተኞች ሆነን እንደተወለድን ስናውቅ፣ የእግዚአብሔር ርኅራሄ እንደሚያስፈልገን እና በውሃ፣ በደም እና በመንፈስ በኢየሱስ ቤዛነት መዳን እንደሚያስፈልገን እንገነዘባለን። ገደቦቻችንን ስንገነዘብ፣ በራሳችን ጻድቃን መሆን እንደማንችልና ስለ ኃጢአቶቻችንም ወደ ገሃነም እንደምንሄድ ስናውቅ፣ በኢየሱስ ቤዛነት ላይ ከመደገፍ በቀር ሌላ አማራጭ የለንም።
በራሳችን በእግዚአብሔር ፊት ትክክልም ጥሩም መሆን እንደማንችል ማወቅ አለብን። ስለዚህ፣ ወደ ገሃነም የምንሄድ ኃጢአተኞች መሆናችንን በእግዚአብሔር ፊት መቀበል አለብን፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ ከኃጢአቴ አድነኝ እና አዘነልኝ” በማለት እግዚአብሔር እንዲራራልን ልንጸልይ ይገባናል። ያን ጊዜ እግዚአብሔር በእርግጥ በቃሉ ይገናኘናል። በዚህ መንገድ፣ እኛ መዳን እንችላለን።
እኛ የዳዊትን ጸሎት እንደ እግዚአብሔር የተጻፈ ቃል መመልከት ይቀናናል። “በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ” (መዝሙረ ዳዊት 51፡4)።
ዳዊት ወደ ገሃነም ሊጣል የሚችል ክፉ የሆነ የኃጢአት ጅምላ መሆኑን ያውቅ ነበር፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት አምኖ ተቀበለ። “ጌታ ሆይ ኃጢአተኛ ብለህ ከጠራኸኝ ኃጢአተኛ ነኝ፤ ጻድቅ ብትለኝ ጻድቅ ነኝ፤ ካዳንከኝ እድናለሁ፤ ወደ ገሃነም ከላክኸኝ ደግሞ ወደ ገሃነም እገባለሁ።”
ትክክለኛው እምነት ይህ ነው። የዳንነው በዚህ መንገድ ነው። በኢየሱስ ቤዛነት ለማመን ዝግጁ እንሆን ዘንድ ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ልንሆን የሚገባን እንደዚህ ነው።
 
 

ኃጢአቶቻችን ምን እንደሆኑ በትክክል ማወቅ አለብን

 
ሁላችንም የአዳም ዘሮች ስለሆንን ሁላችንም በልቦቻችን ውስጥ ፍትወቶች አሉብን። ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ይነግረናል? እርሱ እንዳናመነዝር ይነግረናል። በልቦቻችን ውስጥ ነፍስ ማጥፋት አለ፣ እግዚአብሔር ግን ምን ይነግረናል? እግዚአብሔር እንዳንገድል ይነግረናል። ሁላችንም በልቦቻችን በወላጆቻችን ላይ እናምጽባቸዋለን፣ እርሱ ግን እንድናከብራቸው ይነግረናል። የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ትክክል እና መልካም እንደሆነ እና ሁላችንም በልባችን ኃጢአት እንዳለን ልንገነዘብ ይገባናል።
ይህ ትክክል ነው ወይስ አይደለም? ፈጽሞ ትክክል ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ምን ማድረግ ይገባናል? እኛ የኃጢአት ጅምላች፣ ተስፋ የለሽ ኃጢአተኞች መሆናችንን መቀበል አለብን። ትናንት መልካም ሥራ ስለሠራን ጻድቃን ነን፣ ዛሬ ኃጢአት ስለሠራን ኃጢአተኞች ነን ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም። ኃጢአተኞች ሆነን የተወለድን ነን። ምንም ነገር ብናደርግ አሁንም ኃጢአተኞች ነን። በኢየሱስ ውሃ እና ደም መቤዠት ያለብን ለዚህ ነው።
ኃጢአተኞች የሆንነው በምግባሮቻችን ማለትም በማመንዘር፣ ነፍስ በመግደል፣ በሌብነት ወዘተረፈ አይደለም፣ ኃጢአተኞች የሆንነው ኃጢአተኞች ሆነን ስለተወለድን ነው። አስራ ሁለት አይነት ኃጢአቶችን ይዘን ተወልደናል። በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኞች ሆነን ስለተወለድን በራሳችን ጥረቶች ከቶውኑም መልካም ልንሆን አንችልም። በጎ መስሎ መቅረብ ብቻ ነው የምንችለው።
እኛ እንደ መግደል መስረቅና ወዘተረፈ ያሉ በኃጢያት የተሞሉ ልቦናዎችን ይዘን ተወልደናል። እንግዲያው፣ እነዚህን ኃጢአቶች ስላልሠራን ብቻ ጻድቅ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? በራሳችን በእግዚአብሔር ፊት ፈጽሞ ጻድቃን ልንሆን አንችልም። ጻድቃን ነን ብንል ይህ ግብዝነት ነው። ኢየሱስ ፈሪሳውያንንና ጸሐፍትን ‘ግብዝ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት’ ብሎ ጠራቸው። ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው ተወልደዋል። በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ይሠራሉ።
በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ከማንም ጋር አልተጣላሁም፣ ማንንም አልደበደብኩም፣ መርፌም ብትሆን ከማንም አልሰረቅሁም የሚል ማንኛውም ሰው እየዋሸ ነው፣ ምክንያቱም ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው ተወልደዋልና። ያ ሰው ውሸታም፣ ኃጢአተኛና ግብዝ ነው። እግዚአብሔር እነርሱን የሚያየው እንደዚህ ነው።
እናንተ ኃጢአተኛ ሆናችሁ የተወለዳችሁ ናችሁ። አንዲት የኃጢአት ድርጊት ባትሰሩ እንኳን ወደ ገሃነም የምትሄዱ ናችሁ። ከሕጉና ከትዕዛዛቱ አብዛኛውን ብትጠብቁም አሁንም ወደ ገሃነም ለመሄድ የታጫችሁ ኃጢአተኞች ናችሁ።
ታዲያ እንዲህ ባለው ዕጣ ፈንታ ፊት ምን ማድረግ ይገባናል? እግዚአብሔር እንዲራራልን ልንጠይቀውና ከኃጢአቶቻችን ለመዳንም በእርሱ ላይ ልንደገፍ ይገባናል። ጌታ ካላዳነን ገሃነም እንወርዳለን። ዕጣ ፈንታችን ይህ ነው።
የእርሱን ቃል የተቀበሉ ሰዎችም እንደዚሁ በእርግጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አምነው ይቀበላሉ። እነርሱ ጻድቃን እንደሆኑም ያውቃሉ። ስለዚህ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይገነዘቡ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መተው ኃጢአት እንደሆነ ያውቃሉ። የእርሱን ቃል የተቀበሉ ሰዎች ከዚህ ቀደም ኃጢአተኞች ቢሆኑም ጻድቃን ናቸው። ዳግመኛ ከቃሉ ተወልደው የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቀበሉ። በእጅጉም የተባረኩ ናቸው።
 
 
በሥራቸው ለመዳን የሚሞክሩ ሰዎች አሁንም ኃጢአተኞች ናቸው
 
በኢየሱስ ካመኑ በኋላም አሁንም ኃጢአተኞች የሆኑት እነማን ናቸው?
በድርጊታቸው ለመዳን የሚሞክሩ ሰዎች ናቸው
 
ገላትያ 3፡10 እና 11ን እንመልከት። “ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና። ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።”
በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎዋል። በኢየሱስ የሚያምኑ ነገር ግን በሥራዎቻቸው ለመጽደቅ የሚሞክሩ ሰዎች የተረገሙ ናቸው። በሥራዎቻቸው ለመጽደቅ የሚሞክሩ ሰዎች ያሉት የት ነው? ከእግዚአብሔር እርግማን በታች ናቸው።
እግዚአብሔር ሕጉን ለምን ሰጠንው? እርሱ ሕግን የሰጠን ኃጢአቶቻችንን እንድንገነዘብ ነው (ሮሜ 3፡20)። እኛ ሙሉ ኃጢአተኞች መሆናችንን እና ወደ ገሃነም እንድንሄድ መወሰናችንን እንድንገነዘብ።
የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው የኢየሱስ ጥምቀት እመኑ፣ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ ትወለዱ። ያን ጊዜ ከኃጢአቶቻችሁ ድናችሁ ጻድቃን ትሆናላችሁ፣ የዘላለም ሕይወትን ታገኛላችሁ፣ መንግሥተ ሰማይ ትገባላችሁ። በልቦቻችሁ ውስጥ እምነት ይኑራችሁ።
 
 
በዓለም ላይ እጅግ ዕብሪተኛው ኃጢአት
 
በዓለም ላይ እጅግ ዕብሪተኛው ኃጢአት ምንድነው?
በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት ለመኖር መጣር እጅግ ዕብሪተኛው ኃጢአት ነው
 
እግዚአብሔርን ከማመን የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም። በእርሱ በረከት እምነት ስላለን ተባርከናል። እግዚአብሔር በእርሱ ቃል ላይ እምነት ያላቸውን ለማዳን ወሰነ።
ዛሬ ግን በምዕመናኖች መካከል በእግዚአብሔር ሕግ ለመኖር የሚሞክሩ ብዙ ክርስቲያኖች አሉ። አብዛኞቹ ክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው። በሕጉ ለመኖር መሞከራቸው የሚያስመሰግን ነው፣ ነገር ግን ይህ እንዴት ይቻላል?
በእግዚአብሔር ሕግ ለመኖር መሞከር ምን ያህል ሞኝነት እንደሆነ መገንዘብ አለብን። አብዝተን በሞከርን ቁጥር ይበልጥ እየከበደ ይሄዳል። እርሱ እንዲህ አለ፦ “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” (ሮሜ 10፡17)። ለመዳን ዕብሪታችንን መጣል ያስፈልገናል።
 
 

ለመዳን የራሳችንን መለኪያዎች መተው ይኖርብናል

 
ለመዳን ምን ማድረግ አለብን?
የራሳችንን መመዘኛዎች መተው አለብን።
 
ሰው መዳን የሚችለው እንዴት ነው? ይህ የሚቻለው እነርሱ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ሲያውቁ ብቻ ነው። የተሳሳቱ አመኔታዎቻቸውንና ጥረቶቻቸውን መተው ባለመቻላቸው ምክንያት እስከ አሁን ድረስ ያልዳኑ ብዙ ሰዎች አሉ።
እግዚአብሔር ሕጉን አጥብቀው የያዙ ሰዎች የተረገሙ ናቸው ይላል። በኢየሱስ ካመኑ በኋላ በሕጉ ለመኖር በመሞከር ቀስ በቀስ ጻድቃን እንደሚሆኑ የሚያምኑ ሰዎች የተረገሙ ናቸው። በእግዚአብሔር ያምናሉ፣ ነገር ግን አሁንም ለመዳን በህጉ መሰረት መኖር አለባቸው ብለው ያስባሉ።
ውድ ወዳጆቼ ሆይ፣ በሕይወት እያለን በሥራዎቻችን ጻድቃን መሆን እንችላለን? እኛ ጻድቃን መሆን የምንችለው በኢየሱስ ቃል በማመን ብቻ ነው፣ ቤዛነትን የምናገኘው ያን ጊዜ ብቻ ነው። በኢየሱስ ጥምቀት፣ በደሙ እና ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ በማመን ብቻ ድነናል።
ለዚህም ነው እግዚአብሔር የእምነትን ሕግ ጻድቅ የምንሆንበት መንገድ አድርጎ ያዘጋጀልን። የውሃውና የመንፈሱ ቤዛነት ያረፈው በሰዎች ሥራዎች ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል እምነት ላይ ነው። እግዚአብሔርም በዚያ እምነት ላይ አድኖናል። እግዚአብሔር ደህንነታችንን ያቀደውና የፈጸመው እንደዚህ ነው።
ሰዎች በኢየሱስ ቢያምኑም የማይድኑበት ምክንያት ምንድን ነው? የውሃውንና የመንፈሱን ቤዛነት ቃል ስላልተቀበሉ ነው። እኛ ግን እንደነሱ ፍጽምና የጎደለን በእግዚአብሔር ቃል ስለ እምነታችን ተቤዠናል።
“ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች” (ማቴዎስ 24፡41)። የቀረው ሰው የሚያመላክተው ገና ቤዛነትን ያላገኘውን ሰው ነው። አንዱ ተወስዶ ሌላው የቀረው ለምንድነው?
ምክንያቱም አንዱ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በማመኑ ነው። ሌላው ግን ሕጉን ለመጠበቅ ጠንክሮ በመስራቱ ውሎ አድሮም ወደ ገሃነም ተጣለ። እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ለመንጠልጠል እየሞከረ ነበር፣ እግዚአብሔር ግን አንድ ተባይ በእግራችን ላይ እየተሳበ በሚወጣበት ጊዜ እንደምናራግፈው አራገፈው። ሰው ሕጉን ለመጠበቅ በመሞከር ወደ እግዚአብሔር እየተሳበ ለመንጠልጠል ቢሞክር በእርግጠኝት ወደ ገሃነም ይጣላል።
በውሃውና በመንፈሱ እምነት መዳን የሚኖርብን ለዚህ ነው።
“ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና።” “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው” (ገላትያ 3፡10-11፣ ሮሜ 1፡17)።
በእግዚአብሔር ቃል አለማመን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ቃል በራስ መለኪያዎች መሠረት ወደ ጎን ገሸሽ ማድረግም እንደዚሁ ኃጢአት ነው። እኛ ሰዎች ሁላችንም ኃጢያተኞች ሆነን ስለተወለድን በእግዚአብሔር ሕግ መኖር አንችልም። በሕይወት ዘመናችንም ሁሉ ኃጢአትን በመሥራት እንቀጥላለን። እዚህ ትንሽ ኃጢአት እንሠራለን፣ ትንሽ እዚያ እና በሄድንበት ቦታ ሁሉ። ሥጋችን ከኃጢአት በቀር ሊረዳ እንደማይችል መገንዘብ ይኖርብናል።
ሰው አንድ ትልቅ የዕበት ባልዲን ይመስላል። ያንን ዕበት ተሸክመነው ለመዞር ብንሞክር፣ በየመንገዱ እናንጠባጥበዋለን። እኛ እንደዛ ነን። በየሄድንበት ሁሉ ኃጢያትን ማፍሰስ እንቀጥላለን። ልታስቡት ትችላላችሁን?
አሁንም ድረስ ቅዱሳን ነን እያላችሁ ታስመስላላችሁን? ራስህን በግልጽ ብታይ፣ በከንቱ ቅዱስ ለመሆን መሞከርህን አቁመህ በኢየሱስ ውሃና ደም ታምን ነበር።
እኛ ግትርነታችንን ጥለን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢያተኞች መሆናችንንም መቀበል ይገባናል። ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቃል ተመልሰን እርሱ በውሃና በመንፈስ እንዴት እንዳዳናቸው ማወቅ አለብን። 

ይህ ስብከት በየኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት ቅርጸት ደግሞ ይገኛል። ከዚህ በታች ባለው የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ጠቅ ያድርጉ።
በውኑ በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ እትም]