Search

ခရစ်ယာန်ယုံကြည်မှုနှင့်ပတ်သက်သောမေးခွန်းများ

ဘာသာ ၁ - ရေနှင့်ဝိညာဥ်တော်အားဖြင့် ဒုတိယမွေးဖွားခြင်း

1-27. “ሐዋርያት በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ታላቅ አፅንዖት እንዳደረጉ” የሚያሳዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?

ከሁሉም በላይ፣ የእኛን ጥምቀት ትርጉም ከኢየሱስ ጥምቀት ትርጉም መለየት አለብን። የውሃ ጥምቀትን በመቀበል ብቻ ዳግም ልንወለድ አንችልም። ዳግም መወለድ የምንችለው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው። እንደ ጥምቀት ወይም ግርዘት ያሉ ሥርዓቶች ለእግዚአብሔር መዳን አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ የአማኞችን የውሃ ጥምቀት ለደህንነታቸው እንደ አስፈላጊ ነገር አይገልጽም። በፋንታው ኢየሱስ ከመጥምቁ ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት ላይ ትልቅ ትኩረት ያደርጋል።
የኢየሱስ ጥምቀት ለመዳናችን ወሳኝና አስፈላጊ እንደሆነ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች ይደግፋሉ። በመጀመሪያ፣ የኢየሱስ ጥምቀት በአራቱም ወንጌሎች በእያንዳንዳቸው ውስጥ ለሙሉ የጽድቅ ሥራው እንደ መግቢያ ሆኖ ተነግሯል። ለምሳሌ የማርቆስ ወንጌል የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚጀምረው በቀጥታ ከኢየሱስ ጥምቀት ነው። ዮሐንስም ወንጌልን የጻፈው ኢየሱስ ከተጠመቀበት ቀን ጀምሮ ‘በነገው’ (ዮሐንስ 1፡29) እና ‘በሦስተኛውም ቀን’ (ዮሐንስ 2፡1) የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም በቀን ቅደም ተከተል ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐንስ 1፡29) በማለት ኢየሱስ በተጠመቀ ቀን ማግስት የእግዚአብሔርን ቃል አወጀ። ይህ ምንባብ መጥምቁ ዮሐንስ እርሱን ባጠመቀው ጊዜ የዓለም ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ያሳያል። ከዚያም “ተፈጸመ” (ዮሐንስ 19፡30) በማለት ለኃጢአቶቻችን ማስተሰረያ በመስቀል ላይ ሞተ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሣ።
ሐዋርያው ጳውሎስም እንዲህ ብሎዋል፦ “መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3)። እዚህ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ብሉይ ኪዳንን ያመለክታል። በብሉይ ኪዳን አንድ ኃጢአተኛ ኃጢአቱን ለማስወገድ መሥዋዕትን ማቅረብ የሚችለው እንዴት ነበር? መሥዋዕቱን ከማረዱ በፊት በኃጢአት መሥዋዕቱ ራስ ላይ እጆቹን መጫን ነበረበት። “በኃጢአት መሥዋዕቱ ራስ ላይ እጆቹን የመጫን” ሂደትን ቢተው፣ ሕገ ወጥ መሥዋዕት በመሆኑ ኃጢአቱን ማስተሰረይ ባልቻለ ነበር።
ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎዋል፦ “ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን?” (ሮሜ 6፡3)። ታዲያ እኛ እንዴት ከኢየሱስ ጋር አንድ ሆነን ልንጠመቅ እንችላለን? በክርስቶስ ኢየሱስ መጠመቅ ማለት በእኛ የውሃ ጥምቀት ሳይሆን በዮርዳኖስ በሆነው የእርሱ ጥምቀት ማመን ነው። መጥምቁ ዮሐንስ እጆቹን በኢየሱስ ራስ ላይ በመጫን ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ወደ እርሱ ያስተላለፈ የመሆኑን እውነታ ስናምን በእርሱ ውስጥ እንጠመቃለን።
“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና” (ገላትያ 3፡27)። በመጥምቁ ዮሐንስ አማካይነት በእምነት ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ ወደ ኢየሱስ ያስተላለፉ ሰዎች ኃጢአት አልባ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነዋል።
“የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ” (ቆላስይስ 2፡11)። ሐዋርያው ጳውሎስ የሥጋን የኃጢአቶች ሰውነት በማስወገድ ከኃጢአት የመዳን መንገድ በእጅ ባልተደረገ መንፈሳዊ ግርዘት መገረዝ እንደሆነ ተናግሯል፤ (በሮሜ 2፡29 ላይ “መገረዝም የልብ መገረዝ ነው” ተብሎዋል)። ያም ማለት በልባችን ውስጥ ያሉትን ኃጢአቶች የሚቆርጥ የኢየሱስን ጥምቀት ማመን ነው።
“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21)። ጥምቀት የሚያድነን ምልክት ነው። ቀድሞውኑም እንደምናውቀው በኖህ ዘመን ሰዎች በውሃ ባለማመናቸው ጠፍተዋል። ዛሬም ቢሆን በኢየሱስ ያምናሉ ብለው የሚናገሩ ነገር ግን ውሃ የሆነውን የኢየሱስን ጥምቀት ስለማያምኑ የሚጠፉ ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎች አሉ።
ሐዋርያው ዮሐንስ በመጀመሪያው መልእክቱ ላይ እንዲህ ብሎ በመጻፍ ስለ ወንጌል ሁሉን ነገር ገልጧል፦ “በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም” (1ኛ ዮሐንስ 5፡6)። ኢየሱስ እኛን ከኃጢአቶቻችን ሁሉ ለማዳን በጥምቀቱና በመስቀሉ ወደ እኛ መጣ። ዮሐንስ እንዲህም ብሎዋል፦ “የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፦ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ” (1ኛ ዮሐንስ 5፡8)። ይህም የኢየሱስ ጥምቀት፣ መስቀሉና መንፈሱ ሁሉ በአንድ ላይ አንድ ፍጹም የሆነ መዳንን እንደሚያዋቅሩ ይነግረናል።
ኢየሱስ ኒቆዲሞስን እንዲህ አለው፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” (ዮሐንስ 3፡5)። እኛ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ተወልደናል። ለመዳንና መንፈስ ቅዱስን እንደ ስጦታ ለመቀበል የሚያስፈልጋችሁ ነገር ቢኖር በእርሱ የውሃ ጥምቀትና መስቀል ማመን ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “ዳግም መወለድ” የሚናገረው ይህንን ነው።
ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ ብሎዋል፦ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ (ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል) እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ” (የሐዋርያት ሥራ 2፡38)። የኃጢአቶችን ሁሉ ፍጹም መታጠብና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለማግኘት በኢየሱስ ጥምቀት ከሙሉ ልባችሁ የማይናወጥ እምነት ሊኖራችሁ ይገባል። ሌላ ምን ማለት እንችላለን? የእርሱ ጥምቀት ለመዳናችን የሚሆን ወሳኝ የጽድቅ ምግባር እንደሆነ ብዙ ምንባቦች የሚደግፉት መሆኑን አትካድ። ክርስትና ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል መመለስ አለበት።
“ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል፤ ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው” (ዕብራውያን 6፡1-2)። እዚህ ላይ የጥንቷን ቤተክርስቲያን እውነተኛ ወንጌል ለማግኘት ፍንጭ ማግኘት እንችላለን። እነርሱ አዲስ ክርስቲያን ለሆኑት ስለ ጥምቀቶች፣ እጆችን መጫን፣ ከሙታን መነሣትና የዘላለም ፍርድ አስተምረዋል።

ሁላችንም ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደና በእግዚአብሔር የጽድቅ ሕግ መሠረት ለኃጢአቶቻችን ለመኮነን በመስቀል ላይ እንደሞተ በልባችን ማመን ይገባናል።