Search

ခရစ်ယာန်ယုံကြည်မှုနှင့်ပတ်သက်သောမေးခွန်းများ

ဘာသာ ၃ - ဗျာဒိတ်ကျမ်း

3-5. የሺህው ዓመት መንግሥት መቼ ይጀምራል? (ይህ የቅድመ መከራ መ”ግሥት ነው ወይስ የድህረ መከራ መንግሥት?)    

 
ብዙ ሰዎች ቅዱሳን የሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ ከመምጣቱ በፊት ይነጠቃሉ፤ በዚህ የመከራ ጊዜም በዚህ ምድር ላይ ሳይሆን ቀድሞውኑም በሺህው ዓመት የክርስቶስ መንግሥት ውስጥ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን እምነት ከእግዚአብሄር ቃል ስናረጋግጠው ሐሳዊ እምነት እንደሆነ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡ 
ጌታ አምላካችን የክርስቶስን መንግሥት ለልፋታቸውና ለወንጌል ሲሉ ሕይወታቸውን ለመስጠታቸው ሽልማት ይሆናቸው ዘንድ ለሺህ ዓመት ስጦታ አድርጎ ይሰጣቸዋል፡፡ ዮሐንስ ራዕ 20፡4 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሄር ቃል ራሶቻቸው የተቆረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፣ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን፣ ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ፡፡›› 
ከላይ ያለው ምንባብ ወደ ሺህው ዓመት መግባት የሚችሉት እነማን እንደሆኑ ይገልጽልናል፡፡ እነዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ ከጸረ ክርስቶስ ጋር ተጋድለው እምነታቸውን ለመጠበቅ ሰማዕት የሆኑና የአውሬውን ምልክት ያልተቀበሉ ለምስሉም ያልሰገዱ ሰዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሄር ስንዴውን ከገለባው ለመለየት የሰው ዘር የአውሬውን ምልክት የመቀበል ወይም ያለ መቀበል ምርጫን ፈቅዶዋል፡፡ እግዚአብሄር ቅዱሳኖችን ለመንጠቅና ለእምነታቸውና በሰይጣን ላይ ለተቀዳጁት ድል የሺህ ዓመቱን የክርስቶስ መንግሥት በሽልማት ለመስጠት ስንዴውን ከገለባው በግልጽ መለየት ይፈልጋል፡፡ 
ጸረ ክርስቶስ እግዚአብሄርን እንዳይቃወም፣ ራሱንም ጣዖት አድርጎ እንዳያስመልክና ሰዎች ምልክቱን እንዳይቀበሉ እጅግ ታላቁ እንቅፋት የእግዚአብሄር ሕዝቦች ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ጸረ ክርስቶስ እነርሱን ለማጥፋት ጥረቶቹን ሁሉ ይጠቀማል፡፡ ቅዱሳን ግን ለአውሬው አያጎበድዱም፡፡ በእምነት ይዋጉታል፡፡ ሰማዕትነታቸውንም ይቀበላሉ፡፡ በዚያውም እግዚአብሄርን ያከብራሉ፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ቅዱሳኖችንም ከሞት በኋላ ያላቸውን ሕይወታቸውን ተስፋ በማድረግ በእግዚአብሄር ላይ ያላቸውን እምነት ይጠብቃሉ፡፡ ጸረ ክርስቶስ በታላቁ መከራ ወቅት በቅዱሳን ላይ እንዲህ ያለ ብዙ መከራን ሲያመጣ እግዚአብሄር ለእርሱና ለተከታዮቹ የሰባቱን ጽዋዎች መቅሰፍቶችና ለዘላለም የሚቃጠለውን የሲዖል ቅጣት አዘጋጅቷል፡፡     
ስለዚህ ይህ ዓለም በሰባቱ ጽዋዎች መቅሰፍቶችና ምድርን በሚመቱ ከዚህ ቀደም አይተው በማያውቁ በታላላቅ የመሬት መናወጦች ሙሉ በሙሉ ይጠፋል፤ ይወድማልም፡፡ ከዚህ የተነሳ የመጀመሪያው ዓለም ዱካውን ሳይተው ይጠፋል፡፡ ያን ጊዜ እግዚአብሄር ዘንዶውን ለሺህ ዓመት በጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ያስረው ዘንድ እንዲይዘው ለመልአኩ ትዕዛዝ ይሰጠዋል፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱሳን በሺህው ዓመት የክርስቶስ መንግሥት ውስጥ ይኖሩ ዘንድ መፍቀድ ከመቻሉ በፊት አስቀድሞ ዘንዶውን በጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ማሰር ይኖርበታልና፡፡ 
ሰይጣን ቅዱሳን ከክርስቶስ ጋር በሚነግሱበት በሺህ ዓመት መንግሥት ውስጥ ስለማይገኝ ከእንግዲህ ወዲህ አሳቾችም ሆኑ እርግማኖች አይኖሩም፡፡ ኢሳይያስ 35፡8-10 የመጀመሪያውን ትንሳኤ ያገኙ ቅዱሳን የሚቀበሉትን የክርስቶስን መንግሥት እንደሚከተለው አብራርቶታል፡- ‹‹በዚያም ጎዳናና መንገድ ይሆናል፤ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንፁሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፡፡ ለንፁሐን ግን ይሆናል፡፡ ተላላፊዎችና ሰነፎች እንኳን አይስቱበትም፡፡ አንበሳም አይኖርበትም፤ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤ ከዚያም አይገኙም፡፡ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፡፡ እግዚአብሄርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፡፡ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፡፡ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሴትንና ደስታን ያገኛሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ፡፡›› 
ከላይ እንደተጠቀሰው ለሺህ ዓመት የሚቆየው የክርስቶስ መንግሥት ይህች ምድር በሰባቱ ዓመት ታላቅ መከራ ውስጥ ካለፈችና ጸረ ክርስቶስም ሙሉ በሙሉ ከጠፋ በኋላ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ይህ መንግሥት ጌታችን ለተሰደዱት፣ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያላቸውን እምነት ለመጠበቅ ሲሉ ሰማዕት ለሆኑትና ይህንን ወንጌል ለመስበክም ለለፉት ቅዱሳን የሚሰጣቸው ሽልማት ነው፡፡