(1ኛ ጴጥሮስ 3፡20-22)
“ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም። ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤ እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።”
በምን አማካይነት ጻድቃን ሆንን? |
በእግዚአብሔር ፀጋ አማካይነት |
እኛ በዚህ ምድር ላይ ተወለድን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚህ ምድር ላይ ከመወለዳችን በፊት እንኳን አስቀድሞ አወቀን። ኃጢአተኞች ሆነን እንደምንወለድና የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በወሰደው ጥምቀቱ አማካይነት እኛን ምዕመናኖች በሙሉ እንደሚያድነን አወቀ። እርሱ አማኞችን ሁሉ አዳነና ሕዝቡ አደረጋቸው።
ይህ ሁሉ የእግዚአብሔር ፀጋ ውጤት ነው። በመዝሙረ ዳዊት 8፡4 ላይ እንዲህ ተባለ፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥ ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?” ከኃጢአቶች ሁሉ የዳኑት የእርሱን ልዩ ፍቅር የተቀበሉ ናቸው። እነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
የእግዚአብሔር ልጆች ከመሆናችን በፊት፣ ጻድቃን ከመሆናችን፣ ከመዳናችንና እርሱን አባት ብለን የመጥራት መብት ከመሰጠታችን በፊት በደሙና በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ያመንን ሰዎች ምን ነበርን? እኛ ኃጢአተኞች ነበርን፣ በዚህ ዓለም ላይ ጤናማ ከሆንን ከ60-70 ወይም ከ70-80 ዓመት ለመኖር የተወለድን ምንም ሌላ ነገር ያልሆኑ ኃጢአተኞች።
ከኃጢአቶቻችን ከመንጻታችን በፊትና በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ወንጌል እምነት ከመያዛችን በፊት መጥፋታችን እርግጥ የሆነ ጻድቃን ያልሆኑ ሰዎች ነበርን።
ሐዋርያው ጳውሎስ እርሱ የሆነውን የሆነው ከእግዚአብሔር ፀጋ የተነሳ እንደሆነ ተናገረ። ልክ እንደዚሁ እኛም አሁን የሆንነውን የሆንነው ፈጽሞ ከእርሱ ጸጋ የተነሳ ነው። ለፀጋው እናመሰግነዋለን። ፈጣሪ ወደዚህ ዓለም ወርዶ አዳነን፣ የእርሱ ልጆች ሕዝቦቹም አደረገን። ለውሃውና ለመንፈስ ቅዱስ የመዳን ፀጋው እናመሰግነዋለን።
እርሱ የእግዚአብሔር ልጆች እና ጻድቃን እንሆን ዘንድ የሚፈቅድበት ምክንያት ምንድነው? እግዚአብሔር ሲያየን የምናምር ስለሆንን ነውን? ወይስ እኛ የሚገባን ዋጋ ስላለን ነውን? ወይስ እኛ በጣም መልካሞች ስለሆንን ነውን? ስለዚህ ምክንያት እናስብ፣ ምስጋና ለማቅረብ ምክንያት ባለበት ምስጋና እናቅርብ።
ምክንያቱ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንድንሆን እና ከእርሱ ጋር በመንግሥተ ሰማይ እንድንኖር ስለፈጠረን ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንድንኖር ይፈቅድልን ዘንድ የእርሱ ሕዝብ አደረገን። እግዚአብሔር በዘላለም ሕይወት እኛን የባረከበት ብቸኛው ምክንያት ያ ነው። እርሱ የራሱ ሕዝብ ያደረገን ከሌሎች ፍጥረታቱ ይልቅ የበለጠ ውብ፣ የበለጠ ዋጋ ያለን፣ ወይም የበለጠ ንጹህ ሕይወት የምንኖር ስለሆንን አይደለም። ብቸኛው ምክንያት እርሱ እኛን መውደዱ ነው።
“ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21)። “ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20)።
የዳኑት ጥቂቶች ብቻ ማለትም ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ናቸው። ታዲያ እኛ ከሌሎች የተሻልን ነን? በፍጹም አይደለም። እኛ ያን ያህል ልዩ አይደለንም፣ ነገር ግን በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ባለን እምነት አማካይነት ግን ድነናል።
የእኛ መዳን ከተዓምራቶች መካከል ተዓምር ነው፣ እና እርሱን አባታችን፣ ጌታችን ብለን መጥራት መቻላችን ከእግዚአብሔር የተሰጠን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሆነ ስጦታና በረከት ነው። ይህንን በጭራሽ ልንክድ አንችልም። ገናም ኃጢአተኞች ብንሆን ኖሮ እርሱን እንዴት አባታችን ወይም ጌታችን ብለን ልንጠራው እንችላለን?
የዳንን መሆናችንን ስናስብ እግዚአብሔር ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደወደደን እናውቃለን። ከእርሱ ፍቅርና ባርኮቶች ባልሆነ ኖሮ፣ ምንም ትርጉም ሳይኖረን ተወልደን እንሞት ነበር፣ እና ሁላችንም ወደ ሲዖል እንሄድ ነበር። እግዚአብሔርን ለባርኮቶቹና በእርሱ ዓይኖች ፊት ልጆቹ እንሆን ዘንድ ብቁዎች ስላደረገን ደጋግመን እናመሰግነዋለን።
በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት የተሰጠን የከበረ ድኅነት
በኖህ ዘመን የነበሩት ሰዎች የጠፉት ለምንድነው? |
በውሃው (በኢየሱስ ጥምቀት) ባለማመናቸው ነው። |
“ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል።” በ1ኛ ጴጥሮስ ላይ በውሃ አማካይነት ስምንት ሰዎች ብቻ እንደዳኑ ተጽፎዋል። በኖህ ዘመን ምን ያህል ሰዎች ነበሩ? ምን ያህል እንደነበሩ የምናውቅበት መንገድ መንገድ የለም፣ ነገር ግን ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ ብለን እንገምት። ከሚሊዮን ሰዎች መካከል በኖህ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ 8 ሰዎች ብቻ ዳኑ።
ተመጣጣኝነቱ ከዛሬው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። እነርሱ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ከ8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች አለ ይላሉ። ዛሬ በኢየሱስ በሚያምኑት ሰዎች መካከል ምን ያህል ሰዎች ከኃጢአቶቻቸው ነጽተዋል? አንድ ከተማን ብቻ ብንመለከት ከእነርሱ በጣም ጥቂቶች ብቻ ይሆናሉ።
250,000 ሰዎችን በያዘችው ከተማ ውስጥ ስንቶች ከኃጢአቶቻቸው ተቤዥተዋል—ምናልባት 200? ታዲያ ተመጣጣኝነቱ ምን ያህል ይሆናል? ይህ ማለት የቤዛነትን በረከት የተቀበለው ከሺህው ውስጥ ከአንድም ያነሰ ነው ማለት ነው።
በኮርያ ካቶሊኮችን ጨምሮ ወደ 12 ሚሊዮን የሚጠጉ ክርስቲያኖች እንዳሉ ይገመታል። ከእነዚህ መካከል፣ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ እንደገና የተወለዱት ምን ያህል ናቸው? በኖህ ዘመን ከመላው የምድር ሕዝብ ውስጥ 8 ሰዎች ብቻ እንደዳኑ በአእምሮዋችን መያዝ አለብን። ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን እንደወሰደ የሚያምኑ ሰዎችን ኃጢአቶች በሙሉ እንዳነጻ ማወቅና ማመን አለብን።
ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ሁላችንንም እንደዋጀን የሚያምኑ ብዙዎች አይደሉም። ታዋቂ የሆነውን ‘የኢየሱስን ትንሳኤ’ ስዕል ተመልከቱ። እዚያ ላይ ምን ያህል ትንሣኤን ያገኙ ሰዎች ይታያሉ? ከእነርሱ መካከል የሥነ መለኮት ሊቃውንት ምን ያህሎቹ ናቸው?
ዛሬ በዓለም ላይ ብዙ የሥነ መለኮት ሊቃውንቶች አሉ፣ ነገር ግን የኢየሱስ ጥምቀት ወሳኝ የቤዛነት እውነት መሆኑን የሚያውቁና የሚያምኑ በጣም ጥቂቶች ሆነው እናገኛለን። አንዳንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ኢየሱስ የተጠመቀበት ምክንያቱ ትሁት ስለነበር ነው ይላሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ እርሱ የተጠመቀው ይበልጥ ሌሎች ሰዎችን ለመምሰል ነው ይላሉ።
ነገር ግን ጴጥሮስንና ዮሐንስን ጨምሮ ሐዋርያት በሙሉ የኢየሱስ ጥምቀት ኃጢአቶቻችን ወደ እርሱ የተላለፉበት እንደሆነ በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ መመስከራቸው ተጽፎዋል፣ እኛም ይህንኑ እናምናለን።
ሐዋርያት በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ኃጢአቶቻችን በጥምቀቱ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ መሰከሩ። ይህ በዚህ በማመን ብቻ መዳን የምንችል መሆናችንን የሚያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ እጅግ አስደናቂ ምስክርነት ነው።
በቤዛነት ጥምቀት ላይ ምንም አይነት ‘ምናልባት’ የሚባል ነገር የለም
የእግዚአብሔርን ወሰን የለሽ ፍቅር የሚያገኘው ማነው? |
በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምን ሰው ነው |
የሐይማኖት ድርጅቶች በሙሉ በአመኔታዎቻቸው ውስጥ ስለ መዳናቸው ተማምነዋል፣ ብዙ ሰዎችም የኢየሱስ ጥምቀት የክርስቲያን ማህበረሰብ ዶግማ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ። ይህ ግን እውነት አይደለም። ከአነበብኳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ መጽሐፎች መካከል፣ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ውስጥ ያለውን ቤዛነት እና ድኅነት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ ስለ ድኅነት የሚናገር አንድም መጽሐፍ ማግኘት አልቻልኩም።
በኖህ ዘመን 8 ሰዎች ብቻ ዳኑ። ዛሬ ምን ያህል እንደሚድኑ አላውቅም፣ ምናልባት ግን ብዙ አይደሉም። የዳኑ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምኑ ሰዎች ናቸው። ብዙ ቤተክርስቲያኖችን በመጎብኘት ላይ እያለሁ፣ የእውነት ወንጌል የሆነውን የኢየሱስን የጥምቀት ወንጌል የሚሰብክ ማንም እንደሌለ በተደጋጋሚ እረዳለሁ።
በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ቤዛነት ካላመንን ገናም ኃጢአተኞች ነን። (ምንም ያህል በታማኝነት ወደ ቤተክርስቲያን መሄዳችን ከቁም ነገር የሚገባ አይደለም።) በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በታማኝነት ቤተክርስቲያን እንሄድ ይሆናል። ነገር ግን አሁንም በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት ካለ ገናም ኃጢአተኞች ነን።
ለ50 ዓመታት ያህል ቤተክርስቲያን ሄደን ከሆነና ነገር ግን አሁንም ድረስ በልቦቻችን ውስጥ ኃጢአት ካለ የ50 ዓመታት እምነታችን ውሸት እንጂ ምንም ነገር አይደለም። የአንድ ቀን እውነተኛ እምነት መያዝ በጣም የተሻለ ነው። በኢየሱስ በሚያምኑ መካከል መንግሥተ ሰማይ የሚገቡት በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ ትርጉም በትክክል የሚያምኑ ብቻ ናቸው።
እውነተኛ እምነት የእግዚአብሔር ልጅ ወደዚህ ምድር የመውረዱንና የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ለመውሰድ የተጠመቀ የመሆኑን እውነት ማመን ነው። መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባን ይህ እምነት ነው። ኢየሱስ ለእናንተና ለእኔ በመስቀል ላይ እንደደማም ደግሞ ማመን ይገባናል። እርሱን ለማመስገን ደግሞ ይህንን ማወቅ ይገባናል።
እኛ ምንድነን? እኛ በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የዳንን የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነን። እንዴት እርሱን ላናመሰግነው እንችላለን? ኢየሱስ እኛን ለማዳን 30 ዓመት ሲሆነው በዮርዳኖስ ተጠመቀ። በዚህም ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ወሰደና በመስቀል ላይ ስለ እኛ ፍርድን ተቀበለ።
ስለዚህ ነገር ስናስብ እርሱን በትህትና ከማመስገን በቀር ልናደርገው የምንችለው ነገር የለም። ኢየሱስ በዚህ ዓለም ያደረገው እያንዳንዱ ነገር ለድኅነታችን የተደረገ ነገር እንደነበር ማወቅ ይገባናል። ኢየሱስ መጀመሪያ ወደዚህ ዓለም መጣ። ተጠመቀ፣ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሣ፣ አሁን በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦዋል።
የእግዚአብሔር ቤዛነት ያለ ምንም ልዩነት ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው። የኢየሱስ ድኅነት በሙሉ ለእናንተና ለእኔ ነው። ለፍቅሩና ለባርኮቶቹ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
እንዲህ የሚለውን የወንጌል መዝሙር እናውቀዋለን። “♫ውብ ታሪክ አለ። በዓለም ላይ ካሉ ብዙ ሰዎች መካከል የእርሱ ፍቅርና ድኅነት ያለኝ እኔ ነኝ። ኦ የእርሱ ፍቅር ምንኛ ግሩም ነው! ለእኔ ያለው ፍቅር፣ ለእኔ ያለው ፍቅር። ውብ ታሪክ አለ። በዓለም ላይ ካሉ ብዙ ሰዎች መካከል፣ እኛ የዳንንና የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆንን ነን። የእርሱ ፍቅር ለብሰናል። ኦ የእግዚአብሔር ፍቅር የእግዚአብሔር ጸጋ። ኦ ፍቅሩ እንደምን አስገራሚ ነው! ለእኔ ያለው ፍቅሩ።♫”
ኢየሱስ እናንተንና እኔን ለማዳን ወረደ፣ እናም የጥምቀቱ ቤዛነትም እንዲሁ ለእናንተና ለእኔ ነው። ወንጌል የተረት ታሪክ ብቻ አይደለም፣ ከልፋት ሕይወታችን አውጥቶ ወደ ውብ የእግዚአብሔር መንግሥት ከፍ የሚያደርገን እውነት ነው። እምነት በእግዚአብሔርና በእኔ መካከል ያለ ግንኙነት ነው።
እርሱ እኛን ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጣ። ኃጢአቶቻችንን ለማንጻትም ተጠመቀና በመስቀል ላይ ፍርድን ተቀበለ።
እውነትን የሚያምኑ ሰዎች እግዚአብሔርን አባታቸው አድርገው መጥራታቸው እንዴት ያለ በረከት ነው! ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ማመን የምንችለውና በእምነታችን ከኃጢአት የምንድነው እንዴት ነው? ይህ የሚቻለው እርሱ ለእኛ ካለው ወሰን የለሽ ፍቅሩ የተነሳ ነው። እኛ አስቀድሞ ከወደደን ከእርሱ የተነሳ ድነናል።
ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ አንድ ጊዜ ለሁሉም አነጻ
“ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡18)። ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤዛነታችን ተጠመቀና ዓመጸኞች የሆንነውን እናንተንና እኔን ለማዳን አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ሞተ።
እኛ የዳንነው ለአንዴና ለመጨረሻ ነው ወይስ ቀስ በቀስ? |
ለአንዴና ለመጨረሻ |
እኛ ለፍርዳችን በእግዚአብሔር ፊት መቆም እንዳይኖርብን፣ እርሱ አንድ ጊዜ በዚህ ምድር ላይ ሞተ። ኢየሱስ እኛ በእግዚአብሔር ፊት መንግሥተ ሰማያት እንድንኖር፣ በሥጋ ወደዚህ ዓለም መጣ፣ እናም በጥምቀቱ፣ በመስቀል ላይ በሞቱና በትንሣኤው ኃጢአቶቻችንን ሁሉ አንድ ጊዜ ለሁሉም ፈጽሞ አነጻን።
ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በደሙ ሙሉ በሙሉ እንዳዳነን ታምናላችሁ? በእርሱ ጥምቀትና ደም ወንጌል የማታምኑ ከሆናችሁ ልትዳኑ አትችሉም። እኛ በጣም ደካሞች ስለሆንን ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ለአንዴና ለመጨረሻ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ፈጽሞ እንዳነጻ ካላመንን ዳግም ልንወለድ አንችልም።
እርሱ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለመውሰድ ተጠመቀ፤ አንድ ጊዜ ለሁሉም ስለ እኛ በመስቀል ላይ ተኮነነ። ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ ቤዛነት የኃጢአተኞችን ኃጢአቶች በሙሉ አንድ ጊዜ ለሁሉም አነጻ።
ኃጢአት በሠራን ጊዜ ሁሉ ንስሐ መግባት፣ ሁልጊዜም ጥሩዎችና ለጋሶች መሆንና ለቤተክርስቲያንም ብዙ ነገሮችን መለገስ ቢኖርብን ኖሮ ሰዎች ነንና ለመዋጀት አዳጋች ይሆንብን ነበር።
ስለዚህ፣ በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ማመን ለመዳናችን አስፈላጊ ነው። በውሃውና በደሙ ማመን አለብን። ዳግመኛ ለመወለድ መልካም ሥራዎችን መሥራት ብቻ አንችልም።
ለድሃው ምርጥ ልብሶችን መግዛት ወይም ለመጋቢዎች ጣፋጭ ምግቦችን ማቅረብ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም። ኢየሱስ የሚያድነው በእርሱ ጥምቀትና ደም የሚያምኑትን ብቻ ነው። እግዚአብሔር በኢየሱስ አማካይነት በጥምቀቱና በደሙ አንድ ጊዜ ለሁሉም እንዳዳነን ብናምን እንድናለን።
አንዳንዶች እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን ቢልም፣ ተጨማሪ አስተሳሰብ ሊሰጡት እንደሚገባ ሊያስቡ ይችላሉ። ይህ የእነርሱ ምርጫ ነው። እኛ ግን በተጻፈው መሠረት በእግዚአብሔር ቃል ማመን ይገባናል።
ዕብራውያን 10፡1-10 ላይ እርሱ ሁላችንንም አንድ ጊዜ ለሁሉም እንዳዳነን ተጽፎዋል። እግዚአብሔር በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ያመኑትን ሰዎች ለአንዴና ለመጨረሻ እንዳዳናቸው እውነት ነው። እኛም ይህንን ማመን አለብን። “♫እርሱ አንድ ጊዜ ሞተ፣ አንድ ጊዜ ለሁሉም አዳነን። ኦ ወንድሞች እመኑና ዳኑ። ሸክሞቻችሁን ከኢየሱስ ጥምቀት በታች አኑሩ።♫” ኢየሱስ አንድ ጊዜ በመጠመቅና አንድ ጊዜ ደሙን በማፍሰስ ከበደልና ከኃጢአቶች ሁሉ አንድ ጊዜ ለሁሉም አድኖናል።
“ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡18)። ኢየሱስ ኃጢአት የሌለበት አምላክ ነው፣ እርሱ ፈጽሞ አልበደለም። ሰዎችን ከኃጢአቶቻቸው ለማዳን በሥጋ ወደ እኛ መጣ። ተጠመቀና የዓመጸኞችን ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደ። ከኃጢአትና ከበደልም አዳነን።
ከውልደት እስከ ሞት ድረስ ያሉት የሰዎች ኃጢአቶች በሙሉ በተጠመቀ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል፣ እርሱ በመስቀል ላይ ሲደማና ሲሞትም ሁሉም ከፍርድ ድነዋል። እርሱ ለኃጢአተኞች ተጠመቀ፣ በኃጢአተኞች ፋንታም ሞተ።
ይህ የጥምቀቱ ቤዛነት ነው። ኢየሱስ ኃጢአተኞች የነበርነውን ሁላችንንም አንድ ጊዜ ለሁሉም አዳነን። እያንዳንዳችን ምን ያህል ደካሞች ነን! ኢየሱስ ከውልደታችን እስከ ሞታችን ድረስ ያሉትን ኃጢአቶች በሙሉ አዳነና በመስቀል ላይ ራሱን ለፍርድ አቀረበ። በኢየሱስ የሚያምን ሰው እርሱ በጥምቀቱና በደሙ አንድ ጊዜ ለሁሉም እንዳዳነን ማመን ይገባዋል።
እኛ ደካሞች ነን፣ ኢየሱስ ግን አይደለም። ኛ ታማኞች አይደለንም፣ ኢየሱስ ግን ነው። እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ለሁሉም አዳነን። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፡16)። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ሰጠን። እግዚአብሔር የዓለምን ኃጢአቶች ሁሉ ለማስወገድ፣ ልጁ ኢየሱስን እንዲጠመቅ አደረገ፣ ይህም ልጁ ለሰው ዘር ሁሉ ፍርድን እንዲቀበል ነው።
ይህ ምንኛ አስገራሚ መዳን ነው! ይህ ምንኛ አስገራሚ ፍቅር ነው! ለፍቅሩና ለመዳኑ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። እግዚአብሔር በኢየሱስ ውሃና ደም፣ በኢየሱስ ጥምቀትና ባፈሰሰው ደሙ፣ እንደዚሁም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ እውነታ የሚያምኑትን አድኖዋቸዋል።
ስለዚህ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች በኢየሱስ ጥምቀትና ደም እውነት በማመን መዳንና ጻድቃን ሆነውም የዘላለም ሕይወት ማግኘት ይችላሉ። ሁላችንም ይህንን ማመን አለብን።
ያዳነን ማነው? ያዳነን እግዚአብሔር ነበር ወይስ ያዳነን ከእርሱ ፍጥረቶች አንዱ ነበር? ያዳነን እግዚአብሔር የሆነው ኢየሱስ ነበር። እኛ የዳንነው በእግዚአብሔር ቤዛነት ስላመንን ነው፣ እና ይህም የቤዛነት መዳን ነው።
ኢየሱስ የመዳን ጌታ ነው
የ‘ክርስቶስ’ ትርጓሜ ምንድነው? |
ካህን፣ ንጉሥና ነቢይ |
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው። ኢየሱስ ማለት አዳኝ ማለት ሲሆን ክርስቶስ ማለትም ‘የተቀባው’ ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን ሳሙኤል ሳዖልን እንደቀባው ነገሥታቶችም ተቀብተዋል፣ ካህናቶችም ተቀብተዋል፣ ነቢይም ተልዕኮውን ለማገልገል መቀባት ነበረበት።
ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣና ለሦስት ተግባራት ተቀባ፦ እነዚያ ተግባራቶችም የካህን፣ የንጉሥና የነቢይ ተግባራት ነበሩ። እርሱ ሰማያዊ ካህን እንደመሆኑ የሰውን ኃጢአቶችን በሙሉ ለመውሰድ ተጠመቀ።
እርሱ የአባቱን ፈቃድ በመታዘዝ ራሱን በአብ ፊት የኃጢአት ቁርባን አድርጎ አቀረበ። “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ። በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ 14፡6)። ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በመውሰድና በመሰቀል በእርሱ የምናምነውን አዳነን።
“የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና” (ዘሌዋውያን 17፡11)። ኢየሱስ ከጥምቀቱ በኋላ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህም እኛ ምዕመናኖች መዳን እንችል ዘንድ ሕይወቱን በእግዚአብሔር ፊት የኃጢአት ደመወዝ አድርጎ አቀረበ።
በመስቀል ላይ ከሞተ በኋላ በሦስተኛው ቀን ተነሳ፣ እናም በእስር ቤት ለታጎሩት መንፈሶች ወንጌልን ሰበከ። ገና ያልተዋጁ ሰዎች በኃጢአት እስር ቤት ውስጥ ያሉ መንፈሳዊ እስረኞችን ይመስላሉ፣ ለእነርሱም ኢየሱስ የወንጌልን እውነት፣ የውሃውንና የደሙን ወንጌል ሰበከላቸው። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሰጥቶናል። በዚህ የሚያምን ማንኛውም ሰው ዳግም መወለድ ይችላል።
የኢየሱስ ጥምቀትና ደሙ ኃጢአተኞችን ያድናል
በእግዚአብሔር ፊት በጎ ሕሊና ሊኖረን የሚችለው እንዴት ነው? |
በኢየሱስ ጥምቀትና ደም እምነት ሲኖረን ነው |
ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን ነው፣ በ1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ላይ እንዲህ ተመሰከረ፦ “ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ።” የኢየሱስ ጥምቀት ውሃ ለኃጢአተኞች መዳን ግዴታ ነው።
ኢየሱስ በጥምቀቱ አማካይነት እነዚህን ኃጢአቶች በራሱ ላይ በመውሰድ የኃጢአተኞችን ሁሉ ኃጢአቶች አጥቧል። በኢየሱስ ጥምቀት ታምናላችሁን? ልቦቻችን በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ከኃጢአቶች ሁሉ ታጥበው እንደነጹ ታምናላችሁን? ልቦቻችን ከኃጢአቶች ሁሉ ታጥበው ነጽተዋል፣ ሥጋችን ግን አሁንም ኃጢአትን ይሠራል።
‘አንድ ሰው ተዋጀ’ ማለት ሰውየው ኃጢአት አይሠራም ማለት አይደለም። እኛ ኃጢአት እንሠራለን። ልቦቻችን ግን በእርሱ ጥምቀት ላይ ባለን እምነታችን የተነሣ ከኃጢአት ነጽተው ይቆያሉ። ይህም “የየሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡21) ማለት ነው።
ኢየሱስ ኃጢአቶቼን ስላጠበና እግዚአብሔርም ፍርድን ለእኔ ስለተቀበለ እንዴት በእርሱ አለማመን እችላለሁ? እግዚአብሔር የሆነው ኢየሱስ በጥምቀቱና በደሙ እንዳዳነኝ እያወቅሁ፣ እንዴት በእርሱ አለማመን እችላለሁ? እኛ በእግዚአብሔር ፊት ድነናል፣ አሁን ሕሊናችን ንጹህ ነው። በእግዚአብሔር ፊት ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን ፈጽሞ አላነጻም ማለት አንችልም፣ እግዚአብሔር አይወደንም ብለን መናገር እንደማንችል ሁሉ።
ሕሊናችን በእጅጉ ስሜታዊ ስለሆነ ስህተትን በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ ይነግረናል። ሕሊናችን ትንሽ እንኳን ከተረበሸ በኢየሱስ ጥምቀት ሳናምን ሙሉ በሙሉ ከኃጢአት ነጻ መውጣት አንችልም። በጎ ሕሊና እንዲኖረን ብቸኛው መንገድ ይህ ነው።
ሕሊናዎቻችን ካስቸገሩን ይህ ማለት አንድ የተሳሳተ ነገር አለ ማለት ነው። የኢየሱስ የጥምቀት ውሃ የኃጢአት ቆሻሻን ሁሉ ያነጻል። ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ በጥምቀቱ ወሰደና ንጹህ አድርጎ አጠበን። ይህንን በትክክል ስናምን ሕሊናዎቻችንም በእውነት መንጻት ይችላሉ። ሕሊናዎቻችን መንጻት የሚችሉት እንዴት ነው? በኢየሱስ ጥምቀትና ደም በማመን ነው። እያንዳንዱ ሰው ከውልደቱ ጀምሮ ክፉና ቆሻሻ ሕሊና አለው። ነገር ግን ኃጢአቶቻችን በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ካመንን ኃጢአቶቻችንን በሙሉ መደምሰስ እንችላለን።
ዳግም የተወለደ ሰው እምነት ይህ ነው። ይህ በንቃተ ሕሊናችሁ የምትቀበሉት አንዳች ነገር አይደለም። ሕሊናችሁ ንጹህ ነውን? ንጹህ የሆነው ጥሩ ሕይወት ስለኖራችሁ ነው ወይስ ንጹሕ የሆነው ኃጢአቶቻችሁ ወደ ኢየሱስ ስለተላለፉና እናንተም በእርሱ ስለምታምኑ ነው? ንጹህ ሕሊና ማግኘት የምትችሉት በዚህ እምነት አማካይነት ብቻ ነው።
ሕይወት ያላቸው ቃሎች አሉ፣ ሕይወት የሌላቸውም ቃሎች አሉ። የሰዎች ሁሉ ሕሊናዎች መንጻት የሚችሉት እንዴት ነው? እኛ ጻድቃን መሆንና በጎ ሕሊና መያዝ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ምሉዕ በሆነው የኢየሱስ ቤዛነት በማመን ነው።
በእርሱ ጥምቀት ማመን ይቀድሰናል ማለት የሥጋ ዕድፍ ተወግዶዋል ማለት ሳይሆን ሕሊናዎቻችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነጽተዋል ማለት ነው። እርሱ ለዚያ ሲል መጣ፣ ተጠመቀ፣ በመስቀል ላይ ሞተ፣ ከሙታን ተነሣ፣ አሁንም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦዋል።
ጊዜው ሲደርስ ኢየሱስ እንደገና ወደዚህ ዓለም ይመጣል። “ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል” (ዕብራውያን 9፡28)። እርሱን በጉጉት የምንጠብቀውንና በእርሱ ጥምቀትና ደም በማመን ኃጢአት አልባ የሆንነውን እኛን ለመውሰድ እንደሚመጣ እናምናለን።
የእምነት ክሊኒካዊ ሙከራ
ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ልንድን እንችላለንን?
|
ፈጽሞ አይቻልም |
በአንዱ ቤተክርስቲያናችን ያልታሰበ አነስተኛ ክሊኒካዊ ሙከራ እንዲካሄድ ሆነ።
የዚህ ቤተክርስቲያን ፓስተር ፓርክ የኢየሱስን የጥምቀት ትርጉም ሳያነሳ፣ በዓለም ላይ ኃጢአት እንደሌለ ለጥንዶቹ ነገራቸው። ባልየው ሌሎች ቤተክርስቲያኖች በሚሄድበት ጊዜ ስብከትን በሚሰማበት ወቅት መተኛት ያዘወትር ነበር፤ ምክንያቱም ፓስተሮች ሁሉ የኢየሱስን ጥምቀት በኩል የሚገኘውን ቤዛነት በመተው ወንጌልን ሲሰብኩ፣ በዚህም በየቀኑ እንዲጸጸት ያስገድዱት ነበር።
ነገር ግን በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ኃጢአቶቹ በሙሉ ወደ ኢየሱስ እንደተላለፉ ሲሰማ ሁለቱንም ዓይኖቹን፣ በልጥጦ ስብከቱን አደመጠ። ይህም ሚስቱ ከእርስዋ ጋር አብሮ ቤተክርስቲያን እንዲሄድ ለማሳመን የሚያደርገውን ጥረት አቀለለላት።
አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀመጠና ሮሜ 8፡1ን ሰማ። “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።” ያን ጊዜ ወዲያውኑ ‘አሃ አንድ ሰው በኢየሱስ ካመነ ኃጢአት የለበትም። እኔም በኢየሱስ ስለማምን ኃጢአት የለብኝም’ ብሎ አሰበ።
ስለዚህ ለሚስቱ ወንድምና ለብዙዎቹ ጓደኞቹ አንድ በአንድ ስልክ ደውሎ “በልባችሁ ውስጥ ኃጢአት አለን? እንግዲያውስ እምነታችሁ ትክክል አይደለም” አላቸው። በዚህ ሁኔታ ፓስተር ፓርክ ተሸበሸበ። ባልየው ስለ ኢየሱስ ጥምቀት አላወቀም፣ ነገር ግን አሁን ኃጢአት እንደሌለበት ለሁሉም ሰው ይሟገት ነበር።
ከዚያም ጥንዶቹ ችግሮች ይገጥሙዋቸው ጀመር። ሚስቲቱ ከባልዋ ይልቅ ይበልጥ ታማኝ ነበረች፤ ሚስቲቱ ከባልዋ ይልቅ ይበልጥ ታማኝ ነበረች፣ ነገር ግን በልብዋ ውስጥ አሁንም ኃጢአት ነበራት፣ ባልዋ ግን ኃጢአት እንደሌለበት ይናገር ነበር። ባልዋ ቤተክርስቲያን የሄደው ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፣ ነገር ግን ያለ ኃጢአት እንደሆነ ተናገረ።
ሚስት ሁለቱም በልቦቻቸው ውስጥ ኃጢያት እንዳለ እርግጠኛ ነበረች። ስለዚህ ነገርም መከራከር ጀመሩ። ባልዋ “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” ስለሚል ኃጢአት እንደሌለበት ተሟገተ። ሚስትም አሁንም ገና በልብዋ ውስጥ ኃጢአት እንዳለ ተከራከረች።
ከዚያ አንድ ቀን፣ ሚስቱ በዚህ ጉዳይ በጣም ተቆጣች፣ ስለዚህ ፓስተሩ ኃጢአቶች በሙሉ ወደ ኢየሱስ ተላልፈዋል ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ሄዳ ለመጠየቅ ወሰነች።
ስለዚህ አንድ ቀን የምሽት አገልግሎት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ ባልዋን ወደ ቤት ልካ ፓስተር ፓርክን ፊት ለፊት አግኝታ ጥያቄ ጠየቀችው። እንዲህ አለችው፣ “አንድ ነገር ልትነግረን እየሞከርህ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ነገር ግን የተደበቀ አስፈላጊ ክፍል እንዳለ እርግጠኛ ነኝ። እባክህ ምን እንደሆነ ነገረኝ።” ያን ጊዜ ፓስተር ፓርክ ከውሃውና ከመንፈስ ቅዱስ ወንጌል ስለ መወለድ ነገራት።
ከዚያም በሮሜ 8፡1 ላይ “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም” ተብሎ የተጻፈው ለምን እንደሆነ ወዲያውኑ ተረዳች። ወዲያውም አመነችና ዳነች። በመጨረሻም በክርስቶስ የሆኑት ሰዎች እንዳይኮነኑ ኃጢአቶቻችን በሙሉ በኢየሱስ ጥምቀት አማካይነት ወደ እርሱ እንደተላለፉ ተረዳች።
የተጻፈውን ቃልም መረዳት ጀመረች። በመጨረሻም የቤዛነት ቁልፉ የኢየሱስ ጥምቀት እንደነበርና እኛም በእርሱ ጥምቀት ቤዛነት ጻድቃን መሆን እንደቻልን አወቀች።
ባልዋ ወደ ቤቱ አልሄደም፣ ነገር ግን ውጭ ሆኖ እርስዋን ሲጠብቃት ነበር። “አሁን ተቤዥተሻልን?” በማለት ጠየቃት።
ነገር ግን ፓስተር ለሚስቱ የነገራትን ከሰማ በኋላ ግራ ተጋባ። ከዚህ በፊት ስለ ኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል ፈጽሞ ሰምቶ አያውቅም ነበር። ያለ ኢየሱስ ጥምቀትም እንኳን በልቡ ውስጥ ከእንግዲህ ወዲህ ኃጢአት እንደሌለው እርግጠኛ ነበር። ስለዚህ በቤታቸው ውስጥ እንደገና ተከራከሩ።
በዚህ ጊዜ አቋሙ ተገለበጠ። ሚስት ባልዋን በልቡ ውስጥ ኃጢአት አለው ወይስ የለውም በማለት ጫና አሳደረችበት። በኢየሱስ ጥምቀት ሳያምን እንዴት ያለ ኃጢአት ሊሆን እንደቻለ ጠየቀችው። ሕሊናውን በጥንቃቄ እንዲመረምር አበረታታችው። ሕሊናውን ሲመረምር አሁንም በልቡ ውስጥ ኃጢአት እንዳለበት ተገነዘበ።
ስለዚህ ወደ ፓስተር ፓርክ ሄዶ በልቡ ውስጥ ኃጢአት እንዳለ ተናዘዘ። እርሱም “እጆቻቸውን በሚለቀቀው ፍየል ራስ ላይ በሚጭኑበት ጊዜ ይህንን የሚያደርጉት ከማረዳቸው በፊት ነው ወይስ ካረዱት በኋላ ነው?” ብሎ ጠየቀ። እርሱ የውሃውንና የመንፈስ ቅዱስን ወንጌል ከዚህ በፊት ፈጽሞ ሰምቶ አያውቅም ነበር። ስለዚህ በእጅጉ ግራ ተጋብቶ ነበር።
የዚያ መንፈሳዊ ሙከራ ነጥብ ይህ ነበር። ኢየሱስ በዮሐንስ መጥምቁ አማካኝነት የዓለምን ሁሉ ኃጢአቶች ወደ እርሱ ለመውሰድ መጠመቅ ነበረበት። በመስቀል ላይ መሞት የሚችለው ያን ጊዜ ብቻ ነበር፣ ምክንያቱም የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና።
“እነርሱ እጆቻቸውን በመሥዋዕቱ ራስ ላይ የሚጭኑት ከመገደሉ በፊት ነበር ወይስ በኋላ?” እርሱ ይህንን የጠየቀው ስለ እጆች መጫንና ስለ ኢየሱስ ጥምቀት ግራ ስለተጋባ ነበር። ስለዚህ ፓስተር ፓርክ የኢየሱስን ጥምቀት ቤዛነት በዝርዝር አብራራለት።
በዚያች ቀን ባልየው ለመጀመሪያ ጊዜ የውሃውንና የመንፈስ ቅዱስን ወንጌል ሰማና ተዋጀ። አንድ ጊዜ ብቻ ወንጌልን ሰምቶ ዳነ።
ይህ የኢየሱስን ጥምቀት የሚመለከተውን ቃል ሳያነሳ፣ የተደረገ ሙከራ ነበር። ኃጢአት የለብንም ልንል እንችላለን፣ ነገር ግን ያለ ኢየሱስ ጥምቀት በእርግጥ አሁንም በልባችን ውስጥ ኃጢአት አለን። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት ኃጢአቶችን በሙሉ አንጽቷል ይላሉ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እንደሌለባቸው በተጨባጭ መናገር የሚችሉት በኢየሱስ ጥምቀትና ደም የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ናቸው።
ፓስተር ፓርክ በእነዚህ ጥንዶች አማካኝነት በኢየሱስ ጥምቀት ላይ ባለን እምነት በኩል የሚመጣውን ቤዛነት ሳይኖረን ከኃጢአቶቻችን ሙሉ በሙሉ መዋጀት እንደማንችል አረጋገጠ።
የመዳን እውነተኛ ምሳሌ፦ የኢየሱስ ጥምቀት
የመዳን እውነተኛ ምሳሌ ምንድነው? |
የኢየሱስ ጥምቀት |
“ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል።” ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በሙሉ ለማንጻትና ሕሊናችንንም እንደ በረዶ ነጭ ለማድረግ ወደ ዓለማችን መጣ። ኢየሱስ ሁሉንም በጥምቀቱ ስለወሰዳቸው ከኃጢአቶች ሁሉ ነጽተናል። እርሱ በጥምቀቱና በደሙ አዳነን። ስለዚህ፣ የሰው ዘር ሁሉ በእርሱ ፊት መንበርከክ አለባቸው።
እኛ በኢየሱስ በማመን ያድነናል። በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን እንዲሁም ወደ ሰማይ እንሄዳለን። በኢየሱስ በማመን ጻድቃን እንሆናለን። እኛ የንጉሥ ካህናት ነን። እግዚአብሔርን አባታችን ብለን መጥራት እንችላለን። የምንኖረው በዚህ ዓለም ላይ ነው፣ ነገር ግን ነገሥታት ነን።
በእርግጥ እግዚአብሔር በውሃውና በመንፈስ ቅዱስ ቤዛነት የምናምነውን ሰዎች እንዳዳነን ታምናላችሁን? ቤዛነታችን ያለ ኢየሱስ ጥምቀት ፈጽሞ ሙሉ ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔርና ኢየሱስ እውነተኛ ነው ብለው የሚቀበሉት እውነተኛ እምነት ኢየሱስ በጥምቀቱ፣ በመስቀሉና በመንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ እንዳዳነን ማመን ነው። ብቸኛው እውነተኛ እምነት ነው።
ኃጢያቶቻችን ኢየሱስ በጥምቀቱ በወሰዳቸው ጊዜ ነጽተዋል፤ እርሱ በመስቀል ላይ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜም ኃጢአቶቻችን በሙሉ ዋጋቸው ተከፍሎዋል። ክርስቶስ ኢየሱስ በውሃና በመንፈስ ቅዱስ አዳነን። አዎ! እናምናለን!
ይህ ስብከት በየኤሌክትሮኒክ መጽሐፍት ቅርጸት ደግሞ ይገኛል። ከዚህ በታች ባለው የመጽሐፉ ሽፋን ላይ ጠቅ ያድርጉ።