Search

خطبات

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 8-12] ማን ሊቃወመን ይደፍራል? ‹‹ሮሜ 8፡31-34››

‹‹ሮሜ 8፡31-34›› 
‹‹እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? እግዚአብሄር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው፤ የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሄር ቀን ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡›› 
 
 
በሮሜ 8፡31-34 ላይ ጳውሎስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማጠቃለልና ወደ መጨረሻ ድምዳሜው በማድረስ ክርስቶስ በምዕመናን ላይ ያለውን የማይነጠል ፍቅር ይመሰክራል፡፡ ይህ ምንባብ በእምነት ጫፍ ላይ የደረሰውን ታላቁን የደህንነት ደስታ ያውጃል፡፡ 
 
ጳውሎስ በሮሜ 8፡31 ላይ ‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?›› እኛም እንደ ጳውሎስ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በጊዜ ሒደት ውስጥ ሲያበራና ድክመቶቻችን ይበልጥ በተገለጡ ቁጥርም የላቀ የደህንነት ወንጌል ሲሆን ገጥሞናል፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ይበልጥ ባገለገልን ቁጥር ይበልጥ በእምነትና በደስታ እንሞላለን፡፡ 
 
ጳውሎስ ያመነበትን ወንጌል ‹‹ወንጌሌ›› (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡8) ብሎ ጠርቶታል፡፡ ጳወሎስ የመሰከረለት ወንጌል በኢየሱስ ጥምቀትና ደም ማመን እንደጂ ሌላ አይደለም፡፡ 
 
ጳውሎስ ‹‹ወንጌሌ›› ብሎ የሰበከው የሃይማኖት ሰዎች የሚያምኑበትን የመስቀል ወንጌል የሚጠቁም ሳይሆን ኢየሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ የመውሰዱን በረከት የሚያውጀውን የውሃና የመንፈሱ ወንጌል የሚጠቁም ነው፡፡ 
 
ይህ ወንጌል ጳውሎስን ታላቅ የድፍረት ሰው አደረገው፡፡ የሐጢያቶችን ይቅርታ ስለተቀበለ የእግዚአብሄር ጽድቅ ልቡን ሞልቶታል፡፡ ስለዚህ ልቡ በመንፈስ ቅዱስም ተሞልቷል፡፡ እርሱ ራሱን በሕይወቱ ሁሉ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመመስከር ራሱን ቀድሶ ሰጥቶዋል፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሰውን ዘር ሐጢያቶች በአንድ ጊዜ የመውሰድ ሐይልና ሥልጣን አለው፡፡ 
 
ታዲያ ጳውሎስ ያመነበትን የውሃና የመንፈስ ወንጌል መቃወም ማን ሊደፍር ይችላል? ማንም! ሮሜ 8፡31 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?››  በዚህ ዓለም ላይ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሰዎች ማን መቃወም ይችላል?  እግዚአብሄር የሰውን ዘር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ከዓለም ሐጢያቶች ካዳነ ሐይሉን በከንቱ መቀማት የሚችል ማነው? በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል  የሚያምኑትን ሰዎች በኢየሱስ ስም ብቻ የሚያምኑም ሆኑ ሰይጣን ራሱ ተዋግተው ሊያሸንፉዋቸው አይችሉም፡፡
 
 

እርሱ በአንድ ጊዜ አጽድቆናል፡፡ 

 
ሮሜ 8፡29-30 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኖአልና፡፡ አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡››  
 
ይህ እግዚአብሄር አብ ሐጢያተኞችን ሁሉ በክርስቶስ ለማዳንና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ጠርቶ በአንድ ጊዜ ሐጢያቶቻቸውን በማንጻት ልጆቹ ሊያደርጋቸው እንዳቀደ ይነግረናል፡፡ ጌታችን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያተኞችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ካዳነ እርሱ ያደረገውን ማን ሊቃወም ይችላል?
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የጸደቁትን መቃወምና ማሸነፍ  ማን ይችላል? ይህ ስሜት የሚሰጥ አይደለም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የጸደቁ ሰዎችን የሚቃወም ቢኖር የሚቃወመው ራሱን እግዚአብሄርን እንደሆነ ማወቅ አለባችሁ፡፡ ማናቸውንም ዋጋ ከፍላችሁ ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ለመዳን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለባችሁ፡፡ በአእምሮዋችሁና በልባችሁ የእውነትን ወንጌል የምትቃወሙ ከሆነ ከሐጢያቶቻችሁ መዳን አትችሉም፡፡ ለሲዖል ትኮነናላችሁ፡፡ 
   
 

የእግዚአብሄር ጽድቅ ያላቸውን ሰዎች ማንም ሊቃወማቸው አይችልም፡፡ 

 
‹‹እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?›› (ሮሜ 8፡31) እግዚአብሄር ከእኛ ጋር መሆኑ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንደወሰደና እንዳዳነን የሚናገረውን እውነታ ያመለክታል፡፡ ታዲያ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው የዳኑትን ሰዎች ማን ሊቃወማቸው ይችላል? ይህ እምነትም ስህተት ነው ማለት ማን ይችላል? ይህ የማይጠቅም ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሰዎች እምነት ተቀብሎዋል፡፡ 
 
ይህንን መቃወም የሚችል ማነው? ኢየሱስ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ወሰደ፡፡ በዚህ የሚያምኑ ሰዎች ተሳስተዋል ማለት የሚችል ማነው? ማንም! 
 
ጳውሎስ በሮሜ 6፡3 ላይ እንዲህ ብሎዋል፡- ‹‹ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደተጠመቅን አታውቁምን?›› ጳውሎስ ሐጢያቶቹ ሁሉ ወደ ኢየሱስ በተላለፉበትና በነጹበት በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ማመኑን መናገሩ ነው፡፡ በዚህም ጳወሎስ ከኢየሱስ ጋር ሞቶ ተነስቷል፡፡ 
 
ገላትያ 3፡27ም እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› ይህ ምንባብ ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ እንደወሰደ፣ ለእነዚህ ሐጢያቶችም በመስቀል ላይ እንደተሰቀለና እንደተነሳ ይነግረናል፡፡ ይህ ሁሉ የተደረገው በዚህ እውነት የሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ልጆች የመሆንን በረከት ሊለግሳቸው ነው፡፡ የጳውሎስ እምነት በኢየሱስ ውስጥ በመጠመቅ፣ ከእርሱ ጋር በመስቀል ላይ በመሞትና ከእርሱ ጋር በመነሳቱ አመኔታ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ በኢየሱስ ካመናችሁ ሐጢያቶቻቸው በሙሉ ነጽተዋል፡፡ እናንተም ከክርስቶስ ጋር በመነሳት የእግዚአብሄር ልጆች ሆናችኋል፡፡
 
‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ለመውሰድ በአጥማቂው ዮሐንስ እንደተጠመቀ የሚያምኑ ሰዎች በክርስቶስ ተጠምቀዋል፡፡ ከዚህ በላይ ከኢየሱስ ጋር በመስቀል ላይ እንደሞቱም ያምናሉ፡፡ በእምነታቸውም ከእርሱ ጋር ተነስተዋል፡፡ 
 
ስለዚህ በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ የሚያምን ማንኛውም ሰው ከሐጢያቶቹ ይድናል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ መሆኑ እርግጥ የሆነውን ያህል በክርስቶስ ጥምቀትና ደም በማመን ከሐጢያቶቻቸው የዳኑ ሰዎች የእግዚአብሄር ልጆች ይሆናሉ፡፡ ‹‹ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና፡፡›› በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን የእግዚአብሄር ልጆች ለመሆን የክርስቶስን ጽድቅ እንለብሳለን፡፡       
 
ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ጥምቀት የተናገረው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ትልቅ በረከት ስላገኘ ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ይህንን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የመጣውን በረከት ገና አልተቀበሉም፡፡ ብዙ ሰዎች ጳውሎስ የሰበከው ወንጌል በመስቀል ላይ ስለፈሰሰው ደም የሚተርክ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ እውነቱ ግን የኢየሱስን ጥምቀትና በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደም አጣምሮ የያዘውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ያመነና ያሰራጭ የነበረ ሰው መሆኑ ነው፡፡    
 
ታዲያ ዛሬ የኢየሱስ ተከታዮች ይህንን የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማያውቁት ለምንድነው? የዚህ ምክንያቱ በጥንቷ የቤተክርስቲያን ዘመን የተሰበከው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በጊዜ ሒደት መቀየሩ ነው፡፡ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ዘመን ምዕመናን በሙሉ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አምነው ሰብከዋል፡፡ 
 
ሆኖም በጊዜ ሒደት ውስጥ ወንጌል ተለውጦ የክርስቶስ ደም ብቻ ሆነ፡፡ የእርሱ ጥምቀትም በስፋት ተገለለ፡፡ ይህም አሁንም እንኳን ብዙ ሰዎች ከጥንቷ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ወንጌል ባፈነገጠው የመስቀል ላይ ደም ብቻ የሚያምኑት ለምን እንደሆነ ያብራራል፡፡ 
 
እነዚህ ሰዎች አሁንም በውስጣቸው ሐጢያት አለ፡፡ የእግዚአበሄር ጽድቅ የተገለጠበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ስለማያውቁ አሁንም ሐጢያተኞች ናቸው፡፡ በኢየሱስ እናምናለን ቢሉም ይህንን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይቃወማሉ፡፡ 
 
መንፈሳዊ ዕውር የሆነ ሰው ምን ሊያይ ይችላል? ዕውር ሰው አንድን ዝሆን በመዳሰስ ሊያውቀው ይሞክር ይሆናል፡፡ አንድ ዕውር ሰው የአንድን ዝሆን እግር በመዳሰስ የቆመ አምድ ነው ይል ይሆናል፡፡ ሌላ ዕውር ሰው ደግሞ አፍንጫውን ይነካና የሆነ ረጅም ነገር ነው ይል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም ከዚህ ቀደም ዝሆን አይተው አያውቁምና፡፡ ልክ እንደዚሁ መንፈሳዊ ዕውር ሰውም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ታላቅነት መናገር አይችልም፡፡ 
 
ስለዚህ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማያውቁ ሰዎች ሊሰበኩት አይችሉም፡፡ ያዩ ሰዎች አንድ ሰው በቃላቶች ሊያብራራ የሚሞክረውን ነገር በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ ዕውር ግን ይህንን ፈጽሞ ረዳት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ 
 
ሰዎች ሐጢያተኞች ሆነው ተወልደዋል፡፡ ከመወለዳችን ጀምሮ መንፈሳዊ ሐጢያተኞች በመሆናችን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት አናውቅም፡፡ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በራሳቸው አዲስ የክርስትና ትርጉም አዘጋጅተዋል፡፡ በኢየሱስ እናምናለን እያሉ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ብቻ  እያመኑ ሐጢያቶቻቸው እንዴት መንጻት ይችላሉ? ጊዜ እየነጎደ ሲሄድም ሐጢያቶቻቸው ይበልጥ እየተቆለሉ ይሄዳሉ፡፡ 
 
ደህንነት በኢየሱስ ደም ብቻ እንደሚገኝ የሚያምኑ ሰዎች ገና መንፈሳዊ ንቃት ያላገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ ኢየሱስ ግን በዮሐንስ 3፡5 ላይ በግልጽ ነግሮናል፡፡ ‹‹ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሄር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡›› ስለዚህ የእግዚአብሄር ልጆች በመሆን ክብር እንድንባረክና ወደ መንግሥቱ እንድንገባ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለብን፡፡ 
 
ጳውሎስ በውሃና በመንፈስ ወንጌል በማመኑ በእምነት እንዲህ አለ፡- ‹‹እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?›› (ሮሜ 8፡31) የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማያውቁ ሰዎች የእግዚአብሄርን ልጆች ሊቃወሙ ይቸላሉን? የእግዚአብሄርን ልጆች ሊቃወሙ ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ፈጽሞ አያሸንፉዋቸውም፡፡ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሰዎች ማሸነፍ አይችሉም፡፡ 
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ የሚቃወሙ ሰዎች ሊሆኑ የሚችሉት የእግዚአብሄር ጠላት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የእርሱን በረከቶች መቀበል አይችሉም፡፡ ማንም ሰው የእግዚአብሄር ጽድቅ በተገለጠበት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምን ደህንነትን ሊያገኝ ወይም ሰማይ ሊያስገባው የሚችል እምነት ሊኖረው አይችልም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በዚህ መንገድ ሐሰተኛውን ወንጌል አሸንፈው ወደ እውነተኛው ወንጌል ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ የእግዚአብሄር ልጆች ዓለምንና ራሱን ዲያብሎስንም ማሸነፍ ይችላሉ፡፡ 
 
አንዳንዶች የኢየሱስን ጥምቀትና ደሙን በግልጽ አይረዱም፡፡ የተሳሳተ ግንዛቤያቸውንም ወደ ሐሰተኛ እምነት ይነዳቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ አምናችሁ በኢየሱስ ጥምቀት ወንጌል በማመን የሐጢያቶችን ይቅርታ ስለ ማግኘት ብዙ የምታስቡ ካልሆነ እምነታችሁ የተሳሳተ ነው፡፡ 
 
በእግዚአብሄር ፊት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች  ወደ እግዚአብሄር ጽድቅ ይደርሳሉ፡፡ እውነተኛ እምነትም ይኖራቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ብቻ የሚያምኑ ሰዎች እንደተሳሳቱ ይነግረናል፡፡ በእርሱ ጽድቅ የማያምኑ ሰዎች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አያምኑም ወይም አይረዱም፡፡ ነገር ግን በእርሱ ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎች ክርሰቶስ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙና ሐጢያቶቻቸውን በወሰደበት ጥምቀቱም ያምናሉ፡፡ 
 
ግትርነታችንን መጣል አለብን፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሚቃወሙ ሰዎች የሐሰት እምነታቸው ትክክል ነው በማለት ይሟዘዛሉ፡፡ በደሙ ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በእርሱ ጽድቅ ላይ ያላቸው እምነት ጎዶሎ ነው፡፡ ሙሉ እምነት ያላቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል  የሚያምኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑና ወደ እርሱ ጽድቅም የሚደርሱ እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ (ማቴዎስ 3፡15፤11፡11) 
 
በደሙ ብቻ በሚያምኑ ሰዎች የተጻፉት መጽሐፎች ዋጋ የሌላቸው ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት በሥነ መለኮት ምሁራን ውይይት ሲደረግባቸው የነበሩት ትምህርቶች አሁን በክርስቲያኖች ችላ ተብለዋል፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ግን ብዙ ትኩረት እያገኘ ነው፡፡ ይህ እውነት ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ያለና በፍጹም የማይለወጥ እውነት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለዘላለም ይኖራል፡፡ ነገር ግን በደሙ ብቻ የሚያምኑ ሰዎች ከሰዎች ትዝታዎች ይሰረዛሉ፡፡ ምክንያቱ ምንድነው? ምክንያቱም የእግዚአብሄር ጽድቅ ገሚስ የሆነው ደም በራሱ በሐጢያተኞች ላይ የሚያመጣው ውጤት የለም፡፡ 
 
በግልጽ አነጋገር ዛሬ አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያኖችም ይሁኑ ወይም አሕዛቦች ብዙ ሐጢያቶችን ይሰራሉ፡፡ በደሙ ብቻ በማመን እነዚህ ሁሉ ሐጢያቶች እንዴት ሊሰረዩ ይችላሉ? በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ትምህርቶች ሰዎችን ሐጢያት በሚሰሩበት ጊዜ ሁሉ እንዲጸልዩ ያስተምራሉ፡፡ ነገር ግን ሐጢያቶቻቸው ይቅር እንዲባሉላቸው እስከ መቼ ድረስ ይጸልያሉ? ምንም ይበሉ የሐጢያቶቻቸውን ይቅርታ አያገኙም፡፡ 
 
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር መጥቶ ሳይጠመቅ እንዲያው በደፈናው እስከ ሞት ድረስ ደሙን አፈሰሰ? ይህ እውነት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በጥምቀቱ ሐጢያቶችን ሁሉ ወሰደ፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) በመስቀል ላይ እንዲሰቀልና ደሙን እንዲያፈስስ ከመፍቀዱ በፊት በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የምታምኑ ከሆነ በየቀኑ የሐጢያቶቻችሁን ይቅርታ ለማግኘት የእርሱን ምህረት መለመን አያስፈልጋችሁም፡፡ በፈንታው በእግዚአብሄር ጽድቅ አምናችሁ ምሉዕ ደህንነትን ተቀበሉ፡፡ 
 
ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በጫንቃው ላይ ለመሸከም ተጠመቀ፡፡ ለዓለም ሐጢያቶችም ለአንዴና ለመጨረሻ ለመኮነን ተሰቀለ፡፡ ደህንነት ሊገኝ የሚችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በማመን ብቻ ነው፡፡ 
              
 
ኢየሱስ ከምንሰራቸው ሐጢያቶች የሚበልጥን ደህንነት ሰጥቶናልን? 
 
ኢየሱስ የሰጠን ቤዛነት ከሰራናቸውና ከምንሰራቸው ሐጢያቶች በጣም የላቀ ነው፡፡ የኢየሱስ ጥምቀትና ደሙ ከሰው ዘር ሐጢያቶች የማይበልጥ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስን አዳኛችን አድርገን ማመንም ሆነ ቤዛነትን መቀበል አንችልም ነበር፡፡ ነገር ግን የጌታ ቸርነት በጣም ታላቅ በመሆኑ የዓለምን ሐጢያቶች ለአንዴና ለጨረሻ በጥምቀቱ አማካይነት ወሰደ፡፡ 
 
ስለዚህ የሰማይ በር በሰፊው ተከፍቷል፡፡ ነገር ግን ማንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምን በዚህ በር መግባት አይችልም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትንም ሰዎች ልትቃወሙ ትችላላችሁ፡፡ ከአስፈሪው የእግዚአብሄር ፍርድ ማምለጥ ግን አትችሉም፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር ጽድቅ የተፈጸመበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማሸነፍ የምትችሉ አይምሰላችሁ፡፡
 
የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል  የሚቃወሙ ብዙ ሰዎች ሐዋርያው ጳውሎስንም የሚቃወሙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ጳውሎስ ያመነበት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስህተት ነበር ማለት የሚችል ማንም ሰው የለም፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅና አዳኛቸው መሆኑን ብቻ አምነዋል፡፡ 
ሮሜ 8፡32 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?›› እግዚአብሄር አብ አንድ ልጁን ወደ ዓለም በመላክ በጥምቀቱ አማካይነት ሐጢያቶች በሙሉ እንዲሸከም በመስቀል ላይ እንዲሞትና እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳንም ዳግመኛ ከሙታን ተነሳ፡፡ 
 
ኢየሱስ የእርሱ ልጅ እንደነበር ሁሉ እኛንም ከዓለም ሐጢያቶች ለማዳንና ልጆቹ ለማድረግ እግዚአብሄር አብ አንድ ልጁን ሰጠኝ፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ሁሉ ልጆቹ፣ ብሩካኖችና ጻድቃን ለማድረግ አንድ ልጁን ይጠመቅ ዘንድ ላከው፡፡ እግዚአብሄር ለሰው ዘር ሁሉ ሰማያዊ በረከቶቹንና የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመለገስ አቀደ፡፡ ከእነዚህ በረከቶች አንዱ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የእርሱ ልጅ መሆን ነው፡፡ 
 
‹‹ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?›› (ሮሜ 8፡32) እዚህ ላይ ‹‹ሁሉን ነገር›› የሚለው የእግዚአብሄርን ስጦታዎች የሚያመላክት ነው፡፡ የምን ስጦታዎች? እግዚአብሄር ኢየሱስን ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ልጆቹ የመሆንን ሥልጣን ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ማለትም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ያመኑ ሰዎች የእግዚአብሄር ልጆች ተደርገዋል፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ያለ ሐጢያት ናቸው፡፡ ጻድቃን ናቸው፡፡ በእርግጥም የተቀደሱ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸው፡፡ 
 
በእነዚህ ሁሉ በማመን የእግዚአብሄር ልጆች የሆኑ ሰዎች የሺህው ዓመት መንግሥትና መንግሥተ ሰማይ ተሰጥተዋቸዋል፡፡ ጻድቃን የሰማይን ክብሮች ሁሉ ለመውረስ ተባርከዋል፡፡ 
 
‹‹ሁሉን ነገር እንዲያው ሰጥቶናል›› የሚለው በአንዳንዶች ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ መሰጠት ተደርጎ ተተርጉሞዋል፡፡ እነርሱ ‹‹ይህ ማለት አንድ ጊዜ በኢየሱስ ካመንን መንፈስ ቅዱስ በተናጥል ይሰጠናል ማለት ነውን?›› ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ እውነት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስታምኑ የሐጢያቶቻችሁን ስርየትና መንፈስ ቅዱስን በአንድ ጊዜ ታገኛላችሁ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሐጢያተኛ ልብ ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ እኛ የሚመጣው ሐጢያቶቻችን በሙሉ ይቅር በተባሉበት ቅጸበት ነው፡፡ 
 
ምዕመናን  መንፈስ ቅዱስን ከመቀበል የሚበልጥ ነገር አላቸው፡፡ ሰማያዊ በረከቶች በሙሉ እስኪሰጡን ድረስ የእግዚአብሄር ስጦታዎች አያቆሙም፡፡ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ እንደ ፈውስ፣ በልሳን መናገርና ትንቢት መናገር ያሉ ችሎታዎች ስጦታዎች እንደሆኑ ወደ ማሰብ ያዘነብላሉ፡፡ በዚህ ምንባብ ላይ የተጠቀሱት ስጦታዎች ግን አባታችን ያለውን ሰማያዊ ነገሮች በሙሉ የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ጳውሎስ ስለ ስጦታዎች ሲናገር እግዚአብሄር የአምላክ ጽድቅ ላላቸው ልጆቹ የለገሳቸውን ነገሮች በሙሉ መናገሩ ነው፡፡ 
 
እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምኑ ሰዎች በጎ ነገሮችን ሁሉ በስጦታ እንደሚሰጠን ተናግሮዋል፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ለሚያምኑ ሰዎች ዳግም የመወለድን ስጦታ ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ክርስቲያኖች በዚህ ዓለም ላይ ሲኖሩ ብዙ ይሰቃያሉ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር መንግሥት ስትመጣ የሰማይ ክብር ይለገሳቸዋል፡፡ 
                     
 
የተመረጣችሁት ያለ ምክንያት ነው አትበሉ፡፡ 
 
ሮሜ 8፡33-34 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው፤ የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሄር ቀን ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡›› 
 
‹‹እግዚአብሄር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?›› እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ያዳናቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል? ማንም! 
 
የሥነ መለኮት ምሁራን አንዳንዶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሲመረጡ ሌሎች ግን እንዳልተመረጡ በመናገር ካልቪንን ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት ‹‹ያለ ቅድመ ሁኔታ›› የሚለውን ቃል በጭራሽ መጠቀም የለብንም፡፡ እንዲህ በማድረጋቸው እግዚአብሄርን ፈጽሞ እንደማያውቁትና ትምህርታቸውም ውሸት እንደሆነ እያስረገጡ ነው፡፡ ቅድመ ሁኔታ የሌለው ምርጫ እግዚአብሄር አንዳንዶችን ያለ ምክንያት መውደድና ሌሎችን ያለ ምክንያት መጥላት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር አንዳንዶችን እየወደደና ሌሎችን እየጠላ እንዴት ጻድቅ ነው ማለት እንችላለን? አምላካችን እንዲህ አይደለም፡፡ አምላካችን በክርስቶስ የሰውን ዘር ሁሉ ይወዳል፤ ይንከባከብማል፡፡ 
 
እዚህ ቁጥር 32 ላይ እንዲህ ይላል፡- ‹‹እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?›› እግዚአብሄር የሰውን ዘር በሙሉ ለማዳን ልጁን ሰጠ፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ አማካይነት በውሃውና በደሙ ቃል በኩል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ እንደወሰደ እንድናምን አድርጎናል፡፡ በቁጥር 33 ላይ እንዲህ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹እግዚአብሄር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?›› እዚህ ላይ ‹‹እግዚአብሄር የመረጣቸው›› የሚለው ቃል እግዚአብሄር አንዳንዶቹን ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደመረጠ አያመላክትም፡፡ እግዚአብሄር ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ መኖር የማይችሉትንና የራሳቸው ጽድቅ የሌላቸውን ሰዎች የመረጣቸው የራሱን ጽድቅ ሊያለብሳቸው ነው፡፡ 
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የተመረጡ ሰዎች ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመምጣቱን፣ የመጠመቁንና ሐጢያቶቻችንንም ሁሉ ለመውሰድ ራሱን መስዋዕት የማድረጉን እውነት የሚያምኑና የሚያርፉ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ከዓለም ሐጢያቶች ያዳናቸውንና ጽድቁን ያለበሳቸውን አምላክ የሚያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡ 
 
ታዲያ ጻድቃንን ማን ሊከሳቸው ይችላል? ማንም! እምነታችን የተሳሳተ ነው የሚል ማንም ሊኖር አይችልም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው የዳኑትንና የእግዚአብሄር ልጆች ለመሆን የተመረጡትን ሰዎች ማንም ሊፈርድባቸው አይችልም፡፡ በመስቀሉ ደም ብቻ የሚያምኑ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐሰተኞች ናቸው ማለትም ሆነ በእግዚአብሄር ፊት መክሰስ አይችሉም፡፡ 
 
አንዳንድ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የእግዚአብሄርን ጽድቅ የለበሱ ሰዎችን በተሳሳተ መንገድ ይኮንኑዋቸዋል፡፡ ይህ ግን ትክክል ነውን? አይደለም! በእግዚአብሄር ፊት ጻድቅ ለመሆን የተመረጡ ሰዎች እምነት በማንም ሰው ፈጽሞ በስህተት ሊኮነን አይችልም፡፡ 
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐጢያተኞች ናቸው የሚሉና እምነታቸውን በተሳሳተ መንገድ መኮነን የሚችል ማነው? እኛ የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠበትን የውሃና የመንፈስ ወንጌል በዓለም ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ሰብከናል፡፡ 
 
ነገር ግን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስበካችን ማንም አልከሰሰንም፡፡ በመስቀሉ ደም ላይ ያለውን እምነት ብቻ እንድናረጋግጥ የጠየቁን ጥቂቶች ነበሩ፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ስህተት ነው ማለት አልቻሉም፡፡ 
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የእግዚአብሄርን ጽድቅ የያዘ ወንጌል ነው፡፡ እውነተኛው ወንጌል ይህ ነው፡፡ ሌሎች ወንጌሎች በሙሉ ጎዶሎዎች ናቸው፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የሰበከው ሐዋርያው ጳውሎስ ከዚህ ከእውነተኛው ወንጌል ውጪ ሌላ ወንጌል ፈጽሞ ሊኖር እንደማይችል ተናግሮዋል፡- ‹‹ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፡፡ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፡፡ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፡፡›› (ገላትያ 1፡8-9)
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ስህተት ነው ማለት የሚችል ሰው የለም፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የማያምኑ ሰዎች ይቃወሙታል፡፡ በእግዚአብሄር የተሰጠው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ውሸት ነው ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ ቀጥሉ፡፡ እግዚአብሄርንም ተቃወሙ፡፡ እኛም ደግሞ በመስቀሉ ደም ብቻ ላይ ትኩረት የሚያደርጉትን ጎዶሎ የሆኑ የሐሰት ወንጌሎችን መዋጋት መቻል ይኖርብናል፡፡ ኢየሱስ በመጀመሪያ ሐጢያቶቻችንን በጥምቀቱ አማካይነት በራሱ ላይ ሳይወስድ እንዴት ሊሰቀል ቻለ?
 
 
በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ምዕመናን ሐጢያት አለባቸው አትበሉ፡፡ 
 
‹‹መክሰስ›› ማለት የፍርድ ውሳኔ እንዲሰጥ መጠየቅ ማለት ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎችን የሚከስ ብቸኛው ሰው ክፉ አድራጊ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ ስለሚያምኑ እምነታቸውን በስህተት መኮነን የሚችል ማነው? እነርሱ ተሳስተዋል ማለት የሚችል ማነው? ማንም የለም፡፡ ያጸደቃቸው እግዚአብሄር ነውና፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐጢያት አለባቸው ብሎ ሊከሳቸው የሚችል ማንም የለም፡፡ 
 
‹‹የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው፡፡›› (ሮሜ 8፡3) በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐጢያት አልባ መሆናቸውን ማወጅ የሚችለው ማነው? እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ እርሱ በጽድቁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናን እንደጸደቁ አውጆዋል፡፡ 
 
‹‹መጽደቅ›› አሁንም ሐጢያት ያለባቸውን ሰዎች አይመለከትም፡፡ የሚመለከተው ሐጢያቶቻቸው በእርግጥም ይቅር ተብሎ ‹‹ሐጢያት አልባና ጻድቅ›› የሆኑትን ሰዎች ነው፡፡ እግዚአብሄር በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሐጢያት አልባ ናቸው ካለ ተሳስተዋል፤ የእግዚአብሄርም ጽድቅ የላቸውም ማለት የሚደፍር ማነው? በዚህ ዓለም ላይ የሚኖር የትኛውም የሥነ መለኮት ምሁር ይህንን ማለት አይችልም፡፡ 
 
የዘመኑ ክርስትና ወደ ሃይማኖታዊ ቅድስና ለመድረስ በሚሞክር የቅድስና ትምህርት ተበሻቅጦዋል፡፡ በእንግሊዝ የሚኖር አንድ የሥነ መለኮት ምሁር ‹‹የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ቅዱስ ነችን?›› በማለት ከጠየቀ በኋላ የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያንም እንከኖች እንዳሉባት ተናገረ፡፡ ይህ የሥነ መለኮት ምሁር ስለ ውሃውና ስለ መንፈሱ ወንጌል እንደማያውቅ በእግዚአብሄርም ጽድቅ እንደማያምን ግልጽ ነው፡፡ 
 
ነገር ግን በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አማኝ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ሙሉ በሙሉ ሐጢያት አልባ ሆንዋል፡፡ በሥጋ ደካማ ቢሆንም አሁንም ፍጹምና እንከን የሌለበት የእግዚአብሄር ጽድቅ አለው፡፡ 
 
በእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ያለ ሐጢያት ነውን? አዎ! ቤተክርስቲያን የተቀደሱና ሐጢያት የሌለባቸው ምዕመናን አብረው በክርስቶስ የሚሰበሰቡባት ሥፍራ ነች፡፡ ምዕመናን ሐጢያት ያለባቸው ከሆኑ የእግዚአብሄር ልጆች አይደሉም፡፡ የቀደሳቸው ምንድነው? የእግዚአብሄርን ጽድቅ በመቀበል ሐጢያት አልባ ያደረጋቸው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ ያላቸው እምነት መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ የሥነ መለኮቱ ምሁር የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያንም ብትሆን እንከኖች እንዳሉባት ተናግሮዋል፡፡ ምክንያቱም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አያምንም ወይም ይህንን ወንጌል አያውቁም፡፡ 
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናን ሐጢያተኞች ናቸው ለማለት ማን ይደፍራል? ‹‹ያጸደቃቸው›› እግዚአብሄር ነው፡፡ እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ሰዎች ደካሞች በመሆናችን ሐጢያቶች ሊኖሩብን ይችላሉን? በእርግጥም አይችሉም! ይህ ማለት ታዲያ ሐጢያቶችን ብንሰራም ሐጢያት የለብንም ማለት ነውን? አዎ ሐጢያተ የለብንም! በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን የሚያስፈልገን ለዚህ ነው፡፡ ሰዎች ሐጢያቶችን የሚሰሩት በድክመቶቻቸው እንጂ ሆነ ብለው አይደለም፡፡ 
 
ሆነ ብለው ሐጢያቶችን የሚሰሩ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ሐጢያቶች ከሰዎች ድክመቶች የተነሳ የሚሰሩ ናቸው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሄር ጽድቅ ስላላቸው በልባቸው ውስጥ ሐጢያት የለባቸውም፡፡ እግዚአብሄር በጽደቁ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ስላስወገደ ሐጢያት የለብንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው›› የሚለው ለዚህ ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ምዕመናን የእግዚአብሄር ጽድቅ ስላላቸው ሐጢያት አልባ መሆናቸውን ያወጀው እግዚአብሄር ነው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ 
 
ኢየሱስ ወደፊት የምንሰራቸውን ሐጢያቶች እንኳን ባይወስድ ኖሮ እንዴት ከሐጢያቶቻችን ልንድንና ዳግመኛ ሐጢያተኞች ላንሆን እንችል ነበር? በእግዚአብሄር ጽድቅ ካመንን በኋላ ሐጢያቶችን ብንሰራና በሐጢያት ብንኖር ይህ አያረክሰንም ወይም ደህንነታችንን አያሰርዝብንም፤ በዚህም ዳግመኛ ለሲዖል የታጨን አያደርገንም? መልሱ አያደርገንም ነው! ደህንነታችን የተገኘው በራሳችን ቅድስና ቢሆን ኖሮ በዓለም ላይ ማን መዳን ይችል ነበር? ማንም! ማንም በሥጋ ፍጹም ሕይወትን መኖርና ትዕዛዛቱንም ፈጽሞ መጠበቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ መጸሐፍ ቅዱስ ‹‹ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ›› (ሮሜ 3፡10) ይላል፡፡ 
   
 
በተፈጥሮ ሰዎች በራሳቸው ምግባሮች የእግዚአብሄረን ጽደቅ መቀበል አይችሉም፡፡ 
 
እግዚአብሄር በአጥማቂው ዮሐንስ የተጠመቀውን አንድ ልጁን በመላክ የሰውን ዘር በሙሉ ከዓለም ሐጢያቶች እንዲያድን በመስቀል ላይ እንዲሞት አደረገው፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች በእምነታቸው ጸድቀዋል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ጻድቃን መገኘት የቻሉት ለዚህ ነው፡፡ አብርሃምም በእግዚአብሄር ቃል በማመን የእምነት አባት ሆነ፡፡ 
 
ብዙ ክርስቲያኖች የእግዚአብሄርን ጽድቅ በመንጻት ትምህርት አማካይነት ማግኘት እንደሚችሉ ቢያምኑም በተጨባጭ ግን አያውቁትም፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምንድነው? ከሰው ጽድቅ በጣም የተለየ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠው በየትኛው ወንጌል ነው? ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ የተገለጠው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ነው፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳናምንበት የማንቀበለው ከሆነ እግዚአብሄርን እየተቃወምን ነው፡፡ 
  
ማንም ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምን ከሐጢያት ሊድን ወይም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሊቀበል አይችልም፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ጥቂት እንኳን ሊቃወም የሚችል ሰው አለን? እኔ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለረጅም ጊዜ አምኜ ሰብኬያለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ወንጌል መቃወም የሚችል ሰው በጭራሽ አላየሁም፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ጽድቅ ወንጌል ከሐጢያቶቻችን ፍጹምና ምሉዕ የሆነ ደህንነትን ስለሚሰጠን ማንም ሰው በእግዚአብሄር ቃል ላይ ተመስርቶ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቃወም አይችልም፡፡ 
 
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ ያላቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል? 
 
ሮሜ 8፡34ን እናንብብ፡- ‹‹የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው፤ የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሄር ቀን ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡›› በእግዚአብሀር ጽድቅ የሚያምኑ ሰዎችን ሐጢያተኞች ናችሁ ብሎ ሊኮንናቸው የሚችል ማነው? 
 
በእምነት ከሐጢያቶቻቸው የዳኑትንና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑትን ምዕመናን ሐጢያተኞች ናችሁ ብሎ መኮነን የሚችል ሰው ማነው? ማንም! ‹‹የሚኮንንስ ማነው?›› የእግዚአብሄር ጽድቅ ምዕመናን ሐጢያተኞች ናቸው ማለት የሚችለው ማነው?
 
የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ በልባችሁ ውስጥ ሐጢያት ካለ ሲዖል ትወርዳላችሁ፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ላይ የሚፈርደው ሐጢያት ስላለባቸው ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ሐጢያቶቻቸው የተወገዱላቸው ሰዎች በእግዚአብሄር አይኮነኑም፡፡ ምክንያቱም የሚያስኮንናቸው ሐጢያት  የለባቸውምና፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑትን እግዚአብሄር ራሱ የማይፈርድባቸው ከሆነ ማን ሊከሳቸው ይደፍራል? በኢየሱስ የሚያምን አማኝ ሐጢያት ካለበት ሐጢያተኛ ስለሆነ  በእግዚአብሄር ይፈረድበታል፤ ይኮነንማል፡፡ ሐጢያተኞች በልባቸው ውስጥ ባሉት ሐጢያቶች ይፈረድባቸውና በሌሎች ሰዎች ይገለላሉ፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ የሚያምን ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የእግዚአብሄርን ጽድቅ ቢቀበል ያ ሰው በእግዚአብሄር ፊት ሐጢያት አልባ ነው፡፡ ማንም ሊከሰው አይችልም፡፡ እንዲህ ባሉ ሰዎች ሕሊና ውስጥ ሐጢያት የለም፡፡   
 
‹‹የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው፤ የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሄር ቀን ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡›› የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ሊሰጠን ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ለመሸከምም ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን ተቀበለ፡፡ ደሙን አፍስሶም በመስቀል ላይ ሞተ፡፡ አዳኛችን ለመሆንም ዳግመኛ ከሙታን ተነሳ፡፡ አሁን በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦ አዳኛቸን በመሆን ይማልድልናል፡፡ 
 
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር ጽድቅ ላላቸው ሰዎችም ይጸልያል፡፡ ልባችን ሲደክም መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በማይነገር ‹‹መቃተት›› በተለየ መንገድ ስለ እኛ ወደ እግዚአብሄር አብ ይጸልያል፡፡ 
 
የእግዚአብሄር ጽድቅ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምኑ ሰዎች ልብ ውስጥ እንደምን ፍጹም ነው? የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍጹምነት የውሃውና የመንፈሱም ወንጌል እንከን የሌለበትና ፍጹም እንደሆነ ይነግረናል፡፡