Search

خطبات

ርዕስ 10፡ ራዕይ (በራዕይ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[5-2] በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በጉ፡፡ ‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 5፡1-14 ››

በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በጉ፡፡
‹‹ ዮሐንስ ራዕይ 5፡1-14 ››
 
ራዕይ 5ን ተመልክተናል፡፡ እዚህ ላይ የእግዚአብሄር ቃል በመጨረሻው ዘመን የሰውን ዘር የሚያድነውና የሚፈርደው ጌታ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ እኛ የምናምንበት ይህ ጌታ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ለሚያምኑ ሰዎች አዳኝ፣ የሰው ዘር ሁሉ ፈራጅና የነገሥታት ንጉሥ መሆኑ ቃሉ ይነግረናል፡፡
 
ብዙውን ጊዜ ኢየሱስን ውስን ጌታ አድርገን እናስበዋለን፡፡ ጌታችን ግን የፍጥረት ሁሉ ዳኛ ነው፡፤
 
ጌታ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በመስጠት ከሐጢያቶቻችን ሁሉ፣ ከፍርድና ከጥፋት አድኖናል፡፡ ስለዚህ ጌታ እውነተኛ አዳኛችንና እውነተኛ አምላክ ሆኖዋል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜም ጌታችን የነገሥታት ንጉሥና የሰው ዘር ሁሉ ዳኛ ነው፡፡ ዛሬ አመስጋኝ ልባችንን ለምናምንበትና ለምንደገፍበት ጌታ እናንቃው፡፡
 
ከቁጥር 1 ጀምሮ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ላይ መጽሐፍ እንዳለ በጉ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ ወዲያው ይህንን መጽሐፍ እንደወሰደ እናያለን፡፡ በመጨረሻው ቁጥር ላይም ጌታ በዚህ ዙፋን ላይ እንደተቀመጠ እናያለን፡፡ ይህ ቃል ጌታ በቅርቡ የምዕመናንና የአላማኒዎች የሰው ዘር ሁሉ ዳኛ እንደሚሆን ይነግረናል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ የሁሉ ፈራጅ የሆነ አምላክ መሆኑን ማወቅና ማመን እንችላለን፡፡
 
ጌታችን ሽልማቶቹንና ቅጣቶቹን ዳግመኛ ለተወለድነው ሰዎች ብቻ አይወስንም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለሰው ዘርና በዩኒቨርስ ውስጥ ላለው ነገር ሁሉ እውነተኛ ዳኛና የነገሥታት ንጉሥ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ሰዎች እኛ ወደ 21ኛው ምዕተ ዓመት ገብተናል ይላሉ፡፡ ይህ ጌታ የሚመለስበት ዘመን ሊሆን ይችላል፡ የጌታ ምጽዓት ቅርብ ነው ስንል የዓለም ጥፋትም እንዲሁ ቅርብ ነው ማለታችን ነው፡፡
 
እዚህ ላይ ከቃሉ መረዳት የምንችለው ነገር ጌታ የሁሉም ዳኛ መሆኑን ነው፡፡ ጌታችን የሰው ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር በመምጣት በ30 ዓመቱ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ በጥምቀቱ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ለሞት በመሰቀልም ለሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ተኮነነ፡፡
 
በሰማይና በምድር ካለ ከእያንዳንዱ የሰው ዘርና ከእያንዳንዱ ፍጡር ክብርንና ስግደትን መቀበል የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የእግዚአብሄር አብን ፈቃድ በመታዘዙና በመፈጸሙ ክብርንና ስግደትን የመቀበል መብት ተሰጠው፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ከአባቱ ሥልጣኑን ሁሉ መውረስ ቻለ፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ሁሉ የሚፈርድበት መብት ተሰጥቶታል፡፡ የሰው ዘር ሁሉ የዳነውና የተኮነነውም በእርሱ ብቻ ነው፡፡ እኛን ያዳነን ጌታ በትክክል ማን እንደሆነ ማወቃችን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ እውቀት በመጨረሻውም ዘመን ቢሆን እምነታችንን አጠንክረን እንድንጠብቅ አስፈላጊ ነው፡፡ እርሱ ምን ዓይነት ሐይል እንዳለው ግልጽ የሆነ ዕውቀት ኖሮን በጌታ ስናምን ይህ ዕውቀት ትልቅ ጉልበት ይሆነናል፡፡
 
እኛን ያዳነን ጌታ ሰውን ሁሉ ለበጎና ለክፉ የሚፈርድ አምላክ ነው፡፡ ይህ ጌታ እንደ እግዚአብሄር አብ ተመሳሳይ ስግደትን ሊቀበል የተገባው ነው፡፡ ምንባቡ ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ በመሞት ሰዎችን ለእግዚአብሄር ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከሕዝብና ከወገን ሁሉ በደሙ ዋጅቶ በምድር ላይ ይነግሱ ዘንድ በአምላካችን ፊት ነገሥታትና ካህናት እንዳደረጋቸው ይነግረናል፡፡
 
ከዚያም ምንባቡ እልፍ አእላፋትና በሺህዎች የሚቆጠሩ መላዕክቶች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጌታን እንዳመሰገኑና እንደሰገዱለት ይነግረናል፡፡ ‹‹የታረደው በግ ሐይልና ባለጠግነት ጥበበም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል፡፡›› ዮሐንስ በቁጥር 13 ላይ ያየውንና የሰማውን በመመስከር ይቀጥላል፡፡ ‹‹በሰማይና በምድርም፣ ከምድርም በታች፣ በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ በረከትና ክብር፣ ምስጋናም፣ ሐይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ፡፡ አራቱም ሽማግሌዎች አሜን አሉ፡፡ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ፡፡›› ታዲያ ፍጡራን ክብርን ሁሉ የሚሰጡት ለማነው? በረከት፣ ክብር፣ ውዳሴና ሐይል ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለተሰጡት በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለበጉ ነው፡፡
 
የሰው ዘር የሚያቀርበው ክብር፣ ምስጋናና አምልኮ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለሆነው ለእግዚአብሄር ተሰጥተዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ የሰውን ዘር ከሐጢያቶቹ፣ ከጥፋትና ከፍርድ በማዳኑ እንደ አብ ተመሳሳይ ሥልጣን አለው፡፡ ለዚህ የስርየት ደህንነትም ከአብ ጋር አብሮ ክብር ሁሉ ተሰጥቶት ስግደት ሁሉ የሚገባው አዳኛችን ሆነ፡፡
 
በዙፋን ላይ የተቀመጠው ጌታና የሁላችንም ዳኛ፣ ልባችንን የሚሞላ ታላቅ ክብርን ያመጣልን አዳኛችን መሆኑን ስናስብ ያ ትክክል ነው፡፡ ጌታ በዩኒቨርስ ውስጥ ሁሉንም ነገር የፈጠረ የነገሥታት ንጉሥ ነው፡፡
 
ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ በውሃውና በደሙ ያዳነን የፍጥረት አምላክ በመሆኑ የሰው ዘር ሁሉና በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ነገር በዙፋኑ ፊት ተንበርክኮ ስግደትን፣ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይህ ጌታ የሁሉ ፈራጅ ሆኖ በክብር ዙፋን ላይ የተቀመጠ አምላክ መሆኑን በማወቃችን እምነታችን በአያሌው ይጠነክራል፡፡ ልባችንም በአያሌው ይበረታል፡፡
 
አንዳንድ ሰዎች ከአራቱ ታላላቅ ጠቢባን አንዱ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ጌታ በፍጹም ሰው አይደለም፡፡ ጌታ የፈጠረን፣ የሰራንና ያዳነን አምላካችን ነው፡፡ ስለዚህ እኛን የፈጠረውን ጌታ በፍጹም ከተራ ሰብዓዊ ፍጡራን ጋር ማወዳደር አንችልም፡፡ ሶቅራጥስም ሆነ ኮንፊሽየስ፣ ቡድሃም ሆነ ሌላ ማንኛውም ፍጡር ከጌታችን ጋር ሊወዳደር አይችሉም፡፡ ኢየሱስ እኛን ለማዳን ሰው ሆኖ ለ33 ዓመት ብቻ ኖረ፡፡ ማንነቱ ግን ከአምላክ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ጥሩ ምሳሌ አይሆን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሰዎች ሰዎችን እንደሚወልዱ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር አብ ልጅ ስለሆነ እግዚአብሄር ነው፡፡
 
ስለዚህ ኢየሱስ ራሱ አምላክ የፍጥረት አምላካችን ነው፡፡ ነገር ግን ጌታ እኛን ለማዳን ወደዚህ ምድር መጣ፡፡ እርሱ ስላዳነን ከእኛ ክብርን ሁሉ ሊቀበል ይገባዋል፡፡ ኢየሱስ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር እንዳልሆነ በልባችን አጽንተን ማመን አለብን፡፡ እኛ ምንኛ ደስተኞችና አመስጋኞች ነን!
 
 

የእግዚአብሄርን ዕቅድ የሚያጠናቅቀው ጌታችን፡፡ 

 
ከጌታ በስተቀር በሰባት ማህተም የታተመውን መጽሐፍ ሊከፍት የሚችል ማንም የለም፡፡ ይህ በሰባቱ ማህተሞች የተዘጋው መጽሐፍ የእግዚአብሄር እኛን ጨምሮ በዩኒቨርስ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ፈጠረ፡፡ ከፍጥረት በፊትም ቢሆን እግዚአብሄር እኛን ልጆቹ ለማድረግ በኢየሱስ ክርስቶስ ዕቅድን አቅዶ ነበር፡፡ ጌታችን እኛን ለማዳንና የሰውን ዘር ለመፍረድ የእግዚአብሄርን የፍጥረት አሳብና ዕቅዱን ለመፈጸም ይህንን የታተመ መጽሐፍ ተቀበለ፡፡
 
የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹በሰማይም ቢሆን፣ በምድርም ላይ ቢሆን፣ ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም፡፡›› በሌላ አነጋገር በመጨረሻ የእግዚአብሄርን ዕቅድ ለመፈጸም የሚችል ማንም አልተገኘም፡፡ ይህንን ማድረግ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር በልጁ አማካይነት ሁሉን ነገር አቀደ፡፡
 
ይህ ማለት ጌታ የእግዚአብሄር ዕቅድ የሆነውንና በሰባት ማህተሞች የታተመውን መጽሐፍ ለመክፈት የፍርድ ሥልጣን አለው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በዚህ ሥልጣን በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድና በእኛ ምትክም በመስቀል ላይ ለእነዚህ ሐጢያቶች ቅጣትን ተቀብሎ እኛን በማዳን የሥላሴ አምላክን እያንዳንዱን የዕቅዱን ክፍል አጠናቀቀ፡፡ ጌታ እኛን በመስዋዕቱና የራሱን ሕይወት በመክፈል ከሐጢያት አድኖን በእግዚአብሄር ፊት የእርሱ ካህናት አደረገን፡፡
 
ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ደህንነት የሚያምኑትንም ከእርሱ ጋር እንዲነግሱ አድርጎዋቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ‹‹በምድርም ላይ እንነግሳለን›› እንደሚል ጌታ በትክክል ወደዚህ ምድር ሲመጣ ሁሉንም ነገር እንደገና ድል ያደርግና በምድር ላይ የሺህ ዓመት መንግሥት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡