Search

ስለ ደራሲው

ሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግ፤

መጋቢ አንደመሆናቸው ሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግ የሐጢያቶችን ስርየት ለመቀበል መልሱን ለማግኘት ብዙ ታግለዋል፡፡ ምርምራቸው በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ እንደተገለጠው በውሃና በመንፈስ የመጣውን የኢየሱስ ክርስቶስን ጽድቅ ለማግኘት መራቸው፡፡ አሁን ላለው አገልግሎታቸው የመራቸው ይህ ግኝት ነው፡፡ ሬቨረ. ጆንግ እስከዚህች ቀን ድረስ እውነተኛውን ወንጌል በመላው ዓለም ለማስፋፋት በ The New Life Mission ከሚገኙ የእርሳቸው አጋር ሠራተኞች ጋር አብረው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወጅ ሕይወታቸውን ለ The New Life Mission የሥነ ጽሁፍ አገልግሎት ቀድሰው ሰጥተዋል፡፡ መጽሐፎቻቸው ከ90 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉመው ታትመዋል፡፡ አሁን ከ150 በላይ በሆኑ አገሮች ይገኛሉ፤ እየተነበቡም ነው፡፡ ለመጽሐፎቻቸው ምስጋና ይሁንላቸውና ብዙዎቹ አንባቢዎቻቸው የሐጢያቶችን ስርየትና መንፈስ ቅዱስን በመቀበል ላይ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ መጽሐፎች በእውነተኛው የተጻፈ የእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሠረቱ ናቸውና፡፡ ሬቨረ. ጆንግ በዓለም ዙሪያ ካሉት አጋር ሠራተኞች ጋር አብረው ድንቅ ለሆነው ሥራው ሁሉ ምስጋናንና ክብርን ለእግዚአብሄር ይሰጣሉ፡፡ ሐሌሉያ!

The New Life Mission

በዳሰሳ ጥናታችን ይሳተፉ

ስለእኛ እንዴት ሰሙ?