Search

ውሎችና ሁኔታዎች፤

  • ውሎችና ሁኔታዎች፤
    ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው ነሐሴ 08፤2019
  • እነዚህ ውሎችና ሁኔታዎች (‹‹ውሎች››፤ ‹‹ውሎችና ሁኔታዎች››) በThe New Life Mission (‹‹ለእኛ›› ‹‹እኛ›› ወይም ‹‹የእኛ››) ከሚንቀሳቀሰው https://www.bjnewlife.org/ ድረ ገጽ (‹‹አገልግሎቱ››) ጋር ያለህን ግንኙነት ያስተዳድራሉ፡፡
  • ይህንን አገልግሎት ከመጠቀምህ በፊት እባክህ እነዚህን ውሎችና ሁኔታዎች በጥንቃቄ አንብባቸው፡፡
  • አገልግሎቱን የማግኘትህና የመጠቀምህ ጉዳይ እነዚህን ውሎች በመቀበልና ከእነርሱ ጋር በመስማማት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እነዚህ ውሎች አገልግሎቱን የሚያገኙ ወይም የሚጠቀሙ ጎብኚዎችን፣ ተጠቃሚዎችንና ሌሎችን ሁሉ ይመለከታሉ፡፡
  • አገልግሎቱን በማግኘት ወይም በመጠቀም በእነዚህ ውሎች ለመታሰር ተስማምተሃል፡፡ ከውሎቹ ከአንዱ ክፍል ጋር ካልተስማማህ አገልግሎቱን ማግኘት አትችልም፡፡
  • መለያዎች፤
    ከእኛ ጋር መለያዎችን በምትከፍትበት ጊዜ ትክክለኛ፣ የተሟላና ሁሌም ወቅታዊ የሆነ መረጃ ማቅረብ አለብህ፡፡ እንዲህ አለማድረግ ውሎችን ማቋረጥን ያስከትላል፡፡ የዚህ ውጤትም በአገልግሎታችን ላይ ያለውን መለያህን ወዲያውኑ ማቋረጥ ይሆናል፡፡
  • የይለፍ ቃልህ የእኛን አገልግሎት የምትጠቀምበት ወይም የሦስተኛ ወገን አገልግሎትን የምትጠቀምበት ይሁን፣ አገልግሎቱን ለማግኘት ወይም ለማናቸውም ተግባራቶች ወይም እንቅስቃሴዎች የምትጠቀምበትን የይለፍ ቃልህን የመጠበቅ ሐላፊነት አለብህ፡፡
  • የይለፍ ቃልህን ለማንኛውም ሦስተኛ ወገን ይፋ ላለማድረግ ተሰማምተሃል፡፡ መለያህ አንዳች የደህንነት ጥሰት ወይም ያልተፈቀደ አጠቃቀም ውስጥ ገብቶ መሆኑን ስታውቅ ወዲያውኑ ልታሳውቀን ይገባል፡፡
  • ከሌሎች የድረ ገጽ ጣቢያዎች የተቆራኙ ማስፈንጠሪያዎች፤
    አገልግሎታችን በThe New Life Mission ባለቤትነት ያልተያዙ ወይም ቁጥጥር ሥር ያልሆኑ የሦስተኛ ወገን የድረ ገጽ ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች ማስፈንጠሪያዎችን ሊይዝ ይችላል፡፡
  • The New Life Mission የማንኛውንም ሦስተኛ ወገን የድረ ገጽ ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች ይዘት፣ ግላዊ ፖሊሲዎች ወይም ተግባራቶች አይቆጣጠርም፤ ለእነርሱም ሐላፊነትን አይወስድም፡፡ The New Life Mission እንዲህ ባሉ የድረ ገጽ ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወይም እንዲህ ካለ ከማንኛውም ይዘት፣ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች አጠቃቀም ወይም ድጋፍ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ተፈጥሮዋል ለተባለ ጉዳት ወይም ኪሳራ ሐላፊ ወይም ተጠያቂ እንደማይሆን ዕውቅና በመስጠት ተስማምተሃል፡፡
  • የምትጎበኛቸውን ማናቸውንም የሦስተኛ ወገን የድረ ገጽ ጣቢያዎች ወይም አገልግሎቶች ውሎችና ሁኔታዎች እንደዚሁም ግላዊ ፖሊሲዎች እንድታነብ አጥብቀን እንመክርሃለን፡፡
  • ገዢ ሕግ፤
    እነዚህ ውሎች የሚተዳደሩትና የሚተረጎሙት የሕግ ድንጋጌዎች ግጭትን ከግምት ሳያስገባ በኮርያ ሪፐብሊክ ሕጎች ጋር በተስማማ መልኩ ነው፡፡
  • የእነዚህን ውሎች አንዳች መብት ወይም ድንጋጌ ለማስፈጸም አለመቻላችን እነዚያን ውሎች እንደ መተው ተደርጎ አይቆጠርም፡፡ የእነዚህ ውሎች አንድ ድንጋጌ በፍርድ ቤት ዋጋ የሌለው ወይም ተፈጻሚነት የሌለው ሆነ ከተያዘ ቀሪዎቹ የእነዚህ ውሎች ድንጋጌዎች ተግባራዊ ሆነው ይቀጥላሉ፡፡ እነዚህ ውሎች አገልግሎታችንን በሚመለከት በእኛ መካከል ያለውን ሁሉንም ስምምነት ያጸናሉ፤ አገልግሎቱን በሚመለከትም በእኛ መካከል ኖረው የነበሩትን ማናቸውንም ቀደም ያሉ ስምምነቶች የሚበልጡና የሚተኩ ናቸው፡፡
  • ለውጦች፤
    እኛ እነዚህን ውሎች በማንኛውም ጊዜ ባለን ብቸኛ ምርጫ ለማሻሻል ወይም ለመተካት መብት አለብን፡፡ ማሻሻያው ተጨባጭ ከሆነ ማናቸውም አዲስ ውሎች ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት ቢያንስ የ30 ቀን ማስታወቂያ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ የጭብጥ ለውጥ የሚያመጣው የሚወሰነው በእኛ ብቸኛ ምርጫ ነው፡፡
  • እነዚያ ማሻሻያዎች ውጤታማ ከሆኑ በኋላ አገልግሎታችንን በማግኘት ወይም በመጠቀም በመቀጠልህ በተሻሻሉት ውሎች ለመታሰር ተስማምተሃል፡፡ ከአዲሱ ውሎች ጋር የማትስማማ ከሆነ እባክህ አገልግሎቱን መጠቀም አቁም፡፡
  • አግኘን፤
    ስለ እነዚህ ውሎች ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉህ እባክህ አግኘን፡፡
The New Life Mission

በዳሰሳ ጥናታችን ይሳተፉ

ስለእኛ እንዴት ሰሙ?