Search

የእምነት መግለጫ፤

01 እኛ እናምናለን፤

መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይንና አዲስ ኪዳናትን ብቻ እንደያዘ፣ ቃል በቃል በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንደተጻፈ፣ በኦሪጅናል ማኑስክሪፕቶች ስህተት የሌለበት፣ ተዓማኒነትና ሥልጣን ያለው የእግዚአብሄር ቃል እንደሆነ፤

02 እኛ እናምናለን፤

ለዘላለም የሚኖር አንድ ስላሴ አምላክ በሦስት ሕላዌዎች ማለትም በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ እንደሚኖር፤

03 እኛ እናምናለን፤

አዳም በእግዚአብሄር አምሳል ተፈጥሮ የዚህ ዓለም ገዥ በሆነው ሰይጣን ተፈትኖ እንደወደቀ እናምናለን፡፡ በአዳም ሐጢያት ምክንያት ሰዎች ሁሉ ጥፋተኝነትን ተቀብለዋል፤ በሙሉም ተበላሽተዋል፡፡ ደህንነትን ለማግኘትም በመንፈስ ቅዱስ መታደስ እንደሚያስፈልጋቸው፤

04 እኛ እናምናለን፤

ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር እንደሆነ፣ ከድንግል እንደተወለደ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ እንደተጠመቀ፣ የእግዚአብሄር በግ ሆኖ እንደተሰቀለ፣ ዳግመኛም ከሙታን እንደተነሳና አሁን በእግዚአብሄር ቀኝ ከፍ ወዳለበት ሰማይ እንዳረገ፤

05 እኛ እናምናለን፤

ደህንነት የሐጢያቶችን ስርየት፣ የክርስቶስን ጽድቅ መቆጠርና የዘላለምን ሕይወት እንደያዘ፤ ይህንም መቀበል የሚቻለው በስራዎች ሳይሆን በእምነት ብቻ እንደሆነ፤

06 እኛ እናምናለን፤

የኢየሱስ ክርስቶስ ምጽዓት ቅርብ እንደሆነና የሚታይና ተጨባጭ እንደሆነ፤

07 እኛ እናምናለን፤

የዳኑት ለዘላለም ሕይወትና በሰማይ ለሚገኘው ብርክትና እንደሚነሱና ያልዳኑት በሲዖል ለሚሆነው ዘላለማዊና ንቁ ሆነው ለሚቀበሉት ቅጣት እንደሚነሱ፤

08 እኛ እናምናለን፤

የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተክርስቲያን በዳግመኛ ልደት ጊዜ ዳግመኛ የተወለዱትን፤ በክርስቶስ ውስጥም በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁትን ብቻ እንደምታካትት፤ እርሱ አሁን በሰማይ እንደሚማልድላቸውና ለእነርሱም ዳግመኛ እንደሚመጣላቸው፤

09 እኛ እናምናለን፤

ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ወደ አሕዛብ ሁሉ እንድትሄድና ወንጌልን ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንድትሰብክ፤ የሚያምኑትንም እንድታጠምቅና እንድታስተምር እንዳዘዛት፤