Search

በነጻ የሚታደሉ የታተሙ መጽሐፎች፣
ኢመጽሐፎችና የኦዲዮ መጽሐፎች፤

እኛ የፖል ሲ. ጆንግን የክርስቲያን መጽሐፎች ለእያንዳንዱ ጎብኚ ፈጽሞ በነጻ እየለቀቅን ነው፡፡

አሁኑኑ ለማሰስና በነጻ የሚታደለውን ተከታታይነት ያለው መጽሐፍ ቅጂ ለመጠየቅ ነጻነት ይሰማህ! በአንድ ጊዜ ከእያንዳንዱ መጽሐፍ አንድ ቅጂና ከፍተኛውን 2 የተለያዩ መጽሐፎችን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ የወረቀት መጽሐፎቻችንን በመቀበል ለመቀጠል የምትፈልግ ከሆነ ወይም በዙሪያህ ላሉት ሰዎች ለማጋራት ተጨማሪ መጽሐፎችን መቀበል የምትወድ ከሆነ ከእኛ ዘንድ ማረጋገጫን ለማግኘት የThe New Life Mission አጋር ሆነህ ተመዝገብ፡፡ እኛ እነዚህን በነጻ የሚታደሉ መጽሐፎች በePub እና PDF እናቀርባለን፡፡
ቋንቋ፤

በእጅጉ የሚመከሩ መጽሐፎች

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ ትርጉም]

አማርኛ 1

በውኑ በውሃውና በመንፈሱ ዳግም ተወልዳችኋልን? [አዲስ የተሻሻለ ትርጉም] Rev. Paul C. Jong

የዚህ መጽሐፍ ዋና ርዕሰ ጉዳይ “በውሃና በመንፈስ እንደገና መወለድ” ነው። በዚህ መጽሐፍ ዋና ርዕሰ ጉዳይ ላይ ኦሪጂናል ነው። በሌላ አባባል፣ ይህ መጽሐፍ እንደገና መወለድ ምን እንደሆነና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በውሃና በመንፈስ እንዴት እንደገና እንደምንወለድ በግልጽ ይነግረናል። ውሃው በዮርዳኖስ የኢየሱስን ጥምቀት ይወክላል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ሁሉም ኃጢአታችን ወደ ኢየሱስ የተላለፈው በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ነው። ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ተወካይና የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር ነበር። አሮን በኃጢአት የማስተስረያ ቀን እጆቹን በተለቀቀው ፍየል ራስ ላይ በመጫን የእስራኤላውያንን ዓመታዊ ኃጢአት ሁሉ ወደ እሱ አሳልፎ ሰጠ። ይህ መስዋዕት ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር ጥላ ነው። የኢየሱስ ጥምቀት የእጅ መጫን ምልክት ነው። ኢየሱስ በዮርዳኖስ በእጅ መጫን መልክ ተጠመቀ። ስለዚህ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ ወሰደና ስለ ኃጢአቱ ለመክፈል ተሰቀለ። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች ኢየሱስ በዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ ለምን እንደተጠመቀ አያውቁም። የኢየሱስ ጥምቀት የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ቃልና የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማይነጠል ክፍል ነው። በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ በማመን ብቻ እንደገና መወለድ እንችላለን።

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (I)

አማርኛ 9

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (I) Rev. Paul C. Jong

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተደበቀውን እውነት ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ መረዳትና ማወቅ የምንችለው የመገናኛው ድንኳን እውነተኛ ጭብጥ የሆነውን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በማወቅ ብቻ ነው፡፡
በመገናኛው ድንኳን አደባባይ የመግቢያ በር ላይ የተገለጡት ሰማያዊው፤ ሐምራዊው፤ ቀዩና ጥሩው በፍታ በአዲስ ኪዳን ዘመን የሰውን ዘር ያዳኑትን የኢየሱስ ክርስቶስ ስራዎች ያሳዩናል፡፡ በዚህ መንገድ የብሉይ ኪዳኑ የመገናኛው ድንኳን ቃልና የአዲስ ኪዳን ቃል ልክ እንደ ጥሩው በፍታ እርስ በርሳቸው በጣም የተቆራኙና የተያያዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ እውነት በክርስትና ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ እውነት ፈላጊ ሰው ለረጅም ጊዜ መደበቁ ያሳዝናል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር በመምጣት በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ በመስቀል ላይም ደሙን አፈሰሰ፡፡ ማናችንም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሳናስተውልና ሳናምን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የተገለጠውን እውነት ማግኘት አንችልም፡፡ አሁን ይህንን የመገናኛውን ድንኳን እውነት መማርና በእርሱም ማመን አለብን፡፡ ሁላችንም በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ባለው በሰማያዊው፤ በሐምራዊው፤ በቀዩ ማግና በጥሩ በፍታ በር የገለጠውን እውነት መረዳትና ማመን ያስፈልገናል፡፡

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (II)

አማርኛ 10

የመገናኛው ድንኳን፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕላዊ መግለጫ (II) Rev. Paul C. Jong

በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የመገናኛውን ድንኳን እንዲሰራ ሙሴን እንዳዘዘው በአዲስ ኪዳንም በውስጣችን ያድር ዘንድ እግዚአብሄር በእያንዳንዳችን ልቦች ውስጥ መቅደስ እንድንሰራ ይፈልጋል፡፡ ይህንን መቅደስ በልቦቻችን ውስጥ የምንሰራበት የእምነት ቁስ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ቃል ነው፡፡ በዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ማጠብና ማንጻት አለብን፡፡ እግዚአብሄር መቅደስን እንድንሰራ ሲነግረን ልቦቻችንን ባዶ እንድናደርግና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እንድናምን እየነገረን ነው፡፡ ሁላችንም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ልቦቻችንን ማንጻት አለብን፡፡
በዚህ የወንጌል እውነት በማመን የልቦቻችንን ሐጢያቶች በሙሉ ስናነጻ ያን ጊዜ እግዚአብሄር በውስጣችን ይኖራል፡፡ በልቦቻችሁ ውስጥ ቅዱስ መቅደስ መስራት የምትችሉት በዚህ እውነተኛ ወንጌል በማመን ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ አንዳንዶቻችሁ ምናልባትም በራሳችሁ ጥረት መቅደሶችን ለመስራት በመሞከር ልቦቻችሁን ለማንጻት የንስሐ ጸሎቶቻችሁን ስታቀርቡ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ጊዜው ይህንን የሐሰት እምነት ትታችሁ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን አእምሮዋችሁን የምታድሱበት ነው፡፡

አዲስ መጽሐፎች

በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I)

Amharic 67

በልባችሁ ውስጥ ግራ መጋባትና ባዶነት ካለ የእውነትን ብርሃን ፈልጉ (I) Rev. Paul C. Jong

ይህ መጽሐፍ ዘግይቶ በተከሰተው ጥንታዊ ታሪክ ውስጥ የተፈጠረው የኒቅያውያን የሐይማኖት መግለጫ ምን ያህል በዛሬው ክርስትና ውስጥ መጥፎ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ያብራራል፡፡
በዚህ ዘመን ዳግመኛ የመወለድን እውነት ለመገናኘት ጥቂት ጨምራችሁ ማጥናት አለባችሁ፡፡ እስከ አሁን ድረስ ስላመናችሁበትም የእምነት መግለጫ ይበልጥ በጥልቀት ማጥናት ያስፈልጋችኋል፡፡
አሁን ከኒቅያውያን የሐይማኖት መግለጫ ውስጥ የተገደፈውንና በአጥማቂው ዮሐንስ በኩል የሆነውን የኢየሱስ ጥምቀት ትርጉም ማወቅ አለባችሁ፡፡ በመሆኑም ይህ በልባችሁ ውስጥ እውነተኛ ደስታን ለመቀበል ዕድል ሊሆን ይገባል፡፡
አሁን ኢየሱስ በተቀበለው ጥምቀት ውስጥ ያለውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል እውነተኛ ዋጋ ትገነዘባላችሁ፡፡ ኢየሱስ ከአጥማቂው ዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ቃል ምን ያህል በነፍሳችሁ ላይ ተጽዕኖ እንደሳደረ ይበልጥ በጥልቀትና በግልጥ ወደ ማወቅ ትመጡና በእምነት ለእግዚአብሄር ክብርን ትሰጣላችሁ፡፡

በPaul C. Jong የተጻፉ ኢመጽሐፎችና ኦዲዮ መጽሐፎች

ለይ፤
ጠቅላላ፤ 57