Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

አጋር ሠራተኛ ከሆንክና "መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች" በሚለው ላይ መልዕክትና ፎቶዎችን መለጠፍ የምትወድ ከሆነ "መልዕክት ለጥፍ" የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግና ግባ፡፡ ልጥፍህ የሚታየው የእኛን ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ይሆናል፡፡

መልዕክት ለጥፍ
ጠቅላላ፤ 16
  • ቁ.16

    እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ!

    አምላክ የሆነው ኢየሱስ ስለኃጢአታችን የሰው ስጋ ለብሶ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከድንግል ማሪያም ተጸንሶ በዳዊት ከተማ ተወለደ፤ እድሜውም ለክህነት ስራ ሲድርስ በ30 ዓመቱ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ስለኃጢአታችን ተጠመቀ፤ በጥምቀቱም በእጆች ስራዓት መሰረት ኃጢአታችንን ሁሉ በስጋው ተሸከመ፤ ስለኃጢአታችንም ተሰደበ፣ ተገረፈ፣ በመስቀል ተሰቀለ ፍርድን ሁሉ ተቀበለ፤ ሞተም በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳ። ሃሌሉያ ኢየሱስ የተወለደው ለዚህ ታላቅ ስራ ነው!ለሚያምን ሁሉ መልካም ገና፤ እግዚአብሄር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ወዳችኋለው!1 ወይም 2 ደቂቃዎን ተጠቅመው፤ ነጻ መንፈሳዊ ኢመጽሀፎትችና ኦዲዮ መጽሀፍቶች ለማግኘት ድርገጹን ይጠቀሙ!https://www.bjnewlife.org/am/book/bookList.php

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 01/07/202574
  • ቁ.15

    ለሚያምን ሁሉ መልካም የትንሳኤ በዓል!

    #ለሚያምን ሁሉ መልካም የትንሳኤ በዓል!!!ምስጋና የሰው ስጋ ለብሶ ስለኅጢአታችን ወደዚች ምድር ለመጣው በ30 ዓመቱም ዮርዳኖስ ላይ በጥምቀቱ የዓለምን ኅጢአት ለወሰደው ስለኅጢአታችንም በሞት ስለተቀጣው በሶስተኛውም ቀን ከሞት ለተነሳው ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁንና በክርስቶስ ሙሉ ጽድቅ ስለማምን እኔም በፊተኛው ትንሳኤ እነሳለው የሺውን ዓመት መንግስትና ዘላለማዊውን መንግስቱን እወርሳለው! በዚህ ታላቅ በረከት ስለባረከኝ አምላኬን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግነዋለው ሃሌሉያ!!!በክርስቶስ ትንሳኤ ላይ ያለን እምነታችን በራሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ተቀባይነት የሚኖረው ከክርስቶ ውልደቱ እስከትንሳኤው ስናምን ነው!በክርስቶስ ጽድቅ አንዳችም ሳትጨምሩ እንዲሁም ሳትቀንሱ ለምታምኑ እህት ወንድሞቼ ሁሉ የክርስቶስ ትንሳኤ ለእኛ ነውና መልካም የትንሳኤ በዓል እያልኩ፡ ሙሉ የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ ያልገባችሁና በስመ ሀይማኖት ውስጥ ተሸሽጋችሁ የሀይማኖቶትቻችሁን ስርዓት ለመታዘዝ የምትደክሙ ሞዕመናን ለእናንተ ኢየሱስ ሁለተኛ ትንሳኤን አዘጋጅቷል! ሁለተኛው ትንሳኤ ለኅጢአተኞች የተዘጋጀ የፍርድ ትንሳኤ ነው! ለነብሳችሁ የምታዝኑ ሁኑ የክርቶስን ሙሉ ጽድቅ በሀይማኖት አስተምሮት ሳይሆን በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ለመረዳት እንዱሁም ለማመን ልባችሁን ከፍቱ! ሊንኩን በመጫን አጭር አስተማሪ ቪዲዮ ተከታተሉ በአድራሻው መሰረት አግኙን!https://youtu.be/T-hYB5yFp3oሙሉ የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ በረከት እንዲያገኛችሁ እጸልያለው ተባረኩ!

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 05/04/202494
  • ቁ.14

    የውሃውንና የመንፈስን ወንጌል የሰጠኝና ከእድሜ ልክ ኃጢአቴ ሁሉ ያዳነኝ ዛሬን ድረስ በህይወት ያኖረኝ ኢየሱስ ይመስገን።

    የውሃውንና የመንፈስን ወንጌል የሰጠኝና ከእድሜ ልክ ኃጢአቴ ሁሉ ያዳነኝ ዛሬን ድረስ በህይወት ያኖረኝ ኢየሱስ ይመስገን።ዛሬ 26ኛ ልደቴ ነው! እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በህይወት የኖርኩት በክርስቶስ ጽድቅ ላይ ባለኝ እምነት ነው ነገንም በክርስቶስ ጽድቅ እኖራለው ሃሌሉያ! አምላክ የሆነው ኢየሱስ የሰው ስጋ ለብሶ ስለኃጢአታችን ያለነውር ከሰማይ ወደ ምድር መጣ፣ አምላክ የሆነው ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሞላው ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ በመጥምቁ ዩሐንስ ስለኃጢአታችን ተጠመቀ ዩሐንስም በኢየሱስ ራስ ላይ እጆቹን በመጫኑ አማካኝነት የዓለምን ኃጢአት በሙሉ ጌታ ኢየሱስ በስጋው ተሸከመ፣ አምላክ የሆነው ኢየሱስ ስለኃጢአታችን ቅጣታችንን ሁሉ ተቀበለ ሞተም፤ በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳ ሃሌሉያ ይህንን ድንቅ ወንጌል ስላመንኩ ጻዲቅ ሆኛለው፣ መፈስ ቅዱስን በልቤ ተቀብያለው፣ ጌታን ማመስገን እችላለው፣ ጌታን በጸሎት መገናኘት እችላለው እንዲሁም ይህንን ድንቅ ወንጌል ለመስበክ ተሹሜያለው! ነገንም በህይወት የምኖረውም ለዚሁ ለወንጌል ስራ ነው አሜን ምነኛ ታደልኩ ሃሌሉያ! ዛሬም ደስ እያለኝ ለእናንተ ከእድሜ ልክ ኃጢህአቴ የነጻውበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አጋራለው፤ በፈቃዳችሁ ሊንኮችን ብትነኩ ጠቃሚ ግብአቶችን ታገኙበታላችሁ! እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ!www.bjnewlfe.org ወይም www.nlmethiopia.com

    • Teferi Oshine
    • Ethiopia
    • 04/02/2024102
  • ቁ.13

    Mesfin Berhanu Ubba`s gospel songs

    #. 1 The New Life Mission · The harvest is plenteous መከሩ ብዙ ነው (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)   መከሩ ብዙ ነው ምናያቸው  ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው የመከሩ ባለቤት ጌታችን  ሠራተኞችን አንሳን ስጠን   (1). የጠፉ በጎች ከፊትህ ይሳቡ ባንተ ምህረትህ ከጎተራው ውስጥ ፍሬ ይግባ ቤትህ በጻድቃን ይገንባ   (2). በምድረ በዳ በራብ ያሉ ተጨንቀው በክፉ የተጣሉ ጌታ ምህረትህ ያግኛቸው እግዚአብሔር ክንድህ ይስባቸው   (3). የቤትህ አገልጋይ ሰራተኞች  ጽድቅን የሚያወሩ ወታደሮች  በየከተማው በገጠሩ  ለሠማይ መንግስት የሚሰሩ  ውኃ ደም መንፈስ ዓላማቸው  የቤትህ ቅናት ሚበላቸው የሰይጣንን ግንብ የሚያፈርሱ የቤቱን ቅጥር የሚያድሱ                               ጌታ ይነሱ                                  ዛሬ ይነሱ                                     ኦ ይነሱ  ጌታ ይነሱ   ዛሬ ይነሱ   አዎ ይነሱ   አሜን ይነሱ ።   ____ The harvest is plenteous (Singer: Mesfin Berhanu)   The harvest is plenteous But workers are few Lord of the harvest Give us the workers   (1). Lost sheep before you Draw in your mercy Let the fruit come from the barn Build your house with the righteous   The harvest is plenteous But workers are few Lord of the harvest Give us the workers   (2). Those who are hungry in the desert Worried and badly thrown Lord have mercy on them May God draw your arms   (3). The staff of your house Soldiers who speak righteousness In every city, in the countryside They Working for the kingdom of heaven The Water blood spirit is their purpose Jealousy of your home what eats them Those who destroy the tower of Satan Renovating the walls of the house                       O Lord arise                         Get up today                            Oh get up O Lord arise Get up today Yes, get up Amen arise.   The harvest is plenteous But workers are few Lord of the harvest Give us the workers     #. 2 The New Life Mission · O Lord, My Fatigue Is Great ጌታ ሆይ ድካሜ ብዙ ነው(ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ጌታ ሆይ ድካሜ ብዙ ነው ምደክምበት ኃጢአቴ ብዙ ነው የማፍርበት ውርደቴን ወሰድከው ከበላዬ  ጸጋህ ጥላ ሆነኝ ከለላዬ ጸጋህ ድጋፍ ሆነኝ መቆሚያዬ ጸጋህ ኃይል ሆነኝ መመኪያዬ።   1.  ወጀቡ ሲነሳ ሊያሰጥመኝ ዓለም ሥጋ ሰይጣን ሲከበኝ የእምነቴ ጋሻ መከታዬ ኢየሱስ ጥምቀትህ ነው መሸሸጊያዬ ኢየሱስ ደምህ ነው መትረፊያዬ  ኢየሱስ ትንሳኤህ ነው ማምለጫዬ   2.  ምመካበት የለኝም ሚያስመካኝ ጽድቄ እንኳ መርገም ነው ሚገለኝ በህግህ የማርከኝ ወድሃለሁ ኢየሱስ ታማኝ ነህ አምንሃለሁ ።   3.  ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ  ማረፊያ ጌታ ኢየሱሴ ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ አዳኜ ጌታ ኢየሱሴ ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ ፍቅር ነህ ጌታ ኢየሱሴ ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ  ወደድከኝ ጌታ ኢየሱሴ ።   _ O Lord, my fatigue is great (Singer Mesfin Berhanu)  ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ O Lord, my fatigue is great, I will tire My sins are many, of which I am ashamed You took away my shame Your grace is my shadow and my protection Your grace is my support Your grace has become my proud.    1. To drown me when the whirlwind arises  The world, the flesh, the Satan surrounds me  My shield of faith  Jesus, your baptism is my refuge Jesus, is your blood is my salvation Jesus, your resurrection is my escape    2. I have nothing to be proud of Even my righteousness is curse killer of me I love you, you forgave me with your law Jesus, you are faithful, I believe you.    3. I will Thank you always My rest Lord Jesus I will Thank you always My savior, Lord Jesus I will Thank you always You are love, Lord Jesus I will Thank you always You love me Lord Jesus.     #.3 The New Life Mission · God Does Not Want An Animal That Has Blemish ነውር ያለውን እንስሳ እግዚአብሔር አይፈልግም(ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ነውር ያለውን እንስሳ እግዚአብሔር አይፈልግም  እጆች ሳይጫንበት ኃጢአት አይተላለፍም  ጌታ የደነገገው የኃጢአት ስርየት ያለው ጠቦቱ ሲታረድ በደሙ መፍሰስ ነው። ~ ይሄ ነው ደኅንነት የኃጢአት ስርየት አለን የሕይወት መንፈስ ህግ እግዚአብሔር የሰጠን።   1. በንስሐ ጸሎት ማንም ከኃጢአት አይነጻም ጻድቅ ሰው ተብሎ ለመንግሥቱ አይበቃም፤ በሕይወት መንፈስ ህግ በእግዚአብሔር ስርዓት  መቅረብ ይሻለናል ለመንጻት ከኃጢአት ።   2. በሕግ በነብያት እግዚአብሔር ተናግሯል  የስርየት ሕጉን በእርግጥ አስተምሯል  ኃጢአትን ላይቆጥር ገብቷል በኪዳኑ በክርስቶስ ስራ አምነው ለሚድኑ።   3. በጥምቀቱ ሰጠኝ  በጎውን ሕሊና የልቤን ሸለፈት ቆርጫለሁና ከሕግ እርግማን  ነጻ አውጥቶናል  ክርስቶስ በስራው ልጁ አድርጎናል።   4. የሰው ፍልስፍና ሃይማኖት ይገድላል  የስርየቱን ሕግ ጻድቅ ያስተውላል  ቃሉን አይሽረውም እግዚአብሔር ይሰራል  በአንዱ መስዋዕት ዘላለም ይምራል።   ___ God does not want an animal that has blemish (Singer Tezera Ermiyas) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ God does not want an animal that has blemish  Sin is not transmitted without the laying on of hands The forgiveness of sins that the Lord has decreed It is the shedding of the blood when the lamb is slaughtered. ~ This is the salvation we have the forgiveness of sins God gave us the law of the spirit of life.   1. No one is freed from sin through the prayer of repentance Being not called as a righteous man and not sufficient for the kingdom In the law of the spirit of life, God`s order It is better to near to be cleansed from sin   2. God spoke through the prophets in the law He really taught the law of atonement He entered with his covenant to not counting the sin For those who believe and saved in the works of Christ.   3. By his baptism he gave me a good conscience For I have cut the foreskin of my heart He freed us from the curse of the law Christ has made us His Son in His work.   4. The Human philosophy religion kills The righteous understand the law of the atonement of God God does not cancel his word He forgives forever through one sacrifice.   #.4 The New Life Mission · There is no easter with being a foreskin ሸለፈታም ሆኖ የለም ፋሲካ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)  ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ሸለፈታም ሆኖ የለም ፋሲካ  የእግዚአብሔር ስርዓት ከቶ አይነካ  የልብን ግርዛት ያላገኘ ሰው የአብርሃም ዘር አይደለም የረከሰ ነው።   1.  ከግብጽ ምድር ከፈርኦን ቤት ከባርነቱ ያወጣኝ እርሱ እግዚአብሔር ነው በስርዓቱ  ሸለፈት ወድቆ ምልክት ኖሮኝ ደም በመቃኔ  ነጻ አውጥቶ ያዘምረኛል በአዲስ ቅኔ።   2.  አዲስ ዘመን ሆኗል አዲስ መንገድ ለኛ በውኃ ደም መንፈስ ተገኝቷል መዳኛ ከኃጢአት ባርነት ከግብጽ  አውጥቶናል ፋሲካችን ጌታ ለእኛ ታርዶልናል።   3.  እንበላለን ፋሲካ በየለቱ እንበላለን  ፋሲካ በህምረቱ  የመከራን ዘመን ተሻግረናል ከመናው ዘወትር ያበላናል ፋሲካ በየቀን ሆኖልናል ምስጋና በየቀን በዝቶልናል።   4.  አላወቀም ይሄ ዓለም የፋሲካን ስርዓቱን  እህል ቂጣ መራራውን የደም ቅጠል ምልክቱን በጨለማ በባርነት  ከውኃ ከደም የራቀ ሰው ከፋሲካ አልደረሰም ዛሬም በኃጢአት በግብፅ ነው።   TRANSLATION ? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ There is no easter with being a foreskin  (Singer Tezera Ermiyas) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ There is no easter with being a foreskin God`s order will never affect A person who has not received the circumcision of the heart He is not the seed of Abraham he is unclean.   1. From the land of Egypt from Pharaoh`s house, from his slavery It is God who brought me out, through the system  The foreskin fell off and the symbol of blood lived on my doorframe He settled me free and he makes me sing a new song.   2. It has become a new era a new way for us In water, blood, spirit found Savior He brought us out of the slavery of sin in Egypt Our Passover has been sacrificed for us.   3. We eat Easter every day We will eat Easter in His mercy We have passed the time of suffering He always feeds us from the manna Easter is every day Gratitude abounds for us every day.   4. This world did not know the easter system Grain bread bitter blood leaf symbol Enslaved in darkness a man far from water and blood He did not arrive from the Passover and is still in Egypt today in sin.     #. 5 The New Life Mission · He lowered and Washed my feet ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን በየቦታው ሚቆሽሸውን  ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን በብዙ እድፍ የተሞላውን   1. ውኃን አዘጋጅቶ ክብሩን ለኔ ትቶ ጭቅቅት ዕድፌን ከላዬ ላይ አሽቶ ሙልጭ አርጎ ያጠበኝ  ከእንግዲህ በኋላ ንጹሕ ሰው ነህ ያለኝ።   2. ኢየሱስ ነው አስታውሰው ያረኩልህን በሕይወትህ ዘመንህ፣ ኢየሱስ ነው አስታውሰው ከእኔ እንዲትኖር እንዲዘልቅ መዳንህ፣ ኢየሱስ ነው ያለኝ እኔን ዮርዳኖስ የሄደው፣ ኢየሱስ ነው የኃጢአት ሸክም ቀንበሮቼን ከላይ የናደው፣ ኢየሱስ ነው ያለፈውን መጪውን በደሌን፣ ኢየሱስ ነው በጥሩ ውኃው ያጠበው ሰውነቴን።   3. ስለዚህ ኖራለሁ እያሰላሰልኩኝ የደሊላን እስር በክርስቶስ ጥምቀት እየበጣጠስኩኝ ቶሎ ሚከበኝን ኃጢአቶቼን ሁሉ የማስወግድበት የእግሬ መታጠብ የእምነቴ መሰረት የኢየሱስ ጥምቀት።    TRANSLATION ? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ He lowered and Washed my feet (Singer Mesfin Berhanu) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ He lowered and Washed my feet The one it gets dirty in everywhere He lowered and Washed my feet which is full of stains   1. He prepared water and left his glory to me He wiped my mud and my stains above on me He washed me full perfectly  He said me you are an innocent person from now on.   2. It is Jesus, remember what I did for you during your life It is Jesus, remember that you`ll live with me and that your salvation lasts It is Jesus said to me the one who went to Jordan It is Jesus, who has broken my yoke of sin It is Jesus, washed my iniquities of the past and the future  It is Jesus, who washed my body with His pure water.   3. So, I`ll live in meditating I`ll break Delilah`s Imprisonment with the baptism of Christ Where I can quickly remove all my sins that surround me The washing of my feet is the foundation of my faith, the baptism of Jesus.   #. 6 The New Life Mission · To keep your traditions ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)  ***** ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዛዝ ንቃችኋል፣ በሰው ስርዓት ተተብትባችሁ ከክርስቶስ ጸጋ ወድቃችኋል፣ ጊዜው ሳያልፍ ባትመለሱ ከጠማማው ከመንገዳቹ፣ ዛሬ ፍርድን እናገራለሁ ገሃነም ነው መጨረሻቹ።   1. በከንፈሩ እያከበረ ከኢየሱስ የራቀ ሰዉ፣ በፍርድ ቀን በእውነት ያፍራል አላውቅህም ዞርበል ሲለዉ፣ ሳይደርስብህ አሁን ተመለስ የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቁጣ፣ ካለህበት ሰፊው ጎዳና ሳይረፍድብህ  ቶሎ በል ውጣ።   2. ተው ተመለስ አንተ ወንድሜ ተው ተመለስ ከሞት ጎዳና፣ ተው ተመለስ ኃጢአት ያለበት ተው ተመለስ አልዳነምና፣ ክርስቲያን ነኝ በጌታ ብለህ እራስህን አታታልለው፣ ይልቅ ንስሃ ግባ ተመለስ ያለኽበት በጨለማ ነው፤ ~ ተይ ተመለሺ አንቺ እህቴ ከሞት መንደር ከጠፊው ዓለም፣ በነፍሱ ምስክር የሌለው በእግዚአብሔር መንግስት አይደለም፣ የታል ውኃው ደሙ መንፈሱ ምስክሩ የእምነትሽ፣ ንስሐ ግቢ በጽድቁ ዳኚ ቶሎ አምልጪ ከጥፋትሽ።   3. ንስሃ ግቡ መንግሥቱ ቀርባለች ንስሐ ግቡ ኑና ዳኑ ንስሃ ግቡ ውኃ ደም መንፈሱን ንስሐ ግቡ ወንጌሉን እመኑ ንስሃ ግቡ እውነተኛው ወንጌል ንስሐ ግቡ ይሄው ተገልጧል ይህ ሦስቱ ምስክር ያለው ጻድቅ ሆኖ ከፍርድ ያመልጣል።     TRANSLATION ? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯   Title: To keep your traditions ***** To keep your traditions, You have ignored God`s command; Having been twisted by the system of men, You have fallen from the grace of Christ; If you don`t turn back before the time is up, from your crooked path; Today I speak judgment, hell is your end.   (1) Glorifying with his lips, a man who was far from Jesus; He will be truly ashamed on the Day of Judgment, when saying to him, "I never knew you, turn around"; Turn back right now before it happens to you, what he terrible wrath of God befalls you; From your wide street where you`re in, hurry out from it.   (2) Return my brother, return from the path of death; Turn back, he who has sin, turn back, was not saved; By saying that you are a Christian in the Lord, don`t deceive yourself; Instead, repent & return you are in the darkness. ~ Return, my sister, from the village of death, from the lost world; He who has no witness in his soul, was not in the kingdom of God; Where is the water, the blood & the spirit?, the witness of your faith; Repent & be save by the righteousness of God, quickly escape from your destruction.   (3) Repent, the kingdom is near, Repent, come & be save; Repent, in the gospel of water, blood & spirit, repent, believe in it; Repent, the true gospel, repent, this is what has been revealed; He who has these three witnesses, will be righteous & escape the judgment.   #. 7 The New Life Mission · If Abraham believed God and was justified አብርሃም እግዚአብሔርን አምኖ ከጸደቀ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ አብርሃም እግዚአብሔርን አምኖ ከጸደቀ አብርሃም የእምነት ሰው ሆኖ ከታወቀ  እኔም ቃል ኪዳኑን ብቻ አምናለሁ  ካደኩበት መንደር ወጥቻለሁ እኔም ቃል ኪዳኑን ብቻ አምናለሁ  ባጸደቀኝ መንገድ እጓዛለሁ ።   1.  የእምነት አባቶቼን ትኩር ብዬ አያለሁ  የእነርሱን ፈለግ እከተላለሁ በሕይወት መንፈስ ሕግ እጓዛለሁ  ኢየሱስ መንገዴ ብርሃኔ ነው  የኢየሱስ ጥምቀት መዳኔ ነው  የኢየሱስ ስቅለት ቤዛዬ ነው የኢየሱስ ትንሣኤ  ሕይወቴ ነው። (2*)   2.  በአንዱ አዳም አመጸኛ ሆኜ ተወልጃለሁ፣ በእኔ በስጋዬ  መልካም እንደሌለ አምናለሁ፣ እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት መንፈስ ሕግ ተማምኜ፣ በዓለም ኃጢአት የለም እያልኩ አውጃለሁ በእርሱ ሆኜ።   3.  ጻድቃን በእምነት በሕይወት ይኖራሉ የእግዚአብሔርን ጽድቅን ብቻ ይገልጣሉ ከእምነት ወደ እምነት ከፍታቸው  ሊኖሩ ይገባል ለጌታቸው።   4.  ነገር ግን ለጥፋት ቢመለሱ ዓለምን ቢወዱ በልባቸው፣ አፈግፍገው ለውድቀት ቢበቁ በዚህ አይደሰትም አምላካቸው፣ በወንጌል ሳያፍሩ በእውነቱ እስከ ለዘለዓለም በጸኑበት፣ የሕይወት አክሊል አለ ከፊታቸው ባመኑበት ጌታ ማያፍሩበት።     TRANSLATION ? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ If Abraham believed God and was justified (Singer Tezera Ermiyas) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ If Abraham believed God and was justified If Abraham is known as a man of faith And also I only believe in his promise I left the village where I grew up I only believe in his promise I will walk in the way that approves me.   1. I look at my fathers of faith I follow their footsteps I walk by the law of the spirit of life Jesus is my way my light The baptism of Jesus is salvation The crucifixion of Jesus is my redemption The resurrection of Jesus is my life.   2. I was born as a rebel in one Adam I believe that there is no good in my flesh I believe in the law of the spirit of life given by God I declare that there is no sin in the world.   3. The righteous shall live their life by their faith They only reveal God`s righteousness From faith to faith their height They must live for their Lord.   4. But if they turn to destruction if they love the world in their hearts If they retreat and fall their God will not be pleased with this In which indeed if they persevered up to end without being ashamed of the gospel There is a crown of life before them in which they will not be ashamed of the Lord they have trusted.   #. 8 The New Life Mission · Let me preach the gospel ወንጌል ልስበክ (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ 1.  ከልብ የሚፈልቅ ደስታ ለአምላኬ የማደርሰው፣ እኔም በሐሴት የምሞላው ነፍሴም ጠግባ የምትርሰው፣ ድካሞቼን እያራገፍኩ እንደ ንስር ምታደሰው፣ ወንጌል ስሰብክ ሳወራ ነው ምሰለጥን የምነግሰው።   ወንጌል ልስበክ ልበርታ ወንጌል ልስበክ ለጌታ ወንጌል ልስበክ ለራሴ ግድ ደርሶብኝ ስለጠራኝ እሩጫውን ትሩጥ ነፍሴ።   2.  ተስፋ አለኝ አሻግሬ በእምነቴ ምቆምበት፣ ተስፋ አለኝ የምወርሰው በንግስና ምነግስበት፣ ተስፋ አለኝ የሚያጽናና የሚያጸናኝ ምጸናበት፣ ተስፋ አለኝ ሚያበረታ ብድራቴን የማይበት።   3.  ብስብሱ ስጋ ተዋጅቶ ያንቀላፋ ጻድቅ ተነስቶ ከፍ ከፍ ብሎ ወደላይ ሲታደም በበጉ ሰርግ ላይ አያለሁ አይቀርም ምጽዓቱ ወርሳለው በጊዜው በሰዓቱ ።   4.  ማራናታ እያልኩ ምጠራው በግርማ ሞገስ የተፈራው ፈጥኖ እንዲመጣ ሙሽራው በወይኑ ቦታ ላይ ተግቼ ሰራለው  የሚያየኝን ውዴን በእርግጥ እያዋለው።     TRANSLATION ? ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯   Let me preach the gospel (Singer Mesfin Berhanu) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ 1. I bring joy from my heart to my God And also I am full of joy, and my soul is satisfied I shake off my fatigue and renew it like an eagle When I preach the gospel when I talk I train.   Let me preach the gospel let me be strong Let me preach the gospel to the Lord Let me preach the gospel to myself I care because he called me, so run the race my soul.    2. I have hope and stand by my faith I have hope that I will inherit a kingdom I have hope that comforts and strengthens me I have hope that shines that will not destroy my debt.   Let me preach...    3. Rotten meat redeemed Sleeping righteous awakened up Raised up and up At the wedding of the lamb I`ll see, his coming is inevitable I`ll inherit just in time.   Let me preach...    4. I call him Maranatha The one whose majesty is terrible The bridegroom to come I`ll work strong in the vineyard I`ll see he who sees me my dear .   Let me preach...

    • Mesfin Berhanu Ubba
    • Ethiopia
    • 03/02/202498
  • ቁ.12

    ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡

    ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡ብዙዎችን ገድለዋል፡፡ የእምነት ሕይዎታቸውንም አሰልቺ አድርጎባቸዋል፡፡ይህ ትምህርት ምንድ ነው? የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ይጸድቃል ግን #በቅድስና ቀስ በቀስ እያደገ ይመጣል የሚል ትምህርት ነው: ወይም የህደት ቅድስና ይባላል፡፡ሰው በክርስቶስ ካመነ በኃላ ኃጢአትን መስራት እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ ይሄድና መጨረሻ ላይ ክርስቶስን መስሎ ቁጭ ይላል የሚል ትምህርት ነው፡፡ይህ ትምህርት በጣም ማራኪና ደስ የሚል ትምህርት ይመስላል፡፡.ይህን ለመጀመራያ ጊዜ ሲትሰሙ ልባችሁ ይነካል፡፡ከዚያም በኃላ ዘመናችሁን ኢየሱስን ለመምሰል እየታገላችሁ ትጨርሳላችሁ፡፡ እውነታው ግን ይበልጥ በሞከራችሁ ቁጥር የማይቻል መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ብዙ ኃጢአት ውስጥ ትወድቃላችሁ፡፡ ሕሊናችሁ ሲወቅሳችሁ ደግሞ የንሰሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡አሁንም ትሞክራላችሁ ከዚያም ትወድቃላችሁ፡፡እንደገና ደግሞ የንስሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡ ይህ አሰልቺ ዑደት ይቀጥላል፡፡ ሲያቅታችሁ የማስመሰል/የግብዝነት ሕይወት ትለማመዳላችሁ፣ምን ታደርጋላችሁ ምንም አማራጭ የለማ፡፡ ይህ የተሳሳተ ትምህርት ነው ብሎ የሚያስብ ማንም የለም፡፡ምንክንያቱም ብዙ ማሳመኛ በሚመስሉ ጥቅሶች ታጅቡዋል ፡፡.ለምሳሌ ጳውሎስ…..‹‹እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ›› ብልዋል፤ኢየሱስ ደግሞ ‹‹አባቴ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ›› ብልዋል….‹‹#በቅድስና #ተመላለሱ››…የሚሉ .ሌላ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፡፡ዳሩ ግን እነዚህ ጥቅሶች ብዙዎች እንደሚረዱ አይደሉም፡፡ጳውሎስ በእውነት ኢየሱስን የመሰለው ኃጢአትን ባለመስራት ነውን? ኢየሱስ ፍጹማን ሁኑ ሲለን በስጋችሁ ምንም ኃጢአት መስራት የለባችሁም እያለ ነውን? እነዚህ መልዕክቶች ምን ማለት ናቸው? በቅድስና መመላለስ ማለት ምን ማለት ነው?.እነዚህን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት መጀመረያ የራስችሁን አስተሳሰብና አረዳድ አሽቀንጥራችሁ ጣሉ፡፡በመቀጠል የሚከተሉትን እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችን በማንበብ እምነተችሁን አስተካክሉ፡፡ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሰተ መንገድ በመረዳት የእምነት ሕይዎታችውን ለመኖር ሲሞክሩ በጣም ይከብዳችሁዋል፤ መጨረሻ ላይ ተስፋ ይቆርጡና ተራ ሃይማኖተኛ ሆኖ በአለም ይመላለሳሉ፡፡ ትክክለኛውን የእምነት መንገድ፣ #ዳግም #የመወለድ ምስጢርና #ድል #ነሺ #የእምነት #ሕይወት እንዴት መኖር እንደምንችል የሚያሳዩ ድንቅ መጽሐፍት አሉን፡፡.የበለጠ ለመረዳት እነዚህን ነፃ የክርስቲያን መንፈሳዊ መጽሐፍ ያግኙ፡፡ጌታ ኢየሱስ ‹‹በነፃ ተቀብላቿዋል በነፃ ስጡ›› ሲላለ፣ የኃጢያትን ስርየትን የሚያሰገኝ የመዳንን እውቀት የሚሰጡትን መጽሐፍት #በነፃ እንሰጣለን፤ በአድራሻችሁ እንልካለን፡፡ አድራሻችሁን ፃፉልን፡፡ . የኃጢአታችሁን ስርየት በማግኘት በመንፈሳዊ በረከት ተባረኩ!09105551900910367615bjnewlife.orgYohannes Make Mara, Ethiopia

    • Yohannes Make Mara
    • Ethiopia
    • 04/09/2023123
The New Life Mission

በዳሰሳ ጥናታችን ይሳተፉ

ስለእኛ እንዴት ሰሙ?