Search

ስለ እኛ

The New Life Mission

The New Life Mission በነጻ በሚታደሉት የክርስቲያን መጽሐፎች አማካይነት በውሃና በደም የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን መገናኘት ትችል ዘንድ ባሉት ችሎታዎች ሁሉ በተሻለው መንገድ ጌታን ለማገልገል የተሰጠ ነው፡፡ በነጻ የሚታደሉት መጽሐፎቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተመሠረቱ በመሆናቸው ሰዎች በውሃና በመንፈስ መወለድ የሚችሉበትን ተጨባጭ እውነት ቀለል ባለ ግልጥነት ያብራራሉ፡፡ በሕትመትና በኤሌክትሮኒክ ስሪቶች የቀረቡትን መጽሐፎቻችንን እንድታነብና በእነዚህ መጽሐፎች ውስጥ ተገለጠውን እውነት እንድታገኝ እናደፋፍርሃለን፡፡ በዚህ የጨለማ ዘመን ውስጥ በጣም ብዙ ሰዎች እውነትን እየተጠሙ ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች ወደ እግዚአብሄር ጽድቅ ለመምራት የመብራት ቤት ሆነው ማገልገል የሚችሉ የክርስቶስ ወታደሮችን እንሻለን፤ ከእነርሱም ጋር መሥራት እንፈልጋለን፡፡ የ The New Life Mission በነጻ የሚታደሉ የክርስቲያን መጽሐፎች በአጠቃላይ 65 ቅጾችን ይዘው የሰውን ዘር ደህንነት፣ የክርስቲያንን ሕይወት፣ የሺህውን ዓመትና የመንግሥተ ሰማይን ተስፋ፣ የዘላለምንም ሕይወት በሚያብራራ የእግዚአብሄር ቃል የተሞሉ ናቸው፡፡ እነዚህ መጽሐፎች የመንግሥተ ሰማይ መዝገቦች እንደተደበቁበት እርሻ ናቸው፡፡ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ተብሎ የተጠራውን የከበረ መዝገብ እንድታገኝና ያለህን ሁሉ በመሸጥ ይህንን እርሻ እንድትገዛ እንፈልጋለን፡፡ በመጽሐፎቻችን አማካይነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ልንመራህ እንፈልጋለን፤ በክርስቶስም ከአንተ ጋር አብረን የጽድቅን ሥራ ልንሠራ እንፈልጋለን፡፡

ከተፈጥሮ ጥፋቶች፣ ከሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታና ከኳንተም ስሌት አነሳስ ጋር አብሮ አሁን ይህ ዓለም ልክ መስመሩን እንደሳተ ባቡር ወደ መጨረሻው የጥፋት መዳረሻ በጣም በፍጥነት እየነጎደ ነው፡፡ በሰው ታሪከ ውስጥ ዓለም አሁን እያየ እንዳለው ዓይነት በጣም ፈጣን ለውጦች ያየበት ጊዜ የለም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ጌታ ወደዚህ ምድር ከመመለሱ በፊት ያለውን የጥፋቶችና የመከራዎች ጅማሬ የሚጠቁሙ ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ እንዲህ ባሉ ጊዜያቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከዚህ ዓለም ጋር የተቆራኘ ተጨማሪ የጥድፊያ ሕይወትን ከመምራት በቀር ምርጫ የላቸውም፡፡ በዚህ ምክንያት ልቦቻቸው ይበልጥ ከእግዚአብሄር እየራቁ ነው፡፡ አንድ ቀን ጸረ ክርስቶስ እግዚአብሄርን በመቃወም ይነሳና ዓለምን ይገዛል፡፡ ስለዚህ አሁን እየኖርን ያለነው በመንፈሳዊ ረሃብ ዘመን ውስጥ እንደሆነ በመገንዘብ ጌታ በሰጠን የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ቃል ማመንና የእርሱ ሕዝብ መሆን አለብን፡፡ እንዲህ ባለ ዘመን ውስጥ የምንኖር ሁላችን The New Life Mission የደህንነትን ብርሃን እያበራ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ለምን ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ መዳን እንደሚገባችሁ ምክንያቱንና ትክክለኛውን መልስ ይጠቁማችኋል፡፡

  • ታሪክና ዓላማ፤

    The New Life Mission በ1991 በሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግ የተመሠረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ገለልተኛ የሚሽን ድርጅት ነው፡፡ ዓላማው በሥነ ጽሁፍ አገልግሎቱ አማካይነት በተለያዩ ቅርጸቶች የእግዚአብሄርን ቃል በመላው ዓለም ለእያንዳንዱ ሰው ማሰራጨት ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉምና እያንዳንዱ ሰው በውሃና በመንፈስ ዳግመኛ መወለድ እንዲችል የአገልግሎቱ ትኩረት የታተሙ መጽሐፎችን፣ ኢ-መጽሐፎችንና ኦድዮ መጽሐፎችን በማተምና በመበተን ላይ ያረፈ ነው፡፡ The New Life Mission ዋና መሥሪያ ቤቱ በሰሜን ኮርያ፤ ሴዑል ሲሆነ በዓለም ዙሪያ ከ90 በላይ በሚሆኑ አገሮች አጋር ሠራተኞች አሉት፡፡ እነዚህ አጋር ሠራተኞች ከሬቨረ. ጆንግ ጋር አብረው ግባቸውን የእግዚአብሄርን መንግሥት በመገንባት ላይ አኑረዋል፡፡

  • አገልግሎት፤

    በነጻ የሚታደሉ የክርስቲያን መጽሐፎችን፣ ኢመጽሐፎችንና ኦድዮ መጽሐፎችን መተርጎምና ማተመም፡፡

    የሥነ ጽሁፍ አገልግሎት ወንጌልን በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት እጅግ ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም የሬቨረ. ፖል ሲ. ጆንግን ተከታታይ የክርስቲያን መጽሐፎች ከ90 በላይ በሆኑ ዋና ቋንቋዎች አሳትመናል፡፡ ተጨማሪ ነፍሳቶችን ወደ ጌታ ጽድቅ ለመምራትም ጠንክረን በመሥራት እንቀጥላለን፡፡ ተርጓሚና/ወይም አርታኢ በመሆን ከአገልግሎታችን ጋር እንድትቀላቀል ብታስብ እንወዳለን፡፡ ፍላጎት ካለህ እባክህ ‹‹አጋር ሠራተኛ ለመሆን ተመዝገብ›› የሚለውን ቁልፍ ጠቅ አድርግ፡፡