ማውጫ
ክፍል አንድ — ስብከቶች
1. ለመዳን አስቀድመን ስለ ኃጢአቶቻችን ማወቅ አለብን (ማርቆስ 7፡8-9፣ 20-23)
2. ሰዎች ኃጢአተኞች ሆነው የተወለዱ ናቸው (ማርቆስ 7፡20-23)
3. ነገሮችን በሕጉ መሠረት ብናደርግ ሕጉ ሊያድነን ይችላልን? (ሉቃስ 10፡25-30)
4. ዘላለማዊው ቤዛነት (ዮሐንስ 8፡1-12)
5. የኢየሱስ ጥምቀት እና የኃጢአቶች ማስተስረያ (ማቴዎስ 3፡13-17)
6. ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው በውሃ፣ በደምና በመንፈስ ቅዱስ ነው (1ኛ ዮሐንስ 5፡1-12)
7. የኢየሱስ ጥምቀት ለኃጢአተኞች የድኅነት እውነተኛ ምሳሌ ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20-22)
8. የተትረፈረፈው ቤዛነት ወንጌል (ዮሐንስ 13፡1-17)
ክፍል ሁለት — አባሪ
1. ተጨማሪ ማብራሪያ
2. ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
(Amharic)
የዚህ መጽሐፍ ዋና ርዕሰ ጉዳይ “በውሃና በመንፈስ እንደገና መወለድ” ነው። በዚህ መጽሐፍ ዋና ርዕሰ ጉዳይ ላይ ኦሪጂናል ነው። በሌላ አባባል፣ ይህ መጽሐፍ እንደገና መወለድ ምን እንደሆነና በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በውሃና በመንፈስ እንዴት እንደገና እንደምንወለድ በግልጽ ይነግረናል። ውሃው በዮርዳኖስ የኢየሱስን ጥምቀት ይወክላል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ሁሉም ኃጢአታችን ወደ ኢየሱስ የተላለፈው በመጥምቁ ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ነው። ዮሐንስ የሰው ዘር ሁሉ ተወካይና የሊቀ ካህኑ የአሮን ዘር ነበር። አሮን በኃጢአት የማስተስረያ ቀን እጆቹን በተለቀቀው ፍየል ራስ ላይ በመጫን የእስራኤላውያንን ዓመታዊ ኃጢአት ሁሉ ወደ እሱ አሳልፎ ሰጠ። ይህ መስዋዕት ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር ጥላ ነው። የኢየሱስ ጥምቀት የእጅ መጫን ምልክት ነው። ኢየሱስ በዮርዳኖስ በእጅ መጫን መልክ ተጠመቀ። ስለዚህ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ ወሰደና ስለ ኃጢአቱ ለመክፈል ተሰቀለ። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ክርስቲያኖች ኢየሱስ በዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ ለምን እንደተጠመቀ አያውቁም። የኢየሱስ ጥምቀት የዚህ መጽሐፍ ቁልፍ ቃልና የውሃና የመንፈስ ወንጌል የማይነጠል ክፍል ነው። በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀሉ በማመን ብቻ እንደገና መወለድ እንችላለን።
(German)
Das Hauptthema dieses Titels ist "aus Wasser und Geist von neuem geboren zu werden." Er hat die Orginalität zu diesem Thema. Mit anderen Worten, dieses Buch sagt und deutlich, was es bedeutet, wiedergeboren zu werden und wie man aus Wasser und Geist in strikter Übereinstimmung mit der Bibel wiedergeboren wird. Das Wasser symbolisiert die Taufe Jesu im Jordan und die Bibel sagt, dass alle unsere Sünden an Jesus weitergegeben wurden, als Er von Johannes dem Täufer getauft wurde. Johannes war der Vertreter der gesamten Menschheit und ein Nachkomme von Aaron dem Hohepriester. Aaron legte seine Hände auf den Kopf des Sündenbocks und gab alle jährlichen Sünden der Israeliten am Versöhnungstag an ihn weiter. Es ist ein Schatten von den zukünftigen Gütern. Die Taufe Jesu ist das Gegenbild des Auflegens von Händen.
Jesus wurde in Form des Auflegens von Händen im Jordan getauft. Also nahm Er alle Sünden der Welt durch Seine Taufe weg und wurde gekreuzigt, um für die Sünden zu bezahlen. Aber die meisten Christen wissen nicht, warum Jesus im Jordan von Johannes dem Täufer getauft wurde. Jesus Taufe ist das Schlüsselwort dieses Buches und der unverzichtbare Teil des Evangeliums des Wassers und des Geistes. Wir können nur von neuem geboren werden, wenn wir an die Taufe Jesu und Sein Kreuz glauben.
Next
Amharic 2: ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል ተመለሱ
German 2: Rückkehr zum Evangelium des Wassers und des Geistes
ተጨማሪ