Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።

  • Daniel Tesfaye Heramo
  • Ethiopia
  • 10/30/2021 1863

ሰላም!
ዳንኤል ተስፋዬ እባላለሁ።
ከእኔ ሕይወት ትማሩ ዘንድ የደህንነት ምስክርነቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።
ተወልጄ ያደኩት  በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ
ነው።አባቴ የቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሲሆን ከአንድም ሁለት ቦታ
የመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ በሌሉባቸው ቦታዎች ቤ/ክ በመትከል
ብዙ ሰዎችን ጴንጤ አድርጉዋል።በቤተሰባችን ውስጥም ቋሚ የሆነ
የማለዳ ፣የቀትርና የማታ ፕሮግራሞች ይደረጋሉ።ራሴን ወደ
ማወቅ ደረጃ ላይ ስደርስ (የ7ተኛ ክፍል ተማሪ እያለው ነው)
አንድ ቀን የምሽት ፕሮግራማችን ላይ አባቴ "ዳንኤል" ብሎ
ሲጠራኝ "አቤት አባባ" አልኩኝ።"ጌታን መቀበል ትፈልጋለህ?"
ሲለኝ ፣ ጥያቄው እንግዳ ስለነበረብኝና እኔ ጌታን ተቀብያለው ብዬ
አስብ ስለነበር ፈራ ተባ እያልኩ "እንዴ አባባ እስከዛሬ ጌታን
አልተቀበልኩም ማለት ነው? ለማለት አስቤ ፊት ፊቱን ሳየው"
ሃሳቤ ገባው መሰለኝ ሳልጠይቀው እንዲህ አለኝ።
ይኸውልህ ልጄ ክርስትና የሚወረስ ነገር አይደለም።ወደህ
አምነህ የምትከተለው ነገር ነው።ሲለኝ እንዴ አባባ እኔ እኮ
ክርስቶስን የምከተለው ወድጄ ነው አልኩት።ከዛም በል
እንግዲህ ወደህ የምትከተል ከሆነ ተነስና እጆችህን ወደላይ
በማንሳት እኔ የምለውን ደግመህ በማለት ጌታን ተቀበል አለኝ
እኔም በደስታ እጄን አንስቼ አባቴ የሚለውን በመከተል"አለምንና
ሴጣንን ክጃለው፤ኃጢያትን ክጃለው፤ጌታ ሆይ ስሜን በህይወት
መዝገብ ላይ ፃፈው..." ስል ጌታን ተቀበልኩ።ከዛም የተለያዩ
ትምህርቶችን በመከታተል ተጠመኩ ፣ወደ አገልግሎት ውስጥ
ተሰማራው።እያደኩ ስመጣም የታዋቂ ፓስተሮችንና
ወንጌላውያንን አገልግሎት በሬድዮ (በተለይ የምስራች ድምጽን)፣በመፅሄት፣እንዲሁም
ስብከቶቻቸውን በካሴት አጥብቄ እከታተል ነበር፤ የሃይስኩል
ተማሪ እያለው ትዝ ይለኛል፤ሃጢያት ያስጨንቀኝ፤ቅጀት
ያስጨንቀኝ ጀመረ።የምሰማቸው ስብከቾች ሁሉ ተቀደስ፤ኃጢያት
አትስራ ነው፤የምሰማቸው መገለጦች ያሳቅቁኝ ነበሩ" አንድ ሴት
አለሽ/አንድ ሰው አለህ በቅርቡ ይሄንና ያንን ሃጢያት
ሰርተሃል..." የሚሉ አሳቃቂ መገለጦች።
እኔ በወቅቱ በአፍላ እድሜዬ ላይ እንደመገኘቴ በየቀኑ በተግባር
ባላመነዝርም ባሳብ ግን የምዳራቸው ሴቶች ነበሩ፤እናም "አንድ
ሰው አለህ አመንዝረህ የመጣህ"የሚሉ መገለጦችን በሰማው
ቁጥር በጣም እሳቀቅ ነበር፤ከዛም ያው አንድ በተግባር
የሚያመነዝር ሰው ስለማይጠፋ ያ ሰው ብድግ ሲል ሁፈይ እኔን
አደለም ማለት ነው ብዬ እፅናናለው።ነገር ግን ለጊዜው
ነው፤ወዲያው ሃጢያቴ እንደጭጋግ ይከበኝና እጨነቃለው።በዛ
ላይ ለሊት በጣም ያቃዠኛል።እፀልያለው።አፀልያለው። ነገር ግን
ሁሌም ኃጢያት ያስጨንቀኛል።ስለ ኃጢያቶቼ የንስሃ ፀሎት
ፀልያለው።ደስ ይለኛል።ግን ደሞ ወዲያው ተመልሼ ራሴን
ኃጢያት ስሰራ አገኘዋለው።ያኔ በቃ እኔ መቀደስ የማልችል ሰው
መሆኔ ገባኝ።ባህሪዬ ጥሩ ስላልሆነ መፅሀፍ ቅዱስ መያዝ ራሱ
አፍራለው።የማፍረው በመፅሀፍ ቅዱስ ሳይሆን በራሴ ባህሪ ነው።
አንዳንድ እኔ በደንብ የማውቃቸው ሴትና ወንድ ጓደኞቼ መፅሀፍ
ቅዱስ ይዘው ሽር ብትን እያሉ ቸርች ሲሄዱ ሳይ በድፍረታቸው
እደነቃለው።እኔ ግን ማስመሰልን እንደነሱ ስላልተካንኩበት ነው
መሰለኝ የሃጢያቴን ብዛት ሳስብ ራሴን ለጌታ ያልተገባው አድርጌ አስብ ነበር።
የ10ኛ ክፍል ውጤት መቶልኝ የፕሪፕ ተማሪ ስሆን፤የተለያዩ
ጥያቄዎችን በማንሳት ስለ እምነቴ ራሴንና የተለያዩ አገልጋዮችን
መጠየቅ ጀመርኩ።ከዛም ማቴ7:21-23ን አንድ ቀን ሳነብ አንድ
ነገር ግልፅ ሆነልኝ።ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ስም አጋንንት
አውጥተው፣በሽተኛ ፈውሰው፣ትንቢት ተናግረውና ብዙ
ተሃምራትን አድርገ ገሃነም የሚገቡ ከሆነ እኔማ ብዬ
መዳኔን100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እንደማልችል
ገባኝ፤ከነዚህ ሰዎች አንዱ አለመሆኔን ማረጋግጥበት ነገር
አልነበረም።በዛ ላይ ኃጢያት ያለበት ሰው በኢየሱስ ቢያምንም
እንኳ መንግስተሰማይ መግባት እንደማይችል አውቃለው።
የሚገርመው አንድ እንግዳ ሰው አግኝቶኝ በጌታ ነህ? ብሎ
ቢጠይቀኝ "አዎ፤ተጠምቄያለው፤በክርስቶስ ፀድቂያለው" ብዬ
መልሳለው።አዬ መፅደቅ እቴ?! ኃጢያት በሰራው ሰሃት ሁሉ ግን
አለመፅደቄ ኃጢያት ያለብኝ ሰው መሆኔ ቁልጭ ብሎ
ይታየኛል።ሰዎች ድኛለው በጌታ ነኝ የሚሉት ቃላት ሁሉ ባዶ ይሆንብኛል።
ከዛም በቃ አምሮዬ ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ
መፅደቅ ማለት ምን ማለት ነው? በአዳም የገባው ኃጢያት ሚባለው የትኛው ነው? 
እኔ ብቻ ነኝ አጢያት መስራት ማቆም
ያቃተኝ ወይስ ሁሉም ሰው እንደኔ ነው?....ብዙ
ጥያቄዎች።በዚህ መሃል ኢንትራንስ ውጤት መጥቶልኝ አ.አ.ዩ
ገባው።እውነት እኔ ድኛለው?
የሚለው ጥያቄዬ ተጠናክሮ ከኔ ጋር ካንፓስ ገባ።
ትንሽ ግን "ፌሎ አቴንድ" ሳደርግ፤በለስላሳ ሙዙቃ ታጅበን
ስናመልክ ምናምን በቃ ሁሉን እረሳለው።ደስ ይለኛል።በእንባ
ታጅቤ ያመለኳቸው ጊዜያቶችን አልረሳቸውም።የማልዋሻቹ ነገር
ግን ከፌሎ እንደወጣው ሁሉን እረሳለው።"የኔን አምልኮ
በእርግጥ እ/ር ይቀበለዋል?" ስል አስባለው።እንደ አብዛኞቹ
የፌሎ ጓደኞቼ ሻይ ቡና ብዬ ዶርሜ ገባና ላይብረሪ ሄጄ
ካጠናው ቡሃላ ብዙ ጊዜ ስለእምነቴ አስባለው።እንዲህ እንዲህ
እያልኩ የመጀመሪያ አመት ፍሬሽ ማንነቴን ጨረስኩና ወደ
ቤተሰብ ጋር ለመሄድ በተሰናዳሁበት ወቅት አንድ በጣም
የምወደው ከክርስቲያን ቤተስብ የሆነ ዶርምሜቴ፤ዳኒ ወክ
እናድርግ ብሎኝ 6 ኪሎን ለቀን ወደ ፬ ኪሎ ማዝገም ጀመርን፤
ድንገት ግን አራት ኪሎ ስንደርስ አንድ ወጣት መንፈሳዊ መፅሀፍ
በሃያ አያ ብር ብቻ! ሲል ጓደኛዬ  "ዳኒ ክረምቱን
እንድናነበው ለምን መንፈሳዊ መፅሀፉን አንገዛውም"
አለኝ።በነገራችን ላይ ጓደኛዬ ከእኔ እጅጉን የተሻለ አንባቢ
ነው።ለመንፈሳዊ ነገሮች ያለው ጥማት እኔን እራሱ ያስከነዳል። በቃ መፅሀፉን ገስተን ሁለታችንም ወደየቤተሰቦቻችን
መረሽን።ክረምቱን እኔ ትንሽ እሱ በደንብ አንብቦ ሁለተኛ አመት
ላይ ተገናኘን ። ከዛም አስቀድመን ተደዋውለን ስለነበር ለፌሎ
እንዲመቸን ከሌሎች ክርስቲያን ተማሪዎች ጋር አንድ ዶርም
ያዝን። ጓደኛዬ የኔንና የራሱን መፅሀፍ አንብቦ ጨረሰ።ሌላም
ተጨማሪ ራሱ ፀሐፊው የፃፈውን ሁለት መፅሀፍ አነበበ።
ከዛም ፌሎ እርግፍ አድርጎ ተወና ከትምህርቱ በላይ መፅሀፍ
ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። እኔና ሌሎች ዶርም ሜቶቹ ፌሎ
እንዳይቀር መከርነው።አልሰማንም።ጭራሽ አንድ ቀን እኔ "እኛ
በጌታ የሆንን ሰዎች" እያልኩ ሳወራ።"ዝም በል ባክህ አንተ
አልዳንክም" ብሎ አስደነገጠኝ።"ኸረ ባኪህ እኔማ ድኛለው"
አልኩት።"እኔም የዳንኩት አሁን ነው አትሸወድ" አለኝ።ኸረ
ፍልስፍና ጀመርሽ? በማለትም ላልሰማው ጆሮዬን ደፍኜ ለአንድ
ሴሚስተር ያህል ተከራከርኩት።ፌሎ ስሄድ ምሰማቸው ስብከቶች
ማስተዋል ጀመርኩ፤የህግ ት/ት እና ምድራዊ ስኬትን ሚያራግቡ ናቸው።
አንድ ቀን እስቲ ዝም ብዬ በጭፍን ከምቃወመው ላዳምጠው
ብዬ የተረዳውን እንዲነግረኝ ጠየኩት እርሱም እንዲህ በማለት
ዳግም የምወለድበትን እውነታ ነገረኝ፦
 እኛ ሰዎች የምንድነው አስቀድመን ስለኃጢያቶቻችን ስናውቅ
ነው።የምንወለደው 12 ኃጢያቶችን በልባችን ይዘን ነው
(ማር7:20-23) ።አለኝ ክፍሉን አወጣውና አነበብኩት።እውነት
ነው እኔ በዘመኔ ስሰራቸው የነበሩ ኃጢያቶች ናቸው።"እነዚህን
ኃጢያቶች በልብህ እንዳሉ ታምናለህ?"ሲለኝ።"በሚገባ" አልኩት
። "እስከለተሞትህስ እንደምትሰራቸው ታምናለህ?" ሲለኝ አዎን አልኩት ።
እኔ ግን በኢየሱስ አምናለሁ እኮ አልኩት። ታምናህ እኔም አምን ነበር ታውቃለህ ግን ዳግመኛ አልተወለድኩም ነበር ። አንተም ዳግመኛ አልተወለድክም ።
ይህን ሲለኝ ትንሽ እንደመብሸቅ አልኩና " እንደውም ልንገርህ እኔ በስህተት መንገድ ከሆንኩ ኢየሱስ እንደጳውሎስ ተገልጦ ተመለስ ይበለኝ ። " አልኩት ያኔ እንዲህ አለኝ " እግዚአብሔር የሚናገረን እኛ በምንፈልገው መንገድ ሳይሆን እርሱ በፈለገው መንገድ ነው አለኝ ።
ያኔ በልቤ ለማመን ወሰንኩ ። በዚህ ወቅት በዮሐንስ መልዕክት ላይ የተጻፈ አንድ የnlm መጽሐፍ አንብቤ
ጨርሼ ነበር ።
ስለብሉይ ኪዳን የስርየት ህግ ፣ስለህግ አላማ ፣ ስለኢየሱስ ጥምቀት ፣ ስለመስቀል ሞቱና ዘላለማዊ ስርየቱ ፣ ስለንስሃ ጸሎት አላስፈላጊነት፣ ስለሰው ጽድቅና የእግዚአብሔር ጽድቅ ልዩነት አወኩ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለየው ። ድኜ ቀረው ።
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ኃጢአቶቼን ሙሉ በሙሉ እንደወሰደልኝ አውቄ በልቤ ስቀበል ፤
ኢየሱስ በመስቀል ተሰቅሎ በውኃና በደም በደሎቼን እንደደመሰሳቸው እንደተኮነነልኝ ሳምን ፤ኢየሱስ በትሣዬው አዲስ ፍጥረትና ኃጢአት አልባ እንዳደረገኝ በልቤ ሳምን
ድኜ ቀረው ።
አሁን ላዳነኝ ለዚህ ጌታ ከወንድሞቼና እህቶች  ጋር  በመሆን የወንጌልን ስራ እየሰራው አለው።
ስለሁሉ ጌታ ኢየሱስ የተመሰገነ  ይሁን! !
Daniel Tesfaye Heramo, Ethiopia