ወንጌልን ስንሰብክ በጥበብ መስበክ እንዳለብን የእምነት አባቶቻችን ይመክሩናል! ያ እጅግ በጣም ድንቅ ምክር ነው! ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ከዕለት ዕለት ህይወትችን ስንነሳ ዳግም ካልተወለዱ ሰዎች ጋር በሚኖሩን የተለያዩ ግንኙነቶቻችን መልካም ግንኙነቶችን ማድረግ ይኖርብናል! ያም ወንጌልን በምንሰብካቸው ሰዓት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርልናል! ሌላው ለዓለም ህጎችም መገዛት ይኖርብናል ምክንያቱም የዓለም ህጎችን ተላልፈን ወንጌልን መስበክ አይቻልምና! የዓለም ህጎችን መታዘዝ ስንል ግን ሁሉንም ህጎች መቀበል ማለት አይደለም! መታዘዝ ያለብን እምነታችንን የማይነኩ ሲሆኑ ብቻና ብቻ መሆን አለበት! የእምነት አባቶቻችን እምነታቸውን የሚነኩ የዓለም ህጎችን አንቀበልም በማለት ሰማዕት ሆነዋል! እኛም የዛሬዎቹ ጻድቃን በእምነታችን የሚመጣብንን ማንኛውንም ነገር መታዘዝም ሆነ መቀበል የለብንም! በሌላ በኩል ወንጌልን በጥበብ መስበክ ማለት ባገኘናቸው የወንጌል በሮች ሁሉ በመጠቀም ወንጌልን መስበክ አለብን ማለት ነው! በሌላ አነጋገር አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ወንጌልን መስበክ አለብን ማለትም ነው! ሁላችንም እዚጋ አንድ ማስታዋል ያለብን ነገር ወንጌልን በየትኛው ዘርፍ መስበክ እንዳለብን ማወቅ አለብን ያም ማለት የትኛው ዘርፍ ወንጌልን ለመስበክ እንደሚቀርበን መገንዘብ ማለት ነው! በቸርች ውስጥ ወንጌልን በማሰራጨት ሂደት ላይ ከትናንሽ ሀላፊነቶች ጀምሮ እስከ ትላልቅ ሀላፊነቶች አሉ! ለምሳሌ ቤ/ክንን ማጽዳት, ለወንጌል ስርጭት መውጣት, የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን መስራት, ለቅዱሳን ምግብ ማብሰል, ስብከቶችን መስበክ, ዝማሬዎችን ማዘጋጀት ሌሎችም የመሳሰሉ ስራዎች ይኖራሉ! አንድ ጻድቅ ሁሉንም ሀላፊነቶች ብቻውን መወጣት በፍጽም አይችልም ሁላችንም ግን የየራሳችንን ሀላፊነቶች ስናውቅ ሀላፊነቶቻችንን በአግባቡ መወጣት እንችላለን እዚጋ ዋናው መልዕክት አንዳችን ያለአንዳችን በጋራ ካልሆነ በቀር በግላችን በፍጥነት መራመድ አለመቻላችን ነው! እኛ ቅዱሳን ባለንበት ውስብስብ ዓለም ውስጥ የውሀውንና የመንፈሱን ወንጌልን በአራቱም ማዕዘናት የማሰራጨት ሃላፊነት አለብን ይሄን ስል የእኔ ሃላፊነት ምንድነው በየትኛውስ ዘርፍ ነው ማገልገል ምችለው? ጥያቄውን ለራሳችን እየመልስን በምንችለው ሁሉ ወንጌልን መስበክ ይኖርብናል! ሁላችንም ባለን አቅም በትጋት ወንጌልን የምንሰብክ ከሆነ በዛም ድንቅ ስራ እስከመጨረሻው የምንጸና ከሆነ ወንጌላችን በመላው ዓለም ይደረሳል ከዛም በእርግጥም ኢየሱስ ይመጣል የተስፋውንም ቃል ይጠብቃል! ከበደላችን ሁሉ ያነጻን እስካለንበት ጊዜ ድረስ በእምነት ያቆመን እግዚአብሔር ይመስገን እስከሞት ድረስት በሚታመን እምነትም ይባርከን! ወንድማችሁ Teferi Oshine Tanto Ethiopia/Hawassa