Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

የእምነት ምስክርነት

  • Teferi Oshine
  • Ethiopia
  • 11/19/2021 2051

ሰላም ቅዱሳን ጸጋው የበዛላችሁ ከእግዚአብሔር የተሰጠን እውነተኛው ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን! ዛሬ ከእምነት ምስክርነታችን እንድንማማር የእምነት ምስክርነቴን ልጽፍላችሁ ወደድኩ! እግዚአብሔር ቢፈቅድ በእምነት ህይወቴ የሚገጥሙኝን መልካምና ክፉ ገጠመኞቼን እንድንማርባቸው በቀጣይ ጊዜያት ልጽፍ እመኛለው!!! ዳግም መቼ እንደተወለድኩ ትክክለኛ ቀኑን ወሩንና አመቱን አላስታውስም!  ግን ጻድቅ ያደረገኝ እግዚአብሔር ይመስገን! እንዴት ዳግም እንደተወለድኩ ማብራራት እችላለው!  ከ6 አመቴ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ ድረስ ያደኩት በፕሮቴስታንት ሀይማኖት ውስጥ ነበር! የውሃውን እና የመንፈሱን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ ከጎረቤት የሚኖር የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አርበኛ ስራውን ሊሰራ የመንደሩን ህጻናት ሰበሰበ በሰዓቱ እኔ የ10 አመት ልጅ ነበርኩ!  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ 14 አመቴ በመንደራችን ከህጻናቱ ጋር ከአርበኛው የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እየሰማውና ቤተሰብ ከሚልከኝ ሀይማኖት ቤት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉ ነብያት ታሪክ እየተማርኩ ቀጠልኩ በ11 እና 12 ዓመቴ፣ የክርስቶስን ጽድቅ መሰረታዊ የድነት እውቀት እየለየው መጣው!  ያም የክርስቶስ ጽድቅ በልቤ እንዲታተም አደረገ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ!!!  13 እና 14 አመት ሲሆነኝ የክርስቶስ ፅድቅ በልቤ ሲያብብ አየሁ!  ስለ ሰው ማንነት፣ ስለ ሕግ፣ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ስለ ብሉይ ኪዳንኑና ስለ አዲስ ኪዳኑ የስርየት ሥርየት፣ ስለ ውኃ ደም መንፈስ መሠረታዊ የደኅነት እውቀትና በአጠቃላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ወንጌል የበለጠ ተረዳው።  ሳላስበው ወንጌልን ስሰብክ እና ውሸታሞችን እየተቃወምኩ የሬቨረንድ ፓውልሲ ጆንግን መጽሃፍ የማሰራጭ ሆኜ እያገለገልኩ መጣው!  ሀዋሪያው ጳውሎስ "እኔ ከሰበኩላችሁ ወንጌል ውጭ ማንም በሰብካችሁ የተረገመ ይሁን" ገላቲያ 1፥7-9  እንዳለው እኔም ከአውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውጭ ሌላ ወንጌል ሁሉ ከሰይጣን መሆኑን የውሃውንና የመንፈሱ ወንጌል በመስበክ አረጋግጣለው! ወንጌላችን ሌላ አደለም (ኢየሱስ እንደመስዎዕቱ በግ ያለነውር ከሰማይ መቷል በእጆች መጫን ስርዓት በጥምቀቱ የዓለምን ሁሉ ሀጢአት ወስዷል ሰለሀጢአትም ዋጋን ሁሉ ከፍሏል በእርግጥም ሞቷል በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነስቷል የሚል ነው ሀሌሉያ!) በሚገርም ሁኔታ እዚሁ 14ኛ አመቴ ላይ እያለው ጥምቀት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ከተረዳው በኋላ ፕሮቴስታንቶች እድሜክ 14 ደርሷል ብለው የጥምቀት ትምህርት እንድጀምር ተነገረኝ! መንፈስ ቅዱስ ወደ ውቡ ወንጌል (የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል) ጠቅልሎ ሊወስደኝ ሲወድ ያንን አደረገ! እኔ ባህሪዬ ዝምተኛና አይንአፋር ነኝ¡ የዛን ቀን ግን በሙሉ ድፍረት የተለያዩ ጥያቄዎችንና ንግግሮችን ሳደርግ እንደነበር አስታውሳለው ከጥያቄዎቼ አንዱ ኢየሱስ ለምን ተጠመቀ? የሚል ነበር ምንም እንኳን ብዙ እና ከእኔ ትላልቅ ቢሆኑም ኢየሱስ ለምን እንደተጠመቀ አያውቁም ነበር በተዋቡ ቃላት የተሳሳቱ መልሶችን ብቻ ይመልሳሉ! በንግግራቸው ሁሉም እንደህጻናት ይታዩኝ ጀመር! ከዛን ጊዜ ጀምሮ በእኔ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ማድረስ ጀመሩ ለጓደኞቼ በሙሉ ተፈሪ የስዕተት አስተምህሮት ውስጥ ገብቷል እርሱን እንዳትሰሙት የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጡ! በዚህ ሁሉ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ድፍረት ሲሆነኝ እምነትን ሲሰጠኝ አንደበቶቼን ሲዳስስ እንደነበር አያለው፡ በመጨረሻም የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል አሸንፎ ሙሉ እኔነቴን ለውሃውና ለመንፈሱ ወንጌል አቅርብያለው በድጋሚ ምስጋን ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን!!! ከዛን ጌዜ ጀምሮ ሳልቀላቅል ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ውሃ ጣፍጦኝ እየጠጣው ነው! ውቡ ወንጌላችን በዓለም ሁሉ ይድረስ!!! ሁላችንም እስከሞት ድረስ በእምነታችን እንድንጸና አባታችን ኢየሱስ በነገር ሁሉ ይርዳን! ወዳችኋለው ተባረኩ! ወንድማችሁ ተፈሪ ኦሺኔ ታንቶ Ethiopia/Hawassa