Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 12/12/2022 1833

 

ርዕስ፦ መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)

(1). መዳን የለም ከሥርዓቱ መንገድ ተሸሽቶ
ደም አንጠልጥሎ እጆች የመጫን ህጉ ተከድቶ
አብ ያቀደው ነውርና እንከን ዕድፍ የሌለው
ምታመንበት መቆሚያ ዓለት አለኝ የምለው


ውኃ ነው፣ ደሙ ነው፣ መንፈሱ ሰማይ ያወቀው  
ውኃው ነው፣ ደሙ ነው፣ መንፈሱ አብ ያረቀቀው

(2). ተቀብያለሁ በነፍስ ያደረ ምስክርነት 
 ይሄ ነው ደንህነት የማያሳፍር ድንቅ ልጅነት
 በላይ በሰማይ የእ/ር አብ ዕቅድ የሆነ
በኢየሱስ ሥራ ከዓለማት በፊት የተወሰነ
በሰማያዊ በቀይ ሐምራዊ ጥልፍ የተሰራ
ጥሩ በፍታ ነው ያደመቀው እጅግ የጠራ።

(3). የኢየሱስ ጥምቀት ነው የዓለምን ኃጢአት የወሰደው 
በሞት ኩነኔ ፍርድ የራቀበት የፈጸመው 
የእኔ በደሎች አንዲትም ሳትቀር ተሽሮልኛል
የእግዚአብሔር ፍቅር በልጁ በኩል እኔን ምሮኛል።

(4). የማዳኑን ቃል አላጓድልም
ከሥርዓቱ ውጭ ንቅንቅ አልልም
እርሱ በላከው በዮሐንስ እጅ በተደረገው 
ዮርዳኖስ ሄጄ በኢየሱስ አምኜ እኔ ድኛለው፡፡

(5). በተጠረገው መንገድ ኃጢአት በሌለው ጎዳና
ከላይ በተመረቀው በአዲስ ኪዳን በጸና
በኢየሱስ በበሩ በኩል በሕይወቴ ብርሃን በርቶ 
ጻድቅ ሰው ሆኜ እጓዛለሁ ሥራዬ ሁሉ ተሰርቶ፡፡

(6). መስዋቴን ይዤ እንከን አልባውን እንደተጻፈው
እጄን ጭኜበት ክፋት በደሌ ሁሉ ተላልፈው
ምህረት የሚያስገኝ ደምን ይዤ ነው ምቀርብ ከፊቱ
ደወል ይሰማል የምስራች ነው  አውደ ምህረቱ።