ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡
Yohannes Make Mara
Ethiopia
04/09/2023 2230
ክርስትና ውስጥ በጣም ስር የሰደደው አደገኛው በሽታ የቀስ በቀስ ቅድስና ትምህርት ነው፡፡ብዙዎችን ገድለዋል፡፡ የእምነት ሕይዎታቸውንም አሰልቺ አድርጎባቸዋል፡፡ ይህ ትምህርት ምንድ ነው? የሰው ልጅ አንድ ጊዜ ይጸድቃል ግን #በቅድስና ቀስ በቀስ እያደገ ይመጣል የሚል ትምህርት ነው: ወይም የህደት ቅድስና ይባላል፡፡ ሰው በክርስቶስ ካመነ በኃላ ኃጢአትን መስራት እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ፣ እያቆመ ይሄድና መጨረሻ ላይ ክርስቶስን መስሎ ቁጭ ይላል የሚል ትምህርት ነው፡፡ይህ ትምህርት በጣም ማራኪና ደስ የሚል ትምህርት ይመስላል፡፡ . ይህን ለመጀመራያ ጊዜ ሲትሰሙ ልባችሁ ይነካል፡፡ከዚያም በኃላ ዘመናችሁን ኢየሱስን ለመምሰል እየታገላችሁ ትጨርሳላችሁ፡፡ እውነታው ግን ይበልጥ በሞከራችሁ ቁጥር የማይቻል መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ብዙ ኃጢአት ውስጥ ትወድቃላችሁ፡፡ ሕሊናችሁ ሲወቅሳችሁ ደግሞ የንሰሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡አሁንም ትሞክራላችሁ ከዚያም ትወድቃላችሁ፡፡እንደገና ደግሞ የንስሀ ጸሎት ትጸልያላችሁ፡፡ ይህ አሰልቺ ዑደት ይቀጥላል፡፡ ሲያቅታችሁ የማስመሰል/የግብዝነት ሕይወት ትለማመዳላችሁ፣ምን ታደርጋላችሁ ምንም አማራጭ የለማ፡፡ ይህ የተሳሳተ ትምህርት ነው ብሎ የሚያስብ ማንም የለም፡፡ምንክንያቱም ብዙ ማሳመኛ በሚመስሉ ጥቅሶች ታጅቡዋል ፡፡ . ለምሳሌ ጳውሎስ…..‹‹እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ›› ብልዋል፤ ኢየሱስ ደግሞ ‹‹አባቴ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ›› ብልዋል…. ‹‹#በቅድስና #ተመላለሱ››…የሚሉ .ሌላ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ጥቅሶች ብዙዎች እንደሚረዱ አይደሉም፡፡ጳውሎስ በእውነት ኢየሱስን የመሰለው ኃጢአትን ባለመስራት ነውን? ኢየሱስ ፍጹማን ሁኑ ሲለን በስጋችሁ ምንም ኃጢአት መስራት የለባችሁም እያለ ነውን? እነዚህ መልዕክቶች ምን ማለት ናቸው? በቅድስና መመላለስ ማለት ምን ማለት ነው? . እነዚህን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት መጀመረያ የራስችሁን አስተሳሰብና አረዳድ አሽቀንጥራችሁ ጣሉ፡፡በመቀጠል የሚከተሉትን እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችን በማንበብ እምነተችሁን አስተካክሉ፡፡ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሰተ መንገድ በመረዳት የእምነት ሕይዎታችውን ለመኖር ሲሞክሩ በጣም ይከብዳችሁዋል፤ መጨረሻ ላይ ተስፋ ይቆርጡና ተራ ሃይማኖተኛ ሆኖ በአለም ይመላለሳሉ፡፡ ትክክለኛውን የእምነት መንገድ፣ #ዳግም #የመወለድ ምስጢርና #ድል #ነሺ #የእምነት #ሕይወት እንዴት መኖር እንደምንችል የሚያሳዩ ድንቅ መጽሐፍት አሉን፡፡ . የበለጠ ለመረዳት እነዚህን ነፃ የክርስቲያን መንፈሳዊ መጽሐፍ ያግኙ፡፡ጌታ ኢየሱስ ‹‹በነፃ ተቀብላቿዋል በነፃ ስጡ›› ሲላለ፣ የኃጢያትን ስርየትን የሚያሰገኝ የመዳንን እውቀት የሚሰጡትን መጽሐፍት #በነፃ እንሰጣለን፤ በአድራሻችሁ እንልካለን፡፡ አድራሻችሁን ፃፉልን፡፡ . የኃጢአታችሁን ስርየት በማግኘት በመንፈሳዊ በረከት ተባረኩ! 0910555190 0910367615 bjnewlife.org Yohannes Make Mara, Ethiopia
ዝርዝር፤