Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

Mesfin Berhanu Ubba`s gospel songs

  • Mesfin Berhanu Ubba
  • Ethiopia
  • 03/02/2024 1613

#. 1
መከሩ ብዙ ነው (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)
 
መከሩ ብዙ ነው ምናያቸው 
ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው
የመከሩ ባለቤት ጌታችን 
ሠራተኞችን አንሳን ስጠን
 
(1). የጠፉ በጎች ከፊትህ
ይሳቡ ባንተ ምህረትህ
ከጎተራው ውስጥ ፍሬ ይግባ
ቤትህ በጻድቃን ይገንባ
 
(2). በምድረ በዳ በራብ ያሉ
ተጨንቀው በክፉ የተጣሉ
ጌታ ምህረትህ ያግኛቸው
እግዚአብሔር ክንድህ ይስባቸው
 
(3). የቤትህ አገልጋይ ሰራተኞች 
ጽድቅን የሚያወሩ ወታደሮች 
በየከተማው በገጠሩ 
ለሠማይ መንግስት የሚሰሩ 
ውኃ ደም መንፈስ ዓላማቸው 
የቤትህ ቅናት ሚበላቸው
የሰይጣንን ግንብ የሚያፈርሱ
የቤቱን ቅጥር የሚያድሱ        
                      ጌታ ይነሱ         
                        ዛሬ ይነሱ         
                           ኦ ይነሱ 
ጌታ ይነሱ  
ዛሬ ይነሱ  
አዎ ይነሱ  
አሜን ይነሱ ።
 
____
The harvest is plenteous (Singer: Mesfin Berhanu)
 
The harvest is plenteous
But workers are few
Lord of the harvest
Give us the workers
 
(1). Lost sheep before you
Draw in your mercy
Let the fruit come from the barn
Build your house with the righteous
 
The harvest is plenteous
But workers are few
Lord of the harvest
Give us the workers
 
(2). Those who are hungry in the desert
Worried and badly thrown
Lord have mercy on them
May God draw your arms
 
(3). The staff of your house
Soldiers who speak righteousness
In every city, in the countryside
They Working for the kingdom of heaven
The Water blood spirit is their purpose
Jealousy of your home what eats them
Those who destroy the tower of Satan
Renovating the walls of the house
                      O Lord arise
                        Get up today
                           Oh get up
O Lord arise
Get up today
Yes, get up
Amen arise.
 
The harvest is plenteous
But workers are few
Lord of the harvest
Give us the workers
 
 
#. 2
ጌታ ሆይ ድካሜ ብዙ ነው(ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ጌታ ሆይ ድካሜ ብዙ ነው ምደክምበት
ኃጢአቴ ብዙ ነው የማፍርበት
ውርደቴን ወሰድከው ከበላዬ 
ጸጋህ ጥላ ሆነኝ ከለላዬ
ጸጋህ ድጋፍ ሆነኝ መቆሚያዬ
ጸጋህ ኃይል ሆነኝ መመኪያዬ።
 
1. 
ወጀቡ ሲነሳ ሊያሰጥመኝ
ዓለም ሥጋ ሰይጣን ሲከበኝ
የእምነቴ ጋሻ መከታዬ
ኢየሱስ ጥምቀትህ ነው መሸሸጊያዬ
ኢየሱስ ደምህ ነው መትረፊያዬ 
ኢየሱስ ትንሳኤህ ነው ማምለጫዬ
 
2. 
ምመካበት የለኝም ሚያስመካኝ
ጽድቄ እንኳ መርገም ነው ሚገለኝ
በህግህ የማርከኝ ወድሃለሁ
ኢየሱስ ታማኝ ነህ አምንሃለሁ ።
 
3. 
ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ 
ማረፊያ ጌታ ኢየሱሴ
ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ
አዳኜ ጌታ ኢየሱሴ
ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ
ፍቅር ነህ ጌታ ኢየሱሴ
ተመስገን ልበልህ ሁልጊዜ 
ወደድከኝ ጌታ ኢየሱሴ ።
 
_
O Lord, my fatigue is great (Singer Mesfin Berhanu) 
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
O Lord, my fatigue is great, I will tire
My sins are many, of which I am ashamed
You took away my shame
Your grace is my shadow and my protection
Your grace is my support
Your grace has become my proud.
 
 1.
To drown me when the whirlwind arises 
The world, the flesh, the Satan surrounds me 
My shield of faith 
Jesus, your baptism is my refuge
Jesus, is your blood is my salvation
Jesus, your resurrection is my escape
 
 2.
I have nothing to be proud of
Even my righteousness is curse killer of me
I love you, you forgave me with your law
Jesus, you are faithful, I believe you.
 
 3.
I will Thank you always
My rest Lord Jesus
I will Thank you always
My savior, Lord Jesus
I will Thank you always
You are love, Lord Jesus
I will Thank you always
You love me Lord Jesus.
 
 
#.3
ነውር ያለውን እንስሳ እግዚአብሔር አይፈልግም(ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ነውር ያለውን እንስሳ እግዚአብሔር አይፈልግም 
እጆች ሳይጫንበት ኃጢአት አይተላለፍም 
ጌታ የደነገገው የኃጢአት ስርየት ያለው
ጠቦቱ ሲታረድ በደሙ መፍሰስ ነው።
~
ይሄ ነው ደኅንነት የኃጢአት ስርየት አለን
የሕይወት መንፈስ ህግ እግዚአብሔር የሰጠን።
 
1.
በንስሐ ጸሎት ማንም ከኃጢአት አይነጻም
ጻድቅ ሰው ተብሎ ለመንግሥቱ አይበቃም፤
በሕይወት መንፈስ ህግ በእግዚአብሔር ስርዓት 
መቅረብ ይሻለናል ለመንጻት ከኃጢአት ።
 
2.
በሕግ በነብያት እግዚአብሔር ተናግሯል 
የስርየት ሕጉን በእርግጥ አስተምሯል 
ኃጢአትን ላይቆጥር ገብቷል በኪዳኑ
በክርስቶስ ስራ አምነው ለሚድኑ።
 
3.
በጥምቀቱ ሰጠኝ  በጎውን ሕሊና
የልቤን ሸለፈት ቆርጫለሁና
ከሕግ እርግማን  ነጻ አውጥቶናል 
ክርስቶስ በስራው ልጁ አድርጎናል።
 
4.
የሰው ፍልስፍና ሃይማኖት ይገድላል 
የስርየቱን ሕግ ጻድቅ ያስተውላል 
ቃሉን አይሽረውም እግዚአብሔር ይሰራል 
በአንዱ መስዋዕት ዘላለም ይምራል።
 
___
God does not want an animal that has blemish (Singer Tezera Ermiyas)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
God does not want an animal that has blemish 
Sin is not transmitted without the laying on of hands
The forgiveness of sins that the Lord has decreed
It is the shedding of the blood when the lamb is slaughtered.
~
This is the salvation we have the forgiveness of sins
God gave us the law of the spirit of life.
 
1.
No one is freed from sin through the prayer of repentance
Being not called as a righteous man and not sufficient for the kingdom
In the law of the spirit of life, God`s order
It is better to near to be cleansed from sin
 
2.
God spoke through the prophets in the law
He really taught the law of atonement
He entered with his covenant to not counting the sin
For those who believe and saved in the works of Christ.
 
3.
By his baptism he gave me a good conscience
For I have cut the foreskin of my heart
He freed us from the curse of the law
Christ has made us His Son in His work.
 
4.
The Human philosophy religion kills
The righteous understand the law of the atonement of God
God does not cancel his word
He forgives forever through one sacrifice.
 
#.4
ሸለፈታም ሆኖ የለም ፋሲካ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ) 
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ሸለፈታም ሆኖ የለም ፋሲካ 
የእግዚአብሔር ስርዓት ከቶ አይነካ 
የልብን ግርዛት ያላገኘ ሰው
የአብርሃም ዘር አይደለም የረከሰ ነው።
 
1. 
ከግብጽ ምድር ከፈርኦን ቤት ከባርነቱ
ያወጣኝ እርሱ እግዚአብሔር ነው በስርዓቱ 
ሸለፈት ወድቆ ምልክት ኖሮኝ ደም በመቃኔ 
ነጻ አውጥቶ ያዘምረኛል በአዲስ ቅኔ።
 
2. 
አዲስ ዘመን ሆኗል አዲስ መንገድ ለኛ
በውኃ ደም መንፈስ ተገኝቷል መዳኛ
ከኃጢአት ባርነት ከግብጽ  አውጥቶናል
ፋሲካችን ጌታ ለእኛ ታርዶልናል።
 
3. 
እንበላለን ፋሲካ በየለቱ
እንበላለን  ፋሲካ በህምረቱ 
የመከራን ዘመን ተሻግረናል
ከመናው ዘወትር ያበላናል
ፋሲካ በየቀን ሆኖልናል
ምስጋና በየቀን በዝቶልናል።
 
4. 
አላወቀም ይሄ ዓለም የፋሲካን ስርዓቱን 
እህል ቂጣ መራራውን የደም ቅጠል ምልክቱን
በጨለማ በባርነት  ከውኃ ከደም የራቀ ሰው
ከፋሲካ አልደረሰም ዛሬም በኃጢአት በግብፅ ነው።
 
TRANSLATION ?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
There is no easter with being a foreskin  (Singer Tezera Ermiyas)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
There is no easter with being a foreskin
God`s order will never affect
A person who has not received the circumcision of the heart
He is not the seed of Abraham he is unclean.
 
1.
From the land of Egypt from Pharaoh`s house, from his slavery
It is God who brought me out, through the system 
The foreskin fell off and the symbol of blood lived on my doorframe
He settled me free and he makes me sing a new song.
 
2.
It has become a new era a new way for us
In water, blood, spirit found Savior
He brought us out of the slavery of sin in Egypt
Our Passover has been sacrificed for us.
 
3.
We eat Easter every day
We will eat Easter in His mercy
We have passed the time of suffering
He always feeds us from the manna
Easter is every day
Gratitude abounds for us every day.
 
4.
This world did not know the easter system
Grain bread bitter blood leaf symbol
Enslaved in darkness a man far from water and blood
He did not arrive from the Passover and is still in Egypt today in sin.
 
 
#. 5
ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን
በየቦታው ሚቆሽሸውን 
ዝቅ ብሎ አጠበ እግሬን
በብዙ እድፍ የተሞላውን
 
1.
ውኃን አዘጋጅቶ ክብሩን ለኔ ትቶ
ጭቅቅት ዕድፌን ከላዬ ላይ አሽቶ
ሙልጭ አርጎ ያጠበኝ 
ከእንግዲህ በኋላ ንጹሕ ሰው ነህ ያለኝ።
 
2.
ኢየሱስ ነው አስታውሰው ያረኩልህን በሕይወትህ ዘመንህ፣
ኢየሱስ ነው አስታውሰው ከእኔ እንዲትኖር እንዲዘልቅ መዳንህ፣
ኢየሱስ ነው ያለኝ እኔን ዮርዳኖስ የሄደው፣
ኢየሱስ ነው የኃጢአት ሸክም ቀንበሮቼን ከላይ የናደው፣
ኢየሱስ ነው ያለፈውን መጪውን በደሌን፣
ኢየሱስ ነው በጥሩ ውኃው ያጠበው ሰውነቴን።
 
3.
ስለዚህ ኖራለሁ እያሰላሰልኩኝ
የደሊላን እስር በክርስቶስ ጥምቀት እየበጣጠስኩኝ
ቶሎ ሚከበኝን ኃጢአቶቼን ሁሉ የማስወግድበት
የእግሬ መታጠብ የእምነቴ መሰረት የኢየሱስ ጥምቀት። 
 
TRANSLATION ?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
He lowered and Washed my feet (Singer Mesfin Berhanu)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
He lowered and Washed my feet
The one it gets dirty in everywhere
He lowered and Washed my feet
which is full of stains
 
1.
He prepared water and left his glory to me
He wiped my mud and my stains above on me
He washed me full perfectly 
He said me you are an innocent person from now on.
 
2.
It is Jesus, remember what I did for you during your life
It is Jesus, remember that you`ll live with me and that your salvation lasts
It is Jesus said to me the one who went to Jordan
It is Jesus, who has broken my yoke of sin
It is Jesus, washed my iniquities of the past and the future 
It is Jesus, who washed my body with His pure water.
 
3.
So, I`ll live in meditating
I`ll break Delilah`s Imprisonment with the baptism of Christ
Where I can quickly remove all my sins that surround me
The washing of my feet is the foundation of my faith, the baptism of Jesus.
 
#. 6
ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ) 
*****
ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትዛዝ ንቃችኋል፣
በሰው ስርዓት ተተብትባችሁ ከክርስቶስ ጸጋ ወድቃችኋል፣
ጊዜው ሳያልፍ ባትመለሱ ከጠማማው ከመንገዳቹ፣
ዛሬ ፍርድን እናገራለሁ ገሃነም ነው መጨረሻቹ።
 
1.
በከንፈሩ እያከበረ ከኢየሱስ የራቀ ሰዉ፣
በፍርድ ቀን በእውነት ያፍራል አላውቅህም ዞርበል ሲለዉ፣
ሳይደርስብህ አሁን ተመለስ የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቁጣ፣
ካለህበት ሰፊው ጎዳና ሳይረፍድብህ  ቶሎ በል ውጣ።
 
2.
ተው ተመለስ አንተ ወንድሜ ተው ተመለስ ከሞት ጎዳና፣
ተው ተመለስ ኃጢአት ያለበት ተው ተመለስ አልዳነምና፣
ክርስቲያን ነኝ በጌታ ብለህ እራስህን አታታልለው፣
ይልቅ ንስሃ ግባ ተመለስ ያለኽበት በጨለማ ነው፤
~
ተይ ተመለሺ አንቺ እህቴ ከሞት መንደር ከጠፊው ዓለም፣
በነፍሱ ምስክር የሌለው በእግዚአብሔር መንግስት አይደለም፣
የታል ውኃው ደሙ መንፈሱ ምስክሩ የእምነትሽ፣
ንስሐ ግቢ በጽድቁ ዳኚ ቶሎ አምልጪ ከጥፋትሽ።
 
3.
ንስሃ ግቡ መንግሥቱ ቀርባለች ንስሐ ግቡ ኑና ዳኑ
ንስሃ ግቡ ውኃ ደም መንፈሱን ንስሐ ግቡ ወንጌሉን እመኑ
ንስሃ ግቡ እውነተኛው ወንጌል ንስሐ ግቡ ይሄው ተገልጧል
ይህ ሦስቱ ምስክር ያለው ጻድቅ ሆኖ ከፍርድ ያመልጣል።
 
 
TRANSLATION ?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
 
Title: To keep your traditions
*****
To keep your traditions, You have ignored God`s command;
Having been twisted by the system of men, You have fallen from the grace of Christ;
If you don`t turn back before the time is up, from your crooked path;
Today I speak judgment, hell is your end.
 
(1)
Glorifying with his lips, a man who was far from Jesus;
He will be truly ashamed on the Day of Judgment, when saying to him, "I never knew you, turn around";
Turn back right now before it happens to you, what he terrible wrath of God befalls you;
From your wide street where you`re in, hurry out from it.
 
(2)
Return my brother, return from the path of death;
Turn back, he who has sin, turn back, was not saved;
By saying that you are a Christian in the Lord, don`t deceive yourself;
Instead, repent & return you are in the darkness.
~
Return, my sister, from the village of death, from the lost world;
He who has no witness in his soul, was not in the kingdom of God;
Where is the water, the blood & the spirit?, the witness of your faith;
Repent & be save by the righteousness of God, quickly escape from your destruction.
 
(3)
Repent, the kingdom is near, Repent, come & be save;
Repent, in the gospel of water, blood & spirit, repent, believe in it;
Repent, the true gospel, repent, this is what has been revealed;
He who has these three witnesses, will be righteous & escape the judgment.
 
#. 7
አብርሃም እግዚአብሔርን አምኖ ከጸደቀ (ዘማሪ ተዘራ ኤርምያስ)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
አብርሃም እግዚአብሔርን አምኖ ከጸደቀ
አብርሃም የእምነት ሰው ሆኖ ከታወቀ 
እኔም ቃል ኪዳኑን ብቻ አምናለሁ 
ካደኩበት መንደር ወጥቻለሁ
እኔም ቃል ኪዳኑን ብቻ አምናለሁ 
ባጸደቀኝ መንገድ እጓዛለሁ ።
 
1. 
የእምነት አባቶቼን ትኩር ብዬ አያለሁ 
የእነርሱን ፈለግ እከተላለሁ
በሕይወት መንፈስ ሕግ እጓዛለሁ 
ኢየሱስ መንገዴ ብርሃኔ ነው 
የኢየሱስ ጥምቀት መዳኔ ነው 
የኢየሱስ ስቅለት ቤዛዬ ነው
የኢየሱስ ትንሣኤ  ሕይወቴ ነው። (2*)
 
2. 
በአንዱ አዳም አመጸኛ ሆኜ ተወልጃለሁ፣
በእኔ በስጋዬ  መልካም እንደሌለ አምናለሁ፣
እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት መንፈስ ሕግ ተማምኜ፣
በዓለም ኃጢአት የለም እያልኩ አውጃለሁ በእርሱ ሆኜ።
 
3. 
ጻድቃን በእምነት በሕይወት ይኖራሉ
የእግዚአብሔርን ጽድቅን ብቻ ይገልጣሉ
ከእምነት ወደ እምነት ከፍታቸው 
ሊኖሩ ይገባል ለጌታቸው።
 
4. 
ነገር ግን ለጥፋት ቢመለሱ ዓለምን ቢወዱ በልባቸው፣
አፈግፍገው ለውድቀት ቢበቁ በዚህ አይደሰትም አምላካቸው፣
በወንጌል ሳያፍሩ በእውነቱ እስከ ለዘለዓለም በጸኑበት፣
የሕይወት አክሊል አለ ከፊታቸው ባመኑበት ጌታ ማያፍሩበት።
 
 
TRANSLATION ?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
If Abraham believed God and was justified (Singer Tezera Ermiyas)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
If Abraham believed God and was justified
If Abraham is known as a man of faith
And also I only believe in his promise
I left the village where I grew up
I only believe in his promise
I will walk in the way that approves me.
 
1.
I look at my fathers of faith
I follow their footsteps
I walk by the law of the spirit of life
Jesus is my way my light
The baptism of Jesus is salvation
The crucifixion of Jesus is my redemption
The resurrection of Jesus is my life.
 
2.
I was born as a rebel in one Adam
I believe that there is no good in my flesh
I believe in the law of the spirit of life given by God
I declare that there is no sin in the world.
 
3.
The righteous shall live their life by their faith
They only reveal God`s righteousness
From faith to faith their height
They must live for their Lord.
 
4.
But if they turn to destruction if they love the world in their hearts
If they retreat and fall their God will not be pleased with this
In which indeed if they persevered up to end without being ashamed of the gospel
There is a crown of life before them in which they will not be ashamed of the Lord they have trusted.
 
#. 8
ወንጌል ልስበክ (ዘማሪ መስፍን ብርሃኑ)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
1. 
ከልብ የሚፈልቅ ደስታ ለአምላኬ የማደርሰው፣
እኔም በሐሴት የምሞላው ነፍሴም ጠግባ የምትርሰው፣
ድካሞቼን እያራገፍኩ እንደ ንስር ምታደሰው፣
ወንጌል ስሰብክ ሳወራ ነው ምሰለጥን የምነግሰው።
 
ወንጌል ልስበክ ልበርታ
ወንጌል ልስበክ ለጌታ
ወንጌል ልስበክ ለራሴ
ግድ ደርሶብኝ ስለጠራኝ እሩጫውን ትሩጥ ነፍሴ።
 
2. 
ተስፋ አለኝ አሻግሬ በእምነቴ ምቆምበት፣
ተስፋ አለኝ የምወርሰው በንግስና ምነግስበት፣
ተስፋ አለኝ የሚያጽናና የሚያጸናኝ ምጸናበት፣
ተስፋ አለኝ ሚያበረታ ብድራቴን የማይበት።
 
3. 
ብስብሱ ስጋ ተዋጅቶ
ያንቀላፋ ጻድቅ ተነስቶ
ከፍ ከፍ ብሎ ወደላይ
ሲታደም በበጉ ሰርግ ላይ
አያለሁ አይቀርም ምጽዓቱ
ወርሳለው በጊዜው በሰዓቱ ።
 
4. 
ማራናታ እያልኩ ምጠራው
በግርማ ሞገስ የተፈራው
ፈጥኖ እንዲመጣ ሙሽራው
በወይኑ ቦታ ላይ ተግቼ ሰራለው 
የሚያየኝን ውዴን በእርግጥ እያዋለው።
 
 
TRANSLATION ?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
 
Let me preach the gospel (Singer Mesfin Berhanu)
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
1.
I bring joy from my heart to my God
And also I am full of joy, and my soul is satisfied
I shake off my fatigue and renew it like an eagle
When I preach the gospel when I talk I train.
 
Let me preach the gospel let me be strong
Let me preach the gospel to the Lord
Let me preach the gospel to myself
I care because he called me, so run the race my soul.
 
 2.
I have hope and stand by my faith
I have hope that I will inherit a kingdom
I have hope that comforts and strengthens me
I have hope that shines that will not destroy my debt.
 
Let me preach...
 
 3.
Rotten meat redeemed
Sleeping righteous awakened up
Raised up and up
At the wedding of the lamb
I`ll see, his coming is inevitable
I`ll inherit just in time.
 
Let me preach...
 
 4.
I call him Maranatha
The one whose majesty is terrible
The bridegroom to come
I`ll work strong in the vineyard
I`ll see he who sees me my dear .
 
Let me preach...