የውሃውንና የመንፈስን ወንጌል የሰጠኝና ከእድሜ ልክ ኃጢአቴ ሁሉ ያዳነኝ ዛሬን ድረስ በህይወት ያኖረኝ ኢየሱስ ይመስገን።
ዛሬ 26ኛ ልደቴ ነው! እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በህይወት የኖርኩት በክርስቶስ ጽድቅ ላይ ባለኝ እምነት ነው ነገንም በክርስቶስ ጽድቅ እኖራለው ሃሌሉያ!
አምላክ የሆነው ኢየሱስ የሰው ስጋ ለብሶ ስለኃጢአታችን ያለነውር ከሰማይ ወደ ምድር መጣ፣ አምላክ የሆነው ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሞላው ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ በመጥምቁ ዩሐንስ ስለኃጢአታችን ተጠመቀ ዩሐንስም በኢየሱስ ራስ ላይ እጆቹን በመጫኑ አማካኝነት የዓለምን ኃጢአት በሙሉ ጌታ ኢየሱስ በስጋው ተሸከመ፣ አምላክ የሆነው ኢየሱስ ስለኃጢአታችን ቅጣታችንን ሁሉ ተቀበለ ሞተም፤ በሶስተኛውም ቀን ከሞት ተነሳ ሃሌሉያ ይህንን ድንቅ ወንጌል ስላመንኩ ጻዲቅ ሆኛለው፣ መፈስ ቅዱስን በልቤ ተቀብያለው፣ ጌታን ማመስገን እችላለው፣ ጌታን በጸሎት መገናኘት እችላለው እንዲሁም ይህንን ድንቅ ወንጌል ለመስበክ ተሹሜያለው! ነገንም በህይወት የምኖረውም ለዚሁ ለወንጌል ስራ ነው አሜን ምነኛ ታደልኩ ሃሌሉያ!
ዛሬም ደስ እያለኝ ለእናንተ ከእድሜ ልክ ኃጢህአቴ የነጻውበትን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አጋራለው፤ በፈቃዳችሁ ሊንኮችን ብትነኩ ጠቃሚ ግብአቶችን ታገኙበታላችሁ! እግዚአብሔር ሁላችሁንም ይባርክ!
www.bjnewlfe.org ወይም www.nlmethiopia.com