Search

መልዕክቶች ከአጋር ሠራተኞች፤

ለሚያምን ሁሉ መልካም የትንሳኤ በዓል!

  • Teferi Oshine
  • Ethiopia
  • 05/04/2024 2070

#ለሚያምን ሁሉ መልካም የትንሳኤ በዓል!!!
ምስጋና የሰው ስጋ ለብሶ ስለኅጢአታችን ወደዚች ምድር ለመጣው በ30 ዓመቱም ዮርዳኖስ ላይ በጥምቀቱ የዓለምን ኅጢአት ለወሰደው ስለኅጢአታችንም በሞት ስለተቀጣው በሶስተኛውም ቀን ከሞት ለተነሳው ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁንና በክርስቶስ ሙሉ ጽድቅ ስለማምን እኔም በፊተኛው ትንሳኤ እነሳለው የሺውን ዓመት መንግስትና ዘላለማዊውን መንግስቱን እወርሳለው! በዚህ ታላቅ በረከት ስለባረከኝ አምላኬን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግነዋለው ሃሌሉያ!!!
በክርስቶስ ትንሳኤ ላይ ያለን እምነታችን በራሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ተቀባይነት የሚኖረው ከክርስቶ ውልደቱ እስከትንሳኤው ስናምን ነው!
በክርስቶስ ጽድቅ አንዳችም ሳትጨምሩ እንዲሁም ሳትቀንሱ ለምታምኑ እህት ወንድሞቼ ሁሉ የክርስቶስ ትንሳኤ ለእኛ ነውና መልካም የትንሳኤ በዓል እያልኩ፡ ሙሉ የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ ያልገባችሁና በስመ ሀይማኖት ውስጥ ተሸሽጋችሁ የሀይማኖቶትቻችሁን ስርዓት ለመታዘዝ የምትደክሙ ሞዕመናን ለእናንተ ኢየሱስ ሁለተኛ ትንሳኤን አዘጋጅቷል! ሁለተኛው ትንሳኤ ለኅጢአተኞች የተዘጋጀ የፍርድ ትንሳኤ ነው! ለነብሳችሁ የምታዝኑ ሁኑ የክርቶስን ሙሉ ጽድቅ በሀይማኖት አስተምሮት ሳይሆን በመጽሀፍ ቅዱስ መሰረት ለመረዳት እንዱሁም ለማመን ልባችሁን ከፍቱ! ሊንኩን በመጫን አጭር አስተማሪ ቪዲዮ ተከታተሉ በአድራሻው መሰረት አግኙን!

https://youtu.be/T-hYB5yFp3o

ሙሉ የሆነው የክርስቶስ ጽድቅ በረከት እንዲያገኛችሁ እጸልያለው ተባረኩ!