Search

ስብከቶች፤

ርዕስ 9፡ ሮሜ (በሮሜ መጽሐፍ ላይ የተሰጡ ሐተታዎች)

[Chapter 9-1] የምዕራፍ 9 መግቢያ፡፡

የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ለእስራኤሎችና ለአሕዛቦች!  

 
ጳውሎስ ለራስ ወገኖች ብዙ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቡ ውስጥ እንዳለ የተናገረው ለምንድነው? ጳውሎስ ከልቡ ለሚወዳቸው ዘመድ ወንድሞቹ ምኞት ስለነበረው ስለ እነርሱ ከክርስቶስ የተለየ የተረገመ ሊሆን ስለወደደ ነው፡፡ በሥጋው ወገኞቹ ይድኑ ዘንድ ከልቡ ፈለገ፡፡
 
በዚህ በመጨረሻው ዘመን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለመላው ዓለም በመስበክ በአያሌው እንደሰታለን፡፡ የእግዚአብሄር እጅግ ትልቁ ትኩረት ይህንን የእውነት ወንጌል ማሰራጨት ነው፡፡ ዳግም የተወለዱ ምዕመናኖች እጅግ አስፈላጊው ግብም ይኸው ነው፡፡ እስራኤሎች በመጨረሻው ዘመን የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል መቀበል ወይም አለመቀበላቸው ትኩረታችንን የሚስብ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እስራኤሎች ይድኑ ዘንድ መጸለያችንን መቀጠል አለብን፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ወንጌልን ሲቀበሉ የጌታችን ዳግም ምጽአት እንደሚቀርብ እናውቃለንና፡፡
 
የዚህ ዓመት የጸሎት ርዕሰ ጉዳዮቼ ዓለም በወንጌል እንዲዳረስና እስራኤሎችም እውነተኛውን ወንጌል እንዲቀበሉ ነው፡፡ እስራኤሎች ከራሳቸው ወገን የተነሱትን የእግዚአብሄር አገልጋዮች እንዲሸከሙዋቸውም እጸልያለሁ፡፡ በአንድ ወቅት እግዚአብሄር ሕጉን ለእስራኤሎች ሰጠ፡፡ በፊታቸውም የካህናት መንግሥት አደረጋቸው፡፡ ክርስቶስም ራሱ በሥጋ ከእስራኤሎች መጣ፡፡ እነርሱ ግን በእርሱ ለማመን አሻፈረን አሉ፡፡ አሁንም ድረስ ከፈቃዱ ማፈንገጣቸውን በመቀጠል እግዚአብሄርን ይቃወማሉ፡፡
  
 

ጌታ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ እምነትን ማግኘት እንደሚከብድ ነግሮናል፡፡ 

 
ከኢየሩሳሌም የመነጨው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመላው ዓለም እንዲሰራጭ የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ዘመን የሰዎች ልብ ደንድኖዋል፡፡ ብዙ ሰዎች እውነትን ከመሻት ርቀዋል፡፡
 
በቅርቡ ኢየሱስ በሕጋዊ መንገድ የተወለደ ልጅ አለመሆኑን የሚያሳይና ‹‹የመጨረሻው የኢየሱስ ፈተና›› የሚል ስያሜ ያለው ፊልም በኮርያ ተለቆ ነበር፡፡ በስድቦች የተሞላና ዋናው መልዕክቱም ኢየሱስ ልዑል ሲድሃርታ ማለትም ቡድሃ እንደነበረው ሁሉ ተራ ሰው ብቻ እንጂ ፈጽሞ አምላክ አይደለም የሚል ነበር፡፡ ይህ ፊልም ኢየሱስ አምላክና አዳኛችን የመሆኑን እውነት ረግጦዋል፡፡ እግዚአብሄር ‹‹የሰው ልጅ በመጣ  ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆን?›› (ሉቃስ 18፡8) ያለው ለዚህ ነው፡፡
 
እኛ የምናምንበት ኢየሱስ ክርስቶስ ከማናቸውም ፍጥረታቶች የላቀና ለዘላለም ሊመሰገን የሚገባው አምላክ ነው፡፡ ከእራኤሎች ተወልዶ በዮሐንስ በመጠመቅ፤ የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶ በመስቀል ላይ በመድማት ሞተ፡፡ በሦስተኛውም ቀን ዳግመኛ ከሙታን ተነሳ፡፡ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉም አዳኝ ሆነ፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ የሆነው ጌታ በእርሱ የሚያምኑትን በማጽደቅ ከሐጢያቶቻችን አዳነን፡፡
 
ጳውሎስ ምንም ያህል ብዙ እስራኤሎች ቢኖሩም የእግዚአብሄር ልጆች የሚሆኑት የአብርሃም ዘሮች በኢየሱስ የሚያምኑት ብቻ እንደሆኑ ተናግሮዋል፡፡
 
እስራኤሎች ወደፊት ብዙ ችግሮችና መከራዎች ይገጥሙዋቸዋል፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ ከእነርሱ አንዳንዶቹ በመጨረሻ ጌታችንን አዳኛቸው አድርገው ወደ ማመን ይመጡ ዘንድ ነው፡፡ ጌታችንን የእስራኤሎችን ጨምሮ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ቢወስድም እነርሱ ግን አሁንም ድረስ ኢየሱስን አዳኛቸው አድርገው ለማመን አሻፈረኝ ብለዋል፡፡
 
ደካሞች ናችሁን? አንዳንዶቻችን ከሌሎች ይልቅ በጣም ደካሞች ወይም በጣም ብርቱዎች ልንሆን እንችላለን? በእግዚአብሄር ፊት ግን ሁላችንም በድካም ተሞላን ነን፡፡ ከሐጢያት አርነት የወጣን የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የምንችለው ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በጫንቃው ላይ እንደተሸከመ፣ እንደተፈረደበትና በእኛ ምትክም በመስቀል ላይ በመሞት እንደተቀጣ በማመን ነው፡፡ እኛ ሕዝቦቹ ባደረገንና ከሐጢያት አርነት ባወጣን የእግዚአብሄር ሐይል ማመንና ማመስገን አለብን፡፡ ጌታችን በእርግጥም ታላቅ ነው፡፡
 
አንዳንድ ሰዎች ሁሉ ነገር የሚኖረው በሰዎች ምክንያት ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ለምሳሌ ሕጎች የሚተገበሩት በሰዎችና ለሰዎች ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር ከሰዎች የመነጨ እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን፡፡ ነገሮች የሆኑት በእግዚአብሄር ፈቃድ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ዓለምና መላውን ዩኒቨርስ የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ እኛን የሚያስተዳድሩን ሰው ሰራሽ ሕጎች እንኳን በመሰረታዊነት የተደነገጉት በእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡
 
እግዚአብሄር በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ ስለሚሰራና እያንዳንዱም ነገር እንደ ፈቃዱ ስለሚገለጥ በሁሉም ነገሮች ውስጥ ጽድቁን ፈልገን ማግኘት ይገባናል፡፡ ደካሞች በነበርን ጊዜ፣ በእግዚአብሄር ላይ ሐጢያት በሰራን ጊዜና በሐጢያታችን ምክንያት ከእርሱ ጋር በተለያየን ጊዜ እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስን ለመላክ ቃል ገባ፡፡ ኢየሱስን ሥጋ ለብሶ እንዲመጣና ከዓለም ሐጢያቶች እኛን ያዳነበትን ጥምቀት እንዲጠመቅ በማድረግ ተስፋውን ፈጸመ፡፡
 
የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል በእያንዳንዱ የዓለም ማዕዘን ሲሰራጭ የእግዚአብሄር መሰረታዊ ዕቅድ ይፈጸማል፡፡ በዓለም ላይ ያሉ ሁነቶች ሲገለጡ ስንመለከት አሜሪካና እስራኤል ማዕከል ሆነው ማየት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር ጣልቃ ካልገባ ሌላ የዓለም ጦርነት መቀስቀሱ እንደማይቀር አምናለሁ፡፡
 
የዓለም ንግድ ማዕከሎች ሲወድሙ አስገራሚ ተጽዕኖዋቸው በመላው ዓለም ታውቋል፡፡ በዚህ ጊዜና ዘመን ዓለም እንደገና ጦርነት ውስጥ ቢገባ ምን እንሆናለን? በእርግጥም ከሌላ የዓለም ጦርነት ማገገም አንችልም፡፡ ተፈጥሮ እንኳን እኛ ካደረስንባት ፍጹም የጥፋት ጉዳቶች ማገገም አትችልም፡፡ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል በሰላም ለመላው ዓለም መስበክ እንችል ዘንድ እንደምትጸልዩ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የእኛ ጭንቀት በዓለም ላይ ሰላም ከሌለ ይህንን ማድረግ የማንችል መሆናችን ነው፡፡ ሁላችንም ስለ ሰላም መጸለይና ጦርነትንና ሽብርተኝነትን ለማጥፋት መትጋት ይኖርብናል፡፡
 
የሰዎችን ሐጢያቶች የትኛውም ሰው ሰራሽ ሃይማኖት ሊያስወግደው አይችልም፡፡ ከሐጢያቶቻችን ሊያድነን የሚችለው ክርስቶስና እርሱ ብቻ ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን ሊደመሰሱና ሊኮነኑ የሚችሉት ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ብቻ ነው፡፡ ይህ በረከት በእግዚአብሄር ጽድቅ ለሚያምኑ ሰዎች ተሰጥቷል፡፡ ከሐጢያቶቻችን መዳን የምንችልበት ብቸኛው መንገድ በክርስቶስ ጥምቀትና በደሙ በማመን ነው፡፡ ሌላ መንገድ የለም፡፡ ብዙ የሃይማኖት ሰዎች ለማድረግ በሚመርጡት ልማዳዊ የንስሐ ጸሎት ይቅርታን አናገኝም፡፡ ለሐጢያቶቻችን ስርየት የምናገኝበት ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ሥጋ ለብሶ በመምጣት በጥምቀቱ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወስዶ በመስቀል ላይ በመሞት ሙሉ በሙሉ ከሐጢያቶቻችን ባዳነን በእግዚአብሄር ጽድቅ በማመን ነው፡፡
      
 
በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እውነት በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ 
 
ይህ እውነት በእያንዳንዱ የዓለም ማዕዘን መሰበክ አለበት፡፡ በዚህ እውነት አለማመን የእስራኤሎችና የአሕዛቦች ሐጢያት መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡ እያንዳንዱ ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን አለበት፡፡
ሁለቱም ብሄሮች እስራኤሎችና አሕዛቦች በዚህ ዓለም ላይ ሲኖሩ በሐጢያት ከመቀጠል መቆጠብ አልቻሉም፡፡ ጌታችን ግን በጥምቀቱ እነዚህን ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ዕልባት አበጅቶላቸዋል፡፡ ከኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ከሆነው ደሙ የበለጠ በጣም ግልጽና በጣም ቀላል እውነት ሊኖር ይችላልን? ዮሐንስ ኢየሱስን ለምን አጠመቀው? እርሱ በዮሐንስ የተጠመቀውና የተሰቀለው በአንድ ጊዜ ሐጢያቶቻችንን መውሰድ ይችል ዘንድ ነበር፡፡ ሰዎች ይህንን እውነት ባለማመን ወይም በልባቸው ባለመቀበል በሐጢያቶቻቸው ምክንያት ራሳቸውን ወደ ማጥፋት እየነጎዱ ነው፡፡
 
ኢየሱስ ‹‹እንዲህ›› (ማቴዎስ 3፡15) የተቀበለው ጥምቀት ጽድቅን ሁሉ ፈጽሞዋል፡፡ ‹‹እንዲህ›› ለሚለው ቃል ግሪኩ ‹‹ሁቶስ- ጋር›› ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹በዚህ መንገድ›› ‹‹በጣም ተስማሚ›› ወይም ‹‹ከዚህ ውጪ ሌላ መንገድ የለም›› ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል ኢየሱስ ከዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት አማካይነት የሰውን ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ለዘላለም እንደወሰደ ያሳያል፡፡ ኢየሱስ በዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ ስለወሰደ መስቀሉን መሸከምና በእኛ ፋንታም በመስቀል ላይ መድማት ቻለ፡፡ ይህ መላው የሰው ዘር ከሐጢያቶቹ የሚድንበት የስርየት እውነት መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡
 
ጌታችን እንዲህ ነግሮናል፡- ‹‹እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፡፡ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡፡›› የኢየሱስ ጥምቀትና ደሙ ከሐጢያቶቻችን ያዳኑን የእግዚአብሄር እውነት ናቸው፡፡ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ የስርየት እውነት ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ጋር አብሮ እስከ ዘላለም ድረስ መዝለቅ አለበት፡፡ እግዚአብሄር አብ ሐጢያተኞች በኢየሱስ ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ስርየትን ያገኙ ዘንድ መወሰኑ ፈቃዱ ነው፡፡ ለደህንነታችን በእርሱ ጥምቀትና ደም ስናምን እግዚአብሄር ለእኛ በወሰነው መሰረት ማመናችን ነው፡፡ ሐጢያቶቻችን ስርየትን የሚያገኙት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን ብቻ ነው፡፡
 
በዚህች ቅጽበት ለደህነታችሁ በመስቀሉ ላይ ደም ብታምኑ ትጸድቃላችሁ፡፡ በሌላ አነጋገር ካላመናችሁ አሁንም ሐጢያተኞች ናችሁ ማለት ነው ‹‹ሁሉ ሐጢአትን ሰርተዋልና፤ የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡›› ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ይቅርታን አግኝትን የእግዚአብሄር ልጆች መሆን የምንቸችለው ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኛችን አድርገን በማመን ብቻ ነው፡፡ ሰው በዚህ የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የማያምንበት ምክንያት ሊኖረው አይገባም፡፡ ይህ የደህንነት ወንጌል የማያስፈልገው ሰው የለም፡፡ ሁሉም ያስፈልገዋል፡፡ ከሐጢያቶቹ ለመንጻት ፈቃደኛ ካልሆነ በስተቀር የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል እውነት በፊቱ በግልጽ ተቀምጦለት ሳለ ማመን የማይፈልገው ለምንድነው?
 
ብዙዎች በመላው ዓለም የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ተቀብለው ርቀው በመሄድ በስብከት እያሰራጩት ነው፡፡ ከእነርሱ አንዳንዶቹ በፈቃዳቸው መጽሐፎቻችንን ለማሰራጨት ጠይቀዋል፡፡ በመስቀሉ ደም ብቻ በማመን ከሐጢያቶቻችሁ ድናችሁ ከሆነ በየቀኑ የንስሐ ጸሎቶችን ቢደጋግምም በሐጢያት መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ጸሎቶች ማብቂያ የሌላቸው ልማዶችና የሃይማኖት ሥርዓት ልምምዶችና ናቸውና፡፡
 
የንስሐ ጸሎቶችን በማቅረብ ሐጢያቶቻችሁን ለማንጻት የምትሞክሩ ከሆናችሁ እግዚአብሄርን በመቃወም የከፋ ሐጢያት እየሰራችሁ ነው፡፡ ምክንያቱም ድርጊታችሁ በራሳችን ጥረት ሳይሆን ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በመውሰድ በእኛ ፋንታ በተቀጣበት ጥምቀቱና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ብቻ ሊፈጸም የሚችለውን የእግዚአብሄር ጽድቅ ያዋርዳልና፡፡
 
ኢየሱስን አዳኛችሁ አድርጋችሁ ከተቀበላችሁ ስርየታችሁ ከኢየሱስ ጥምቀትና ከስቅለቱ እንደሚመጣ እመኑ፡፡ ኢየሱስ ሐጢያተኞችን ከሐጢያቶቻቸው ለማዳን ቃል ገብቷል፡፡ የእግዚአብሄርን ጽድቅ ለመፈጸም በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ በመጠመቅና በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ተስፋውን ፈጽሞዋል፡፡ በዚህ እውነት ላለማመን የምናቀርበው ምን ምክንያት አለ? ለደህንነታችሁ በኢየሱስ ጥምቀትና ባፈሰሰው ደሙ ማመን አለባችሁ፡፡
 
ኢየሱስ በተጠመቀ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ የመውሰዱ እውነት በማቴዎስ 3፡13-17 ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ እውነት ለማመን አሻፈረኝ የሚሉ ለሐጢያቶቻቸው በሙሉ ይቅርታን ማግኘት የማይፈልጉ ብቻ ናቸው፡፡ እናንተ የእግዚአብሄር ልጅ መሆንና የዘላለምን ሕይወት መቀበል የምትችሉት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ብቻ ነው፡፡ ሌላ ምንም ነገር ከሐጢያቶቻችሁ ሊያድናችሁ አይችልም፡፡ በዚህ እውነት ከማመን የበለጠ ምንም ግሩም ነገር የለም፡፡ ከይቅርታው የበለጠ ሌላ የተሻለ የእግዚአብሄር ስጦታ የለም፡፡ እግዚአብሄር ከሰጠን ብዙ ስጦታዎች መካከል ከሁለም የተመረጠው ስጦታ የሐጢያቶችን ስርየት ነው፡፡
 
እግዚአብሄር የሰጠን ሁለተኛው ምርጥ ስጦታ የምንነግስበት መጪው ሺህ ዓመት ሲሆን ሦስተኛው ስጦታ ደግሞ ከዚያ በኋላ ከእግዚአብሄር ጋር በመንግሥተ ሰማይ የምንኖርበትና የምንነግስበት ነው፡፡ እግዚአብሄር በዚህ በመጨረሻው ዘመን እንኳን ይህ የደህንነት እውነት ለእስራኤሎችና ለአሕዛቦች እንዲገለጥ ፈቅዶዋል፡፡
 
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተተነበየው ከእስራኤሎች መካከል ሁለት የእግዚአብሄር አገልጋዮች ይነሳሉ፡፡ እግዚአብሄርም በእነርሱ በኩል አስገራሚ የወንጌል ተዓምራቶችን ያደርጋል፡፡ ያን ጊዜ እስራኤሎች እግዚአብሄር ከራሳቸው ወገን በሚያስነሳላቸው ሁለት አገልጋዮች አማካይነት የውሃውንና የመንፈሱን ውጌል ይሰሙና ብዙዎች ኢየሱስን መሲሃቸው አድርገው ወደ ማመን ይመጣሉ፡፡ ዮሐንስ ‹‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና!›› (ዮሐንስ ራዕይ 22፡20) ብሎ በመለመን እንደጠበቀ እኛም ያንን ቀን እንጠብቃለን፡፡
 
ጌታ ዳግም የሚመጣበት ጊዜ ሲቀርብ ይቅርታ ባገኛችሁበትና በዳናችሁበት በዚህ እውነት በማመናችሁ ምን ያህል ዕድለኞች እንደሆናችሁ ትገነዘባላችሁ፡፡ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እውነት በማመን ከሐጢያቶቻችሁ ሁሉ ትድኑ ዘንድ የልቤ ቅን ፍላጎት ነው፡፡ ዓለም ይለወጥ ይሆናል፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከሐጢያቶቻችን ያዳነበት የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ግን ፈጽሞ የማይለወጥ ዘላለማዊ እውነት ነው፡፡ የማይለወጠውን የሥርየት ደህንነት ለማግኘት በዚህ እውነት ማመን አለብን፡፡ የእግዚአብሄር የደህንነት እውነት የእናንተ ይሁን፡፡
              
 
እግዚአብሄር የምህረት ዕቃዎች አድርጎ አዳነን፡፡ 
 
ሮሜ ምዕራፍ 9 እግዚአብሄር ያዕቆብን ከኤሳው የበለጠ ስለወደደው እንዳዳነው መዝግቦዋል፡፡ ስለዚህ ያዕቆብ የምህረት ዕቃ ሲሆን ኤሳው የቁጣ ዕቃ ሆነ፡፡ ይህ ለምን የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ማለትም እግዚአብሄር ከኤሳው ይልቅ ለያዕቆብ ያደላልን? ‹‹እግዚአብሄር ሌላውን ያለ ቅድመ ሁኔታ ጠልቶ አንዱን በራሱና ሆነ ብሎ በአድልዎ ሊወድደው ስለመረጠ ቅድሚያ ውሳኔውና ምርጫው የተሳሳተ ነው›› ብለው የሚከራከሩ ብዙ ሰዎች እንደሚኖሩ አያጠራጥርም፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረውን ዓለም ስንመለከት ፍጥረታቶቹ ምን ያህል ንጹህና ውብ እንደሆኑ ማየት እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር የፈጠራቸው ተክሎች፣ እንሰሶችና ሌሎች ነገሮች ሁሉ እጅ ፍጹማን ይመስላሉ፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር አንዱን ወድዶ ሌላውን መጥላቱ እንዴት አድልዎ ሊሆን ይችላል? ነገሩ እንዲህ አይደለም፡፡
 
በአዳምና በሄዋን አለመታዘዝ ሐጢያት ወደ ዓለም ገባ፡፡ በዚህ ሐጢያት ምክንያት ከእነርሱ በኋላ የመጡት ሁሉ በሐጢያት እንዲቀጥሉ ተወሰነባቸው፡፡ ለሲዖል ከመኮነንም ማምለጥ አልቻሉም፡፡ እግዚአብሄር ያዕቆብን ከሐጢያት ማዳኑና ኤሳውን አለማዳኑ እርሱ ስህተት መስራቱን የሚያሳብቅ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በዓይኖቹ ፊት እንዲህ ለማድረጉ ምከንያት አለው፡፡
 
በክርስትናው ማህበረሰብ ውስጥ እንደ ኤሳው የሚንቀሳቀስ ብዙዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡ እንዲህ ያለ ሰው መቼም ወይም የትም ቦታ ቢደረግ ከማለዳ እስከ ምሽት ድረስ የሚደረግ የአምልኮ ፕሮግራም አያመልጠውም፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም በቤታቸው ከሚያሳልፉት ጊዜ ይበልጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሳልፋሉ፡፡ ከሥራ ሲወጡ ወደ ቤታቸው ሳይሆን ወደ ቤተክርስቲያን ይሮጣሉ፡፡ እኛ እነዚህን ሰዎች ‹‹የሃይማኖት ሯጮች›› ብለን ልንጠራቸው እንችላለን፡፡ ሆኖም ከእነርሱ መካከል የእግዚአብሄርን ጽድቅ ከምራቸው ያልያዙ ብዙዎች አሉ፡፡ ምክንያቱም የራሳቸውን ጽድቅ ለመገንባት እየሞከሩ ነውና፡፡ እንዲህ በማድረጋቸውም የእግዚአብሄርን ጽድቅ ችላ እያሉ ነው፡፡
 
የእግዚአብሄርን ጽድቅ ችላ ያሉ ሰዎችም ቢሆኑ አሁንም ድረስ ሰማይ መሄድና ሐጢያቶቻቸው ይቅር እንዲባሉ ይፈልጋሉ፡፡ ጥረቶቻቸው ግን ከሐጢያቶቻቸው ለመዳን መሞከር ነው፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ ጽድቅ ለሚያምኑ ሰዎች በእግዚአብሄር ጽድቅ የማመኑ እምነት ለሁሉም ሰው እንዳልተሰጠ ተናግሮዋል፡፡
 
ታዲያ በእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያምኑ ምን አይነት ሰዎች ናቸው? እነዚህ የራሳቸውን ሐጢያተኝነት የሚያምኑና በአእምሮዋቸውም ከንቱዎች መሆናቸውን የሚገነዘቡ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በተገለጠው ስርየቱ አማካይነት የተገለጠውን የእግዚአብሄር ጽድቅ ሲያውቁ ወዲያው የሚያምኑና ክብሩን ለእግዚአብሄር የሚሰጡ ሰዎች ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር ጽድቅ አምነን ድነናል ማለት የእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያስፈልገን ምስኪን ሰዎች ነን ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ በቀሪው ሕይወታችን በሐጢያት ለመኖር የተኮነንን እንሆናለን፡፡
 
ነገር ግን በእግዚአብሄር ፊት የራሳቸውን ጽድቅ የሚሹ ሰዎች ትምክህተኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ‹‹ጌታ ሆይ አስራት ሰጥቻለሁ፡፡ ሌሊቱን ሁሉ ወደ አንተ ስጸልይ ቆይቻለሁ፡፡ በየቀኑ የሚደረጉት የማለዳ አገልግሎቶች ላለፉት አስር ዓመታቶች ፈጽሞ አላመለጡኝም፡፡ ለአንተም ጥሩ ምግባሮች አድርጌያለሁ›› ይሉ ይሆናል፡፡
 
ሆኖም እግዚአብሄር ይበልጥ የሚደሰተው ፈጽሞ ጽድቅ እንደሌላቸው ቢያውቁ ነው፡፡ ያን ጊዜ በራሳቸው ጥረት የሌላቸውንና ሊኖራቸው የማይችለውን ነገር ለማረጋገጥ በመሞከር ፋንታ በውሃውና በመንፈሱ ስርየት አማካይነት በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን ያስፈልጋቸዋል፡፡
 
በአሁኑ ጊዜ በክርስትናው ማህበረሰብ ውስጥ የራሳቸውን ጽድቅ ለማሳየት በመሞከር ሁሉንም አይነት ነገሮች የሚያደርጉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም ቃሎቻቸውን በታማኝነት ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በኩል በተገለጠው የእግዚአብሄር ጽድቅ ስለማያምኑ ሐጢያቶቻቸው ፈጽሞ አልነጹም፡፡ እግዚአብሄር ፍጻሜያቸውን ይወስናል፡፡ ሁላችንም የጌታችን ጥምቀትና ደም የስርየት እውነት መሆኑን በማመን ባላቸው እምነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት አግኝተው የእግዚአብሄር ልጆች እንዲሆኑ እንመኛለን፡፡
    
ሐዋርያው ጳውሎስ የደህንነት ዕቃዎችን በሚመለከት እግዚአብሄር የሚምረውን እንደሚምርና ለሚራራለትም እንደሚራራ ተናግሮዋል፡፡ ታዲያ እግዚአብሄር የሚምራቸው ሰዎች እነማን ናቸው? ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሄር ቃል ለመኖር ከልባቸው ቢጥሩም መኖር አይችሉም፡፡ ቃሉን ለማመንና በቃሉ ለመኖር እውነተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም በተደጋጋሚ ይሰናከላሉ፡፡ በእግዚአብሄርም ፊት ያዝናሉ፡፡ ጸጸት ይሰማቸዋል፡፡ ለሲዖል ኩነኔ የታጩ እንደሆኑም ያስባሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ምድራዊ ዓለምና በእግዚአብሄር መንግሥት ምስኪኖች እንደሆኑ በመረዳት እግዚአብሄር እንዲምራቸው ይለምናሉ፡፡ እግዚአብሄር ካልማራቸው መዳን እንደማይችሉ ስለሚያውቁ የእርሱን ምህረት አብዝተው ይለምናሉ፡፡
 
በሌላ አነጋገር ከሐጢያት መዳን እግዚአብሄር ለሚያዝንላቸውና ለሚምራቸው ነው፡፡ እግዚአብሄር አንድያ ልጁ በጥምቀቱ ሐጢያቶቻቸውን በሙሉ በራሱ ላይ በመውሰድ፣ በመስቀል ላይ በመሞትና ከሙታን በመነሳት የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ለእነዚህ ሰዎች ሰጥቶዋቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ ያደረገው እነርሱን ከተጋረጠባቸው ጥፋት ለማዳን ነው፡፡ አባታችን ለምስኪኖች ይራራል፡፡
 
ነገር ግን እግዚአብሄር በዚህ ዓለም ላይ ከሚምራቸው ሰዎች ይልቅ የሚቆጣቸው ብዙ ሰዎች ያሉ ይመስላል፡፡ እግዚአብሄር በዛሬው የክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ የምህረት ዕቃዎችና የቁጣ ዕቃዎች እንዳሉት ነግሮናል፡፡ በሌላ አነጋገር በእግዚአብሄር የተወደዱ ሰዎችና በእርሱ ያልተወደዱ ሰዎች አሉ፡፡
 
ሮሜ 9፡17 እንዲህ ይነግረናል፡- ‹‹መጽሐፍ ፈርዖንን ሐይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሳሁህ ይላልና፡፡›› እግዚአብሄር እንደ ፈርዖን ያሉ ሰዎች እንዲነሱ የፈቀደው ሐይሉ ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ ነገር ግን ስሙ በመላው ዓለም ይታወቅ ዘንድ ለምህረት ዕቃዎች ፍቅሩን አሳይቷል፡፡ በሐጢያቶቻችንና በእግዚአብሄር ቁጣ ምክንያት ሁላችንም ለሲዖል ታጭተናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የጽድቅ ፍቅሩን ስለሰጠን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ ምክንያቱም በእርሱ ለምናምነው ለእኛ ምህረትን አድርጎልናልና፡፡
በእግዚአብሄር ጽድቅ የማያምኑና የራሳቸውን ጽድቅ በመከተል የሚደሰቱ ሰዎች እግዚአብሄርን እየተቃወሙ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለቁጣው ያስቀራቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፡፡ የእርሱ ብርቱ ቁጣ ይገለጥ ዘንድ እርሱን የሚቃወሙ ሰዎች ሊኖሩ ይገባል፡፡ በዚህም የእግዚአብሄር ቅን ፍርድ ይታያል፡፡
 
እንደ ፈርዖን ያሉ ሰዎች የእግዚአብሄርን ጽድቅ ይንቃሉ፡፡ በፈርዖን ላይ አስር መቅሰፍቶችን አወረደ፡፡ የመጨረሻው ሞት ነበር፡፡ እግዚአብሄርን የናቁ ሰዎች የሚጠብቃቸው ብቸኛው ነገር ፍጻሜ የሌለው የእሳት ባህር ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቁጣ ሐይል ይህ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ሐያል ሰዎችና እግዚአብሄርን የሚክዱ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ውሎ አድሮ የቁጣውን ሐይል ለማወጅ ያዋርዳቸዋል፡፡ እርሱን ለመካድ ደንዳና ልብ ያላቸውን የሚተዋቸው ለዚህ ነው፡፡
 
ስለዚህ ለእኛ አስፈላጊው ነገር የምህረት ዕቃዎች መሆን የምንችለው እንዴት ነው የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ በመሆን በእግዚአብሄር ጽድቅ ማመን እንችላለን፡፡ በእግዚአብሄር ፊት የምንመጻደቅበት ምንም ነገር የለም፡፡ የተወለድነው በእርሱ የጽድቅ ፍቅር እንድናምን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቀራጭና ፈሪሳዊ በእግዚአብሄር ፊት የመጸለያቸውን ታሪክ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሄር የፊተኛውን ሲምር የኋለኛውን ግን ተወው፡፡ እንደ ቀራጩ ዓይነት ያሉ ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ምንም ሰናይ ነገር አለማድረጋቸውንና ከክብሩ መጉደላቸውን ብቻ የሚያውቁ ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ምህረቱን እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡
 
እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር የሚለብሱ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደ ፈሪሳዊ ያሉ ሰዎች ግን ብዙውን ጊዜ ለእግዚአብሄር ባደረጉት ነገር አስራትን በመሰጠታቸው በሳምንት ሁልጊዜ መጾማቸውን በመጸለይና ለሃይማኖታቸው ታማኝ በመሆናቸው ይመጻደቃሉ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ከቆምንበት ስፍራ አንጻር ወይ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር እንለብሳለን፤ አለበለዚያም ለቁጣው ቅጣት እንጋለጣለን፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ልባችንን የምናደነድን ከሆነ ሐጢያቶቻችን ለዘላለም ይቅርታን አያገኙም፡፡ ያለ ይቅርታ የወደፊት ዕጣችን ሲዖል ይሆናል፡፡
 
የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል በመላው ዓለም ተሰብኮዋል፡፡ ያልዳኑት ልባቸው ደንዳና ስለሆነ አይድኑም፡፡ በሰዎች ውስጥ ምንም ጽድቅ የለም፡፡ የእግዚአብሄርን የጽድቅ ፍቅር መልበስ የምንችለው በእምነት ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር ቢፈጥራቸውም የእርሱን ጽድቅ ለማወቅ አሻፈረኝ የሚሉትን ይጠላቸዋል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሄር ጽድቅ በሆነው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ ሰዎች ሁላቸውም በእግዚአብሄር የተወደዱ ስለሆኑ የዘላለምን ሕይወት ያገኛሉ፡፡
 
ዛሬ በዚህ ዓለም ላይ የሚኖሩ ብዙ ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር ፊት የቁጣ ዕቃዎች ሆነው እየኖሩ ነው፡፡ ከሮሜ መጽሐፍ የእግዚአብሄር ጽድቅ ምን እንደሆነ መማር የሚያስፈልገን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሄር አንዳንዶችን የወደደው ሌሎቹን ግን የጠላው አንዳንዶቹ በእርሱ ጽድቅ ስለሚያምኑ ሌሎች ግን ስለማያምኑ ነው፡፡ እኔ ልናገረው የምፈልገው እውነት ይህ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለያዕቆብና ለኤሳው ያደረገው ትክክል ነው፡፡ በኢየሱስ በሚያምኑት መካከል በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሳያምኑ በእግዚአብሄር ለመወደድ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ኤሳውን ይመስላሉ፡፡ እግዚአብሄርም በሐጢያቶቻቸው መሰረት ይፈርድባቸዋል፡፡
 
እግዚአብሄር በዓለም ላይ ያሉትን ሐጢያቶች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ይወስድ ዘንድ በዮሐንስ እንዲጠመቅ ልጁን ላከው፡፡ በዚህ እውነት ታምናላችሁን? ከልባችሁስ ታምኑበታላችሁን? የእግዚአብሄር ጽድቅ በተገለጠበት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ስናምን ከሐጢያቶቻችን አርነት እንወጣ ዘንድ የዚህን ዓለም ሐጢያቶች በሙሉ ወስዶ በጫንቃው ላይ በመሸከም በመስቀል ላይ ሞተ፤ ከሙታንም ተነሳ፡፡
 
ነገር ግን በእግዚአብሄር ጽድቅ ሳናምን ይቅርታን ለማግኘት ሞክረን ቢሆን ኖሮ በእርሱ ላይ ሐጢያት መስራታችንን እንቀጥል ነበር፡፡ በእርሱ ጽድቅ ባናምን ኖሮ ኢየሱስ ክርስቶስ በየቀኑ ለሐጢያቶቻችን ይጠመቅና ይሞት ነበር፡፡ እግዚአብሄር ወሰን በሌለው ፍቅሩ እንዲህ ያለውን መንገድ ይመርጥ ነበርን? እግዚአብሄር እኛን ከሐጢያቶቻችን ለማዳን ልጁን በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዲያድነን ለሐጢያቶቻችን ሁሉ አንድ ጊዜ እንዲጠመቅ፣ እንዲሰቀልና ከሙታን እንዲነሳ ላከው፡፡
አምላካችን ጻድቅ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር በጽድቁ ውስጥ የሐጢያቶቻችንን ስርየት አቀደ፡፡ እግዚአብሄር ሐጢያት በሰራን ቁጥር ይቅርታውን እንዲሰጠን ስለምንጸልይ ሐጢያቶቻችንን አይደመስስም፡፡ በፋንታው በእርሱ ጽድቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ያመኑትን ሰዎች ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ ደምስሶዋል፡፡   
 
ከዚያ በኋላ በየቀኑ የምንሰራቸው ሐጢያቶች ምን ይሆናሉ? እነዚህም እግዚአብሄርን ስለ ጽድቁ በምስጋና ስናመልከውና ክብሩን ሁሉ ለእርሱ ብቻ ስንሰጥ መንገድ ይበጅላቸዋል፡፡ ከእግዚአብሄር እይታ አንጻር ኢየሱስ በአንድ ጊዜ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ ወስዶ በመስቀል ላይ ደምቷል፡፡ በእኛ ፋንታም ተኮንኖዋል፡፡ ሙሉ በሙሉ እንድንድንም ሐጢያቶቻችንን በሙሉ በዚህ መንገድ በአንድ ጊዜ ወስዶዋል፡፡ የእግዚአብሄር ጽድቅ ፍቅር የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ ለማስወገድ በዕቅዱ መሰረት ተጠናቋል፡፡
 
ሮሜ 9፡25 እንዲህ ይላል፡- ‹‹እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፡፡›› አዎ እግዚአብሄር ሕዝቡ ያልነበሩትን ሕዝቤ ብሎ እንደሚጠራቸው ተናግሮዋል፡፡ የምናምንበት የእግዚአብሄር ጽድቅ ተጨባጭ እውነት እንጂ ንድፈ አሳብ ስላልሆነ በእርሱ ጽድቅ በማመን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ድነናል፡፡ ይህ ተጨባጭ እውነት ስለሆነ የእርሱን ጽድቅ ችላ የሚሉ ሰዎች ልክ እንደ ኤሳው ይጠላሉ፤ ይኮነናሉ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት በራሱ ጽድቅ የሚመካ ሰው የለም፡፡
 
እግዚአብሄር እኛን ከሐጢያቶቻችን ሁሉ ነጻ ለማውጣት በጽድቁ አዳነን፡፡ ታዲያ እርሱን እንዴት ላናመሰግነውና ላናወድሰው እንችላለን? የእግዚአብሄርን ጽድቅ ወንጌል ከማሰራጨት ልንቆጠብ አንችልም፡፡