Search

የመገናኛው ድንኳን ጥናት፤

  • የመገናኛው ድንኳን፤
  • የመገናኛው ድንኳን የእስራኤላውያንንና በእርሱ የሚያምነውን የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች ይቅር ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ ነበር፡፡ የመገናኛው ድንኳን ብቸኛው ባለቤት ጌታችን ነው፡፡ እርሱ የእያንዳንዱን ሰው ሐጢያቶች በሙሉ በአንድ ጊዜ የደመሰሰና በተመሳሳይ ጊዜም ለሰው ዘር ሁሉ ራሱ የመስዋዕት ቁርባን ነበር፡፡
  • የእስራኤል ሕዝብ በየቀኑ ሐጢያት የሠሩ ቢሆኑም በመስዋዕቱ ስርዓት መሠረት በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ባለው ነውር የሌለበት የመስዋዕት እንስሳ ራስ ላይ እጆቻቸውን በመጫን ሐጢያቶቻቸውን በቁርባኑ ላይ ማሻገር ቻሉ፡፡ የሐጢያቶችን ስርየትና የሐጢያቶቻቸውን መንጻትና እንደ በረዶ ነጭ ሆነው መለወጥ የቻሉት በካህናቶቹ አገልግሎትና በመስዋዕት ቁርባኑ በማመናቸው ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ የእስራኤል ሕዝብና አህዛቦች የሆንን እኛ የመገናኛው ድንኳን እውነተኛ አካል በሆነው የኢየሱስ ጥምቀትና መስዋዕት በማመን ሁላችንም የሐጢያቶቻችን ሁሉ ስርየትና ከጌታ ጋር ለዘላለም የመኖርን በረከት ለብሰናል፡፡
  • እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ አህዛቦችም በሙሉ ደግሞ የመገናኛው ድንኳን ጌታ በሆነው በኢየሱስ በማመን ብቻ ከሐጢያቶቻቸው በሙሉ ነጻ መውጣት ይችላሉ፡፡ የመገናኛው ድንኳን እግዚአብሄር ለእያንዳንዱ ሰው የሰጠው የሐጢያት ስርየት ስጦታ ምን እንደሆነ ያስተምረናል፡፡ ስለዚህ የመገናኛው ድንኳን ራሱ የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጫ አካል ነበር፡፡
  • ኢየሱስ የሐጢያተኞች አዳኝ ሆነ፡፡ እርሱ/እርስዋ ማንም ይሁኑ እያንዳንዱ ሐጢያተኛ በኢየሱስ ጥምቀት፣ በመስቀል ላይ ደሙና እርሱ ራሱ አምላክ በመሆኑ እውነት በማመን ብቻ ሐጢያት አልባ መሆን ይችላል፡፡ በሰማያዊው፣ በሐምራዊውና በቀዩ ማግ ላይ ባለን እምነት ማለትም በኢየሱስ ጥምቀት፣ በደሙና በመለኮትነቱ በማመን ከእግዚአብሄር ፍርድ መዳን እንችላለን፡፡ የመንግሥተ ሰማይ መግቢያ በር ኢየሱስ ነው፡፡
  • የሐዋርያት ሥራ 4፡12 እንዲህ ይላል፡- ‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች የለምና፡፡›› ሰዎችን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸው ማዳን የሚችለው ኢየሱስ እንጂ ሌላ ማንም ሰው አይደለም፡፡ ከኢየሱስ በቀር አዳኝ የለም፡፡ ዮሐንስ 10፡9 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፤ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል፡፡›› 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5 እንዲህ ይላል፡- ‹‹አንድ እግዚአብሄር አለና፤ በእግዚአብሄርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡›› ማቴዎስ 3፡15ም እንዲህ ይላል፡- ‹‹ኢየሱስም መልሶ፡- አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው፡፡›› እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች ይህንን እውነት ይመሰክራሉ
  • ኢየሱስ በሰው ስጋ ወደዚህ ምድር መጣ፡፤ ጥምቀቱን በመቀበልና (ሰማያዊ ማግ) ደሙን በማፍሰስ (ቀይ ማግ) ሐጢያተኞችን አድኖዋል፡፡ ስለዚህ ለሐጢያተኞች ሁሉ የደህንነት በር ሆንዋል፡፡ የመገናኛው ድንኳን አደባባይ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ እንደተሸመነ ሁሉ ኢየሱስም ወደዚህ ምድር በመምጣት በመጀመሪያ ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀት የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ስለዚህ እርሱ የመስዋዕት ቁርባን፤ የእግዚአብሄር በግ ሆነ፡፡ (ዮሐንስ 1፡29)
  • ሁለተኛ እንዲህ የሐጢያተኞችን በደሎች በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ ከወሰደ በኋላ በእነርሱ ምትክ ሞተና ለሚያምኑት ሰዎች አዲስ ሕይወትን ሰጣቸው፡፡ ሦስተኛ ይህ ኢየሱስ ራሱም አምላክ ነበር፡፡ ዘፍጥረት 1፡1 እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመጀመሪያ እገዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡›› ዘፈጥረት 1፡3 እንዲህ ይላል፡- እግዚአብሄርም፡- ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ፡፡›› ኢየሱስ ሌላ ማንም ሳይሆን ይህ የሎጎስ አምላክ መላውን ዩኒቨርስና በውስጡ ያለውን እያንዳንዱን ነገር በቃሉ የፈጠረ አምላክ ነበር፡፡
  • እግዚአብሄር ሙሴን የመገናኛውን ድንኳን አደባባይ በር ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩ በፍታ እንዲሠራ ነገረው፡፡ ራሱ አምላክ የሆነው ኢየሱስ በሰው ስጋ ወደዚህ ምድር በመምጣት ሐጢያተኞችን ጻድቃን የማድረጉን ሥራ አጠናቀቀ፡፡ በጥምቀቱና በመስቀል ላይ ሞቱም የራሱን ሕዝብ ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ አዳነ፡፡ እነዚህ ሦስቱ አገልግሎቶች ክርስቶስ ሐጢያተኞችን ያዳነበት መንገድ ናቸው፡፡ የዚህ እውነት ማስረጃም ናቸው፡፡
  • ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን 4፡4-6 ላይ እንዲህ አለ፡- ‹‹በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት፣ ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ፡፡›› ይህ ቃል የሚያመለክተው በሰማያዊው፣ በሐምራዊው፣ በቀዩ ማግና በነጩ በፍታ የተበጀውን የሐጢያት ደህንነት ነው፡፡
  • የመገናኛውን ድንኳን ስንመረምር ትክክለኛውን እውነት መገንዘብ አለብን፡፡ በዚህም የሐጢያቶቻችንን ሁሉ ይቅርታ በማግኘትም መባረክ አለብን፡፡