በብሉይ ኪዳን፦ ልክ እንደ ሌሎቹ መሥዋዕቶች ሁሉ የማስተስረያ መሥዋዕት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይቀርብ ነበር። ሊቀ ካህኑ ራሱን አንጽቶ ሥርዓቶችን ለማከናወን በሚለብሳቸው የተለመዱ መደበኛ ልብሶች ፋንታ ቅዱስ የሆኑትን የበፍታ መጎናጸፊያዎች ይለብሳል፤ ለእርሱና ለቤተሰቡም የኃጢአት ቁርባን ይሆን ዘንድ ወይፈን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆን ዘንድም አውራ በግ ይመርጣል (ዘሌዋውያን 16፡3-4)።
ሊቀ ካህኑ ኃጢአትን ለማስተላለፍ እጆቹን በቁርባኖቹ ራስ ላይ ጫነ። እጆችን መጫን የማስተስረያ ቀን አስፈላጊው ክፍል ነበር። ይህ ባይከናወን ኖሮ ያለ እጆች መጫን የኃጢአት ማስተስረያ ሊፈጸም አይችልም ነበር፤ ስለዚህ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አይከናወንም ነበር፣ የእስራኤሎችን ዓመታዊ ኃጢአቶችም ማስተላለፍ አይቻልም ነበር።
በዘሌዋውያን 16፡21 ላይ “አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕያው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዝዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰድደዋል” ይላል።
እርሱ ከሕዝቡ የኃጢአት መሥዋዕቶች ይሆኑ ዘንድ ሁለት ፍየሎችን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆን ዘንድም አንድ አውራ በግ ወሰደ (ዘሌዋውያን 16፡5)። ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ በጌታ ፊት ሁለት ፍየሎችን ያቀርብና አንዱን ‘ለይሖዋ’ ሌላውን ‘ለየሚለቀቅ ፍየል’ አድርጎ ለመለየት ዕጣዎችን ይጥላል።
ለይሖዋ የሆነው ፍየል የኃጢአት መሥዋዕት ሆኖ ይቀርብ ነበር፣ የሚለቀቀው ፍየል ደግሞ የእስራኤልን ሕዝብ ዓመታዊ ኃጢአቶች ለማስተስረይ በጌታ ፊት ሕያው ሆኖ ይቀርብና ከዚያም ወደ ምድረ በዳ ይሰደድ ነበር (ዘሌዋውያን 16፡7-10)።
የእስራኤል ኃጢአቶች በሊቀ ካህኑ እጆች መጫን ወደሚለቀቀው ፍየል መተላለፍ ነበረባቸው። ከዚያም የእስራኤልን ኃጢአቶች በሙሉ በራሱ ላይ የወሰደው የሚለቀቀው ፍየል ሕዝቡና እግዚአብሔር መካከል ሰላም እንዲሆን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዳል። በዚህም የእስራኤል ዓመታዊ ኃጢአቶች ይነጹ ነበር።
በአዲስ ኪዳን፦ በተመሳሳይ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ ተጠመቀ (በብሉይ ኪዳን እጆች መጫን የሚመስለው)፣ የእግዚአብሔርን መዳን የሚፈጽም የመሥዋዕት በግ ሆኖ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ ወሰደ (ዘሌዋውያን 20፡22፣ ማቴዎስ 3፡15፣ ዮሐንስ 1፡29፣ 36)።
በብሉይ ኪዳን ዕጣዎቹ ከመጣላቸው በፊት አሮን ለራሱና ለቤተሰቡ የኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ወይፈን ያርዳል (ዘሌዋውያን 16፡11)። ከዚያም በጌታ ፊት ካለው መሠውያ ላይ በተወሰደ የእሳት ፍም የተሞላ ጥና ወስዶ ከተወቀጠው ከጣፋጭ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወስድና ከመጋረጃው በስቲያ ይዞት ይገባል። ከዚያም የዕጣኑ ጢስ በስርየት መክደኛው ላይ ይሰፍፍ ዘንድ በጌታ ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምረዋል። ከወይፈኑም ደም የተወሰነውን ይወስድና በስርየት መክደኛው ላይና ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጨዋል ይረጨዋል (ዘሌዋውያን 16፡12-19)።
በማስተስረያ ቀን አሮን በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጆቹን መጫን በፍጹም መተው አይቻልም። አሮን እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ የእስራኤልን ኃጢአቶችና በደሎች ሁሉ ወደ ፍየሉ ራስ ያስተላልፋል። ከዚያም ተስማሚ ሰው ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ወስዶ ይለቀዋል። የሚለቀቀው ፍየል የእስራኤልን ኃጢአቶች ይዞ በምድረ በዳ ይቅበዘበዝና በመጨረሻም ለእነርሱ ሲል ይሞታል። ይህ በብሉይ ኪዳን የነበረው የስርየት መሥዋዕት ነበር።
ይህ በአዲስ ኪዳንም ተመሳሳይ ነው፣ ነገር ግን እንደ የሚለቀቀው ፍየል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ የዓለምን ኃጢአቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወስዶ፣ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ሞተ።
ስለዚህ አሁን ከኃጢአቶች ሁሉ መዳን ሰማያዊ ሊቀ ካህን ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትና ስቅለት ውጭ ሊመጣ አይችልም። ይህ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግም የመወለድ መዳን ፍጻሜ ነው።